3 days ago
“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

2 months ago
የም/ቤቱ 23ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል
#ethiopia | ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ያካሄዳል።
ምክር ቤቱ በነገው ስብሰባው በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል የተደረጉ የብድር ስምምነቶችን ለማፅደቅ የወጡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በሴራሊዮን ሪፐብሊክ፣ በአንጎላ ሪፐብሊክ፣ በባንግላዲሽ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ እንዲሁም በኢስዋቲኒ ንጉሠ ነገሥት መንግሥታት መካከል የተፈረሙትን የሁለትዮሽ የአየር አገልግሎት ስምምነት ረቂቅ አዋጆች አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ያፀድቃል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል ለማቋቋም የተፈረመውን ስምምነት ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተያያዘም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በቬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም የኦፊሻል የአገልግሎት ፓስፖርት ለያዙ ዜጎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመውን ስምምነት ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ያፀድቃል።
በመጨረሻም ምክር ቤቱ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ፣ የግብርና ቢዝነስ ኩባንያ፣ የምግብ ሥርዓትና ሥርዓተ ምግብ፣ የኢትዮጵያ የካርበን ገበያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ይመራል ያለው መናኸሪያ ኤፍ ኤም ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 months ago
ምክር ቤቱ 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል
*****************
6ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱን 18ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሴራሊዮን ሪፐብሊክ፣ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በአንጎላ ሪፐብሊክ፣ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በባንግላዲሽ ሕዝባዊ ረፐብሊክ እንዲሁም በኢፌዴሪ መንግሥት እና በኢስዋቲኒ ንጉሠ ነገሥት መንግሥታት መካከል የተደረገውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረቡ አራት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የሚመራ ይሆናል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል ለማቋቋም የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።
በመጨረሻ ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በቬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ኦፊሻል የአገልግሎት ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የሚመራ ሲሆን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት መርምሮ እንደሚያፀድቅም የሚጠበቅ መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ebc #ethiopia #hopr

5 months ago
"የሕገመንግስታዊ ሃይማኖት ታሪክና እና የገዢው ሕገመንግስት ሕጋዊ እይታ"
በፋንታሁን ደለለው ,Lawyer
መግቢያ #ethiopia | የዚህ ጽሁፍ አላማ በኢትዮጵያ በታሪክ የነበሩትን ህገመንግስቶች በመዳሰስ ከሀይማኖታዊ ህገመንግስት ጋር ያላቸውን ትስስር በመለየት ባህርያቸውን ከዚህ አንጻር በመለየት ህገ መንግስታዊ ሀይማኖት ምንድነው የሚለውን አንባቢው ግንዛቤ እንዲኖረው ነው።
1. ህገ መንግስታዊ ሀይማኖት ምንድነው?
መንግስታዊ ሀይማኖትን እንደምንረዳው በንጉሱ ጊዜ መንግስት ሀገርን የሚመራው የሀይማኖትን ስረአት ተከትሎ መሆኑ ነው። በዚህ በኢፊድሪ ህገመንግስት ስረአተ መንግስት ግን የሀይማኖትና መንግስት ስረአት የተለያየበት/Secularism/ የሰፈነበት የዲሞክራሲያዊ መርሆች የበለጸጉበት መንግስትም ሆነ ሀይማኖት በየራሳቸው ህጋቸውን የሚያካሂዱበት አስተማማኝ ህግ የተዘረጋበት መሆኑን ማስተዋል ይቻላል።
2. ፍተሀነገስት
ፍተሀነገስት የ923 ዓ.ም ህገመንግስት በአዋጅ ጸድቆ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ፍትህ መንፈሳዊ እና ፍትህ ስጋዊ ተብሎ ሁለቱንም አገልግሎት ይሰጥበት ሲሆን ማለትም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንንም ሆነ የአለማዊ ነገር የሚመራበት እንደ ነበር ከታሪክ መዛግብት መረዳት የሚቻል ነው። ፍተሀ ነገስት ከአረብ ቋንቋ ወደ ግእዝ ተተርጉሞ ስራ ላይ የዋለው በአጼ ዘረአይ ያእቆብ ዘመነ መንግስት (1444_ 1468 ) ዓ.ም ነው።
የ1923 ህገመንግስት ስራ ላይ ከመዋሉ በፊትም ነገስታቶች ፍትህን ለማስፈን ፍርድ ውሳኔን ለመስጠት ይረዳ የነበረ ሲሆን በኋላም የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ወእጨጌ ርእሰ ሊቀነጳጳሳት ዘ መንበረ ተክለሐይማኖት በሚመሩበት በ5ኛው እትም በ1990 ዓ.ም የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የምትመራበት ስረአት ተደርጎ እንዲቀጥል አድርገዋል።
ይህ የ1923 ዓ.ም ህገመንግስት ፣ ህገመንግስት ተብሎ መሰየሙ እና በአዋጅ በመጽደቁ ለሀገራችን የህግ እድገት አንድ ትልቅ ምእራፍ ያሳየ ቢሆንም ሀይማኖትን ከመንግስት የለየ አይደለም።
3. በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገመንግስት የትኛው ነው?
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዘመናዊ ህገ-መንግስት በሐምሌ 9 ቀን 1923 ዓ.ም. በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጸድቆ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ ታሪክ የፍትሐ ነገሥትን ሥርዓት በመተካት ለመጀመሪያ ጊዜ የተረቀቀ ሕጋዊ ሰነድ ነው። ይህ ህገ-መንግስት 11 ምዕራፎችና 85 አንቀጾች የያዘ ሲሆን፣ በዋናነት የንጉሠ ነገሥቱን ፍጹም ሥልጣንና የአልጋ ወራሽ ሁኔታን ያረጋገጠ ነበር።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገመንግስት በ1923 ዓ.ም የወጣው ነው። ይህ ህገ-መንግስት 11 ምዕራፎችና 85 አንቀጾች የያዘ ሲሆን፣ በዋናነት የንጉሠ ነገሥቱን ፍጹም ሥልጣንና የአልጋ ወራሽ ሁኔታን ያረጋገጠ ነበር።
የዚህ ህገ-መንግስት ዋና ዋና ነጥቦች እንሚከተለው ተቀምጧል።
የንጉሠ ነገሥቱ ሥልጣን፦ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥትና ሃይማኖት መሪ፣ እንዲሁም የዘውድ አገዛዙን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ፍጹም ሥልጣን የያዘ ነበር።
የዘር ሐረግ፦ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከንጉሥ ሰለሞንና ከንግሥተ ሳባ ዘር የወረዱ (የቀዳማዊ ምኒልክ ዘር) መሆን እንዳለባቸው ደንግጓል።
መሬት እና ህዝብ፦ መሬትና የኢትዮጵያ ህዝብ የንጉሠ ነገሥቱ (ዘውዱ) እንደሆነ ይገልጻል።
የፓርላማ መዋቅር፦ ህገ-መንግስቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እንዲቋቋም ቢያደርግም፣ ስልጣኑ ከንጉሡ በታች ነበር።
ዘመናዊነት፦ የመንግስት መዋቅሮችን፣ ሚኒስቴሮችንና የሥራ በጀት አወጣጥን በህግ ለመምራት የተሞከረበት የመጀመሪያው እርምጃ ነበር።
ሀይማኖትንና የመንግስት መዋቅርን አስተኖብሮ የያዘ በመሆኑ ህገመንግስታዊ ሀይማኖት ለማለት የሚያስደፍር ነው።
4. የ1948 ህገመንግስት
ይህ ህገመንግስት ዲሞክራሲያዊ ህገመንግስት ተብሎ የወጣ የጸደቀበት ሀይማኖት ከመንግስት የተለየበት ህገመንግስት፣የዜጎች፣ የሀይማኖቶች መሰረታዊ መብቶች የተረጋገጠበት ሀገርን/መንግስትን ለመምራት የሚያስችል የመንግስት የበላይ ህግ መሆኑ ነው።
5. የደርግ መንግስት ህገመንግስት
ይህ ህገ መንግስት ከሀይማኖት አስመልክቶ ሳይሆን ሀገርን ለመምራት የሚያስችል የበላይ ህግ ሆኖ በ1979 የወጣ ህግ ነው። ሀይማኖታዊ ህገመንግስት የሚያስብለው ባህሪም የለውም።
6. የኢፊድሪ ህገመንግስት
ይህ የሰብአዊነት እና የዲሞክራሲያዊ መርሆችን በማካተት የግለሰብ እና የቡድን መብቶችን በማቀፍ የታወቀ ሲሆን ሀይማኖታዊ መንግስት እንደሌለ መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆኑን በአንቀጽ 11 ላይ ተደንጎ የተቀመጠ ነው።
7. ምክረ ሀሳብ
ሲወርድ ሲዋረድ እስከ 1948 ህገመንግስት ድረስ ሀይማኖታዊ ከሆነ ህገመንግስት የጸዳ ያልነበረ ሲሆን ከ1948 ዓ.ም ጀምሮ ግን ሀይማኖታዊ ህገመንግስት የሌለ ሲሆን የኢፊድሪ ህገመንግስትም በተመሳሳይ ከሀይማኖት የተለየ ሀይማኖታዊ ህገመንግስት ባለመሆኑ መንግስታዊ ሀይማኖት አይደለም ብሎ መደምደም ይቻላል።
https://www.facebook.com/s...
https://t.me/Fantahunlawye...
