3 days ago
በትግራይ ክልል ግጭት በማገርሸቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያለው ስጋት ዳግም አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ‼️
በሀገር የመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የክልሉ ነዋሪዎች ዳግም ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመጋለጥ ስጋት እንደደገነባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ እንደገለጹት ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ከደረሱበት አሰቃቂ ጥቃቶች ሳያገግምና ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ አዲስ ግጭት ውስጥ መግባቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋቱን ይበልጥ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።
በትግራይ ክልል ያገረሸው ግጭት ከአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጊያዎች ጋር ተደማምሮ በሀገሪቱ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች እየደረሰ መሆኑን የገለጸው አምነስቲ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች መርማሪ አካላትን ሥራ በአስቸኳይ መመለስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት፤ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በርካታ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ያስታወሰው ተቋሙ በጥፋተኞች ላይ ምርመራ እና ክስ ያለማቅረብ አካሄድ ልማዳዊ ሊሆን አይገባም ብሏል።
የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ፣ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም ለነጻ የሰብአዊ መብት ተከታታዮች፣ ለሰብአዊ እርዳታ አቅራቢዎች እና ለገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን ያልተገደበ እንቅስቃሴ ፈቃድ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።
Seledadotio

4 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ኦገስት 1 ቀን በትግራይ ኃይሎች እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) መካከል ዳግም ያመረቀዘውን ግጭት ተከትሎ፣ የክልሉ ነዋሪዎች ለአዲስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አደጋ መጋለጣቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ቀጠናዊ ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ ባወጡት መግለጫ፣ ማህበረሰቡ ከዚህ ቀደም የተፈጸሙበትን አሰቃቂ በደሎች ያለ ምንም ፍትህ እና ተጠያቂነት እያስተናገደ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ አዲሱ የትጥቅ ግጭት ነዋሪዎቹን ወደ ከፋ አደጋ ውስጥ ጥሏቸዋል ብለዋል።
ቀጠናዊ ዳይሬክተሩ አክለውም ይህ በትግራይ ዳግም ያገረሸው ጦርነት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ቀጥሎ ከሚገኘው እና ተቋማቸው ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እየመዘገበበት ካለው የትጥቅ ግጭት ጋር ሲደመር፣ ሀገሪቱ አፋጣኝ የሆነ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ምርመራ ዘዴዎችን ወደ ነበረበት መመለስ እንዳለባት አመላካች ነው ሲሉ አሳስበዋል። ከህዳር 2013 እስከ ህዳር 2015 ዓ.ም. በተካሄደው ጦርነት የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሊባሉ የሚችሉ ከባድ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ያስታወሰው ተቋሙ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ታማኝ ምርመራ አለማድረግን እና የጥፋተኞችን የህግ ተጠያቂነት ማስፈን አለመቻልን እንደ መደበኛ አሰራር ሊቆጥረው አይገባም ሲል አስጠንቅቋል።
በመሆኑም አምነስቲ ኢንተርናሽናል የፌደራል እና የትግራይ ባለስልጣናት የሲቪሎችን ጥበቃ ጨምሮ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት መስፈርቶችን እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል። ከዚህም ባሻገር ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ታዛቢዎች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢዎች ያለምንም እንቅፋት በቦታው ተገኝተው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ ተማጽኗል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ከሚገኙ ባለስልጣናት ጋር በአስቸኳይ በመነጋገር በግጭቱ ለተጎዱ የትግራይ አካባቢዎች የነጻ ሚዲያዎች እና የሰብዓዊ መብት ታዛቢዎች ተደራሽነት እንዲረጋገጥ ተቋሙ ወትውቷል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ይደረግ የነበረው ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ክትትል የተቋረጠው፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን (ICHREE) እና የአፍሪካ የሰብዓዊ እና ህዝቦች መብት ኮሚሽን አጣሪ ቡድን የስራ ጊዜ ማብቃቱን ተከትሎ መሆኑን መግለጫው አስታውሷል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ዓለም አቀፍ የተጠያቂነት ጥረቶችን ለመከላከል ሲጠቀምበት የነበረውን የሽግግር ፍትህ ሂደት እርግፍ አድርጎ ትቶታል ሲል መግለጫው ወቅሷል። በሌላ በኩል ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የትግራይ ባለስልጣናት ነጻ ሚዲያዎችን ከማፈን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በግዳጅ ወደ ጦርነት ከመመልመል እና የዜጎችን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት ከመገደብ ጋር የተያያዙ አፋኝ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መመዝገባቸውን አምነስቲ አጋልጧል።

14 days ago
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እንዲታሰሩ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርምር፣ ተሟጋችነት፣ የፖሊሲ እና የዘመቻዎች ከፍተኛ ዳይሬክተር ኤሪካ ጉዌቫራ ሮዛስ የእስራኤል መሪ በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት እንዲታሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።ሮዛስ በቅርቡ ኔታንያሁ የአሜሪካ ከተማን ቢጎበኝ እንዲታሰሩ የጠየቁትን የኒውዮርክ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ የተናገሩትን አስተጋብተዋል።
ሮዛስ በኤክስ ላይ በጻፉት መልዕክት “የአሜሪካ ባለስልጣናት የሰብአዊ መብቶችን ማስከበር እና የህግ የበላይነትን ማክበር አለባቸው” ሲሉ ተናግረዋል።ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በ2024 በኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ማዉጣቱ ይታወሳል፡፡ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው የዘር ማጥፋት ጦርነት ወቅት የጦር ወንጀሎችን ፈጽማለች በሚል ክስ ቀርቧል።
በሌላ መረጃ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በዌስት ባንክ ታል መንደር በተፈፀመው የተኩስ ልውውጥ አንድ እስራኤላዊ ከተገደለ በኋላ አጥብቀው ምላሽ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።"በአሸባሪዎቹ እና በሚያደራጁት እንዲሁም በሚደግፉት ላይ በሙሉ ኃይላችን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል፡፡
አክለዉም በይሁዳና በሰማሪያም የሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ቦታ እንዲያገኝ አንፈቅድም ሲሉ ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።የፍልስጤም ባለስልጣናት የእስራኤል ኃይሎችም ሆኑ ሰፋሪዎች በስፍራዉ ላይ አራት ፍልስጤማውያንን በመግደል ተጠያቂ እንደሆኑ ተናግረዋል።

1 month ago
የሊቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት የአራት አጎራባች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ አገዱ
የምሥራቅ ሊቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት የአራት አጎራባች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ አገዱ። የባለሥልጣናቱ እርምጃ በምዕራባዊ የሊቢያ የባሕር ወደብ በኩል ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚያልሙ ተሰዳጆችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በሊቢያ ባለሥልጣናት እገዳ የተጣለባቸው የሱዳን፤ የኤርትራ፣ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። የሊቢያ የባሕር ወደብ የተሻለ ሕይወትን አልመው ወደ አውሮጳ ለመሰደድ የሚሞክሩ በርካታ የአፍሪቃ ተሰዳጆች የሚያዘወትሩት መሸጋገሪያ መስመር ነው።
ተሰዳጆቹ በሕገወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች አማካኝነት ለጉዞ አስተማማኝ ባልሆኑ ትናንሽ ጀልባዎች ከመጠን በላይ ተጠቅጥቀው የሚሳፈሩ ሲሆን ባሕር ላይ በሚያጋጥመው አደጋ በሺህዎች የሚቆጠሩት ካሰቡበት ሳይደርሱ ሕይወታቸው እንደሚቀጠፍ በየጊዜው ይዘገባል። ትናንት ይፋ የተደረገው እገዳ የሱዳን፤ የኤርትራ፤ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ተሰዳጆች በየብስም ሆነ በባሕር እና በአየር ወደ ሊቢያ ግዛት እንዳይገቡ ከልክሏል። መግለጫው አክሎም ክልከላው ዲፕሎማቶች፤ የጤና እና የትምህርት ዘርፍ ሠራተኞችን እንደማይመለከት አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ከሌላ ሃገር ወደ ሊቢያ የሚላኩ ስደተኞችን ጉዳይ በተመለከተ በምሥራቅ እና ምዕራብ የሊቢያ መንግሥታት መካከል ላለፉት ወራት ውጥረት አስነስቷል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው ስደተኞች ላይ በተደረገው ክትትል በሺህዎች የሚቆጠሩ በዚሁ ምክንያት ታስረዋል። የተመድ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ሊቢያ ውስጥ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኞች ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት የሱዳን ዜጎች ናቸው። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚፈልጉ ቢሆንም ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎች በባሕር ላይ ቃኚዎች እየተያዙ ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ እየተደረገ ነው። ስደተኞቹ በሊቢያ መንግሥታት እስር ቤቶች የሚያዙ ሲሆን እንግልት፤ የግዳጅ የጉልበት ሥራ፤ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈር እና ማሰቃየት እንደሚፈጸምባቸው ተገልጿል። የተመድ መርማሪ ኮሚሽንም ስደተኞቹ ላይ የሚደርሰውን እንግልት በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው ብሎታል።
DW Amharic

