ከህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ጽሕፈት ቤት ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የተላከ ባለ ሁለት ገጽ ደብዳቤ
ሙሉ ደብዳቤው እንደሚከተለው ይነበባል
አፋጣኝ ሰብአዊ ጣልቃ ገብነት እንዲደረግ የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ
ለክቡር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ጉዳዩ፦ በትግራይ ውስጥ በተፈናቃዮች ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የረሃብ እልቂት እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መጣስ
ክቡራን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አስታራቂዎች፤
በትግራይ፣ ኢትዮጵያ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊና ሆን ተብሎ የተደረገ የረሃብ ማባባስ ሁኔታ በተመለከተ ይህንን ደብዳቤ በከፍተኛ አጣዳፊነት እንጽፋለን።
ከህዳር 2013 ዓ.ም (ኖቬምበር 2020) ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ከቀጠለው ሞት በኋላ፣ በታህሳስ 2018 (ዲሴምበር 2025) የሟቾች ቁጥር ከጦርነቱ ጊዜ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
በትግራይ በሚገኙ የተፈናቃይ ማዕከላት — ህጻጽ፣ ሽሬ፣ ዓድዋ፣ ዓቢይ ዓዲ፣ ዓዲግራት፣ መቐለ እና ሌሎችም — በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የፕሪቶሪያውን ስምምነት አንቀጽ 4 በሚጥስ መልኩ ስልታዊ ለሆነ ረሃብ ተጋልጠዋል።
የሰዎች አካል ወደ አፅምነት ተቀይሯል፣ ቁስላቸው ላይ ዝንብ ይወርራል፤ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በ2015-2016 (2023-2024) በሳምንት አንዴ ከነበረበት አሁን በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ወደ መሆን ተሸጋግሯል።
ህፃናትና አዛውንቶች በከፍተኛ ቁጥር እያለቁ ነው።
የፌዴራል መንግስት ጥሰቶች፡-
* ሀሰተኛ መግለጫዎች፡- የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዕርዳታ እያቀረብኩ ነው የሚለው ፕሮፓጋንዳ እንጂ በተግባር ወደ ተፈናቃዮች የደረሰ ትርጉም ያለው ዕርዳታ የለም።
* ቀጥተኛ እንቅፋት መፍጠር፡- መንግስት ማህበረሰቡ የሚያደርገውን የርስ በርስ መረዳዳት ወንጀል አድርጎታል። በማህበራዊ ሚዲያ ገንዘብ የሚያሰባስቡ የማህበረሰብ አንቀሳቃሾች ዛቻ እየደረሰባቸው ነው። የቲክቶከሮች በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ወደ መንግስት አካውንት እንዲያስገቡ የተገደዱ ሲሆን የሕዝብ መረዳጃ ሀብቶችም እየተወረሱ ነው።
ከዳያስፖራ የሚላክ የገንዘብ ድጋፍም ታግዷል።
* ያልተፈታው የስር መሰረት ችግር፡- ከ1 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች አሁንም በወረራ እና በ"ፅዳት" ስር ወደሚገኘው ምዕራብ ትግራይ መመለስ አልቻሉም።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ተመላሾችን በሚመለከት የገባው ቃል ሳይፈጸም ቀርቷል።
አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚፈለጉ ነጥቦች፡-
* አስቸኳይ ሰብአዊ ተደራሽነት፡- የመንግስትን እንቅፋት በመዝለል ምግብ፣ ውሃ እና የህክምና ቁሳቁሶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለሁሉም የተፈናቃይ ማዕከላት እንዲደርሱ መጠየቅ።
* ገለልተኛ ምርመራ፡- የታህሳስ 2018ቱን የችግር መባባስ፣ የአምስት ዓመቱን የሞት መጠን እና ስልታዊ የዕርዳታ ክልከላን የሚያጠና የሐቅ መፈለጊያ ልዑክ በአስቸኳይ መሰማራት። በ60 ቀናት ውስጥም ይፋዊ ሪፖርት ማቅረብ።
* የፕሪቶሪያ ስምምነትን ማስከበር፡- ኢትዮጵያ በአንቀጽ 4 ላይ ለፈጸመቻቸው ጥሰቶች ተጠያቂ ማድረግ። ተፈናቃዮች ወደ ምዕራብ ትግራይ የሚመለሱበትን ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ መጠየቅ።
* ገደቦችን ማንሳት፡- መንግስት በዜጎች እና በዳያስፖራ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረት ላይ የጣለውን ክልከላ እንዲያቆም ጫና ማድረግ። የተወረሱ የዕርዳታ ገንዘቦችን መመለስ።
* ይፋዊ ተጠያቂነት፡- ድርጊቱን የሚያወግዙ መግለጫዎችን ማውጣት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ማድረግ፣ እንዲሁም ዕርዳታ በሚያግዱ ባለስልጣናት ላይ የታለመ ማዕቀብ መጣል ይገኙበታል።
ከአምስት ዓመታት እልቂት በኋላ፣ ታህሳስ 2025 (2018 ዓ.ም) የችግሩ ሁኔታ ከከረረ ቀውስ ወደ አስከፊ እልቂት የተሸጋገረበት ወቅት ነው። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያየ ቃል የተገባላቸው ህዝቦች በከፍተኛ ቁጥር እያለቁ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተተገበረ ሊቆጠር አይችልምአሁን ዝምታን መምረጥ ተባባሪነት ነው።
የተፈናቃዮች መጠለያ ማዕከላት የጅምላ መቃብር ሳይሆኑ በፊት፣ የፕሪቶሪያ ተስፋ የትውልድ እፍረት ሳይሆን በፊት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለንጊዜ የሚለካው በየቀኑ በሚቆጠሩ አስከሬኖች ነው አሁኑኑ እርምጃ ይወሰድ።
በአክብሮት እና በአስቸኳይ የቀረበ፣
(ፊርማ)
ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ፒ.ኤች.ዲ)
የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር
ለግልባጭ፡-
* ተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (UN OCHA)
* ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC)
* ድንበር የለሽ ሐኪሞች (MSF)
* ሂውማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch)
* አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International)

5 months ago