Fantahun Delelew
ዋና ዋና ማጣቀሻዎች
1. የኢፊድሪ ህገመንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987
2. የደርግ ህገመንግስት
3. የ 1923 ህገመንግስት
4. የ 1948 ህገ መንግስት
5. ፍተሀነገስት

Yederaw Support:
በራሱ ቀብር ላይ የተገኘው ደራሲ
#ethiopia | መንግሥቱ የተወለደው በ 1920 ዓ.ም በቀድሞው የሲዳሞ ክፍለ ሐገር፣ በቡሬ ገጠራማ መንደር ውስጥ ነው። የቤተሰቦቹ ሕይወት በግብርና ስራ ላይ የተመሰረተ ስለነበር መንግሥቱም ገና በልጅነቱ የወላጆቹን ስራ በአቅሙ ያግዝ ነበር። የመንግሥቱ ሕይወት በፈተና የተሞላች መሆን የጀመረችው ገና በማለዳው ነበር።
በዚያው የልጅነት እድሜው እባብ ነድፎት ለስድስት ሳምንታት ያህል ሕሊናውን ስቶ ከሰነበተ በኋላ ከሞት ተረፈ።
ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት የመንግሥቱን የትውልድ መንደር ሲያቃጥል መንግሥቱ ከእሳቱ የተረፈው በተዓምር ነበር። ቤታቸው ሲቃጠል መንግስቱ የሚሄድበት አጥቶ በቤት ውስጥ ይቅበዘበዝ ነበር። በሚቃጠለው በነመንግስቱ ቤት ወስጥ ሰው መኖሩን የተረዳ አንድ የአካባቢው ሰው ወደ ቤቱ ውስጥ በመግባት መንግሥቱን ከሞት አተረፈው።
በፋሺስቶች መምጣት የተደናገጠው የአካባቢው ሰው ቤቱን ትቶ ሲሸሽ ፈረስ መጋለብ የማይችለው መንግሥቱ በፈረስ ሊያመልጥ ወሰነና ከፈረስ ላይ ወጣ። የፈረሱ ፍጥነት አስደንግጦት ከፈረሱ ላይ ለመውረድ ወሰነ፤ ለስላሳ መሬት አገኘሁ ብሎ ከፈረሱ ላይ ተፈናጥሮ ሲወርድ ድንጋይ ላይ ቢወድቅም ከሞት መትረፍ ችሏል።
የሞትን ደጅ እየረገጡ መመለስ የተለማመደው መንግሥቱ በአንድ ወቅት በከብት ጥበቃ ላይ ሳለ ጅብ ተሸክሞት ሊሄድ ሲታገለው የለበሰውን ደበሎ ለጅቡ ሰጥቶ ማምለጥ ችሏል። ለዚህም ነው መንግሥቱን ከልጅነቱ ጀምረው የሚያውቁት ሰዎች ‹‹ሕይወቱ በሙሉ የፈተና ዘመን ነበር›› ብለው የሚመሰክሩት።
መንግሥቱ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ገብቶ ፊደል መቁጠር ቻለ። ከፍ ሲልም በወታደርነት ለማገልገል ተመዘገበ። በውትድርናው ግን አልገፋበትም። ከውትድርናው ዓለም ወጥቶ በፖስታና ቴሌፎን ሚኒስቴር ውስጥ ተቀጠረ ። በስራው የተመሰገነ ታታሪ ሰራተኛ ስለነበርም በአጭር ጊዜ ውስጥ እድገት አግኝቶ ወደ ድሬዳዋ ተዛወረ።
ደመወዙ ግን አጥጋቢ ስላልሆነለት ስራውን ለቆ በእጥፍ ደመወዝ በምድር ባቡር ኩባንያ ውስጥ ተቀጠረ። የፖስታና ቴሌፎን ሚኒስቴር ይህን የመንግሥቱን ድርጊት ሲሰማ ወደ ቀድሞ ስራው በግዳጅ መለሰው። መንግሥቱ ግን ለአለቆቹ ውሳኔ የሚመች አልሆነም። ‹‹አለቃም ይሁን ምንዝር በእጄ ከመጥፋቱ በፊት በሰላም አሰናብቱኝ›› ብሎ አስፈራራቸው። ይህ ፉከራው ሳያዋጣው ስለቀረ ሌላ መላ ዘየደ። ‹‹ራሴን አጠፋለሁ›› ብሎ ማስፈራራት የመንግሥቱ ሌላኛው ዘዴ ነበር። እንዳጋጣሚ ሆኖ ይህኛው መላ ሰራለትና መስሪያ ቤቱ ‹‹ ራስህን ከምታጠፋ እንለቅሃለን›› ብሎ አሰናበተው።
ወደ ምድር ባቡር ኩባንያ ሄዶ ለጥቂት ጊዜያት ያህል ከሰራ በኋላ ‹‹የኩባንያው ስራ አስኪያጅ እብሪት አስመረረኝ›› በማለት ስራውን በፈቃዱ ለቀቀ። ጥቂት ሰንብቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጥሩ ደመወዝ በመዝገብ ቤት ሹምነት ተቀጠረ። በመዝገብ ቤት ሹምነት ጥቂት ከሰራ በኋላ ወደ ትርጉም ክፍል ተዛወረ። ከዚያም ወደ ባንኩ አስተዳደር ክፍል ስልጣን ቢጤ አገኘ።
በወቅቱ ሁለት ጊዜያት ያህል ጥሩ የደመዝ ጭማሪ ማግኘት ችሏል። ጭማሪዎቹን ያገኘበት መንገድ ግን የተለየ ነበር። ይኸውም ሕንዳዊውን የባንኩን ሥራ አስኪያጅ በሽጉጥ በማስፈራራት ነበር። ሌላ አጋጣሚ ተፈጥሮ ሳይሳካ ቀረ እንጂ መንግሥቱ ከሽጉጥ ተሻግሮ በናስማስር ጠመንጃ በማስፈራራት ሦስተኛ ጭማሪ ለማስደረግ እየተዘጋጀ ነበር።
‹‹ባሕል አስከብራለሁ›› በሚል ምክንያት በርኖስ እየለበሰ ቢሮ መግባት ጀምሮም ነበር። በዚህም ተከሶ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በብዙ ልመና በርኖሱን አወ ለቀ። በዚህ የተናደደው መንግሥቱ ባንኩን በጋዜጣ ጽሑፍ ሙልጭ አድርጎ ተሳደበ። ይባስ ብሎም ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የባንኩን አገልግሎትና አሰራር ሊጎበኙ ወደ ባንኩ በሄዱበት ወቅት መንግሥቱ ወደ ክፍሉ ደብቆ ያስገባው ተጣጣፊ አልጋ ላይ ተኝቶ ተገኘ። ለምን ቢሮ ውስጥ እንደተኛ ሲጠየቅም ‹‹አለቆቼ ስራ ስለማይሰጡኝ የምሰራው ስራ ሳይኖር በከንቱ ደመወዝ እንደሚከፈለኝ ለማሳወቅ ነው›› ብሎ ተናገረ። በዚህ አድራጎቱ የተበሳጩት አለቆቹ በማግሥቱ የስንብት ደብዳቤ በፖሊስ እጅ ደረሰው።
በባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ውሳኔ ያልተስማማው መንግሥቱ መስሪያ ቤቱ ላይ ክስ መሰረተ። መንግሥቱ መስሪያ ቤቱን አሸነፈ። ነገር ግን ጉዳዩን ተከታትሎ ሳያስፈፅም በማስታወቂያ ሚኒስቴር በጋዜጠኛነት ተቀጠረ። በዚህኛው መሥሪያ ቤት የመንግሥቱ መንፈስ የተረጋጋ መሰለ። በወቅቱ በጋዜጣ ላይ በሚያቀርባቸው ጽሑፎቹ በብዙዎች ዘንድ እውቅና ለማግኘት በቃ። መንግሥቱ በወቅቱ በጽሑፎቹ ይዳስሳቸው የነበሩት ርዕሰ ጉዳዮች አብዛኞቹ የሥራ ባልደረቦቹ የማይደፍሯቸው ነበሩ።