Sponsored by
Surafel
2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኒው ዮርክን ማዕከል ያደረገ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በትምህርት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ከሚደርስባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ከሄይቲ፣ ፍልስጤም፣ ዩክሬን እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር በቀዳሚነት ተሰልፋለች።
እ.ኤ.አ በ2010 የተመሰረተው እና ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ዩኒሴፍ ጋር በቅርበት የሚሰራው 'Global Coalition to Protect Education from Attack (GCPEA)' የተሰኘው ጥምረት፣ በ2026 ይፋ ባደረገው ዋና ሪፖርት ኢትዮጵያን የትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ወታደራዊ አጠቃቀም ከ100 በላይ ሪፖርት ከተደረገባቸው ሶስት ሀገራት አንዷ አድርጓታል።
በሪፖርቱ ግኝት መሰረት ከጃንዋሪ 2024 እስከ ዲሴምበር 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ በዓለም ዙሪያ በትምህርት ተቋማት ላይ ከ8,500 በላይ ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ሪፖርት ጋር ሲነጻጸር የ40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በነዚህም ጥቃቶች ቢያንስ 10,600 ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ዘርፍ ሰራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና ዩኒቨርሲቲዎችን ለወታደራዊ አገልግሎት የማዋል ተግባር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ሰነዱ አጋልጧል። በዚህም ከ1,900 በላይ ጉዳዮች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ሪፖርት ጋር ሲነጻጸር እጥፍ የሚጠጋ ነው።
ሪፖርቱ የትምህርት ተቋማትን ለወታደራዊ አገልግሎት ማዋል ትምህርት ቤቶችን ለተቃራኒ ኃይሎች ጥቃት አጋልጦ እንደሚሰጥ እና የትምህርት ተደራሽነትን እንደሚያስተጓጉል አስገንዝቧል። በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ትምህርት ቤቶችን ለወታደራዊ አገልግሎት የማዋል ድርጊት መጨመሩ ለዓለም አቀፉ ቁጥር ማደግ አስተዋጽኦ ካደረጉት ክስተቶች አንዱ መሆኑን ጠቅሷል።
በሪፖርቱ በተካተተው ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለይም በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች የትጥቅ ግጭቶች መቀጠላቸውን ሰነዱ ያትታል። በነዚህ አካባቢዎች የድሮን ጥቃቶች፣ የከባድ መሳሪያ ድብደባዎች፣ አፈናዎች እና የዘፈቀደ እስራቶች የተፈጸሙ ሲሆን፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መገደቡም ሁኔታውን ይበልጥ አወሳስቦታል። በእነዚህ ክልሎች በግጭት ምክንያት የተፈጠሩ መስተጓጎሎች ተማሪዎችን እና ተቋማትን ክፉኛ በመጉዳት የመማር ማስተማር ስራው ለረጅም ጊዜ እንዲቋረጥ አድርገዋል።
ሪፖርቱ በልዩነት ካነሳቸው ክስተቶች መካከል በጃንዋሪ 2024 በአማራ ክልል መርሃቤቴ ወረዳ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት አቅራቢያ የደረሰው የድሮን ጥቃት ይገኝበታል። በጥቃቱ ወቅት አንድ ታጣቂ ቡድን በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ ሰፍሮ እንደነበር እና ትምህርት ቤቱ ስራ ላይ በነበረበት በዚያን ሰዓት ለማምለጥ የሞከሩ በርካታ ተማሪዎች መቁሰላቸውን ሪፖርቱ አስፍሯል። ከ2,600 በላይ ተማሪዎች ይመዘገቡበት በነበረው በዚህ ትምህርት ቤት፣ ከክስተቱ በኋላ በርካቶች ወደ ክፍል እንዳልተመለሱ ሰነዱ ያሳያል።
ድርጅቱ ይህንን ክስተት በትምህርት ተቋማት አቅራቢያ ፈንጂ መሳሪያዎችን መጠቀም የተማሪዎችን ተሳትፎ እንዴት እንደሚጎዳ እና የትምህርት እንቅስቃሴን እንደሚያስተጓጉል በምሳሌነት አቅርቦታል። ማስታወሻ፦ ይህንን ሪፖርት ያወጣው 'Global Coalition to Protect Education from Attack' በዋናነት የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው አሜሪካን ማዕከል ካደረገው 'ታይድስ ፋውንዴሽን' (Tides Foundation) መሆኑ በዘገባው ተጠቁሟል።

