15 hours ago
ሳዑዲ አረቢያ 4 ኢትዮጵያውያንን በሞት ስትቀጣ፤ ለ1,655 ዜጎች ደግሞ ምህረት አደረገች።
ሳዑዲ አረብያ በዚህ ሳምንት 4 ኢትዮጵያውን በሞት ስትቀጣ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ 1655 ዜጎቿ በምህረት እንዲለቀቁ ማደረጓን አስታውቃለች።
የበሳዑዲ የሞት ቅጣት ተበይኖባቸው ፍርዳቸውን በተለያዩ እስር ቤቶች ሆነው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዳሉም ከቤተሰቦቻቸው አንዱ ለዶቼቬለ ተናግሯል።
በሳዑዲ አረብያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር መረጃ መሠረት ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ሁለት ኢትዮጵያውያን በናጅራን ግዛት፣ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ/ም ሌሎች ሁለት ኢትዮጵያውያን በአሲር ግዛት በስቅላት ተገድለዋል።
አራቱም ኢትዮጵያውያን በሞት የተቀጡት ወደ ሳዑዲ አረቢያ አደንዛዥ ዕፅ ይዘው በመግባታቸው ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ እስር ቤት የሚገኙ 1655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ ምህረት እንዲሰጣቸው ማድረጉን በዚሁ ሳምንት አስታውቋል።
በሳዑዲ አረብያ በስቅላት ስለተገደሉትም ሆነ በምኅረት ስለተለቀቁት ኢትዮጵያውያን ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ዶቼቬለ ለኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነበያት ጌታቸው የእጅ ስልክ ላይ ቢደውልም ስልካቸው አልተነሳልንም። #dw
Seledadotio

22 hours ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው
እዉቅናን የሚያገኙት 100 ታዋቂ አፍሪቃውያን የአመራር እና ቢዝነስ ጉባኤ ላይ ነዉ።
የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው መሆኑ ተዘገበ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ ማራኪሽ ላይ በሚካሄደዉ ታዋቂ አፍሪቃዉያን የአመራር እና ቢዝነስ ጉባኤ ላይ መሆኑ ተዘግቧል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር፤ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ እና የቀድሞዋ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ዶ/ር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ዘንድሮ በሚካሄደው 100 ታዋቂ አፍሪቃውያን የአመራር እና ቢዝነስ ጉባኤ በሞሮኮ ማራኬሽ ላይ፤ ክብር እና እውቅና ከሚሰጣቸዉ ታዋቂ የአፍሪቃ መሪዎች እና ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል።
ጉባኤዉ፤ በአህጉሪቱ እና ከአህጉሪቱ ዉጭ ባሉ ሀገራት መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ ዲፕሎማቶች እና ለውጥ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት እያደገ የመጣ ተሳትፎን ተከትሎ በማራኬሽ ሞሮኮ ከሰኔ 19 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2018 እንደሚካሄድ የዝግጅቱ አዘጋጆች አስታውቀዋል። ይፋ በተደረገዉ ዘገባዉ መሰረት፤ በዳቭዳን የሰላም እና የጥብቅና ፋውንዴሽን እና በ100 በጣም ታዋቂ የሰላም ቁንጮ የአፍሪካ አጋሮች ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ይህ ዓመታዊ ጉባኤ፤ ልህቀትን ለማክበር፣ ፈጠራን ለማራመድ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስፈን፣ ድንበር ዘለል አጋርነቶችን ለማጠናከር እና ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት የሚሰራ የአፍሪቃ ግንባር ቀደም መድረኮች አንዱ ነው።
DW Amharic

23 hours ago
Book your flight with Ethiopian Airlines from Bujumbura to our online destinations worldwide and save USD 50.
https://www.ethiopianairli...
#flyethiopian #bujumbura
https://www.ethiopianairli...
#flyethiopian #bujumbura
2 days ago
የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር መቐለ ዉስጥ ተወያዩ::
የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በቅርቡ የትግራይ ክልል ርዕሰ-መስተዳድርነታቸውን መልሰው ከተረከቡት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር መቐለ ዉስጥ ተወያዩ። የ89 ዓመቱ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ወደ መቐለ የተጓዙት የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተፈራረሙትን ግጭት የማቆም ሥምምነት አፈጻጸም የመከታተል ኃላፊነት የተጣለባቸውን ወታደራዊ ባለሙያዎች አስከትለው ነው።
የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ኦባሳንጆ እና አብረዋቸው ከተጓዙ ልዑካን ተገናኝተው መነጋገራቸውን በፌስቡክ ፎቶግራፎች አስደግፎ ባሠራጨው መልዕክት አስታውቋል።
ከቅርብ ወራት ወዲሕ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና የህወሓት ልዩነት እየተካረረ ነዉ። ህወሓት በጳጉሜ 2012 በተካሔደ ምርጫ የተቋቋመ የክልል ምክር ቤቱን ወደ ሥራ በማስመለስ ደብረፅዮን ርዕሰ-መስተዳድርነቱን እንዲረከቡ አድርጓል።
ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ "ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የአፍሪካ ኅብረትን ጥረት እንዲደግፉ" በኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ ዳግም የተሾሙት ከአንድ ወር ገደማ በፊት ነበር። የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ከጥቅምት 2013 እስከ ጥቅምት 2015 የተካሔደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ግጭት በማቆም ሥምምነቱ እንዲገታ የአፍሪካ ኅብረትን አደራዳሪነት መርተዋል።
DW Amharic #amharic