በጋዜጠኝነት የጀመረው ጽሑፍ ወደ ደራሲነት አሸጋገረው። የድርሰት ስራውን የጀመረው በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ በጋዜጠኛነት ተቀጥሮ ማገልገል ከጀመረ ወዲህ ነበር። የመጀመሪያ ስራውንም ‹‹ሌላው እንደሚያይህ›› በተሰኘ ርዕስ በ 1949 ዓ.ም ለአንባቢያን አደረሰ። መጽሐፉ ልብ ወለድ ሲሆን ከጋዜጠኝነት ወደ ደራሲነት የተሸጋገረበት የበኩር ስራው ነው። ከዚህ በኋላ ብዙ መጽሐፍትን መጻፍ ችሏል።
‹‹ከማን አንሼ›› የተሰኘችው የልብ ወለድ መጽሐፉ የፊት ሽፋኗ ላይ አህያ ሙሉ ሱፍ ከነሰደርያውና ካፖርት ደርባ፣ ባርኔጣ ደፍታ፣ መነጽር አጥልቃ ትታይበታለች። ድርሰቱ በአህያዪቱ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን የመጽሐፏ አንዱ ክፍል የአህያ ጸሎት ነበር። ‹‹በስመ ጎርማንዴዎስ ወሰርዶ ወፋንድያ›› በማለት ጸሎቷን አድርሳ ወደ ቀለቧ እንደምታመራ ተጠቅሷል። አንድ ሰው እጅ እንዲነሳት ተደርጋ የተሳለችው አህያ ‹‹የወቅቱን የፓርላማ አባላት ለመሳደብ ሆን ብሎ ያዘጋጃት ናት›› ይባላል። ከላይ ከተጠቀሱት ሥራዎቹ በተጨማሪ የትርጉም መጽሐፍትንም ለአንባቢያን አድርሷል።
መንግሥቱ ገዳሙ ጥሩ ጸሐፊ ብቻም ሳይሆን ጥሩ አንባቢም ነበር። በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ድንቅ ቤተ-መጽሐፍት አደራጅቶ ነበር። መንግሥቱ ራሱን በራሱ የፈጠረ ምሁር ነበር። በመደበኛ ትምህርት ብዙም ባይገፋም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ጭምር መጽሐፍ (‹‹The Psychology of The White Races››) መጻፍ ችሎ ነበር። ለአንድ ዓመት ሥራ ሲፈታ ግን መጽሐፍቱን በሙሉ ቸበቸባቸው። ከዚያ ጊዜ በኋላም የመጽሐፍት ድሃ እንደሆነ ይነገራል።
መንግሥቱ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ የቆየው ለ15 ዓመታት ያህል ቢሆንም ያቀርባቸው የነበሩት ጋዜጣዊ ጽሑፎች ግን ጥቂት የሚባሉ ነበሩ። ብዕሩን ሲያነሳ ግን ‹‹ጉድ ለማውጣት›› ነበር። በወቅቱ የሚከናወኑና ከባለስልጣናትም ሆነ ከሌላው የኅብረተሰብ ክፍል የተደበቁ ነገሮችን ይፋ ለማውጣት የመንግሥቱ ብዕር ደፋር ነበረች።
‹‹ሞገደኛ›› የሚል ስያሜ የተሰጠውም ከግላዊ ባሕርይውና ድርጊቱ ባሻገር በሙያዊ ተግባሩ ሞጋች ስለነበር ነው። ጽሑፎቹ የሕዝቡን እውነተኛ ሕይወት የሚዳስሱ እንዲሁም ችግሩንና በደሉን ከፍላጐቱ ጋር የሚያመለክቱ ነበሩ። በተለይም የሥርዓቱን ንቅዘት በመዋጋት የሚደርስበት አሳርና መከራ ከሙያው አላገደውም። መንግስቱ ‹‹የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የገና ዳቦ ናቸው›› ሲል ብዙ ጊዜ ተናግሯል።
መንግሥቱ የማተሚያ ቤት እዳ መክፈል ተስኖት ሲሰቃይ ቢሸጡ ኖሮ ከማተሚያ ቤቱ እዳ የሚበልጥ ገንዘብ ሊያወጡ የሚችሉ መጽሐፍቱን ለየድርጅቶቹ በነፃ ያድል እንዲሁም ለመጻሕፍት አዟሪዎችም በነፃና በዱቤ ይሰጥ ነበር። ስለአብዛኞቹ መጽሐፍቱ ይዘት ግን አያስታውስም ነበር፤ የመጽሐፍቱ ቅጂም ኖሮት አያውቅም ነበር ይባላል። ስለመንግሥቱ ገዳሙ ሲነሳ አብሮ የሚታወሰው አወዛጋቢና አስቂኝ ባህርያቱ እንዲሁም በፈተና የተሞላው የሕይወት ጉዞው ናቸው። የመንግሥቱ ሕይወት በሙሉ ውጣ ውረድ የበዛበት ነበር። የሚሰራቸው ነገሮች አብዛኞቹ የሚያስደምሙና የሚያስቁ ነበሩ። ከላይ ከተጠቀሱት አለቆቹን የማስፈራራትና የመናቅ ድርጊቶቹ በተጨማሪ ሌሎች አስገራሚ ባህርያቱንና ድርጊቶቹን በጥቂቱ እንመልከት።
በአንድ ወቅት ለስራ ጉዳይ ወደ አስመራ ይላካል። ታዲያ በየፖሊስ ጣቢያው ስለሚገኙት ማረሚያ ቤቶች ሁኔታ መጻፍ ፈለገ። ባለስልጣኑን ለማስፈቀድ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀረ። ሞገደኛው መንግሥቱ ግን ወንጀል ሰርቶ ፖሊስ ጣቢያ መግባትን ለዓላማው ማሳኪያ አድርጎ ሊጠቀምበት አሰበ። ወደ አንድ መጠጥ ቤት ጎራ ይልና ባዶ ጠርሙሶችን እየመረጠ መሰባበር ጀመረ።
ኡኡታው ቀለጠና ፖሊስ እያዳፋ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰደው። ከሦስት ቀናት በኋላ በዋስ ተለቆ አዲስ አበባ ሲመለስ ስለአስመራ ፖሊስ ጣቢያዎች በርከት ያሉ መጣጥፎችን መፃፍ ቻለ። የአዲስ አበባን ፖሊስ ጣቢያዎች ለመጎብኘት ስላቀደ ሌላ አምባጓሮ ፈጥሮ ፖሊስ ጣቢያዎቹን በእስረኛነት ጎብኝቷቸዋል።
መንግሥቱ አንዱን ምስኪን ፈረንጅ በ700 ብር ደመወዝ ቀጥሮ ካፖርት እያሸከመ በፒያሳ ይዞር ነበር። ይህም ‹‹ፈረንጅ የሐበሻ አሽከር አይሆንም›› የሚለው አመለካከት ስህተት መሆኑን በተግባር ለማሳየት ነበር።
4 ኪሎ አካባቢ አንድ ተወዳጅ ውስኪ ቤት ነበር። ታዲያ የውስኪ ወዳጆች ቤቱን ከአፍ እስከገደፉ ድረስ እየሞሉት መቀመጫ አይገኝም ነበር። አንድ ቀን መንግሥቱ ከአንድ የውጭ ጋዜጠኛ ጋር ውስኪ ለመጠጣት ወደ ውስኪ ቤቱ ሲሄድ እንኳን መቀመጫ መቆሚያም ይጠፋል። መንግሥቱ በሩ ላይ ቆሞ አጨበጨበ።
ጠጪው ሁሉ ፀጥ ሲል በወቅቱ የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድን ጨምሮ ብዙ የመንግሥት ሹማምንትን ስም እያነሳ መሳደብ ጀመረ። ምድረ ጠጪም ‹‹የመንግሥቱ ስድብ ያሳፍሰናል›› በሚል ስጋት ሂሳቡን እየከፈለ ቤቱን ለቆ ወጣ። ቤቱ ጭር ሲል መንግሥቱ ከወዳጁ ጋር ምቹ ሶፋ ላይ ተቀምጦ ውስኪን መጠጣት ጀመረ።