4 months ago
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የሂውማን ራይትስ ዎችን ሪፖርት "ከእውነት የራቀ" እና "ወገንተኛ" በማለት አጣጣሉ
በአማራ ክልል ሥር የተመሰረተው 'የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን' ምክትል አስተዳዳሪ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በትግራይ ተወላጆች ላይ "አድሏዊ አሰራር" ተዘርግቷል መባሉን አስተባበሉ።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎች ረቡዕ ሚያዚያ 14፣ 2018 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት የአማራ እና ትግራይ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች "መታወቂያ እንዳያገኙ" እና "ፈቃድ ሳይኖራቸው ጉዞ እንዳያደርጉ" የሚከለክሉ "አድሎአዊ አሰራሮች" ተዘርግተዋል በማለት ከስሷል።
' የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን' ምክትል አስተዳዳሪ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከቢቢሲ ጋር ባረጉት አጭር ቆይታ ሪፖርቱን "ከእውነት የራቀ" እና "ወገንተኛ" ሲሉ አጣጥለውታል።
የመብት ተሟጋች ድርጅቱ በኮሎኔል ደመቀ ላይ ማዕቀብ እንዲጣልባቸው መጠየቁንም በሚመለከት ሲመልሱ "እኔ ወንጀለኛ አይደለሁም" ብለዋል።
"እኛ እዚህ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አስተዳደር የትግራይ ሰዎችን በማንነታቸው የሚገፋ አስተዳደር የለንም" ያሉት ኮሎኔል ደመቀ፣ ሂውማን ራይትስ ዎች ከዚህ በፊትም "እኛን ለመወንጀል ሞክሮ እንደነበር" እናውቃለን ሲሉ ለቢቢሲ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም፤ የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው አካባቢዎች ይፈጸማሉ ስላላቸው ጥሰቶች ሪፖርት ያዘጋጀው ስፍራው ላይ የሚገኙ እና ከወራት በፊት የተሰደዱ 40 ነዋሪዎችን አነጋግሮ መሆኑን ገልጿል።
የእርዳታ ሠራተኞችን፣ ዲፕሎማቶችን እና ሌሎች ባለሙያዎችን በማነጋገርም መረጃ ማሰባሰቡን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋሙ አስታውቋል።
በትግራይ ጦርነት ወቅት "በመቶ ሺህዎች" የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከእነዚህ አካባቢዎች "በግዳጅ" መፈናቀላቸውን ያስታወሰው መግለጫው፤ የትግራይ ተወላጆች አሁንም ድረስ "በባለሥልጣናት እና የጸጥታ ኃይሎች" ጥሰት እየተፈጸመባቸው ነው ሲል ከስሷል።
ኮሎኔል ደመቀ በበኩላቸው "እኛ እንደእርሱ አድርገን አይደለም የያዝናቸው። እንደማንኛውም ሰው መታወቂያም፣ ፋይዳም ያውጡ ብለን ፈቅደናል። ከዚህ ውጪ እኛ ፋይዳ አልተሰጠንም ብሎ ወደ እኛ የመጣ አቤቱታም የለም" ብለዋል።
ኮሎኔሉ ሪፖርቱ ላይ የቀረበውን መረጃ "ህወሓት የሰጣቸው ሪፖርት እና የአካባቢውን ስም ለማጥፋት፣ በዓለም አቀፍ ገጽታውን ለማበላሸት ፈልገው የሚሰሩት ካልሆነ ይህ እውነት ላይ የተመሰረተ ነው አልልም" ሲሉ በምላሹ ተችተዋል።
በሂውማን ራይትስ ዎች "የአንድ ወገን ደጋፊ" በሚመስል ሪፖርት "ማዘናቸውንም" ገልጸዋል።
ሪፖርቱ ላይ የትግራይ ተወላጆች በዘፈቀደ እየታሰሩ መሆኑን "እንቅስቃሴያቸውን፣ የሥራ ዕድላቸውን እንዲሁም አገልግሎቶችን የማግኘት መብታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ የሚገድብ አድሎአዊ ሥርዓት" እየተዘረጋ መሆኑ ተጠቅሷል።
በአካባቢዎቹ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች "ከከተማቸው ለቅቀው ለመሄድ" ከዞን አስተዳደሩ "ጊዜያዊ ፈቃድ" ማግኘት እንዳለባቸው ባደረገው ክትትል እንደደረሰበትም ተቋሙ ገልጿል።
ቢቢሲ የትግራይ ክልል ተወላጆች ላይ ይደርሳል ስለተባለው አድሏዊ አሰራር የጠየቃቸው 'የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን' ምክትል አስተዳዳሪ፣ "የትግራይ ሰዎች በመሆናቸው ያገለልናቸው ነገር የለም" ሲሉ አስተባብለዋል።
በአካባቢው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች "እንደማንኛውም ሰው" አገልግሎቶችን እየተጠቀሙ መሆኑንም ዘርዝረዋል።
ሪፖርቱ በአካባቢው አሁን ያለውን ሁኔታ አያንጸባርቅም ያሉት አስተዳዳሪው፣ ሂውማን ራይትስ ዎች በጉዳዩ ላይ እርሳቸውንም ሆነ አስተዳደራቸውን አለማነጋገሩን ጠቅሰዋል። የሰብአዊ መብቶች ተቋሙ በበኩሉ በክትትሉ የደረሰባቸውን ግኝቶች "ለኢትዮጵያ መንግሥት" አቅርቦ ምላሽ አለማግኘቱን በሪፖርቱ አስፍሯል።
ሂውማን ራይትስ ዎች አነጋገርኳቸው ያላቸው ነዋሪዎች "ትክክለኛ መሆናቸው መረጋገጥ አለበት" ያሉት ኮሎኔል ደመቀ፣ የትግራይ ተወላጆች በመንግሥት ተቋማት እንደ ማንኛውም ነዋሪ አገልግሎቶችን እንደሚያገኙ፣ በአካባቢው በሚኖሩበት ወቅትም "እንደማንኛውም ነዋሪ በሰላም እንዲንቀሳቀሱ እያደረግን ነው" ብለዋል።
ሂዩማን ራይትስ ዎች በሰኔ 2015 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት በምዕራብ ትግራይ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚፈጸሙ "ማሰቃየቶች"፣ "እስራት"፣ እና "የመንቀሳቀስ ገደብ"ን ጨምሮ "ማንነትን መሠረት ያደረጉ ወንጀሎች" እንዲፈጸሙ አዝዘዋል ወይም መርተዋል በማለት በስም ጠቅሷቸዋል።
ሌላኛው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአካባቢው የዘር ማጽዳት እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል እንደተከናወነ በገለጸበት የሚያዝያ 2015 ዓ.ም. ሪፖርት ላይም በስም ተጠቅሰዋል።
ሂዩማን ራይትስ ዎች ረቡዕ ዕለት ባወጣው ሪፖርት ደግሞ የኢትዮጵያ አጋር የሆኑ አካላት "እንደ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ" ያሉ አመራሮችን "ዒላማ ያደረገ ማዕቀብ" እንዲጥሉ ጠይቋል።
ኮሎኔሉ ለዚህ ምላሽ ሲሰጡ " (ስቀው). . .እኔ እነዚህን ከትግራይ ሰዎች ውጪ ናቸው አልልም፤ እነዚህ ህወሓት ትናንትና በየቦታው ያስቀመጣቸው በስመ ሂውማን ራይትስ ዎች ተቋሙን ተጠቅመው የሚያራምዱት የራሳቸውን የፖለቲካ ፍላጎት ለማስተግበር ካልሆነ እኔን የሚመለከት ነው ብዬ አላስብም" ብለዋል።
አስተዳደሩ "ገለልተኛ" የሆነ አካል በአካባቢው ተፈጽሟል የሚላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አጣራለሁ የሚል ከሆነ ፈቃደኛ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"ገለልተኛ" የሆኑ የመገናኛ ብዙኃን እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች "የትግራይ ሰዎች ላይ የደረሰውን ብቻ ሳይሆን የወልቃይት ሰዎች ላይም የደረሰውን የሚያጣራ ከሆነ" አስተዳደራቸው በሩ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከአካባቢው የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች አስተዳደሩ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ስር ከሆነ በኋላ ምን ያህል ተመልሰዋል ተብለው የተጠየቁት ኮሎኔል ደመቀ "ከአስር ሺህ በላይ እዚህ አለ። በራሱም አልሄድም ብሎም የቀረ አለ። ተደናግጦም ወጥቶ የተመለሰም አለ። ኢትዮጵያዊ ነኝ እስካለ ድረስ የመኖር መብቱ የተጠበቀ ነው" ብለዋል።
ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ለሁለት ዓመት ከተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በፊት በትግራይ ክልል ይተዳደር የነበረ ሲሆን ከጦርነቱ በኋላ ደግሞ በአማራ ክልል ስር በተመሰረተ የዞን መዋቅር በመተዳደር ላይ ይገኛል፡፡
የትግራይ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የተፈናቀሉ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ላለፉት አምስት ዓመታት ወደ መኖሪያቸው አልተመለሱም።
BBC

የአውሮፓ ህብረት ስደተኞችን ከአህጉሩ ውጪ ለማቆየት ወሰነ
የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ጥገኝነት የተከለከሉ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እስኪመለሱ ድረስ ከአውሮፓ ውጭ በሚገነቡ የማቆያ ማዕከላት እንዲቆዩ የሚያስገድድ አዲስ የጥገኝነት ፖሊሲ አፅድቋል።
ማዕከላቱ በሰሜን አፍሪካ ወይም በባልካን ሀገራት ከሚገኙ የሶስተኛ ወገን ሀገራት ጋር በሚደረግ ስምምነት የሚገነቡ ሲሆን፣ ዓላማውም የመመለስ ሂደትን ማፋጠንና ስደተኞች እንዳይሰወሩ መቆጣጠር ነው።
ይህ ሕግ የመነሻ ሀገራት ዜጎቻቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆኑ፣ ስደተኞችን ምንም አይነት የባህል ወይም የቤተሰብ ትስስር ወደሌላቸው ሶስተኛ ሀገራት ለመላክ የህግ ማዕቀፍ ይፈጥራል።
ሕፃናት ከዚህ አሰራር ውጭ ቢሆኑም፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ውሳኔውን "የሰብአዊ መብት ጥሰት ማዕቀፍ" ሲል ወቅሶታል።
ማዕከላቱ በፈረንጆቹ 2027 ሥራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።
ምንጭ: ዪሮኒውስ

6 months ago
ስደተኞችን ለወታደራዊ አላማ‼️
ኤርትራ ስደተኞችን ከግብፅ በኃይል ለወታደራዊ ምልመላ እየመለሰች መሆኑ ታወቀ‼️
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ውጥረት መንገሱን ተከትሎ ግብፅ የኤርትራ ስደተኞችን ኢላማ ያደረገ የእስር ዘመቻዎችን አባብሳለች፣ይህም ስደተኞቹን ለወታደራዊ አላማ ወደ ኤርትራ ለመመለስ ነው።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከጥር 10/2026 ጀምሮ በካይሮ፣ ጊዛ፣ አሌክሳንድሪያ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ በኤርትራ ስደተኞች ላይ የእስር ዘመቻዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አረጋግጧል።
ግምቶች እንደሚያሳዩት ከ3,000 በላይ የኤርትራ ስደተኞች ታስረዋል (አንዳንድ ሪፖርቶች ከ25,000 በላይ ሊሆን ይችላል) ብለዋል።
እስካሁን ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከ5,000 በላይ ስደተኞች ለወታደራዊ አላማ ወደ ኤርትራ ተመልሰዋል፣ሌሎቹ ደግሞ በተለያዩ የእስር ቦታዎች ታስረዋል።
seledadotio

በናይጄሪያ በ20 ቀናት ውስጥ የ323 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | በናይጄሪያ በየካቲት ወር የመጀመሪያዎቹ 20 ቀናት ብቻ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ቢያንስ 323 ሰዎች መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
ደካማ የመንግሥት ጥበቃ እና "የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች"
አምነስቲ ባወጣው መግለጫ፣ ይህ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ አስተዳደር ለዓመታት በታጠቁ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶችን ለማስቆም የሚያስችል ውጤታማ ስትራቴጂ እንደሌለው ማሳያ ነው ብሏል።
በተለይ ደግሞ በአንዳንድ አካባቢዎች ታጣቂዎቹ ጥቃት ከመፈጸማቸው በፊት ለነዋሪዎቹ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደሚልኩ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ እየታወቀ ግን ጥቃቱን መከላከል አለመቻሉ የመንግሥትን ድክመት ይበልጥ አጉልቶታል።
"መንግሥት አሳልፎ ሰጥቶናል" - ነዋሪዎች
በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች መንግሥት ለደኅንነታቸው ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ "ለታጣቂዎች አሳልፎ ሰጥቶናል" የሚል ከፍተኛ ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ መንግሥት የዜጎቹን ደኅንነት የመጠበቅና የመከላከል ቀዳሚ ግዴታውን እንዳልተወጣ በማሳሰብ፣ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nigeria #amnestyinternational #humanrights #securitycrisis #africanews #የናይጄሪያዜና