7 days ago
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ከጠዋቱ 1፡00 – 8፡00
በአዲስ አበባ ብሔረ ፅጌ፣ በአዲስ ታየር ፋብሪካ፣ በቀይ አፈር፣ በሳሪስ አቦ፣ በቦል ቡልቡላ፣ በአዋሽ ሌዘር ፋብሪካ፣ በሳሪስ አደይ አበባ፣ በአዲስ ሰፈር፣ ኦስካ ሜታል ፋብሪካ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 3፡00 – 9፡00
በካዎ ጄጄ ፋብሪካ፣ 40/60 ኮንዴሚኒየም፣ በአወልያ፣ በአስኮ ገብርኤል፣ በአዲስ ሰፈር፣ በሚኪሊላንድ፣ በሳንሱሲ፣ በከታ መምህራን ሰፈር እና አካባቢው
✅ከጠዋቱ 12፡00 –11፡00
የአዳሚ ቱሉ ገንዳ አርባ 132 ኪ.ቮ አግሮ ኢንዱትሪ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት በታወር ቁጥር 3 እና በቁጥር 4 መካከል የሚገኘው ጀላን 33 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ መስመር የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
✅ከጠዋቱ 2፡00 – 11፡00
መቀሌ ማጂክ ትምህርት ቤት፣ መከላኪያ ኮንዶሚኒየም፣ ደብረ ዳሞ፣ ሓወልቲ፣ ሰማዕታት፣ ዲ.ደብልዩ (DW) ቢሮ፣ ፕላኔት ሆቴል፣ አብርሃ ካስል፣ ማዕበል ሬስቶራንት፣ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ጅብሩክ፣ ቀደማይ ወያኔ፣ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፣ መስኪድ፣ ቀበሌ 04 እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡30 – ምሽቱ 4፡00
• ወንጂ እርሻ፣ ፖሊስ ኮሌጅ ፣ AISO4፣ AIS፣ አዋሽ መልካሳ፣ ሲሬ፣ ሁሩታ፣ ዴራ፣ ዲና ፉድ ኮምፕሌክስ፣ አሉሚኒየም ሰልፌት (Aluminium Sulphate) ፋብሪካ/ኮምፕሌክስ (በፌዝ ተጠቃሚነቱ ይለያያል)።
✅ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡00
ጁኒፐር ግላስ ፋብሪካ ፣ደብረ ብርሃን ከተማ (ሀቢታት፣ ጮሌ እና ተባሴ) ፣ የባትሪ ፋብሪካ፣ ሞሪጋ ፋብሪካ፣ ደጋ ውሃ ፋብሪካ፣ ሐገረ ማርያም፣ ጊናገር፣ ጫጫ፣ ሸኖ አና አካባቢዎች
✅ከቀኑ 7፡00 – 11፡00
ደብረ ብርሃን ከተማ፣ አጎንሌላ፣ መንዲዳ፣ ደነባ አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

👉በአዲስ አበባ ብሔረ ፅጌ፣ በአዲስ ታየር ፋብሪካ፣ በቀይ አፈር፣ በሳሪስ አቦ፣ በቦል ቡልቡላ፣ በአዋሽ ሌዘር ፋብሪካ፣ በሳሪስ አደይ አበባ፣ በአዲስ ሰፈር፣ ኦስካ ሜታል ፋብሪካ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 3፡00 – 9፡00
👉በካዎ ጄጄ ፋብሪካ፣ 40/60 ኮንዴሚኒየም፣ በአወልያ፣ በአስኮ ገብርኤል፣ በአዲስ ሰፈር፣ በሚኪሊላንድ፣ በሳንሱሲ፣ በከታ መምህራን ሰፈር እና አካባቢው
✅ከጠዋቱ 12፡00 –11፡00
👉የአዳሚ ቱሉ ገንዳ አርባ 132 ኪ.ቮ አግሮ ኢንዱትሪ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት በታወር ቁጥር 3 እና በቁጥር 4 መካከል የሚገኘው ጀላን 33 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ መስመር የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
✅ከጠዋቱ 2፡00 – 11፡00
👉መቀሌ ማጂክ ትምህርት ቤት፣ መከላኪያ ኮንዶሚኒየም፣ ደብረ ዳሞ፣ ሓወልቲ፣ ሰማዕታት፣ ዲ.ደብልዩ (DW) ቢሮ፣ ፕላኔት ሆቴል፣ አብርሃ ካስል፣ ማዕበል ሬስቶራንት፣ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ጅብሩክ፣ ቀደማይ ወያኔ፣ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፣ መስኪድ፣ ቀበሌ 04 እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡30 – ምሽቱ 4፡00
👉ወንጂ እርሻ፣ ፖሊስ ኮሌጅ ፣ AISO4፣ AIS፣ አዋሽ መልካሳ፣ ሲሬ፣ ሁሩታ፣ ዴራ፣ ዲና ፉድ ኮምፕሌክስ፣ አሉሚኒየም ሰልፌት (Aluminium Sulphate) ፋብሪካ/ኮምፕሌክስ (በፌዝ ተጠቃሚነቱ ይለያያል)።
✅ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡00
👉ጁኒፐር ግላስ ፋብሪካ ፣ደብረ ብርሃን ከተማ (ሀቢታት፣ ጮሌ እና ተባሴ) ፣ የባትሪ ፋብሪካ፣ ሞሪጋ ፋብሪካ፣ ደጋ ውሃ ፋብሪካ፣ ሐገረ ማርያም፣ ጊናገር፣ ጫጫ፣ ሸኖ አና አካባቢዎች
✅ከቀኑ 7፡00 – 11፡00
👉ደብረ ብርሃን ከተማ፣ አጎንሌላ፣ መንዲዳ፣ ደነባ አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

Sponsored by
Surafel
8 days ago
u12a0u122du1230u1293u120d u1260u12a2u1275u12eeu1335u12eb u12cdu1235u1325 u1265u12d9 u12f0u130bu134a u12a0u1208u12cd - ud83dudc49https://youtu.be/y0bKkD406...
አርሰናል በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ደጋፊ አለው - 👉https://youtu.be/y0bKkD406...
10 days ago
በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኅብረቱ አባል አገራት ኤምባሲዎች ስለ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ያወጡት መግለጫ
በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኅብረቱ አባል አገራት ኤምባሲዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ምርጫ ያልተካሔደባቸው የምርጫ ክልሎች ድምጽ የመስጠት “ዕድል ይሰጣቸዋል” የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ።
በኢትዮጵያ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ መካሄዱን በበጎ እንደሚቀበሉ የኅብረቱ ተልዕኮ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ 25 ኤምባሲዎች ጋር በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ምርጫው በተካሔደ በሁለተኛው ቀን ዛሬ ረቡዕ መግለጫውን ከኅብረቱ ጋር ካወጡ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኤምባሲዎች መካከል የጀርመን እና የፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ተልዕኮዎች ይገኙበታል። የአውሮፓ ኅብረት አባል አገር ያልሆኑት ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊትዘርላንድም ምርጫን በተመለከተ በመግለጫው አቋማቸውን ካንጸባረቁ መካከል ናቸው።
በመግለጫው “የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎች እና የሲቪል ማኅበራት ተዋናዮች ያበረከቱትን አስተዋጽዖ እናደንቃለን” ብለዋል።
የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እንደ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ያላቸውን ጠቃሚ ሚና እንገነዘባለን ያለው የጋራ መግለጫው ዘገባዎቻቸውን በጉጉት እንደሚጠብቅም አስታውቋል።
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ ማካሄድ ያልቻሉ የምርጫ ክልሎች በሙሉ ይህን ለማድረግ እድሉ እንደሚሰጣቸው ተስፋ እናደርጋለን ሲል በኢትዮጵያ የኅብረቱ ልዑካንና የኅብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች የጋራ መግለጫ አስታውቋል።