መንግስቱ ገዳሙ አንጋፋ ጠጪ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ለምን እንደሚጠጣ ሲጠየቅ፤ ‹‹እኔ እኮ ለምን እንደምጠጣ እናንተ ደንቆሮዎች ስለሆናችሁ አይገባችሁም፤ የእኔ አእምሮ ከተራው ሰው አእምሮ በጣም የላቀ ነው። ስለዚህ ከእናንተ ጋር ለመነጋገር ያንን ከፍተኛ አእምሮዬን ወደ እናንተ ደረጃ ላወርደው የምችለው በአልኮል ኃይል ነው›› በማለት መናገሩ ይታወሳል።
መንግሥቱ ከጽሑፉና ከንግግሩ ባሻገር በእለታዊ ድርጊቱ ሁሉ ሥርዓቱን ይቃወም ነበር። አንዲት አህያ ጆሮዋ ላይ ብር ለጥፎ በየመጠጥ ቤቱ እየዞረ፣ አስተናጋጆቹ እንዲታዘዟት ያደርግ ነበር። በዚህም የጊዜው ባለስልጣኖች በገንዘብ እንጂ በአስተሳሰብ ከአህያ እንደማይሻሉ ለማስረዳት ያደረገው ነው ተብሏል።
አህያዋን ይዟት በየቦታው ሲዞር ‹‹ምንድን ነች?›› ብለው ሲጠይቁትም ‹‹የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባልደረባ ነች›› እያለ ይመልስ እንደነበር ይወሳል፤ በዚያ ዘመን ማስታወቂያውን በአህያ እየዞረ የሚያስነግረው ብሔራዊ ሎተሪ፤ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሥር ነበር። በመንግሥቱ እሳቤ አህያዋ የባለስልጣኖች ተምሳሌት ነበረች። የ 1953 ዓ.ም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን ደግፎ ሕዝቡን መቀስቀሱም ስርዓቱን የመቃወሙ ምልክት ነበር።
በሌላ ጊዜ ደግሞ በመስሪያ ቤቱ ግብዣ ላይ የአለቃው አለቃ ባለመገኘታቸው ይወርፋቸዋል። ድርጊቱ ‹‹ክብረ ነክ›› ተብሎ በማግሥቱ ኮሚቴ ተቋቁሞ ለፍርድ ቀረበ። ጥፋቱን የፈጸመበትን ምክንያት እንዲያብራራ ሲጠየቅ ‹‹ሰዎች ገፋፍተውኝ ነው›› ብሎ መለሰ።
እነማን እንደሆኑ ሲጠየቅም ለፍርድ የተሰየሙትን አባላት ስም ጠቀሰ። በዚህ የተነሳ የኮሚቴው አባላት ዳኝነቱን ትተው መንግሥቱን ለመደብደብ ከጀሉ። መንግሥቱ ሮጦ ወጣ፤ የተናደዱት የኮሚቴው አባላት ግን ተከትለው ያባር ሩታል። መንግሥቱ የኮሚቴው አባላት ስሜታቸውን መቆጣጠር የሚችሉ አለመሆናቸውን በአደባባይ አሳየ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ መንግሥቱን ሮም ከተማን እንዲጎበኝ ተጋበዘ። መንጌ ትኬቱን፣ ፓስፖርቱንና ቪዛውን በእጁ ካስገባ በኋላ በበረራው ዋዜማ ቀን ወደ አለቃው ዘንድ ሄዶ ከሳምንት በኋላ ወደ አውሮፓ እንደሚሄድና ጉዞውን እንዲፈቅዱለትም አንጀት የሚበላ ደብዳቤ ፅፎ ሰጣቸው።
አለቃውም የሚያስቸግራቸው ሰራተኛቸው በእጃቸው ላይ መውደቁ አስደስቷቸው ‹‹ደብዳቤው ከማኅደሩ ጋር ተያይዞ ይቀመጥ›› የሚል ትዕዛዝ ጽፈው ማመልከቻውን ወደ መዝገብ ቤት ላኩት። መንግሥቱ እንደተጫወተባቸው አለቃው ያወቁት ጠዋት ለስራ ሲፈልጉት በዚያው ቀን ጠዋት ቀደም ብሎ ወደ ሮም መብረሩ ሲነገራቸው ነበር።
ሌላኛው የመንግሥቱ ጠባይ አምባጓሮ መውደዱ ነበር። በዚህም ጠባዩ ምክንያት ከመቶ ጊዜ በላይ ተቧቅሷል። አራት ጊዜ በጩቤ ተወግቷል፤ አራት ጊዜ በመኪና ተገጭቷል፤ ህሊናውን እስከሚስት ድረስ ያጋ ጠመውን ጨምሮ 20 ጊዜ ማጅራቱን በወሮበላዎች ተመትቷል። አንድ ሙሉ ሌሊት በቆሻሻ ክምር ላይ አሳልፏል።
አንድ መ/ቤት እየሰራ እያለ አለቃው ዕድገት አግኝተው ወደ ሌላ ቦታ ሲሄዱ የሽኝት ፕሮግራም ይዘጋጅላቸዋል። ለፕሮግራሙ ከሁሉም ሰራተኞች የበለጠ መዋጮ አዋጣ። "ለምን ይሆን ይሄን ያደረከው?" ተብሎ ሲጠየቅ "አለቃዬ እዚህ እንዳይቀር ብሎም ወደዚህ ተመልሶ እንዳይመጣ ነው።" በማለት አስገራሚ መልስ ሰጥቷል።
መንግሥቱ በራሱ ላይ መቀለድም ይወድ ነበር። አንድ ጊዜ ሳይሞት ‹‹ሞቻለሁ›› ብሎ በሌላ ሰው በኩል በማስነገር ወደ መስሪያ ቤቱ ስልክ አስደውሎ የቀብሩ ቦታ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እንደሆነ አሳወቀ። ለቀስተኛው በቤተ-ክርስቲያኑ ተገኝቶ ተሰብስቦ አስከሬን ሲጠብቅ መንግሥቱ ጥቁር ሱፉን ግጥም አድርጎና ባርኔጣውን ደፍቶ ብቅ አለ። ለቀስተኛውን አመስግኖ ሳይሞት ‹‹ሞቻለሁ›› ብሎ ያስነገረው በእውነት ቢሞት የቀብሩ ስነ ስርዓት ምን እንደ ሚመስል በቁሙ ለማየት ፈልጎ ያደረገው መሆኑን ገለፆ ለቀስተኛውን በተነ።
መንግሥቱ በዓለም ዙሪያ ታዋቂ ሰዎችን በሚመዘግበው የ‹‹Who is Who›› ባሕረ መዝገብ ውስጥ ስሙ ሰፍሮለታል። ‹‹ትዳርን ለምርምር የሚጠቀምበት ይመስላል›› እስከሚባል ድረስ አራት ጊዜ አግብቶ አራት ጊዜ ፈትቷል።
መንግስቱ ሊሞት አንድ ሳምንት ሲቀረው "መንግስቱ ገዳሙ ሰሞኑን ይሞታል" እያለ በራሱ ላይ አሟርቶ በተወለደ በ48 ዓመቱ በተናገረው ሳምንቱ ውስጥ ሐምሌ 29 ቀን 1977 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ከስራዎቹ መካከልም፡-
-- አመፀኛ ሞግዚት -- እንኮዬ ደማሜ
-- ብታምንም ባታምንም -- ኮሳሳው ተማሪ
-- የእንስሳት ሮኬት -- ፃድቁ አራምዴ
-- ማጅራት መቺ -- አሳማና ድመት
-- ከምሱር -- አንተ ማን ነህ
-- የሃምሳ አለቃ ገብሬ -- አመሰግንሻለሁ
-- The Psychology of The White Races
-- የአልማዝ እዳ
-- ከማን አንሼ .....… የሚሉት ይጠቀሳሉ።
አዲስ ዘመን (መጋቢት 22 ቀን 2013)
ተጨማሪ የተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች
Via #ሙክታሮቪች
#getutemesgen #getu #ጌጡ

የታሪካዊው የአድዋ የክተት ዓዋጅ መፈተሻ ጥያቄዎች
ጥያቄ 1፦ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የታሪካዊውን የክተት ዓዋጅ ያወጁት መቼ ነበር?