በሰሜን ኮሪያ የ"Squid Game" ፊልምን የተመለከቱ ተማሪዎች በሞት ተቀጡ
የአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International) ከሀገሪቱ የኮበለሉ ስደተኞችን ጠቅሶ ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በሰሜን ኮሪያ የደቡብ ኮሪያን ድራማዎች የተመለከቱ ተማሪዎች የሞት ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል።
📌 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የቅጣቱ መንስኤ፦ ተማሪዎቹ "Squid Game" የተሰኘውን ታዋቂ የደቡብ ኮሪያ ድራማ በድብቅ ሲመለከቱ ተገኝተዋል።
የመንግስት ህግ፦ ሰሜን ኮሪያ ማንኛውንም አይነት የደቡብ ኮሪያ የኪነ-ጥበብ ውጤቶች (ፊልም፣ ሙዚቃ እና መጽሐፍት) በፅኑ ትከለክላለች።
ከባድ ቅጣቶች፦ * ይህንን ይዘት ይዞ መገኘት እስከ 10 ዓመት የሚደርስ የግዳጅ ስራ (Forced labor) ያስቀጣል።
ይዘቱን ለሌሎች ማሰራጨት ደግሞ በሞት ያስቀጣል።
የአምነስቲ ዘገባ፦ ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ መንግስት የውጭ ሀገር ባህል "ርዕዮተ-ዓለማዊ ወረራ" ነው በሚል ወጣቶች ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጥብቋል።
"ይህ ድርጊት የመረጃ የመሰብሰብ እና የመግለጽ ነፃነትን የሚገታ አሰቃቂ እርምጃ ነው" — አምነስቲ ኢንተርናሽናል

7 months ago
በኢራን የተጫረው እሳት አልጠፋ አለ
🔴 የኢራን ውጥረት የሟቾች ቁጥር 36 ደረሰ
#ethioopia | በኢራን በተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ አስከፊ ግጭት ማምራቱ ተገለጠ። ላለፉት 10 ቀናት በዘለቀው በዚህ ተቃውሞ ቢያንስ 36 ሰዎች መገደላቸውን መቀመጫውን በውጭ ያደረገው "ሀራና" የተሰኘው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አስታውቋል።
📊 የጉዳቱ ዝርዝር በአኃዝ
እንደ ተሟጋች ድርጅቱ ዘገባ ከሆነ፦
* ሟቾች፦ 34 ተቃዋሚዎች እና 2 ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች።
* እስራት፦ በአጠቃላይ 2,076 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
* ጉዳት፦ ከ60 በላይ ተቃዋሚዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።
* ስርጭት፦ ተቃውሞው ከአገሪቱ 31 አውራጃዎች ውስጥ ወደ 27ቱ ተስፋፍቷል።
🏥 የሆስፒታሎች ወረራ እና ዓለም አቀፍ ውግዘት
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ፣ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ እና የፖሊስ ልዩ ሃይሎች በሆስፒታሎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጿል። የጸጥታ ሃይሎቹ ወደ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ፣ የመስታወት በሮችን በመሰባበር እና የህክምና ሰራተኞችን ጨምሮ በውስጥ ያሉትን ሰዎች በመደብደብ "ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ" እርምጃ መውሰዳቸውን ድርጅቱ አጋልጧል።
የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ዲፓርትመንት በበኩሉ በሆስፒታሉ ላይ የተፈጸመውን ወረራ “በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ግልጽ ወንጀል” ሲል አውግዞታል።
⚖️ የመንግስት ምላሽ
የኢራን ባለስልጣናት እስካሁን አጠቃላይ የሟቾችን ቁጥር ይፋ ባያደርጉም፣ ሶስት የጸጥታ አባላት መገደላቸውን አረጋግጠዋል። ከፊል መንግስታዊ ሚዲያዎች በበኩላቸው፣ የጸጥታ ሃይሎች "ሁከት ፈጣሪዎች" ባሏቸው ወገኖች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን እየዘገቡ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ኢራን #ህዝባዊተቃውሞ #ሰብአዊመብት #አምነስቲ #ኢኮኖሚቀውስ #ዓለምአቀፍዜና #iranprotests #humanrights

ከህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ጽሕፈት ቤት ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የተላከ ባለ ሁለት ገጽ ደብዳቤ
ሙሉ ደብዳቤው እንደሚከተለው ይነበባል
አፋጣኝ ሰብአዊ ጣልቃ ገብነት እንዲደረግ የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ
ለክቡር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ጉዳዩ፦ በትግራይ ውስጥ በተፈናቃዮች ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የረሃብ እልቂት እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መጣስ
ክቡራን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አስታራቂዎች፤
በትግራይ፣ ኢትዮጵያ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊና ሆን ተብሎ የተደረገ የረሃብ ማባባስ ሁኔታ በተመለከተ ይህንን ደብዳቤ በከፍተኛ አጣዳፊነት እንጽፋለን።
ከህዳር 2013 ዓ.ም (ኖቬምበር 2020) ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ከቀጠለው ሞት በኋላ፣ በታህሳስ 2018 (ዲሴምበር 2025) የሟቾች ቁጥር ከጦርነቱ ጊዜ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
በትግራይ በሚገኙ የተፈናቃይ ማዕከላት — ህጻጽ፣ ሽሬ፣ ዓድዋ፣ ዓቢይ ዓዲ፣ ዓዲግራት፣ መቐለ እና ሌሎችም — በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የፕሪቶሪያውን ስምምነት አንቀጽ 4 በሚጥስ መልኩ ስልታዊ ለሆነ ረሃብ ተጋልጠዋል።
የሰዎች አካል ወደ አፅምነት ተቀይሯል፣ ቁስላቸው ላይ ዝንብ ይወርራል፤ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በ2015-2016 (2023-2024) በሳምንት አንዴ ከነበረበት አሁን በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ወደ መሆን ተሸጋግሯል።
ህፃናትና አዛውንቶች በከፍተኛ ቁጥር እያለቁ ነው።
የፌዴራል መንግስት ጥሰቶች፡-
* ሀሰተኛ መግለጫዎች፡- የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዕርዳታ እያቀረብኩ ነው የሚለው ፕሮፓጋንዳ እንጂ በተግባር ወደ ተፈናቃዮች የደረሰ ትርጉም ያለው ዕርዳታ የለም።
* ቀጥተኛ እንቅፋት መፍጠር፡- መንግስት ማህበረሰቡ የሚያደርገውን የርስ በርስ መረዳዳት ወንጀል አድርጎታል። በማህበራዊ ሚዲያ ገንዘብ የሚያሰባስቡ የማህበረሰብ አንቀሳቃሾች ዛቻ እየደረሰባቸው ነው። የቲክቶከሮች በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ወደ መንግስት አካውንት እንዲያስገቡ የተገደዱ ሲሆን የሕዝብ መረዳጃ ሀብቶችም እየተወረሱ ነው።
ከዳያስፖራ የሚላክ የገንዘብ ድጋፍም ታግዷል።
* ያልተፈታው የስር መሰረት ችግር፡- ከ1 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች አሁንም በወረራ እና በ"ፅዳት" ስር ወደሚገኘው ምዕራብ ትግራይ መመለስ አልቻሉም።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ተመላሾችን በሚመለከት የገባው ቃል ሳይፈጸም ቀርቷል።
አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚፈለጉ ነጥቦች፡-
* አስቸኳይ ሰብአዊ ተደራሽነት፡- የመንግስትን እንቅፋት በመዝለል ምግብ፣ ውሃ እና የህክምና ቁሳቁሶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለሁሉም የተፈናቃይ ማዕከላት እንዲደርሱ መጠየቅ።
* ገለልተኛ ምርመራ፡- የታህሳስ 2018ቱን የችግር መባባስ፣ የአምስት ዓመቱን የሞት መጠን እና ስልታዊ የዕርዳታ ክልከላን የሚያጠና የሐቅ መፈለጊያ ልዑክ በአስቸኳይ መሰማራት። በ60 ቀናት ውስጥም ይፋዊ ሪፖርት ማቅረብ።
* የፕሪቶሪያ ስምምነትን ማስከበር፡- ኢትዮጵያ በአንቀጽ 4 ላይ ለፈጸመቻቸው ጥሰቶች ተጠያቂ ማድረግ። ተፈናቃዮች ወደ ምዕራብ ትግራይ የሚመለሱበትን ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ መጠየቅ።
* ገደቦችን ማንሳት፡- መንግስት በዜጎች እና በዳያስፖራ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረት ላይ የጣለውን ክልከላ እንዲያቆም ጫና ማድረግ። የተወረሱ የዕርዳታ ገንዘቦችን መመለስ።
* ይፋዊ ተጠያቂነት፡- ድርጊቱን የሚያወግዙ መግለጫዎችን ማውጣት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ማድረግ፣ እንዲሁም ዕርዳታ በሚያግዱ ባለስልጣናት ላይ የታለመ ማዕቀብ መጣል ይገኙበታል።
ከአምስት ዓመታት እልቂት በኋላ፣ ታህሳስ 2025 (2018 ዓ.ም) የችግሩ ሁኔታ ከከረረ ቀውስ ወደ አስከፊ እልቂት የተሸጋገረበት ወቅት ነው። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያየ ቃል የተገባላቸው ህዝቦች በከፍተኛ ቁጥር እያለቁ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተተገበረ ሊቆጠር አይችልምአሁን ዝምታን መምረጥ ተባባሪነት ነው።
የተፈናቃዮች መጠለያ ማዕከላት የጅምላ መቃብር ሳይሆኑ በፊት፣ የፕሪቶሪያ ተስፋ የትውልድ እፍረት ሳይሆን በፊት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለንጊዜ የሚለካው በየቀኑ በሚቆጠሩ አስከሬኖች ነው አሁኑኑ እርምጃ ይወሰድ።
በአክብሮት እና በአስቸኳይ የቀረበ፣
(ፊርማ)
ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ፒ.ኤች.ዲ)
የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር
ለግልባጭ፡-
* ተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (UN OCHA)
* ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC)
* ድንበር የለሽ ሐኪሞች (MSF)
* ሂውማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch)
* አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International)