11 days ago
u12c8u12f0 u1235u122b u1308u1265u1270u1293u120d! ud83dudc49 https://youtu.be/BbbTGvDou...
ወደ ስራ ገብተናል! 👉 https://youtu.be/BbbTGvDou...
22 days ago
አስገዳጁ የቤት ኪራይ ውል አዋጅ ሊያበቃ ነው፦ ምን ትላላችሁ?
*የቤት ኪራይ ዋጋ ጉዳይ እንዴት አደረጋችሁ?
*ለቤት ኪራይ የምትከፍሉት ተመጣጣኝ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?
ቤት አከራዮች ቤት ካከራዩ በኋላ ለሁለት ዓመት የቤት ኪራይ እንዳይጨምሩ እና ያከራዩትንም ቤት እንዳያስለቅቁ ይከለክል የነበረው አዋጅ ተግባራዊነቱ ሊያበቃ ጥቂት ጊዜያት ቀርተውታል ። የአዋጁ ተግባራዊነት መጠናቀቅን ቤት ተከራዮች በስጋት ተውጠው ቤት አከራዮች ደግሞ ጓግተው ነው የሚጠብቁት ። ምን ይከሰት ይኾን?
መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ የነበረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሳምንታት ብቻ ነው የቀሩት ። አስገዳጁ የሁለት ዓመት የውል ዘመን እና የዋጋ ቁጥጥር ማዕቀፍ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ መጠነኛ መረጋጋትን ፈጥሮ መቆየቱ ይነገርለታል ። የአዋጁ ተግባራዊነት ሊያበቃ ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቀርቷል ።
DW
seledadotio

23 days ago
በትግራይ ትምህርት ቤቶች በደመወዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ምክንያት ግንቦት 30 ሊዘጉ ነዉ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከነዳጅ እጥረት፣ ከደመወዝ መዘግየት እና ከትምህርት መሠረተ ልማት መስተጓጎል ጋር በተያያዘ ምክንያት ከታቀደው አንድ ወር ቀደም ብሎ እንደሚያበቃ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉሽ የፌደራል መንግሥት የበጀት ድልድል እና የነዳጅ አቅርቦቶችን መከልከሉ በክልሉ «የመምህራን ደሞዝ በወቅቱ እና በአግባቡ መክፈል» የማይቻል አድርጎታል ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል።
የክልሉ የትምህርት ቢሮ ፤ ለትግራይ ክልል መገናኛ ብዙኃን መግለጫ መስጠቱን ለዶቼ ቬለ የተናገረዉ በመቀሌ ነዋሪ የሆነዉ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አፅብሃ ፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች የ 2018 የትምህርት ዘመን ግንቦት 30 እንዲዘጋ ወስኗል። ትምህርት ቢሮዉ ለዚህ ምክንያት የሰጠዉ አንደኛ -የፌደራል መንግሥት በጀት እየላከ ባለመሆኑ ፤ ሁለተኛ ፤ መምህራን ደሞዝ እያገኙ ስላልሆነ ሥራቸዉን እየለቀቁ በመዉጣታቸዉ ትምህርት ቤቶች እየተዘጉ በመሆኑ ነዉ ሲል አክሏል። ወላጆች ልጆቻቸዉን ትምህርት ቤት የሚያደርሱበት ነዳጅ ባለማግኘታቸዉ የግል ትምህርት ቤቶች እንዲሁ ፤ ግንቦት 30 ቀን እንዲዘጉ ተወስኗል። ለ12 ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ግን እንደሌሎች ክልሎች ሁሉ በትግራይ ክልልም ተማሪዎች በተመሳሳይ ቀን ለፈተና ይቀመጣሉ።
ይሁን እና ይህን የትግራይ ክልል የትምህርት ቢሮ መግለጫ የሰሙ የክልሉ ነዋሪ፤ ተማሪዎቹ ትምህርታቸዉ ቀደም ብሎ እንዲዘጋ የተወሰነዉ፤ ምናልባት በትግራይ ክልል እና በፊደራል መንግሥት መካከል ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ዉስጥ ገብቷል ሲል ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አፅብሃ ለዶቼ ቬለ DW ገልጿል።
ባለፈዉ ሳምንት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሃት) መካከል የነበረዉ ዉዝግብ ሰሞኑን ረገብ ያለ መስሏል። አዲስ የተሰማ ነገርም የለም ሲል ጋዜጠኛዉ አክሎ ለዶቼ ቬለ ተናግሯል።

25 days ago
«ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ከተባለዉ ዉሳኔ ጀርባ ያሉት ከ 100 የማይበልጡ ናቸዉ» ሳሞራ ዩኑስ
የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ በትግራይ ክልል ህወሓትን ወደ ስልጣን ለመመለስ የተደረገዉን ውሳኔ አጥብቀዉ ተቃወሙ። በዚህ ሳምንት ከውጋሕት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "የቀድሞ አመራሮች እና ምክር ቤት (በትግራይ) ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑ ህዝቡን ከልክ በላይ ጭንቀት ውስጥ ከቶታል „ብለዋል። ሳሞራ የህወሓት ነባር ታጋይና አባልም ነበሩ።
ሳሞራ አክለውም የትግራይ ህዝብ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የግል ንብረት ስላልሆነ በፓርቲው ታግቶ መቀመጥ የለበትም ሲሉም አክለዋል። ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልል ምክር ቤትና አስተዳደር «ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ከተባለዉ ዉሳኔ ጀርባ ያሉት ከ 100 የማይበልጡ ናቸዉ፣ ውሳኔዉን ያሳለፉትም ከተጠያቂነት ለመዳን ያሰበ ዓላማን የያዘ ነዉ» ብለዉ እንደሚያስቡ ሳሞራ ዩንስ ተናግረዋል።

የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት ተመሠረተ
«የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» የተባለ ስብስብ አዲስ አበባ ዉስጥ ተቋቋመ። የተለያዩ የሃገር ዉስጥ መገናኛዎች እንደዘገቡት፤ ከስምንት ወራት በፊት የትግራይ ለውጥ ፈላጊ ኃይሎች ንቅናቄ በሚል የተቋቋመው ማህበር ማኒፌስቶውን በማሻሻል «የትግራይ የሰላም ለውጥ ምክር ቤት» በሚል አዲስ አበባ ላይ የመጀመሪያ የምስረታ ጉባዔውን ትናንት ሰኞ አደርጓል።
በምክር ቤቱ ምስረታ ጉባዔ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተደራዳሪዎች መካከል የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ጀነራል ጎዕሽ ገብረ ፣ ሰባት ማህበራዊ መሠረታቸውን ትግራይ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የቀድሞ የክልሉ አመራሮች፣ የቀድሞ ወታደራዊ አዛዦችና ታጋዮች እንዲሁም ማህበራት መገኘታቸዉን የአገር ዉስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። አቶ ጌታቸዉ ረዳ እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ በቅርቡ መቀሌ እንደሚገባ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ ምስረታ ዋና አላማ በክልሉ የሚስተዋለውን ሕገ-መንግስታዊ ስርዓት እና የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ በጉልበት ስልጣን የተቆጣጠረውን የህወሓትን ቡድን በማስወገድ በክልሉ ምርጫ ተደርጎ ህጋዊ መንግስት እንዲመሠረት በተደራጀ መንገድ በመጓዝ ሰላማዊ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር ነው መባሉም ተመልክቷል።
ከዚህ ሌላ ትግራይ ክልልን ከጦርነቱ ወደነበረችበት ሕገ መንግሥታዊ የግዛት ቅርጿ በመመለስ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ በተደራጀ ሁኔታ መስራት ነዉ። ምክር ቤቱ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ስምረት፣ ባይቶና፣ ዓረና ትግራይ፣ ትንሳኤ 70 እንደርታ እና ቃንቺ ሀቂ እንዲሁም በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱትን የሀራ_መሬት ታጋዮችን ወታደራዊ ክንፍ ማሰባሰቡ ተገልጿል።

28 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ መንግሥት ዛሬ እንዳስታወቀው፣ በእስራኤል እና በሊባኖስ (በተለይም በሄዝቦላህ) መካከል ያለው እና ደካማ መሠረት ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት ለተጨማሪ 45 ቀናት ተራዝሟል። ይህ ማራዘሚያ ይፋ የተደረገው፣ በኢራን የሚደገፈው የሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ከእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) ጋር እያደረገ ያለውን ግጭት፣ እንዲሁም ወደ እስራኤል ግዛት የሚተኩሳቸውን ሚሳኤሎች እና ድሮኖች ባላቆመበት ሁኔታ ውስጥ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል።
የስምምነቱ መራዘም የተነገረው፣ በዋሽንግተን ዲሲ ሲካሄድ የነበረው ሦስተኛው ዙር የእስራኤል እና ሊባኖስ የድርድር መድረክ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት ይህንኑ ድርድር “እጅግ ፍሬያማ” ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ የተኩስ አቁሙ መራዘም “ተጨማሪ የሰላም እርምጃዎችን ለማምጣት ያስችላል” ብለዋል።
ለተከታታይ ሁለት ቀናት በዘለቀው በዚህ ሦስተኛ ዙር ድርድር ላይ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለቱም ወገን የተውጣጡ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል። እስራኤልን ወክለው በአሜሪካ የእስራኤል ተጠባባቂ የመከላከያ አታሼ ብርጋዴር ጄኔራል አሪክ ቤን ዶቭ እና የ IDF ስትራቴጂክ ክፍል ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል አሚካይ ሌቪን ተገኝተዋል። ቃል አቀባይ ፒጎት እንዳስታወቁት፣ የድርድሩ የፖለቲካዊ ውይይት ክፍል በመጪው ጁን 2 እና 3 እንደገና የሚቀጥል ሲሆን፤ የደህንነት ጉዳዮችን የሚመለከተው ውይይት ደግሞ የሁለቱ አገራት ወታደራዊ ልዑካን በተገኙበት በፔንታጎን ሜይ 29 ይጀመራል።
በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሌይተር በበኩላቸው፣ ውይይቱን "ግልጽ እና ገንቢ" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል። "የሚቀጥሉትን እርምጃዎች በጉጉት እጠብቃለሁ፤ ውጣ ውረዶች መኖራቸው ባይቀርም የስኬት ዕድሉ ግን ሰፊ ነው። በድርድሩ ሂደት ሁሉ ቅድሚያ የምንሰጠው ግን የዜጎቻችንን እና የወታደሮቻችንን ደህንነት ነው" ብለዋል።
የሊባኖስ ልዑካንም የተኩስ አቁሙ መራዘምን በበጎ የተቀበሉት ሲሆን፣ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተነጥለው በፔንታጎን እና በስቴት ዲፓርትመንት በተናጠል እንዲታዩ መደረጉን አድንቀዋል። "ሊባኖስ ሉዓላዊነቷን በማስከበር እና የሕዝቧን ደህንነት በመጠበቅ በድርድሩ ውስጥ ገንቢ ተሳትፎዋን ትቀጥላለች" ሲል ልዑኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላምም፣ ሊባኖስ ለውጭ ኃይሎች ፍላጎት (በተለይ ሄዝቦላህ ለኢራን ሲል የከፈተውን ጦርነት በማመልከት) የምትከፍለው ዋጋ አብቅቷል ያሉ ሲሆን፣ አረብ አገራት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በድርድሩ የቤሩትን አቋም እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ስምምነቱ ከኤፕሪል 16 ጀምሮ በሥራ ላይ ቢሆንም፣ አሜሪካ እስራኤል በሄዝቦላህ አባላት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንድትፈጽም ፈቅዳለች። በዚህም ምክንያት ሐሙስ እና አርብ ድርድሩ እየተካሄደ በነበረበት ጊዜም ጭምር የዕለት ተዕለት ጥቃቶች አልቆሙም። ሄዝቦላህ በደቡብ ሊባኖስ የጸጥታ ቀጠና የፈጠሩትን የእስራኤል ኃይሎች ኢላማ ማድረጉን ቀጥሏል። አርብ ዕለት ሄዝቦላህ ወደ ሰሜን እስራኤል በተለይም ወደ ኪሪያት ሽሞና እና መቱላ ድሮኖችን ያስወነጨፈ ቢሆንም እስካሁን የደረሰ ጉዳት አልተዘገበም።
በተመሳሳይ የእስራኤል ኃይሎች (IDF) በሊባኖስ ጥቃታቸውን አጠናክረዋል። የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ አርብ ዕለት እስራኤል በጢሮስ አውራጃ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 37 ሰዎች ቆስለዋል። እስራኤል ይህንን ጥቃት የፈጸመችው ቀደም ብላ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ከሰጠች በኋላ ሲሆን፣ ጥቃቱ ሄዝቦላህ የሚጠቀምባቸውን መሠረተ ልማቶች ኢላማ ያደረገ መሆኑን ገልጻለች።
የግጭቱ አሃዞች እንደሚያሳዩት፣ እስካሁን በደቡብ ሊባኖስ 19 የእስራኤል ወታደሮች እና አንድ ሲቪል ኮንትራክተር የተገደሉ ሲሆን፤ በእስራኤል በኩል ደግሞ ከ2,000 በላይ የሄዝቦላህ ታጣቂዎች (በመቶዎች የሚቆጠሩ የ 'Radwan' ልዩ ኃይል አባላትን ጨምሮ) መገደላቸውን IDF አስታውቋል።