ሀ) መስከረም 17 ቀን 1887 ዓ.ም
ለ) መስከረም 17 ቀን 1888 ዓ.ም
ሐ) ጥቅምት 17 ቀን 1888 ዓ.ም
መ) የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም
ጥያቄ 2፦ በክተት ዓዋጁ መሠረት፣ አፄ ሚኒሊክ "ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም" በማለት ጽኑ እምነታቸውን የገለጹት በማን ላይ ነበር?
ሀ) በጦር መሪዎቻቸው ብቃት
ለ) በዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች
ሐ) በእግዚአብሔር ረዳትነት
መ) በሠራዊቱ ብዛት
ጥያቄ 3፦ በራስ መኮንን ወልደሚካኤል መሪነት አስቀድሞ ወደ ጦር ግንባር የዘመተው የትኛው ጦር ነው?
ሀ) የጎጃም ጦር
ለ) የትግራይ ጦር
ሐ) የሐረር ጦር
መ) የጉራጌና ጨቦ ጦር
ጥያቄ 4፦ በአድዋ ጦርነት ወቅት የጉራጌና የጨቦን ጦር የመሩት ታዋቂ የጦር መሪ ማን ነበሩ?
ሀ) ራስ ቢትወደድ መንገሻ
ለ) ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ
ሐ) ደጃዝማች ወልዴ አሻግሬ
መ) ንጉሥ ተክለሃይማኖት
ጥያቄ 5፦ አብዛኛው የደቡብ፣ የምስራቅ፣ የምዕራብና የመካከለኛው ኢትዮጵያ ጦር ንጉሠ ነገሥቱን ተከትሎ የከተመበት (የሰፈረበት) ቦታ የት ነው?
ሀ) አሽንጌ ሐይቅ
ለ) ደጋ ሐሙስ
ሐ) መቀሌ
መ) ወረኢሉ
መልሳቹን ኮመንት ላይ አስቀምጡልን 👇

ቪቫ ምኒልክ! ቪቫ ጣይቱ!"
ከአድዋ ድል በኋላ የጣልያን ጋዜጦች ያሰፈሩት የውርደት ማስታወሻ
እንደሌላው ጥቁር ህዝብ ኋላ ቀር እና ቶሎ ይሸነፋል የተባለው የኢትዮጵያ ጦር ነጭን አሸነፈ ከሚባል የላም ወተት ነጭ ሳይሆን ጥቁር ነው ቢባል ብዙ ሰው ያምን ነበር።
ግን ሆነ ወተቱም ነጭ አይደለም ።ኢትዮጵያም ሊገዛት የመጣውን የጣልያን ጦርን አሸነፈች።
የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. የፀሐይ ጮራ የኤርትራን ተራሮች ተሻግሮ የአድዋን የምድር ገጽ ሲያሞቀው፣ በአውሮፓ ምድር “የማይሸነፍ” ተብሎ የሚታመነው የጄነራል ኦሬስቴ ባራቲዬሪ ጦር እንዲህ ባለ አሳፋሪ ሁኔታ ይበተናል ብሎ ያሰበ አልነበረም።
ነገር ግን ድል በኢትዮጵያ እጅ ነበረች። አድዋ ላይ የፈነዳው መድፍ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን አውሮፓን በተለይም ጣልያንን ከእነ መሠረቷ አናወጣት።
ዜናው ሮም የደረሰው ዘግይቶ ቢሆንም፣ የደረሰበት ፍጥነትና ያስከተለው ድንጋጤ ግን በጣልያን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነበር። የሮም መንገዶች በለቅሶ፣ በቁጣና በጩኸት ተሞሉ፤ ጋዜጦችም የቀለም እንባ አነቡ።
የመጀመሪያዎቹ የቴሌግራም መልእክቶች ሮም ሲደርሱ የጣሊያን ጋዜጦችና ሕዝቡ ለማመን ተቸግረው ነበር። "እንዴት?" የሚለው ጥያቄ በየአምደ-ጋዜጣው ሰፈረ።
Il Corriere della Sera እና ሌሎች ታዋቂ ጋዜጦች በድንጋጤ ተዋጡ። ለአመታት "ኋላ ቀር" እና "ያልሰለጠነ" ተብሎ ሲሰበክለት የነበረው የአፍሪካ ጦር፣ የአውሮፓን ዘመናዊ ጦር አሳዶ መምታቱ የብሔራዊ ኩራት ውድቀት ሆነ።
የጣልያን ጋዜጦች እንደዘገቡት፣ ጦርነቱ የተጠናቀቀው በሽንፈት ብቻ ሳይሆን በውርደት ነበር። ከ70% በላይ የሚሆነው የጣልያን ጦር ተደምስሷል። 289 ከፍተኛ መኮንኖች፣ ብርጋዴር ጄነራል ዳቦርሚዳ እና አሪሞንዲን ጨምሮ በጦር ሜዳ ወድቀዋል። 6,000 የሚጠጉ የጣልያን ወታደሮች ሲገደሉ፣ 3,000 የሚሆኑት ደግሞ በምኒልክ እጅ ተማረኩ። ይህ አሃዝ ለጣልያን ጋዜጠኞች "የማይዋጥ መራራ ጽዋ" ሆነ ። አይክዱት ነገር ምን ያድርጉት። ያፈጠጠ እውነት ሆነ።
የድሉ ዜና ጣልያን ሲደርስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፍራንቸስኮ ክሪስፒ መንግሥት መረጋጋት ተሳነው። ሕዝቡ ወደ አደባባይ ወጣ። የሚገርመው ግን፣ ሕዝቡ የገዛ መንግሥቱን እየረገመ፣ የድል አድራጊዎቹን የምኒልክንና የጣይቱን ስም መጥራት መጀመሩ ነበር።
በሮም፣ በሚላን፣ በናፖሊና በፓቪያ ጎዳናዎች ላይ "Viva Menelik! Viva Taytu!" (ምኒልክ ይኑር! ጣይቱ ትኑር!) የሚሉ ድምፆች አስተጋቡ።
ይህ ጩኸት ለንጉሠ ነገሥቱ ካላቸው ፍቅር የመነጨ ሳይሆን፣ ልጆቻቸውን ለማይረባ ጦርነት ወደ ማገዶነት በላከው የክሪስፒ መንግሥት ላይ ያላቸውን ጥሪት ጥላቻ ለመግለጽ ነበር።
ጋዜጦች አንደፃፉት የባቡር ሐዲዶች ተነቃቅለዋል፣ የቴሌግራፍ ሽቦዎች ተቆርጠዋል። በተለይም ሴቶች "ልጆቻችንንና ባሎቻችንን አትውሰዱብን" በሚል በባቡር ሐዲድ ላይ በመጋደም ወታደሮች ወደ አፍሪካ እንዳይጓዙ አግደዋል።
L'Italia የተሰኘው ጋዜጣ እንዲህ ሲል ዘግቧል፦
"በፓቪያ የሚገኙ እናቶችና ሚስቶች ባቡር ጣቢያውን በመውረር ወታደሮችን ከባቡር ላይ ጎትተው አውርደዋል። ሐዲዱን ነቃቅለውታል። ፖሊሶችና ወታደሮች ቁጣውን መቆጣጠር አልቻሉም።"