9 months ago
ኢራን በአስገድዶ መድፈር የተከሰሰን ሰው በአደባባይ ስቅላት ቀጣች
ኢራን በሰሜን ሴምናን ግዛት ውስጥ ሁለት ሴቶችን አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተገኝቶበት የሞት ፍርድ የተፈረደበትን ሰው በአደባባይ ሰቅላ እንዲሞት ማድረጓን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የሞት ፍርዱ የተፈጸመው በባስታም ከተማ ውስጥ ሲሆን፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ካፀደቀ በኋላ መሆኑን የፍትህ አካሉ ይፋዊ ሚዲያ የሆነው ሚዛን ኦንላይን ዘግቧል።
የግዛቱ የፍትህ አካል ኃላፊ የሆኑት መሐመድ አክበሪን ዋቢ ያደረገው የሚዛን ዘገባ፣ ውሳኔው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ልዩ ግምገማ ከተደረገለት በኋላ መረጋገጡንና ተግባራዊ መደረጉን ገልጿል።
የግዛቱ ባለስልጣናት እንደተናገሩት፣ ሰውየው ሁለቱን ሴቶች በማታለል በኃይል አስገድዶ እንደደፈረና ተጎጂዎቹን በማስፈራራትና በማዋረድ እንደዛተባቸው ተገልጿል።
ተከሳሹ ማንነት አልተገለጸም። ኢራን የሞት ፍርዶችን ብዙውን ጊዜ የምትፈጽመው በእስር ቤቶች ውስጥ ሲሆን፣ ነገር ግን ለአንዳንድ ከባድ ወንጀሎች ፍርዶቹ በይፋ ሊፈጸሙ ይችላሉ።
አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እንደሚሉት፣ ኢራን ከቻይና ቀጥላ በዓለም ላይ ሁለተኛዋ ትልቋ የሞት ፍርድ ፈጻሚ ሀገር ነች።

አምነስቲ አሜሪካ በየመን በፈፀመችው የአየር ጥቃት በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መገደላቸውን አስመልክቶ የጦር ወንጀል ምርመራ እንዲደረግ አሳሰበ
ባሳለፍነው 2017 ዓ.ም ሚያዚያ ወር አሜሪካ በየመን ሁቲዎች በሚያስተዳደሩት የስደተኞች መጠለያ ላይ በፈፀመችው የአየር ጥቃት በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መገደላቸውን ተከትሎ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ድርጊቱ የጦር ወንጀል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ሲል ገልጾ ምርመራ እንዲደረግ አሳሰበ።
አምነስቲ፣ የአሜሪካ ጦር ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በፈፀመው እና የ”ኦፕሬሽን ራፍ ራይደር” ዘመቻ አካል የሆነው ጥቃት “ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግን የጣሰ ነበር” ብሏል።
እንደ ተቋሙ ገለጻ የአየር ጥቃት የተፈፀመበት መጠለያ ጣቢያ የሁቲ ባለሥልጣናት በህገወጥ ስደት ምክንያት ያሰሯቸውን ስደተኞች የያዘ ሲሆን፣ ቦታውም “የሚታወቅ ሰላማዊ ሰዎች የሚገኙበት ቦታ ነበር”።

11 months ago
የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ ከተማ ገባ !
እስራኤል በጋዛ ከተማ ላይ የምድር ላይ ጥቃት መጀመሯ ተሰማ ።
ሰኞ እለት በእስራኤል ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር የተገናኘው ሩቢዮ የእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ የምድር ዘመቻ መጀመሩን በተናገሩ ማግስት የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ በሙሉ አቅሙ እያቀና መሆኑ ተገልጿል ።
እስራኤል ማክሰኞ ዕለት በጋዛ ከተማ ላይ የጀመረችዉን እና በአንድ ቀን ብቻ በርካታ አካባቢዎች ላይ ያለእረፍት እየፈፀመች የሚገኘዉን የምድር ላይ ጥቃት ተከትሎም
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትስ "ጋዛ እየተቃጠለች ነው" ሲሉ እና እስራኤል "ተልኮዋን እስክታጠናቅ ገላጋይ እንደማትሰማ በምንም ሁኔታ ወደኋላ እንደማትመለስ ሁሉም ማወቅ አለበት" ሲሉ ቃል ገብተዋል ።
የእስራኤል የፖለቲካ ተንታኝ ኦሪ ጎልድበርግ ሰኞ እለት እንደተናገሩት በጋዛ ከተማ ላይ የተፈፀመው ጥቃት በጣም ከባድ መሆኑን የቦምብ ጥቃቱ "በማዕከላዊ እስራኤል ይሰማል" በማለት "መጥፋት" እና "የዘር ማጥፋት" ሲሉ ተናግረዋል.
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው፣ ከእስራኤል በግዳጅ ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ እና በእስራኤል የቦምብ ጥቃት በመፈጸማቸው 70,000 ሰዎች ጋዛ ከተማን ለቀው ወጥተዋል። የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን የመጓጓዣ መንገድ ወይም እንደ ምግብ እና ውሃ ያሉ አስፈላጊ ነገሮች የላቸውም። ብሏል
ይህ የሆነው ሃማስ ቀደም ሲል የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸውን ቢገልጽም፣ ከእስራኤል ጋር ግን ምክረ ሀሳቡን ውድቅ በማድረግ ጥቃቱን ማባባሱን ተከትሎ ነው።
ሃማስ በበኩሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርን በመተቸት መግለጫ አውጥቷል፣ “በግልጽ የጽዮናውያን ፕሮፓጋንዳ የሚደግፍ እና የዘር ማጽዳትን ይደግፋል” ሲል ከሷል።
ቡድኑ አክሎም ትራምፕ “የዘር ማፅዳት ወንጀልን እና በጋዛ ሰርጥ 65,000 የሚጠጉ ንፁሃን ዜጎችን ሰማዕትነት ችላ ብለዋል” ብሏል።
"የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር የጦር ወንጀለኛውን ኔታንያሁ እየደገፈ ይገኛል ።
ለዚህም እስረኞችን ወደ መፍታት እና በሰርሪፕ ላይ የሚካሄደውን ጭካኔ የተሞላበት የዘር ማጥፋት ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ ሁሉንም እድሎች ለማጥፋት እየሰራ የነበረዉን የኳታሩን ዉይይት ላይ የተደራዳሪ ልዑካን ቡድን የግድያ ሙከራ ነው በማድረግ አበላሽቷል" ሲል መግለጫው ቀጥሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነትን ለመቀበል የቀናት ወይም የሳምንታት ጊዜ ብቻ ነው ያለው ሲሉ ተናግረዋል ።
ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ስለዚህ እኔ እንደማስበው ስምምነት የሚፈጸምበት በጣም አጭር ጊዜ ያለን ይመስለኛል" ከአሁን በኋላ ወራት የለንም እና ምናልባት ቀናት እና ምናልባትም ጥቂት ሳምንታት ይቀሩናል" ብለዋል.
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት በጋዛ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ እንዲያቆሙ፣ ሰብአዊ ርዳታዎችን ሙሉ በሙሉ እንዲደርሱ እና በስትሪፕ ውስጥ ረሃብ የሚያስከትሉ ፖሊሲዎችን እንዲያቆሙ ጥሪ እያቀረቡ ሲሆን አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የዘር ማጥፋት እንደሆነ በመግለጫቸው ገልፀዋል ።
አእስራኤል በበኩሏ ሉአላዊነቷን ለማስጠበቅና ደህንነቷን ለማስከበር እንደሆነ ትገልፃለች ሲል ያስነበበው The New Arab የዜና ወኪል ነዉ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