29 days ago
በኤራን ዩራንየም ጉዳይ ሩስያ ድጋፍ የማድረግ ሃሳብ ማቅረቧን ኢራን አረጋገጠች
ኢራን ከምዕራቡ ዓለም ጋር በሚያወዛግባት በኒዩክልየር ጉዳይ ላይ ሩስያ የበኩሏን ድጋፍ የማድረግ ሃሳብ እንዳቀረበች ኢራን አረጋገጠች። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ ዛሬ ኒውዴልሂ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በሩስያ ጉብኝታቸው ወቅት ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ስለ ዩራንየም ጉዳይ መነጋገራቸውን ገልጸው፤ ድጋፍ ለመስጠት ላቀረቡት ሀሳባቸውም አመሰግናቸዋለሁ ብለዋል።
ከብሪክስ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን አራግቺ በሰጡት በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ፑቲን በቅርቡ ስለዚሁ ጉዳይ የተናገሩትን አረጋግጠዋል። ፑቲን ባለፈው ሳምንት ሀገራቸው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጎናጸፈችው ድል በተዘከረበት የመታሰቢያ እለት ሩሲያ በከፍተኛ ደረጃ የበለፀገ ዩራኒየምን ከኢራን ወስዳ ለማከማቸት ዝግጁ መሆኗን አስታውቀው ነበር።
የኢራን የኒዩክልየር መርሀ ግብር ሲያወዛግብ ብዙ ዓመታት አስቆጥሯል። ዩናይትድ ስቴትስ እሥራኤል እና ምዕራባውያን ሀገራት ቴህራን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያዎችን ለማምረት ትፈልጋለች ሲሉ ይከሷታል። ኢራን ግን ይህን ታስተባብላለች። ምዕራቡ ዓለም ኢራን አሁን ያላት የዩራንየም ክምችት ከለማ በርካታ የኒዩክልየር ጦር መሣሪያዎች ለመስራት በቂ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሚገኘው ዩራንየም ከሀገሪቱ እንዲወጣ ግፊት እያደረጉ ነው። ዩራንየሙ ከምድር በታች ከሚገኙ የኢራን የኒዩክልየር ተቋማት በአንዱ ውስጥ ተከማችቷል ተብሎ ይገመታል።

1 month ago
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቻይና አቀኑ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎችን አስከትለው ወደ ቻይና አቀኑ። ትራምፕ እና የቻይና አቻቸው ሺ ዢንፒንግ ሐሙስ እና አርብ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ስብሰባ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚካሔደው በኢራን ጦርነት የኢነርጂ ዋጋ በከተኛ መጠን ባሻቀበበት ወቅት ነው። የአሜሪካ እና የቻይና የንግድ ልውውጥ እና የአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው።
በአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ቀዳሚ የሆኑ የአሜሪካ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎች ከዶናልድት ትራምፕ ጋር ወደ ቻይና አቅንተዋል። ለአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ቁልፍ ግብዓት የሆኑ ቺፖች በማምረት የሚታወቀው የንቪዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀንሰን ሑዋንግ፣ የአፕል ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ እና የቴስላው ኤለን ሙስክ ከልዑካን ቡድኑ መካከል ይገኙበታል።
በቤጂንግ በሚደረገው የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ አሜሪካ ለታይዋን የምትሸጠው የጦር መሣሪያ ጉዳይ ከሺ ዢንፒንግ እንደሚነጋገሩ ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ብለው አሳውቀዋል። የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ግን ታይዋን የቻይና አንድ አካል በመሆኑ አሜሪካ የሚኖራትን ወታደራዊ ግንኙነትም ይሁን ከዚህ ቀደም የተስማማቸውን የጦር መሣሪያ ሽያጭ አጥብቀው ተቃውመዋል። ባለፈው ታኅሳስ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር 11 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሣሪያዎች ለታይዋን እንደሚሸጥ ይፋ አድርጎ ነበር።