የጣልያን ጋዜጦች ጄነራል ባራቲዬሪን "ከዳተኛ" እና "ደካማ" እያሉ መክሰስ ጀመሩ። Della Tribuna Illustrata የተሰኘው መጽሔት በወቅቱ በነበሩ ስዕላዊ መግለጫዎች የጦርነቱን አስከፊነትና የጣልያንን ሠራዊት መበተን ለሕዝቡ አሳይቷል። "የአቢሲኒያ ጀግኖች የጣልያንን ጦር እንደ ቅጠል አረገፉት" የሚሉ ዘገባዎች የአውሮፓን የበላይነት ስነ-ልቦና ሰባበሩት።
ንጉሥ ኡምቤርቶ ቀዳማዊ ልደታቸው ሊከበር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት፣ አገሪቱ በሐዘን እንድትዋጥና የልደት በዓሉ እንዲሰረዝ አዘዙ። ጋዜጦች "ብሔራዊ የሐዘን ቀን" በማለት የፊት ገጻቸውን በበቀልና በውርደት ስሜት ሞሉት።
የእቴጌ ጣይቱ ሚና በጣልያን ጋዜጦች ዓይን
ለጣልያን ጋዜጠኞችና የታሪክ ጸሐፊዎች እጅግ አስገራሚው ነገር የሴት መሪ (የእቴጌ ጣይቱ ብጡል) በጦር ሜዳ መገኘት ነበር።
ጣይቱ ወታደሮቻቸውን እየመሩ፣ የመድፍ ተኩስ እየመጠኑና የውሃ መገናኛዎችን በመዝጋት የጣልያንን ጦር ለጥም መዳረጋቸው በጋዜጦች ላይ እንደ ትልቅ ተዓምር ተወርቷል።
"ይህች ሴት የጦር ጥበብን ከየት አመጣችው?" የሚሉ ጥያቄዎች በጋዜጦች አምዶች ላይ ተስተውለዋል።
የአድዋ ሽንፈት የክሪስፒን መንግሥት ጠራርጎ ወሰደው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዱ። ጣልያን በታሪኳ አይታው የማታውቀውን የዲፕሎማሲ ውርደት ተከናነበች። ጥቅምት 1889 ዓ.ም. የተፈረመው የአዲስ አበባ ውል፣ ጣልያን የኢትዮጵያን ሙሉ ነፃነት እንድታውቅና የወጫሌን ውል እንድትሰርዝ አስገደዳት።
የብሪታኒያው ጦር ዘጋቢ አውገስተስ ዊልዴ በወቅቱ እንደጻፈው፦
"ከቀትር በኋላ የአድዋ ጦርነት ድምፅ ሲጠፋ፣ የጣልያን ጦር ተስፋ ቆርጦ ይሸሽ ነበር። ሽብር በኤርትራ ምድር ነገሠ። በዕለቱ ማብቂያ ላይ የኢትዮጵያ ጦር አሁንም 3 ሚሊዮን ጥይት በእጁ ይዞ ነበር። ጣልያኖች ግን አንድም ቀን ለመዋጋት የሚያስችል አቅም አልነበራቸውም።"
የአድዋ ድል በጣልያን ጋዜጦች ላይ የታተመው በውርደት፣ በለቅሶና በቁጣ ቢሆንም፣ ለቀሪው ዓለም ግን የነፃነት ብርሃን ነበር። የአድዋ ድል የአውሮፓውያንን "የማይሸነፍነት" ተረት ሰባብሮ፣ የፓን-አፍሪካኒዝም እና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት መሠረት ሆኗል።
ዛሬም ድረስ አድዋ ሲነሳ፣ የሮም ጋዜጦች የፈሰሰው እንባና የኢትዮጵያ ጀግኖች ያንጸባረቁት ድል በታሪክ ገጾች ላይ በደመቀ ቀለም ተጽፎ ይገኛል።

የደም ትስስርና የነፍስ ጩኸት፡ ከዐድዋ ተራሮች እስከ ጋርቬይ
ዐድዋ አንድ ሺ ጊዜ ቢነገር አንድ ሺ መልዕክት ያለው ድል ነው።ዓለም በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ለጥቁር ሕዝቦች አስከፊ ነበረች። አፍሪካ በበርሊን የካርታ ጠረጴዛ ላይ እንደ ታረደ በሬ በቅርጫ ተከፋፍላ፣ ልጆቿ በገዛ ምድራቸው ባዕድ ሆነው ነበር።
በባሕር ማዶ፣ በአሜሪካና በካሪቢያን ደሴቶች፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቁሮች ከማንነታቸው ተላቀው፣ ስማቸው ተፍቆ፣ እንደ ቁስ ተቆጥረው በነጮች እርሻ ውስጥ በባርነት አለንጋ ይገረፉ ነበር። ጥቁር መሆን የውርደት፣ የዝቅተኝነትና የሽንፈት ምልክት ተደርጎ የታተመበት ያ ዘመን፣ ለብዙዎች ተስፋ የሞተበት ድቅድቅ ጨለማ ነበር።
ነገር ግን፣ በዚህ ሁሉ ስቃይና እንባ መካከል፣ ከአፍሪካ ቀንድ አንዲት ብርሃን ብልጭ አለች። ያቺ ብርሃን ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘች "አድዋ" ትባላለች።
በዛ ዘመን የኢትዮጵያ ተራሮች በጭስና በደም ተሸፍነዋል። ንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ፣ ገበሬውን፣ ቄሱን፣ ሸማኔውንና አርሶ አደሩን አስተባብረው ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀውን የጣሊያን ጦር ፊት ለፊት ተጋጠሙት። ያ ዛረም ድረስ ምናከብረው የድል ቀን ለነጭ ገዢዎች የውርደት፣ ለጥቁር ሕዝቦች ግን የትንሳኤ ቀን ነበር።
ድሉ ሲበሰር "ጥቁር ሰው ነጭን ማሸነፍ ይችላል!" የሚለው ዜና በባርነት ቀንበር ስር ላሉት ወንድሞቻችን የነፃነት ወንጌል ሆነ። ይህ ዜና ጃማይካ ደሴት ላይ ወደሚገኘውና ገና በልጅነቱ የዘሩን መገፋት እያየ ወደሚያለቅሰው ወጣቱ ማርከስ ጋርቬይ ደረሰ።
ማርከስ ጋርቬይ በጃማይካ ሲያድግ፣ በዙሪያው የሚያየው ድህነትን፣ ንቀትንና የጥቁርነትን ስብራት ነበር። ነገር ግን ስለ አድዋ ሲሰማ፣ በውስጡ አንድ ታላቅ እሳት ነደደ። ጋርቬይ ኢትዮጵያን በአካል አይቷት አያውቅም፤ ነገር ግን በልቡ ውስጥ ኢትዮጵያ "የእናት ምድር" ምልክት፣ የክብር ተራራ፣ የነፃነት መቅደስ ሆና ተቀረጸች።
ጋርቬይ "Universal Negro Improvement Association" (UNIA) የተባለውን ማኅበር ሲመሠርት፣ በቢሊዮን ለሚቆጠሩ ጥቁር ሕዝቦች የነገራቸው አንድ ትልቅ እውነት ነበር፦ "እናንተ አገር የሌላችሁ ተቅበዝባዦች አይደላችሁም፤ እናንተ አድዋ ላይ ታሪክ የሠሩ የጀግኖች ወንድሞች ናችሁ!" እያለ ይጮኽ ነበር። ጋርቬይ ለጥቁር ሕዝቦች የሰጠው ሰንደቅ ዓላማ መነሻው የአድዋው የኢትዮጵያ ባንዲራ ነበር። ቀዩ—ስለ ነፃነት የፈሰሰውን ደም፣ ጥቁሩ—የሕዝቡን ክብር፣ አረንጓዴው ደግሞ የአፍሪካን ተስፋ ይወክሉ ነበር።