ቡርኪናፋሶ የተመሳሳይ ጾታ ግኑኝነት የሚከለክል ህግ አፀደቀች !
በካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ የሚመራው የቡርኪና ፋሶ የሽግግር ፓርላማ፤ ካቢኔ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻም ሆነ ግኑኝነት የሚከለክል ህግ ማፅደቁ ተነገረ ።
ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ወንጀል በሚያደርግ መልኩ የሀገሪቱን ቤተሰብ ህግ ለማሻሻል ያሳለፈውን ውሳኔ በመከተል ይህንን ድርጊት የሚከለክል አዋጅ ያፀደቀው ፓርላማው ድርጊቱን ገላጭ የሆኑ ባንዴራ ቀለማት ተግባራትም መፈፀም ዘብጥያ እንደሚያስወርዱ ገልጿል ።
ሰኞ ዕለት በሙሉ ድምጽ የጸደቀው አዲሱ አዋጅ የተመሳሳይ ጾታን ግንኙነት ውስጥ የተገኙ ሰዎችን እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት እንደሚቀጡ በሀገሪቱ ዜግነት የሌላቸው አጥፊዎች ከአገር እንደሚባረሩ። ደንግጓል።
በ1960 ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ያገኘቸው
ከሳህል ሀገራት አንዷ የሆነችው ቡርኪና ፋሶ ከዚህ ቀደም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከፈቀዱ 22 የአፍሪካ ሀገራት አንዷ የነበረች ሲሆን ከዚህ በኋላ ግን ከማህበረሰቡ የሚያስገልል በገዘብና በእስር የሚስቀጣ የቤተሰብ ህግ በማድረግ በአንድ ድምፅ አጽድቋል ።
አዲሱ ህግ ወዲያውኑ ተግባራዊ ይሆናል ፣በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የእስር ቅጣት እና የገንዘብ ቅጣት አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ የፍትህ ሚኒስትር ኢዳሶ ሮድሪግ ባያላ በመንግስት ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
ህጉ ተግባራዊ እንዲሆን የሚጠበቀው ቀጣይ ሂደት የሀገሪቱ ወታደራዊ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ፊርማ እንደሆነ ፋሶ 24 የዜና ወኪል ዘግቧል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ በቀኝ ግዛት የተገዙ ሀገራት ፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አቋም እያሳዩ የሚገኝ ሲሆን የቡርኪና ፋሶ አጋር የሆነችው ማሊም ባሳለፍነው ህዳር ወር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ወንጀል የሚያደርግ ህግ ያፀደቀች ሲሆን ጋና እና ኡጋንዳና ናይጄሪያ ይጠቀሳሉ ።
ይህን ተከትሎ መግለጫ ያወጣው የመብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ማክሰኞ እንዳስታወቀው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀል መደረጉ የእኩልነት መብትን የሚጥስ “አስደንጋጭ ውድቀት ነው” ብሏል። የጁንታ ዋና አዛዥ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ውሳኔውን እንዲቀለብስ አሳስበዋል።
የሀገሪቱ ፍትህ ሚኒስትር በበኩላቸው ይህ ዉሳኔ የቤተሰብ የማህበረሰብ ደህንነት በዜግነት እና ሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ በመሆኑ ተፈፃሚ ይሆናል ብለዋል ሲሉ ያስነበቡት AP, AFP, Reuters, dpa, KNA የዜና ወኪሎች ናቸው ።

ሰሚ ያጣው የክርስትያኖች ሰቆቃ በፓኪስታን !
ፓኪስታን በፕላኔታችን ከሚገኙ ሀገራት መካከል ቁጥር አንድ ለክርስትያኖች የማትመች ምድራዊ ሲኦል የሆነች ሀገር መባሏና አማኞችም እየደረሰባቸው ያዉን ሰቆቃ የአለም ህዝብ እንዲረዳል ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸዉ ተሰማ ።
ዲሚትራ ስታይኮ የተባለው የዜና አዉታር በፓኪስታን ውስጥ ያለው አናሳ ክርስቲያን ህዝብ ላይ ለሰሚው የሚከብድ የፍትህ መጓደል ስድብ መገለል በውሸት ውንጀላ የታጠቁ አካላትም ጥቃት እየፈፀሙ ቢሆንም በሀገሪቱ የሚገኘው ከህዝቡ 1.6 በመቶው ብቻ የሚሆነው ክርስቲያን ስርአታዊ ስደት እና መገለልን
ላይ ይገኛል ።
በርካታ ችግሮችን በመቋቋም በጽናት የቀጠሉት ክርስትያኖችም በተወለዱበት ሀገር እንደዜጋ እንዲታዩ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል ሲል አርብ እለት ባወጣው ዘገባ ገልጿል ።
በፑንጃብ ግዛት ከተፈጸመው የጃራንዋላ ጥቃት ከሁለት ዓመት በኋላም ቢሆን የስድብ ሕጎችን ማሻሻል፣ የዳኝነት ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እና ሃይማኖታዊ ጭፍን ጥላቻን ለመዋጋት የትምህርት ዘመቻዎችን ማድረግ ባለመቻሉ በክርስትያኖች ላይ ባለ ብዙ አቅጣጫ ጥቃት እየደረሰና የክርስቲያን ማህበረሰቦችን በተለይም ሴቶችን እና ህፃናትን - በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ምስቅልቅል ተዳርገዋል ተብሏል ።
መንግስታዊ ድጋፍ በሚደረግለት አክራሪ ሀይልም 26 አብያተ ክርስቲያናትን እና ከ80 በላይ ቤቶችን ወድሟል ይህም- በፓኪስታን ታሪክ ውስጥ ከነበሩት እጅግ የከፋ ፀረ ክርስቲያናዊ ጥቃቶች አንዱ ሲሆንም - አንድም የጥፋተኝነትና የተጠያቂነት ውሳኔ አልተረጋገጠም ሲል ዲሚትራ ስታይኮው በዜና ማሰራጫ ዴፌንስ ኔት ላይ ጽፏል።
በ2025 እንደ ክርስቲያን ለመኖር በዓለም ላይ ካሉት በጣም አስቸጋሪ ቦታዎች አንዷ ሆና የቀጠለችዉ ፓኪስታን ሰኔ 4፣ 2025 በፋይሳላባድ የሚገኘው የፀረ ሽብር ፍርድ ቤት ቤተክርስቲያንን አቃጥለዋል እና የክርስቲያን ቤት ዘርፈዋል የተባሉ 10 ግለሰቦችን በነፃ አሰናብቷል ያለው ዘገባዉ በነሀሴ 16 ቀን 2023 ለተፈፀመው ጥቃት ፍትህ የሚፈልጉ ክርስቲያኖች ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ አብራርቷል ።
እ.ኤ.አ. ኦገስት 16፣ 2025 ክርስቲያኖች የፍትህ እጦትን ለመቃወም በጃራንዋላ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርጉም መንግስት የሀይል እርምጃ ወስዷል ።
የተጎጂዎች ኮሚቴ የመንግስትን እንቅስቃሴ በማውገዝ ማህበረሰቡን ለመከፋፈል የሚደረገውን ጥረት እንዲያቆም ጥሪ አቅርቧል ።
አስተባባሪው ላላ ሮቢን ዳንኤል “በጣም አዝነናል” ብሏል። "ሁሉም ክርስቲያኖች ሰላማዊ የመቀመጥ እና የማህበራዊ ሚዲያን የመጠቀም የማምለክ ነፃነት ፍትህን እንዲሰጠን እንጠይቃለን." ብሏል
አክሎም ክርስቲያን ሴቶችና ልጃገረዶች በተለይም ድሆች ወይም አካል ጉዳተኞች እየጨመሩ የሚሄዱ የአፈና፣ የአስገድዶ መድፈር እና የግዳጅ እምነት ተከታይ እንዲሆኑ የማስገደድ ጉዳዮች እየተፈጸመ መሆኑን በመገንዘብ ትኩረት እንዲሰጠን በማለት ጥሪ አቅርቧል ። ሲል ያስነበበው የፓኪስታን አብያተክርስቲያናት ድህረገጽና ዲሚትራ ስታይኮው የዜና ወኪል ነዉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደዘገበው በጃራንዋላ ግርግር በቁጥጥር ስር ከዋሉት 5,213 ተጠርጣሪዎች መካከል 380 ያህሉ ብቻ ናቸው ፍርድ ቤት የቀረቡት የተቀሩት ግን ተለቀዋል ሲል ፍትህ መጉደሉን ገልጿል ።
በተመሳሳይ ከአንድ አመት በኋላም 228ቱ ዋስትና ሲፈቀድላቸው 77ቱ ደግሞ ክሳቸው ተቋርጧል። የደቡብ እስያ የአምነስቲ ምክትል ክልላዊ ዳይሬክተር ባቡ ራም ፓውዴል “የተጠያቂነት ቃል ቢገባም የባለሥልጣናቱ ውድቀት ጥፋተኛ ያለመከሰስ ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል” በማለት ጭቆና እንዳለ አረጋግጧል ።