u1265u122du1203u1291 u1290u130b (u1355/u122d) u12ebu130bu1208u1321u1275 u12e8u12a2u1205u12a0u12f4u130d u121du1235u1322u122d https://youtu.be/ZrsIXpkDw...
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ያጋለጡት የኢህአዴግ ምስጢር https://youtu.be/ZrsIXpkDw...
1 month ago
u12a0u12f2u1235 u12a0u1260u1263u1295 u1208u121du1295 u12a0u1295u1228u12a8u1265u121d u12a0u120bu127du1201? https://youtu.be/ZrsIXpkDw...
አዲስ አበባን ለምን አንረከብም አላችሁ? https://youtu.be/ZrsIXpkDw...
1 month ago
ኢራን በዓለም ዋንጫ እንደምትሳተፍ ገለጸች።
ኢራን በዓለም ዋንጫ እንደምትሳተፍ ገለጸች። ኢራን በትልቁ የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ፍላጎቷን ስትገልጽ የውድድሩ አስተናጋጆች ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲቀበሉ ጠይቃለች።
የኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ቅዳሜ እንዳስታወቀው በ2026 የክረምት ወቅት በሚካሄደው የዘንድሮ የዓለም ዋንጫ የሀገሪቱ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ይሳተፋል። ነገር ግን የጋራ አስተናጋጆቹ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ሁኔታዎችን ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ጋር እንዲያስማሙ ጠይቋል።
የኢራን ጥያቄ የተሰማው ካናዳ ባለፈው ወር ከፊፋ ጉባኤ በፊት የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሀላፊ ወደ ወደ ጉባኤው እንዳይገቡ መከልከሏን ተከትሎ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በጎርጎሪያኑ 2024 እንደ ሽብርተኛ ቡድን ከተፈረጀው የኢራን ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለም ክንድ ከሆነው ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ (IRGC) ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ነበር።
"በእርግጠኝነት በ2026 የዓለም ዋንጫ እንሳተፋለን፣ ነገር ግን አስተናጋጆቹ ስጋቶቻችንን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው" ሲል የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋዊ ድረ-ገጹ ላይ አስታውቋል።
ቅድመ ሁኔታዎቹ ቪዛ መስጠት እና ለብሔራዊ ቡድኑ ሰራተኞች አክብሮት መስጠት፣ የቡድኑ ባንዲራ እና ብሔራዊ መዝሙሩ በውድድሩ ወቅት እንዲሁም በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ሆቴሎች እና ወደሚጫወቱባቸው ስታዲየሞች በሚወስዱ መንገዶች ላይ ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግላቸው መጠየቅን ያካትታሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የኢራን የእግር ኳስ ተጫዋቾች በውድድሩ ላይ መገኘታቸው መልካም መሆኑን ተናግረዋል።ነገር ግን አሜሪካ ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የኢራን ልዑካን ቡድን አባላትን እንደ ሽብርተኛ ድርጅትነት ቆጥሮ ፈቃድ ሊከለክል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የኢራን የእግር ኳስ ኃላፊ ታጅ ግን «ሁሉም ተጫዋቾች እና የቴክኒክ ሰራተኞች፣ በተለይም እንደ መህዲ ታሬሚ እና ኢህሳን ሃጅሳፊ ያሉ በእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን ወይም በIRGC ውስጥ ወታደራዊ አ አገልግሎት የሰጡ ያለምንም ችግር ቪዛ ሊሰጣቸው ይገባል» ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።
የዓለማቀፉ የእግር ኳስ ማሕበር ፊፋ ዋና ኃላፊ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በበኩላቸው ኢራን በታቀደው መሰረት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን ዩናይትድ ስቴትስ እንደምታደርግ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) የግል የሕይወት ፍልስፍና እና ቆይታ
#ethiopia | ታዋቂው የጥበብ ሰው ብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) ሕይወትን በቀላል መንገድ የመምራት ልምዱንና የግል አመለካከቱን የሚገልጽበትን የመጀመሪያ ክፍል ቃለ መጠይቅ አቅርቧል።
በዚህ ዝግጅት ላይ አርቲስቱ ነገሮችን ሳያወሳስቡ በመኖር ውስጥ ስላለው ሰላም እና ስለ ቆይታው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ሙሉውን ውይይት በሊንኩ በመከተል መመልከት ይቻላል።
https://youtu.be/s9n-tOraP...
#art #biography #interview #philosophy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ለቴዲ አፍሮ ኢቶሪካ የሙዚቃ አልበም ግራፊክሱን የሠራው ዳዊት ሰሎሞን ታሰረ።
የግራፊክስ ባለሙያው ዳዊት ሰሎሞን በትንትናው ዕለት መታሠሩ ተሰምቷል።
ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ኢቶሪካ ለተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም ግራፊክሱን የሠራው ዳዊት ሰሎሞን መሆኑን ዶቼ ቬለ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከቴዲ አፍሮ ጋር ቅርብ የሥራ ግንኙነት ያላቸው የመረጃ ምንጭ ለዶቼ ቬለ እደገለጹት፤ የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ኢቶሪካ የተሰኘው የሙዚቃ አልበም መውጣቱን ተከትሎ ዳዊትን ጨምሮ የታሰሩ ለአርቲስቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ስምንት ደርሷል።
ዳዊት ጓደኞቹ ጋ በሄደበት አጋጣሚ መያዙን የገለፁልን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት የመረጃ ምንጭ፤ እሱ ከመያዙ በፊት ቤቱ በፖሊስ መፈተሹንም ተናግረዋል።

በናፍጣ እጥረት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ምርት ለገበያ ማቅረብ እያስቸገረ ነው
በሺህዎች የሚቆጠሩ የንግድ እና የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በኢራን ፍኖተ-ሆርሙዝ እንዳያልፉ እገዳ ተጥሎባቸው መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው የነዳጅ እጥረቱ በየቦታው እየተስፋፋ ዋጋውም እየናረ መምጣቱ እየተገለጸ ነው ። በኢራን ክልከላ የተነሳ 22,500 መርከበኞች በ1,550 የንግድ መርከቦች ውስጥ በባሕረ መስመሩ ማለፍ ሳይችሉ መቅረታቸው ከሰሞኑ ተዘግቧል ። የነዳጅ እጥረት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች እክሎችን እየፈጠረ መሆኑን የተለያዩ ሰዎች በምሬት እየተናገሩ ነው ።
በናፍጣ እጥረት ምክንያት እየናረ በመጣው የጭነት መጓጓዣ ዋጋ የተነሳ የሙዝ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቸገራቸውን ለዶይቸ ቬለ (DW) የተናገሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ሙዝ አምራች አርሶአደሮችን መጥቀስ ይቻላል ። አርሶ አደሮቹ እንዳሉት፦ ቀደም ሲል ከ40 እስከ 50 ሺህ ብር ይጫን ነበረው አንድ አይሱዚ የጭነት ተሸርካሪ በአሁኑ ወቅት በአራት እጥፍ በመጨመሩ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ተቸግረዋል ። የአርባምንጭ ከተማ አስተዳዳር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በበኩሉ በናፍጣ አቅርቦት ላይ የሚካሄደውን ማጭበርበር ለመከላከል የኩፖን አሠራር መጀመሩን ዐሳውቋል ።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ሕገ-ወጥ ነው በሚል ውድቅ አድርጎት የነበረውና የምርጫው ሕገ-ወጥነት በፕሪቶሪያ ስምምነት ፀንቶ የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ትናንት መርጧል። በህወሓት ውሳኔ፣ ከስድስት ዓመት በፊት የተቋቋመው የክልሉ ምክር ቤት ወደ ሥራ መመለሱን የሚነቅፉ አስተያየቶች ከልዩ ልዩ አካላት እየተሰሙ ነው።
በጉዳዩ ላይ ዶቼ ቬለ አስተያየት የጠየቃቸው አንድ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተንታኝ፣ «የህወሓት ውሳኔ የፕሪቶሪያውን ግጭት የማቆም ስምምነት ያፈረሰ ነው» ብለዋል። ተንታኙ አክለውም፣ የፌዴራል መንግሥቱ እና ሌሎች ሦስተኛ አካላት ውዝግቡን በሰላም ካልቋጩት፣ በሂደት ግጭት ሊከሰት እንደሚችል አመልክተዋል።
ይህን የህወሓት ውሳኔ ከስምረት እስከ ትዴፓ መሪዎች እና ሌሎችም አካላት ተችተዋል። ውጤቱም አደጋ ያዘለ እንደሚሆን በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።
ስለጉዳዩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት AFP ያነጋገራቸው ተንታኞችም ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የትግራይ ክልልን መልሶ ለመቆጣጠር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር አደገኛ ወደሆነ አስከፊ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል አስጠነቅቀዋል ።
በኖርዌይ የኦስሎ ኒው ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የክልል ጉዳዮች አዋቂ ክጄቲል ትሮንቮል እርምጃው «እጅግ አሳሳቢ» መሆኑን ገልጸው «ድርድር ወይ ግጭት ያስከትል አያስከትል ግልጽ አይደለም» ብለዋል። ሌላው AFP ያነጋገራቸው በቻተም ሀውስ ተንታኝ አቤል አባተ ደምሴ ደግሞ አንድ ግብ ለማሳካት በተደጋጋሚ የሚደረግ ተጽእኖ በቀላሉ ወደ አስከፊ ግጭት ሊያመራ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል ።
በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና ከህወሓት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ማብራሪያ ለመጠየቅ ዶቼቬለ ጥረት ቢያደርግም ምላሽ አላገኘንም። የፌዴራል መንግሥት ስለጉዳዩ እስካሁን በይፋ ያለው ነገርም የለም። (DW)

