ድምፃዊቷ የአለማችን ኮከብ ተባለች !
ቤኒናዊቷ ድምፃዊት አንጄሊኬ ኪዲጆ በሆሊውድ ዝና ላይ የምድራችን ኮከብ ድምፃዊት አዋርድ በመሸለም የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት አርቲስት መሆን ቻለች ።
ይህም ክብር በዓለም ላይ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ነው።
ቤኒን ተወልዳ ያደገችውና በ1983 ዓ.ም በሀገሪቱ በነበረው የኮሚኒስት አገዛዝ ስር የነበረውን የፖለቲካ ጭቆና ወደ ፓሪስ ለመሰደድ የተገደደችው ድምፃዊቷ በፈረንሣይ ውስጥ ነፃነትን ብቻ ሳይሆን ተሰጥኦዋን ፈልጋ በማግኘት በአራት አስርት ዓመታት የስራ ዘመኗ አፍሮቢትን ከጃዝ፣ አር ኤንድ ቢ፣ ፈንክ እና የላቲን ሙዚቃ ክፍሎች ጋር በማዋሃድ 16 አልበሞችን አውጥታለች።
በዜማዎቿም የአፍሪካውያን ባህል አለባበስ ታሪክና የዜማ ስልቶች አስተዋዉቃለች ።
በዚህም 15 ጊዜ የግራሚ እጩነት 5 ጊዜ ደግሞ ግራሚ አዋርድ ማሸነፍ ችላለች ።
አሁንም በዓለም ላይ ካሉት ድንቅ የሽልማት ደረጃዎች ውስጥ አንዱ የሆነዉን Kidjo የኮከብ ሽልማት በመመረጥ በአፍሪካ የመጀመርያዋ አርቲስት ሁናለች ።
ከሙዚቃ ባሻገር፡ ተሟጋች፣ አስተማሪ፣ ለውጥ ፈጣሪ
የሆነችውን ኪዲጆን በባቶንጋ ፋውንዴሽን በኩል የሴቶች ትምህርት ሻምፒዮን የሆነች እና ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነት፣ ለሰብአዊ መብቶች እና ለአየር ንብረት እርምጃዎች ተከታታይ ጠበቃ ስትሆን የዩኒሴፍ በጎ ፈቃድ አምባሳደር ነች።
ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና እንደ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ያሉ ዓለም አቀፍ መድረኮችን በመጋበዝ ክብርን አትርፋለች ።
ኪዲጆ ስለ ሽልማቱ ስትጠየቅም “በዚህ ዓለም ውስጥ በሁሉም ቦታ ቦታ አለህ።" ስትል ተደምጣለች።ለረጂም አመታት ሆሊውድ ቦሊዩድ አርቲስቶች ብቻ ተይዞ የነበረን
ይህን የኮከብነት ክብር ማግኘት በመላው አፍሪካ ኩራትና ውክልና ሌሎች አርቲስቶችንም የሚያኮራ ነው ተብሏል ።
የኔታ ትዩብ ዘጋቢ ታዴ የማመይ ልጅ

11 months ago