12 months ago
በኖርዌይ ኢትዮጵያዊቷን 'በዘረኝነት ተነሳስቶ' በስለት የገደላት ግለሰብ በሽብር እንደሚጠየቅ ተዘገበ
በኖርዌይ የ34 ዓመቷን ኢትዮጵያዊ የማኅበራዊ ሠራተኛ (ሶሻል ወርከር) 'በዘረኝነት ተነሳስቶ' በተደጋጋሚ በስለት ወግቶ የገደላት የ18 ዓመት ግለሰብ ከግድያ በተጨማሪ በሽብርተኝነት እንደሚከሰስ ተዘገበ።
ታሚማ ኒብራስ ጁሃር የተባለችው ይህች ኢትዮጵያዊት ትሠራበት በነበረው የታዳጊዎች ማዕከል ውስጥ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በተደጋጋሚ በስለት ተወግታ መገደሏን ባለሥልጣናት ሰኞ ዕለት ማስታወቃቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
ታሚማ ተጋላጭ ወጣቶችን ከማኅበረሰቡ ጋር ለማዋሃድ በሚሠራ አንድ ማዕከል ውስጥ ትሠራ የነበረ ሲሆን፣ እሷን በመግደል የተጠረጠረው በማዕከሉ ውስጥ ይኖር የነበረ የኖርዌይ ዜጋ ነው።
ታሚማ በኦስሎ ካምፔን በተሰኘ ሰፈር በአንድ የመኖሪያ ተቋም ውስጥ ብቻዋን በሥራ ላይ እያለች ግድያው እንደተፈጸመባት ተዘግቧል።
በዚህ ማዕከል ነዋሪ የሆነው ተጠርጣሪ ከጥቃቱ በኋላ በመዲናዋ ኦስሎ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በግለሰቧ ግድያም እጁ እንዳለ ማመኑን ፖሊስ ገልጿል። ጀርመን የተወለደው ይህ ወጣት በርካታ የሕይወት ዘመኑን ያሳለፈው በኖርዌይ ሲሆን፣ ታሚማን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደላት በኋላ ብዙም ሳይቆይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኖርዌይ መገናና ብዙኃን ዘግበዋል።
ግለሰቧ በስለት በሰውነቷ በተለያዩ ክፍሎች ስለመወጋቷም ተነግሯል። ተጠርጣሪው ከኖርዌይ ካለው የሚዲያ አሠራር ጋር ተያይዞ ስሙ ይፋ አልተደረገም።
በተጠርጣሪው ላይ የቀረበው ክስ ሽብርተኝነትን እንዲያካትት በማድረግ መስፋቱንም ፖሊስ አክሎ ገልጿል።
ግለሰቡ "በምርመራው ወቅት ሌሎች ሰዎችን ለመጉዳት ማቀዱን ተናግሯል" ሲሉ ምክትል ዐቃቤ ሕግ ፊሊፕ ግሪን መግለጻቸው ተዘግቧል።
"በደረስንበት ደረጃ በተወሰነው ማኅበረሰብ መካከል ሽብርን
ለመንዛት አቅዷል ብለን እናምናለን፤ ለዚያም ነው የሽብርተኝነት ምርመራ የምንከፍትበት" ሲሉ ተናግረዋል።
እንደ ዐቃቤ ሕግ ከሆነ ተጠርጣሪው "በሙስሊም ማኅበረሰብ ላይ የጥላቻ አስተያየት ሲሰጥ ተደምጧል።"
ተጠርጣሪው በመስጊድ ላይ ጥቃት ለመንሰዘር ማቀዱን የኖርዌይ መገናኛ ብዙኃን ቢዘግቡም ዐቃቤ ሕግ ይህንን አለማረጋገጡ ተነግሯል።
"በዚህ ሳምንት መጨረሻ አንድ የሚያሳምም እውነት አስታውሰናል። ጥላቻ እና ጽንፈኝነት ሕይወትን ይነጥቃል። ሌሎችን እየረዳች ባለችበት ወቅት ሕይወቷን ያጣችው የታሚማ ግድያ እጅግ አሳዛኝ ነው" ሲል አምነስቲ ኖርዌይ ባወጣው መግለጫ ኃዘኑን አስተላልፏል።
አምነስቲ ሊገለጽ በማይችል ሐዘን ውስጥ ካሉት ለቤተሰቦቿ፣ ለጓደኞቿ እና ለሥራ ባልደረቦቿ መጽናናትን ተመኝቶ "ለደኅንነት፣ ለመከባበር እና ለእኩልነት መቆም የጋራ ኃላፊነታችን ነው" ብሏል።
የሟች ቤተሰብን የወከሉ ጠበቃ በበኩላቸው "ልጃችን፣ እህታችን እና አክስታችንን በማጣችን በጥልቅ ሐዘን፣ ድንጋጤ እና አለማመን ውስጥ ነን" ሲሉ መናገራቸውን በርካታ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ግለሰቡ በኦስሎ ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረበት ወቅት ችሎቱ ለሕዝብም ሆነ ለሚዲያ ዝግ የተደረገ ሲሆን "ግለሰቡ ሚዲያ ባለበት ወቅት ሊገልጽ የሚችለውን ጉዳይ ስለፈራነው ነው" ብለዋል ዐቃቤ ሕግ።
ግለሰቡ ጽንፈኛ የሆኑ መልዕክቶችን እንዳያስተላልፍ የኖርዌይ ባለሥልጣናት ሊገድቡት እንደሚፈልጉ ተነግሯል።
ፖሊስ እና ፒኤስቲ የተሰኘው የኖርዌይ የስለላ ድርጅት የ18 ዓመቱ ወጣት "የቀኝ ክንፍ ጽንፈኛ" እየሆነ ስለመምጣቱ መረጃ እንደደረሳቸው ሚዲያዎች አስነብበዋል።
ታሚማ ኒብራስ ኢትዮጵያ ውስጥ በ1983 እንደተወለደች እና ወደ ኖርዌይም የመጣችው በታዳጊነቷ እንደሆነ በኦስሎ የሚገኘው ኤልደን የተሰኘ የሕግ ተቋም ባልደረባ የሆኑት አኔት ስክጀርቨን ኦርንክቬርን በቤተሰቧ ስም በወጣው መግለጫ አስታውቀዋል።
በኦስሎ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ እያጠናች ከልጆች እና ከታዳጊዎች ጋር ትሠራ እንደነበር መግለጫው አትቶ፤ ሥራዋም ያተኮረው በእኩልነት፣ በዘረኝነት እና በዓለም አቀፍ ግጭቶች ላይ ነበር።
"ቤተሰቧ እንዴት ግድያዋ ሊፈጸም ይችላል" የሚለውን ጭምር መልስ እንደሚፈልጉም መግለጫው አትቷል። በርካቶች ግድያዋን አውግዘው ምላሽ ሰጥተዋል።
ከእነዚህም መካከል የኦስሎ ከተማ አስተዳዳሪ ኢሮክ ላ ሶልበርክ "በካምፔን የተከሰተው ነገር በጣም አሳዛኝ ነው። በኦስሎ ወደ ሥራ መሄድ ችግር ሊሆን አይገባም ነበር" ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
በኖርዌይ እንዲህ ዘርን መነሻ ያደረጉ ጥቃቶች ሲፈጸሙ የመጀመሪያው አይደደለም፤ ከዚህ ቀደምም በርካታ የቀኝ አክራሪ ጥቃቶች ተፈጽመውባታል።
በአውሮፓውያኑ 2011 የቀኝ ክንፍ አክራሪው አንደር ቤህሪንግ ብሬይቪክ በኦስሎ በሚገኝ የመንግሥት መስሪያ ቤት ደጃፍ በአንድ መኪና ላይ ቦምብ በማፈንዳት 77 ሰዎችን መግደሉ ይታወሳል።
ይኸው ግለሰብ በሌበር ፓርቲ የወጣቶች ካምፕ ላይ እሳት ለኩሶ ነበር።
ከአምስት ዓመት በፊት ፊሊፕ ማንሻውስ የተባለ ግለሰብ ከኦስሎ ወጣ ባለ ስፍራ በሚገኝ መስጊድ ላይ ተኩስ ከፍቷል።
በርካቶች ተረባርበው ይህንን ጥቃት በማክሸፋቸው ጉዳት አልደረሰም።
ሆኖም ይህ ግለሰብ በመስጊዱ ላይ ጥቃት ከመክፈቱ በፊት ግማሽ እስያዊ የሆነችውን የማደጎ እህቱን በዘረኝነት ተነሳስቶ ገድሏታል።
ሁለቱም ግለሰቦች 21 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።