በሆርሙዝ ሰርጥ የመርከቦች እጀባን ለጊዜው እንደደምታቋርጥ ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች
ዩናይትድ ስቴትስ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ማለፍ ላልቻሉ የንግድ መርከቦች የጀመረችውን አጀብ ለጊዜው እንደምታቆም አስታወቀች። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመርከቦች እጀባው የቆመው ከኢራን ጋር የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለን ፍላጎት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ምንም እንኳን በቅርብ ቀናት በሰርጡ ግጭቶች የነበሩ ቢሆንም ትራምፕ ግን ወደ ስምምነት የሚያመራ ትልቅ ለውጥ ላይ ተደርሷል ብለዋል። መርከቦችን የማጀቡ ዘመቻ የሰላም ስምምነቱ ሊጠናቀቅና ሊፈረም ይችል እንደሆነ ለማየት ለአጭር ጊዜ ይቆማል ሲሉም ተናግረዋል።
ትራምፕ ይህን ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የምታካሂደውን የማጥቃት ዘመቻ ማጠናቀቋን ትናንት ከተናገሩ በኋላ ነው። ይሁንና ሩብዮ ኢራኖች በሰርጡ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ለሚሰነዝሩት ማንኛውም አዲስ ጥቃት ግን ከባድ ምላሽ እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል።
ኢራን በበኩልዋ የሰላም ስምምነቱን የምትቀበለው አድሏዊ ካልሆነ ብቻ ነው ስትል አስታውቃለች። ለጊዜው እንደሚቋረጥ ዛሬ የተነገረው እጀባ ለሦሶት ቀናት ብቻ ነበር የዘለቀው። «የነጻነት ፕሮጀክት» የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኽው ዘመቻ በሆርሙዝ ሰርጥ የመርከቦች ጉዞ እንዲቀጥል የሚያደርግ ጉልህ ውጤት አለማስገኘቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

u1260u120cu120au1275 u1218u1325u1270u12cd u12c8u1235u12f0u12cd u1232u12ebu1235u1308u1261u129d u2026 u1219u1209u12cdu1295 u1243u1208 u1218u1320u12edu1245 u1260u120au1295u12a9 u12edu12a8u1273u1270u1209 https://youtu.be/2Mjwd-dkD...
በሌሊት መጥተው ወስደው ሲያስገቡኝ … ሙሉውን ቃለ መጠይቅ በሊንኩ ይከታተሉ https://youtu.be/2Mjwd-dkD...
Sponsored by
Surafel
1 month ago
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ አምስት ሰዎች በታጣቂች ተገደሉ።ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ትናንት ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ በተኙበት ገብተው መሣሪያ በመተኮስ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሟች ዘመዶች ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳ ኢንሴኖ በተባለ ከተማ ውስጥ መሆኑን ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አንድ የሟች የቅርብ ዘመድ «ታጣቂዎቹ በተለምዶ አየር ጤና ተብሎ በሚጠራው መንደር እየተኮሱ ነው የገቡት፡፡ወደ መኖሪያ ቤት በመግባት አምስት ሰዎችን ተኩሰው ከገደሉ በኋላ ተመልሰው ሄደዋል፡፡ከሟቾቹ መካከል አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ እናት ከሦስት ልጆቿ ጋር ነው» ብለዋል ፡፡
በከተማው ነዋሪ የሆኑ ሌላ የዐይን አማኝ በበኩላቸው ግድያው መፈጸሙን አረጋግጠው ጥቃት አድራሾቹ በአካባቢው በሽፍትነት የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ሳይሆኑ እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡ዶቼ ቬለ ጥቃቱን በተመለከተ ለማነጋገር በስልክ ያገኛቸው የምሥራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሰረላ መረጃውን አሰባስበው እንደሚገልጹ ቀጠሮ ይዘው ነበር፡፡ነገር ግን በቀጠሮው ሰዓት ሥልካቸው ዝግ በመሆኑ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡
Via DW

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሞት ቅጣት የሚጠባበቁ 65 ኢትዮጵያውያን አሉ ተባለ
👉🏼ሶስት ኢትዮጵያን ባለማወቅ ጫት ከየመን ወደ ሳዑዲ ሲያስገቡ ተይዘዉ ሞት ተፈርዶባቸዋል
ሳዑዲአረቢያ ውስጥ ቢያንስ 65 ኢትዮጵያውያን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተገናኘ ወንጀል የሞት ቅጣት እንደሚያሰጋቸው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎች አሳወቀ።
የሳዑዲ ባለሥልጣናት እስከ ባለፈው ማክሰኞ (ሚያዝያ 13 ቀን፣ 2018 ዓ.ም) ድረስ ሌሎች ሦስት ሰዎችን በስቅላት መቅጣታቸውንም ዛሬ የወጣው ተቋሙ መግለጫ ያመለክታል።
በሂውማን ራይትስ ዎች የስደተኞች እና የፍልሰተኞች መብት ከፍተኛ ተመራማሪ ናዲያ ሐርድማን «ሳዑዲ አረቢያ በመሠረታዊ የፍርድ ሂደት የመታደም መብት በመንፈግ የኃይል ጥቃት ላልቀላቀለ ወንጀል በሞት ለመቅጣት መዘጋጀቷ ለፍልሰተኞች መብት እና ሕይወት ክብር ያለመስጠትን ያንጸባርቃል» ብለዋል።
ባለሙያዋ የሳውድ አረቢያ አጋሮች «ጊዜው ከማለፉ በፊት» በአፋጣኝ ጣልቃ እንዲገቡም ጠይቀዋል።
ሂውማን ራይትስ ዎች ሳውድ አረቢያ አሲር ግዛት በሚገኘው ካሚስ ሙሻይት እስር ቤት ስለሚገኙት ሦስት ታሳሪዎች መረጃ ያላቸውን ሦስት ሰዎችን ስለጉዳዩ መጠየቁን አመልክቷል።
ሦስቱም እስረኞች በቅርቡ ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ጦርነት በነበረበት ወቅት የተሰደዱ መሆናቸውን ገልጿል። የሰብአዊ መብት ይዞታይ አደገኛ በነበረበት በዚያን ወቅት በአስቸጋሪው የስደት መስመር በየመን በኩል ወደ ሳውዲ የገቡ መሆናቸውንም አመልክቷል።
ኢትዮጵያዊያኑ ገንዘብ ለማግኘትም ከየመን ወደ ሳውዲ ጫት መውሰዳቻውንም ከመረጃ ሰጪዎቹ ተረድቷል።
ሆኖም ሳውዲ ውስጥ ጫት በወንጀል እንደሚያስጠይቅ እንደማያውቁም ጠቅሷል። ከታሠሩ አንስቶ በአግባቡ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ፤ በቀረቡበት አጋጣሚም አስተርጓሚ እንዳልነበራቸውና የተላለፈባቸውን ፍርድ ምንነት እንዳልተረዱም ዘርዝሯል።
ሆኖም በፀጥታ ኃይሎች መደብደባቸውና ምንነቱን ያልተረዱት ሰነድ ላይ እንዲፈረሙ መገደዳቸውንም አስታውቋል።
ሂውማን ራይትስ ዎች የሚመለከታቸው መንግሥታት ሳውድ አረቢያ የሞት ቅጣቱን እንድታነሳ ግፊት እንዲያደርጉም አሳስቧል።
Via dw

