Logo
SeledaPost
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እንዲታሰሩ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ
 
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርምር፣ ተሟጋችነት፣ የፖሊሲ እና የዘመቻዎች ከፍተኛ ዳይሬክተር ኤሪካ ጉዌቫራ ሮዛስ የእስራኤል መሪ በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት እንዲታሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።ሮዛስ በቅርቡ ኔታንያሁ የአሜሪካ ከተማን ቢጎበኝ እንዲታሰሩ የጠየቁትን የኒውዮርክ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ የተናገሩትን አስተጋብተዋል።
 
ሮዛስ በኤክስ ላይ በጻፉት መልዕክት “የአሜሪካ ባለስልጣናት የሰብአዊ መብቶችን ማስከበር እና የህግ የበላይነትን ማክበር አለባቸው” ሲሉ ተናግረዋል።ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በ2024 በኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ማዉጣቱ ይታወሳል፡፡ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው የዘር ማጥፋት ጦርነት ወቅት የጦር ወንጀሎችን ፈጽማለች በሚል ክስ ቀርቧል።
 
በሌላ መረጃ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በዌስት ባንክ ታል መንደር በተፈፀመው የተኩስ ልውውጥ አንድ እስራኤላዊ ከተገደለ በኋላ አጥብቀው ምላሽ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።"በአሸባሪዎቹ እና በሚያደራጁት እንዲሁም በሚደግፉት ላይ በሙሉ ኃይላችን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል፡፡
 
አክለዉም በይሁዳና በሰማሪያም የሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ቦታ እንዲያገኝ አንፈቅድም ሲሉ ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።የፍልስጤም ባለስልጣናት የእስራኤል ኃይሎችም ሆኑ ሰፋሪዎች በስፍራዉ ላይ አራት ፍልስጤማውያንን በመግደል ተጠያቂ እንደሆኑ ተናግረዋል።

Seledadotio
Seledadotio
14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.