የሲቪል ማኅበራት ሕግ ረቂቅ ማሻሻያ በኢትዮጵያ ያለውን የሲቪል ማኅበራት እንቅስቃሴ ሊያዳክም ይችላል ሲል አምነስቲ አስጠነቀቀ
#ethiopia | ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ በሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ሕግ ላይ ሊደረግ የታሰበውን ማሻሻያ አጥብቆ በመቃወም፣ ረቂቅ ማሻሻያው ከጸደቀ “አገሪቱን ወደ ሙሉ የሲቪል ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ መዘጋት” እንደሚመራት አስጠንቅቋል።
አምነስቲ ባወጣው መግለጫ፣ ማሻሻያው የሲቪል ማኅበራት ቦርድን በማዋቀር ለመንግሥት አባላት ብዙ መቀመጫ በመስጠት የሲቪል ማኅበራትን ነፃነት እንደሚገድብ ገልጿል።
የታቀደው ማሻሻያ የሲቪል ማኅበራትን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር ሲሆን፣ በተለይም “ፖለቲካዊ ተሟጋችነት” በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ እንዳያገኙ ያግዳል፣ እና አንድ የሲቪል ማኅበር “ለአገር ደኅንነት አስጊ እንደሆነ ከተጠረጠረ” ምዝገባውን ሊያግድ ይችላል።
አምነስቲ ይህንን አሠራር በመቃወም፣ ቃሉ ግልጽ ባለመሆኑ መንግሥት በዘፈቀደ የሲቪል ማኅበራትን ሊያፍን እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።
በተጨማሪም ረቂቅ ማሻሻያው የሲቪል ማኅበራት የባንክ አካውንት ለመክፈትና ብድር ለመውሰድ ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ማግኘት እንደሚኖርባቸው ይገልጻል።
ሂውማን ራይትስ ዎች በተመሳሳይ መልኩ ከወር በፊት ባወጣዉ መግለጫው፣ ይህ ረቂቅ ህግ ከጸደቀ በኢትዮጵያ ውስጥ የሲቪል ማህበራት ነፃነት እና እንቅስቃሴ በእጅጉ ይገደባል የሚል ስጋት እንዳለው መግለፁ ይታወሳል ሲል ካፒታል በገጹ አስነብቧል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ በሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ሕግ ላይ ሊደረግ የታሰበውን ማሻሻያ አጥብቆ በመቃወም፣ ረቂቅ ማሻሻያው ከጸደቀ “አገሪቱን ወደ ሙሉ የሲቪል ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ መዘጋት” እንደሚመራት አስጠንቅቋል።

ሂውማን ራይትስ ዎች በተመሳሳይ መልኩ ከወር በፊት ባወጣዉ መግለጫው፣ ይህ ረቂቅ ህግ ከጸደቀ በኢትዮጵያ ውስጥ የሲቪል ማህበራት ነፃነት እና እንቅስቃሴ በእጅጉ ይገደባል የሚል ስጋት እንዳለው መግለፁ ይታወሳል።

1 year ago
ሳዑዲ አረብያ ሁለት ኢትዮጵያውያን በሞት ቀጣች
#ethiopia | ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያውያንን ትናንት በሞት ቀጣች። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) የሳዑዲ አተቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበው ስማቸው የተገለጸው ሁለቱ የኢትዮጵያ ዜጎች በሞት የተቀጡት አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር ተከሰው ነው። በሳዑዲ አረቢያ የዜና አገልግሎት መግለጫ መሠረት ሁለቱም ሀሽሽ የተባለውን አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር ጥፋተኛ ተብለው ነበር ። በዘገባው ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት ክሱን አረጋግጦ በሰዎቹ ላይ የሞት ቅጣት መበየኑም ተጠቅሷል። ሳዑዲ አረቢያ ከዚህ ዓመት ጥር ወር አንስቶ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ በሞት የቀጣቻቸው የውጭ ዜጎች ቁጥር ቢያንስ 101 ነው። በጎርጎሮሳዊው 2025 ሀገሪቱ በአጠቃላይ 189 ሰዎችን በሞት ቀጥታለች። ከመካከላቸው 88ቱ ዜጎቿ ናቸው። ባለፈው በጎርጎሮሳዊው 2024 ዓ.ም. ቢያንስ 338 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል። በ2023 ደግሞ በሞት የተቀጡት ቁጥር 170 ነበር። በሳዑዲ አረብያ የሚፈጸመው የሞት ቅጣት በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጥብቅ ተወግዟል። #dw

ድምፃዊቷ የአለማችን ኮከብ ተባለች !
ቤኒናዊቷ ድምፃዊት አንጄሊኬ ኪዲጆ በሆሊውድ ዝና ላይ የምድራችን ኮከብ ድምፃዊት አዋርድ በመሸለም የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት አርቲስት መሆን ቻለች ።
ይህም ክብር በዓለም ላይ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ነው።
ቤኒን ተወልዳ ያደገችውና በ1983 ዓ.ም በሀገሪቱ በነበረው የኮሚኒስት አገዛዝ ስር የነበረውን የፖለቲካ ጭቆና ወደ ፓሪስ ለመሰደድ የተገደደችው ድምፃዊቷ በፈረንሣይ ውስጥ ነፃነትን ብቻ ሳይሆን ተሰጥኦዋን ፈልጋ በማግኘት በአራት አስርት ዓመታት የስራ ዘመኗ አፍሮቢትን ከጃዝ፣ አር ኤንድ ቢ፣ ፈንክ እና የላቲን ሙዚቃ ክፍሎች ጋር በማዋሃድ 16 አልበሞችን አውጥታለች።
በዜማዎቿም የአፍሪካውያን ባህል አለባበስ ታሪክና የዜማ ስልቶች አስተዋዉቃለች ።
በዚህም 15 ጊዜ የግራሚ እጩነት 5 ጊዜ ደግሞ ግራሚ አዋርድ ማሸነፍ ችላለች ።
አሁንም በዓለም ላይ ካሉት ድንቅ የሽልማት ደረጃዎች ውስጥ አንዱ የሆነዉን Kidjo የኮከብ ሽልማት በመመረጥ በአፍሪካ የመጀመርያዋ አርቲስት ሁናለች ።
ከሙዚቃ ባሻገር፡ ተሟጋች፣ አስተማሪ፣ ለውጥ ፈጣሪ
የሆነችውን ኪዲጆን በባቶንጋ ፋውንዴሽን በኩል የሴቶች ትምህርት ሻምፒዮን የሆነች እና ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነት፣ ለሰብአዊ መብቶች እና ለአየር ንብረት እርምጃዎች ተከታታይ ጠበቃ ስትሆን የዩኒሴፍ በጎ ፈቃድ አምባሳደር ነች።
ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና እንደ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ያሉ ዓለም አቀፍ መድረኮችን በመጋበዝ ክብርን አትርፋለች ።
ኪዲጆ ስለ ሽልማቱ ስትጠየቅም “በዚህ ዓለም ውስጥ በሁሉም ቦታ ቦታ አለህ።" ስትል ተደምጣለች።ለረጂም አመታት ሆሊውድ ቦሊዩድ አርቲስቶች ብቻ ተይዞ የነበረን
ይህን የኮከብነት ክብር ማግኘት በመላው አፍሪካ ኩራትና ውክልና ሌሎች አርቲስቶችንም የሚያኮራ ነው ተብሏል ።
የኔታ ትዩብ ዘጋቢ ታዴ የማመይ ልጅ

በሳውዲ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጪ ዜጎች በሞት መቀጣታቸው ተነገረ !
በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጪ ዜጎች በአድንዛዥ እፅ ምክንያት የሚፈጸም የሞት ቅጣት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አምነስቲ በሪፖርቱ ላይ ገልጿል።
ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ዓመት 345 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን፣ ይህም አምነስቲ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ነው ብሏል።
ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 180 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ያለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ፣ ይህም ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከጥር 2014 እስከ ሰኔ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ሳዑዲ አረቢያ 1,816 ሰዎችን በሞት መቅጣቷን የአገሪቱ የፕሬስ ኤጀንሲ አስታውቋል።
በሰኔ 2025 ብቻ አገሪቱ 46 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን 37ቱ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ ሲሆን ይህ ማለት ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ በቀን በአማካይ ከአንድ ሰው በላይ በሞት ይቀጣል ማለት እንደሆነ አምነስቲ በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስፍሮታል።

በሳውዲ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጪ ዜጎች በሞት ተቀጡ
#ethiopia | በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጪ ዜጎች በአድንዛዥ እፅ ምክንያት የሚፈጸም የሞት ቅጣት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አምነስቲ በሪፖርቱ ላይ ገልጿል።
ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ዓመት 345 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን፣ ይህም አምነስቲ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ነው ብሏል።
ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 180 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ያለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ፣ ይህም ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከጥር 2014 እስከ ሰኔ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ሳዑዲ አረቢያ 1,816 ሰዎችን በሞት መቅጣቷን የአገሪቱ የፕሬስ ኤጀንሲ አስታውቋል።
በሰኔ 2025 ብቻ አገሪቱ 46 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን 37ቱ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ ሲሆን ይህ ማለት ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ በቀን በአማካይ ከአንድ ሰው በላይ በሞት ይቀጣል ማለት እንደሆነ አምነስቲ በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስፍሮታል። #hagerie_tv

Comments