2 months ago
በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሶስት ኢትዮጵያውያን በጥይት ተገደሉ
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኝ አንድ የፈጣን ምግብ መሸጫ ውስጥ ባጋጠመ የጥይት ጥቃት፣ ሶስት ኢትዮጵያውያን እና ሁለት ናይጄሪያውያን መገደላቸውን የአገሪቱ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት አስታወቁ።
ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት፣ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያደረገችበትን እና የነፃነት ቀኗን (Freedom Day) በምታከብርበት ሚያዝያ 27 ቀን ነው።
ኢትዮጵያውያኑ ግድያው የደረሰባቸው በጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኝ "ማክዶናልድ" የፈጣን ምግቦች መሸጫ ውስጥ ምግብ በመመገብ ላይ ሳሉ መሆኑ ተገልጿል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት ወቅት መጤ ጠል አራማጅ ደቡብ አፍሪካውያን በስደተኞች ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ እያስተላለፉ ባሉበት ወቅት መሆኑ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
ይሁን እንጂ አንድ የአገሪቱ ፖሊስ መኮንን ለተለያዩ አካላት በሰጡት መረጃ፣ ግድያው በኢትዮጵያውያኑ መካከል በነበረ መጠቃቃት ወይም አለመግባባት የተነሳ የተፈጸመ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸዋል።
ፖሊስ ስለ ጥቃቱ መንስኤና ስለ አጥቂዎቹ ማንነት ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።
ዘገባው የ DW ነው
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ደቡብ_አፍሪካ #ጆሃንስበርግ #ኢትዮጵያ #ዜና #southafrica #johannesburg #ethiopians #breakingnews

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሦስት ኢትዮጵያዊያን በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እና የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያዊያኑ ትናንት የተገደሉት በጆሀንስበርግ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ማክዶናልድ በሚባለው የፈጣን ምግቦች መሸጫ ውስጥ በመመገብ ላይ እንዳሉ ነው ፡፡ ጥቃቱ የተፈፀመው መጤ ጠል አራማጅ ደቡብ አፍሪካዊያን በስደተኞች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት የሠልፍ ጥሪ እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው ፡፡
አንድ የአገሪቱ ፖሊስ መኮንን ግን ግድያው ኢትዮጵያዊያኑ እርስ በእርስ ባለቸው መጠቃቃት የተፈጸመ ሳይሆን እንዳልቀረ ጥርጣሬውን ገልጿል፡፡በጥቃቱ ሁለት ናይጄሪያውያንም ተገድለዋል።ጥቃቱ የተፈፀመው የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተደረገበት ቀን መታሰቢያ በሆነው እና በየዓመቱ በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ 27 ቀን በሚከበረው የነፃነት ቀን ነው።Via DW

የኢራኑ ተደራዳሪ ለተጨማሪ ምክክር ወደ ፓኪስታን ተመለሱ
የኢራኑ ተደራዳሪ ለተጨማሪ ምክክር ወደ ፓኪስታን መመለሳቸው ተዘገበ።እንደ አሶሸትድ ፕሬስ ዘገባ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ዛሬ እሁድ ለተጨማሪ ምክክር ወደ ኢስላማባድ ተመልሰዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የልዑካናቸውን የፓኪስታን ጉዞ ቢሰርዙም ዓለም አቀፍ አስታራቂዎች የሰላም ድርድሩን በትክክለኛው መንገድ ለማስቀጠል እየጣሩ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።
እንደ ኢራን የዜና ወኪል አይ ኤስ ኤን ኤ /ISNA/ ዘገባ፣ አባስ አራግቺ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን "ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ በማስቆም ላይ ኢራን ያላትን አቋም እና አመለካከት" ለማንፀባረቅ ከፓኪስታን ባለስልጣናት ጋር ለንግግር ተቀምጠው ነበር።ሚኒስትሩ እስከ ትናንት ቅዳሜ ኢስላማባድ የነበሩ ሲሆን ከዚያም ወደ ኦማን ተጉዘዋል። ሌሎች የኢራን ልዑኮች ደግሞ "ጦርነቱን ከማስቆም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ አስፈላጊውን መመሪያ ለማግኘት" ወደ ቴህራን ተመልሰው ነበር ሲል የዜና አውታሩ ገልጿል።
አባስ አራግቺ ቅዳሜ ምሽት የፓኪስታን መዲና እስላማባድን ለቀው በመውጣታቸው በሁለተኛው ዙር በሚደረገው ውይይት ዙሪያ ግራ መጋባት ፈጥሮ ነበር። ነገር ግን ወደ ሞስኮ ከማምራታቸው በፊት ዛሬ ወደ ኢስላማባድ ተመልሰዋል ሲሉ የኢራን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ዋይት ሀውስ ዓርብ ዕለት ለሁለተኛ ዙር ውይይት ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነርን ያካተተ የልዑካን ቡድን ወደ ኢስላማባድ እንደሚልክ አስታውቋል። ነገር ግን የአራግቺ ፓኪስታንን ለቀው መውጣታቸው ከተዘገበ ብዙም ሳይቆይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ያለው ውይይት መሻሻል አላሰየም በሚል ተልዕኮውን አቋርጠነዋል ብለዋል። ትራምፕ አያይዘውም "በፈለጉት ጊዜ ሊደውሉልን ይችላሉ" ሲሉ ገልፀዋል።

Comments