የጋርቬይ ሕይወት በመከራ የተሞላ ነበር። በዘረኞች እየታደነ፣ በገዛ ወንድሞቹ እየተከዳ፣ በእስር ቤት እየማቀቀ እንኳን፣ ከአንደበቱ የማይጠፋው ቃል "ኢትዮጵያ" የሚል ነበር። ጋርቬይ በሃርለም ጎዳናዎች ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቁሮችን ሰብስቦ ሲያሰልፍ "ወደ አፍሪካ ተመልከቱ" እያለ ሲቀሰቅስ፣ በዓይነ ሕሊናው የሚታየው የምኒልክ ጎራዴና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ነበር።
ጋርቬይ እንዲህ ይል ነበር፦ "እግዚአብሔር ሆይ! ጥቁር ሕዝቦች በራሳቸው መርከብ ወደ እናት ምድራቸው ተመልሰው፣ እንደ አድዋ ጀግኖች በነፃነት የሚኖሩበትን ቀን አሳየኝ!" እርሱ ለዚህ ራዕይ ሲል ክብሩን፣ ገንዘቡንና ጤናውን መሥዋዕት አደረገ።
በወቅቱ የነበሩት ኃያላን መንግሥታት "ይህ ሰው ጥቁሮችን እያነቃ ነው" ብለው ፈሩት። በሐሰት ወንጀል ከሰሱት፣ አሰሩት፣ መጨረሻም ከአሜሪካ አባረሩት።
በ1930 ዓ.ም ንጉሥ ተፈሪ መኮንን "ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ" ተብለው ሲነግሡ፣ በካሪቢያን የሚገኙ የጋርቬይ ተከታዮች በደስታ አበዱ ። ጋርቬይ ቀድሞ "ጥቁር ንጉሥ በአፍሪካ ይነግሣል" ብሎ ተንብዮ ስለነበር፣ የንጉሡ መክሊት ለጋርቬይ ተከታዮች መሲሐዊ ትርጉም ነበረው።
ነገር ግን ታሪኩ እዚህ ላይ አሳዛኝ መልክ ይይዛል። በ1935 ዓ.ም ፋሺስት ጣሊያን በአድዋ የተሸነፈችውን ሽንፈት ለመበቀል በድጋሚ ኢትዮጵያን ስትወርር፣ ጋርቬይ በለንደን ስደት ላይ ነበር። ኢትዮጵያ ስትወረርና ንጉሡ ወደ ስደት ሲመጡ፣ ጋርቬይ ልቡ በሐዘን ተሰበረ። "እንዴት አባቶቻችን አድዋ ላይ ያስከበሩትን ክብር እናጣለን?" ብሎ ምርር ብሎ አለቀሰ። በወቅቱ ከንጉሡ ጋር የነበረው መጠነኛ የሐሳብ ልዩነትና የኢትዮጵያ በጣሊያን እጅ መውደቅ፣ ጋርቬይን ለከፍተኛ ሕመም ዳረገው።
ማርከስ ጋርቬይ በ1940 ዓ.ም በለንደን በብቸኝነት ሲያልፍ፣ የመጨረሻ ቃላቱ ስለ ጥቁር ሕዝብ አንድነትና ስለ አፍሪካ ነፃነት ነበሩ። የሚገርመውና ልብን የሚሰብረው፣ ጋርቬይ ሕይወቱን ሙሉ የዘመረላት፣ ስለ ክብሯ የታገለላትና መላ ሕይወቱን የሰጠላትን ኢትዮጵያን አንድም ቀን በአካል ሳይረግጣት መሞቱ ነው።
እርሱ ለጥቁር ሕዝቦች "ሥር" የሰጠ፣ ከአድዋ ተራሮች የተነሳውን የነፃነት እሳት ወደ ዓለም ያሰራጨ ታላቅ ነፍስ ነበር። እርሱ ሲሞት የነበረው ብቸኝነትና ድህነት፣ ለጥቁር ሕዝብ የከፈለው መሥዋዕትነት ትልቅነት ማረጋገጫ ነው።
ዛሬ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባ ላይ ሲቆም፣ አድዋ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከል ስትሆን፣ የማርከስ ጋርቬይ መንፈስ በዚያ ደጃፍ ላይ ቆሞ ይታያል።
ጋርቬይ በአካል ባይመጣም፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጃማይካና የዲያስፖራ ጥቁሮች ዛሬም "ኢትዮጵያ" እያሉ ይዘምራሉ።
አድዋ ላይ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም፣ በካሪቢያንና በአሜሪካ ለነበሩት ባሮች የነፍስ ምግብ ሆኗቸዋል። ጋርቬይ ደግሞ ያንን ደም ወደ ርዕዮተ ዓለም ቀይሮ፣ ጥቁር ሕዝብ በራሱ እንዲተማመን አድርጓል።
አድዋ እና ጋርቬይ የአንድ ታሪክ ሁለት አካላት ናቸው። አድዋ—ሥጋዊና ሞራላዊ ነፃነትን ሲሰጠን፣ ጋርቬይ—መንፈሳዊና አእምሯዊ ነፃነትን ሰጥቶናል። ዛሬም ድረስ በጃማይካ የሚገኙ ራስተፋሪያውያን ወደ ኢትዮጵያ (ሻሸመኔ) ሲመጡ፣ "ወደ አገራችን ተመለስን" የሚሉት ለዚህ ነው።
የአድዋ ድል ባይኖር ጋርቬይ የሚሰብከው ክብር አይኖርም ነበር። ጋርቬይ ባይኖር ደግሞ የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ተራሮች መካከል ብቻ ተቀብሮ በቀረ ነበር።
ዛሬ ላይ ሆነን ስናስበው፣ ጋርቬይ ማለት በአድዋ የተነሳው የነፃነት ብርሃን በዓለም ዙሪያ እንዲበራ ያደረገ ታላቅ የመብራት ማማ ነው።
ይህ ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ የአፍሪካውያንና የጥቁር ሕዝቦች ትስስር በውቅያኖስ የማይገደብ፣ በባርነት የማይበጠስና በጊዜ የማይደበዝዝ የደም ትስስር መሆኑን ነው። ጋርቬይ በለንደን ስደት ላይ ሆኖ የፈሰሰው እንባ፣ ዛሬ በአፍሪካ አንድነት ውስጥ ፍሬ አፍርቷል።
እኛ የአድዋ ልጆች፣ የማርከስ ጋርቬይ ራዕይ አደራዎች ነን። እርሱ ያላያትን ኢትዮጵያ እኛ ይዘናታል፤ እርሱ የናፈቃትን ነፃነት እኛ እየኖርንባት ነው። ይህን ታላቅ ክብር መጠበቅና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የታሪክ ግዴታችን ነው።
ክብር ለአድዋ ጀግኖች! ዝንተዓለም መታሰቢያነት ለአፍሪካ ኩራት ለማርከስ ጋርቬይ!

