Logo
YenetaTube
ቡርኪናፋሶ የተመሳሳይ ጾታ ግኑኝነት የሚከለክል ህግ አፀደቀች !

‎በካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ የሚመራው የቡርኪና ፋሶ የሽግግር ፓርላማ፤ ካቢኔ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻም ሆነ ግኑኝነት የሚከለክል ህግ ማፅደቁ ተነገረ ።

‎ ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ወንጀል በሚያደርግ መልኩ የሀገሪቱን ቤተሰብ ህግ ለማሻሻል ያሳለፈውን ውሳኔ በመከተል ይህንን ድርጊት የሚከለክል አዋጅ ያፀደቀው ፓርላማው ድርጊቱን ገላጭ የሆኑ ባንዴራ ቀለማት ተግባራትም መፈፀም ዘብጥያ እንደሚያስወርዱ ገልጿል ።

‎ሰኞ ዕለት በሙሉ ድምጽ የጸደቀው አዲሱ አዋጅ የተመሳሳይ ጾታን ግንኙነት ውስጥ የተገኙ ሰዎችን እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት እንደሚቀጡ በሀገሪቱ ዜግነት የሌላቸው አጥፊዎች ከአገር እንደሚባረሩ። ደንግጓል።

‎በ1960 ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ያገኘቸው
‎ከሳህል ሀገራት አንዷ የሆነችው ቡርኪና ፋሶ ከዚህ ቀደም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከፈቀዱ 22 የአፍሪካ ሀገራት አንዷ የነበረች ሲሆን ከዚህ በኋላ ግን ከማህበረሰቡ የሚያስገልል በገዘብና በእስር የሚስቀጣ የቤተሰብ ህግ በማድረግ በአንድ ድምፅ አጽድቋል ።

‎አዲሱ ህግ ወዲያውኑ ተግባራዊ ይሆናል ፣በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የእስር ቅጣት እና የገንዘብ ቅጣት አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ የፍትህ ሚኒስትር ኢዳሶ ሮድሪግ ባያላ በመንግስት ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
‎ህጉ ተግባራዊ እንዲሆን የሚጠበቀው ቀጣይ ሂደት የሀገሪቱ ወታደራዊ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ፊርማ እንደሆነ ፋሶ 24 የዜና ወኪል ዘግቧል።

‎ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ በቀኝ ግዛት የተገዙ ሀገራት ፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አቋም እያሳዩ የሚገኝ ሲሆን የቡርኪና ፋሶ አጋር የሆነችው ማሊም ባሳለፍነው ህዳር ወር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ወንጀል የሚያደርግ ህግ ያፀደቀች ሲሆን ጋና እና ኡጋንዳና ናይጄሪያ ይጠቀሳሉ ።

‎ይህን ተከትሎ መግለጫ ያወጣው የመብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ማክሰኞ እንዳስታወቀው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀል መደረጉ የእኩልነት መብትን የሚጥስ “አስደንጋጭ ውድቀት ነው” ብሏል። የጁንታ ዋና አዛዥ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ውሳኔውን እንዲቀለብስ አሳስበዋል።

‎የሀገሪቱ ፍትህ ሚኒስትር በበኩላቸው ይህ ዉሳኔ የቤተሰብ የማህበረሰብ ደህንነት በዜግነት እና ሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ በመሆኑ ተፈፃሚ ይሆናል ብለዋል ሲሉ ያስነበቡት AP, AFP, Reuters, dpa, KNA የዜና ወኪሎች ናቸው ።


‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ



9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.