6 months ago
"የአፍሪካ አንድነት መሐንዲስ"
ከተማ ይፍሩ (1922-1988 ዓ.ም)
ከተማ ይፍሩ በወጣትነታቸው በውጭ አገር ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በኋላ በንጉሠ ነገሥቱ ዘንድ ባላቸው ከፍተኛ የመረዳትና የመግባባት ችሎታ ተለይተው ታወቁ በ1953 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1961) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙንአፍሪካ በታላቅ የመከፋፈል አደጋ ውስጥ ነበረች።
በወቅቱ አፍሪካ በሁለት ጎራዎች ተከፍላ ነበር
* የካዛብላንካ ቡድን፡ አህጉሪቱ በአንድ ጊዜ ወደ አንድ መንግሥትነት (Continental Government) እንድትጠቃለል የሚፈልጉ (በክዋሜ ንክሩማ የሚመሩ)።
* የሞንሮቪያ ቡድን፡ ቀስ በቀስ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ትብብር ማደግን የሚመርጡ።
በነዚህ በሁለቱ ጽንፍ የያዙ ቡድኖች መካከል የነበረው ልዩነት የአፍሪካን አንድነት አደጋ ላይ ጥሎት ነበር በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ከተማ ይፍሩ በንጉሠ ነገሥቱ ትእዛዝ "የሰላም መልዕክተኛ" በመሆን አህጉሪቱን ያቋረጡት።
በአውሮፕላን ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር እየበረሩ መሪዎችን በማነጋገርና ልዩነቶችን በማጥበብ ትልቅ ሥራ ሠሩ ከተማ ይፍሩ የነበረባቸው ዋነኛው ፈተና "ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመሥረት ሁሉም መሪዎች አዲስ አበባ ላይ እንዲገኙ" ማሳመን ነበር።
ከተማ ይፍሩ የአፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ ላይ እንዲሰበሰቡ ያደረገው ጥረት የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ብስለት ለዓለም ያሳየ ክስተት ነበር።
በከተማ ይፍሩ ከፍተኛ ድካም እና በንጉሠ ነገሥቱ ድጋፍ በግንቦት ወር 1955 ዓ.ም (May 1963) 32 የነፃ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ ላይ ተሰበሰቡ። በጉባኤው ወቅት የድርጅቱ "ቻርተር" ወይም መተዳደሪያ ደንብ ሲረቀቅ የከተማ ይፍሩና የቡድናቸው አበርክቶ ከፍተኛ ነበር።
በወቅቱ የነበረውን ውጥረት በማርገብና የሁለቱን ቡድኖች (ካዛብላንካና ሞንሮቪያ) ሃሳብ አቀናጅቶ አንድ የጋራ ሰነድ እንዲወጣ በማድረግ ረገድ የእሳቸው ብልህነት ወሳኝ ነበር በዚህም ምክንያት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) ተመሠረተ መቀመጫውም አዲስ አበባ እንዲሆን ተወሰነ።
ከተማ ይፍሩ ከአአድ መመስረት በኋላም ለአፍሪካ ነፃነትና አንድነትመትጋታቸውን አላቆሙም
በሞሮኮና አልጄሪያ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የነበሩ የድንበር ውጥረቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረዋል።ገና ነፃ ባልወጡ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የነፃነት ታጋዮች የኢትዮጵያ ድጋፍ እንዲጠናከር አድርገዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የፖለቲካ ማዕከል እንድትሆንና የዲፕሎማሲ አውድማ እንድትሆን መሠረት ጥለዋል።
ከተማ ይፍሩ በሥራቸው ትጉ፣በንግግራቸው ረቂቅና በሃሳባቸው አርቆ አሳቢ ዲፕሎማት ነበሩ ዛሬ የአፍሪካ ሕብረት (AU) በአዲስ አበባ በግርማ ሞገስ ሲቆም ከጀርባው የዚህ ታላቅ ሰው የላብና የጥበብ ውጤት አለበት።
ከተማ ይፍሩ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ "የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባት" ተብለው ቢጠሩ የሚገባቸው አህጉሪቱ በጥርጣሬና በልዩነት በታወከችበት ወቅት ድልድይ ሆነው ስላገናኟት ነው።

Sponsored by
Surafel
6 months ago
የራስነት አሻራ፡ ማንም የማይተካው የህይወት ድርሰት
በአለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ መጽሐፍት አሉ። ሆኖም እያንዳንዱ መጽሐፍ የራሱ የሆነ ጠረን፣ ድምፅና ትርክት አለው። የሰው ልጅም ልክ እንደ መጽሐፍ ነው። እያንዳንዳችን ገና ያልተነበብን፣ ገና ያልተገለጥን ድንቅ ታሪኮች ነን። ነገር ግን ብዙዎቻችን የራሳችንን ታሪክ ከመጻፍ ይልቅ የሌሎችን ታሪክ "ኮፒ" ለማድረግ ስንሞክር እንታያለን።
ይህ "ራስን መሆን" የሚለው ሃሳብ፣ በስነ-ጽሁፍ አለም ውስጥ ትልልቅ ደራሲያን ደጋግመው የገጠሙትና የታገሉት እውነት ነው። በሰዎች ፍላጎትና በህብረተሰብ ግፊት ውስጥ የራስን ማንነት ጠብቆ መቆየት ልክ እንደ አንባቢያን ልብ የሚነካ መጽሐፍ መጻፍ ከባድና ጥልቅ ጥበብ የሚጠይቅ ነው።
1. የደራሲያን "ድምፅ" እና የኦሪጅናልነት ምስጢር
ታዋቂው ደራሲ ኦስካር ዋይልድ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ራስህን ሁን፤ ሌሎቹ ቀድሞውኑ ተይዘዋል" (Be yourself; everyone else is already taken). ይህ ንግግር ለደራሲያን ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የተነገረ የህይወት መመሪያ ነው።
አንድ ደራሲ የሌላውን የአጻጻፍ ስልት ለመቅዳት በሚሞክርበት ቅጽበት፣ የራሱን ትክክለኛ "ድምፅ" (Voice) ያጣል። አንባቢያን የሚፈልጉት ሌላኛው "ሄሚንግዌይ"ን ወይም ሌላኛው "ካሊል ጂብራን"ን አይደለም፤ አንባቢያን የሚፈልጉት አንተን ነው።
ያንተን እይታ፣ ያንተን ስብራትና ያንተን ጥንካሬ ነው። አንተ የራስህን ማንነት ለሌሎች ስትል ስትለውጥ፣ አለም ልታገኝ የምትችለውን አንድ ልዩ ድንቅ ስራ (Masterpiece) እየነፈግካት ነው።
በስነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ፍራንዝ ካፍካ በመጽሐፎቹ ውስጥ የሰው ልጅን ብቸኝነትና የማንነት ፍለጋ ሲገልጽ፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ "በር" እንዳለው ይነግረናል። ያ በር ለአንተ ብቻ የተዘጋጀ ነው፤ ያንን በር አንተ ካልከፈትከው ማንም ሊከፍተው አይችልም።
ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር የራስህን በር ዘግተህ የሌላውን ደጅ እንደማንኳኳት ይቆጠራል።
2. የግለሰቦች ጽናት፡ ከጥላነት ወደ ብርሃን
የአንድ ደራሲ ትልቁ ስኬት የራሱን "ድምፅ" ማግኘቱ እንደሆነ ሁሉ፣ የአንድ ሰውም ትልቁ ድል የራሱን ማንነት ጠብቆ መቆሙ ነው። በታሪክ መድረክ ላይ ያንተን "ሚና" (Role) ሊጫወት የሚችል ማንም የለም።
የሮማው ንጉሠ ነገሥትና ፈላስፋ ማርከስ ኦሬሊየስ በመጽሐፉ ላይ እንደሚነግረን፣ ሰው በዙሪያው ባሉ ግፊቶች መወሰን የለበትም። ንጉሥ ቢሆንም እንኳ የራሱን የውስጥ ማንነት ለመጠበቅ በየቀኑ ከራሱ ጋር ይሟገት ነበር።
"ከውስጥህ የሚፈልቀውን ምንጭ ቆፍረው፤ ሁልጊዜ ካልተጠራጠርከው ሁልጊዜ ይፈልቃል" ይላል።
ወደ ራሳችን ታሪክ ስንመጣ ደግሞ ሻምበል አበበ ቢቂላን እናገኛለን። በ1960ው የሮም ኦሊምፒክ ላይ አበበ በባዶ እግሩ ለመሮጥ ሲወስን ብዙዎች ተገርመው ነበር። የሌሎችን ስታንዳርድ ተከትሎ የተመቸ ጫማ ቢፈልግ ኖሮ፣ ምናልባት ያን ታሪካዊ ድልና ልዩ አሻራ ላናገኝ እንችል ነበር።
አበበ ግን "የራሱን መንገድ" መረጠ። አለም የጫማውን አይነት ስትጠባበቅ፣ እሱ ግን በእግሩ አሻራ የታሪክ አዲስ ምዕራፍ ጻፈ። ይህ የሚያሳየው ሌላውን ለመምሰል አለመሞከር ለትልቅና የማይደገም ድል እንደሚያበቃ ነው።
3. የሀገራት ታሪክ፡ ራስን የመሆን ሉዓላዊነት
ሀገራትም ልክ እንደ ደራሲያን ናቸው። አንዳንዶቹ የሌላውን ሀገር ስልጣኔ፣ ቋንቋና ባህል ቀድተው የራሳቸውን ታሪክ ያጠፋሉ። ኢትዮጵያ ግን በዚህ ረገድ በአለም ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት።
በአድዋ ጦርነት ወቅት፣ ኢትዮጵያውያን ዘመናዊ የታጠቁ ወራሪዎችን ለመመከት የተጠቀሙት የራሳቸውን የአንድነትና የጀግንነት ስልት ነው። ሌላውን ለመምሰል ወይም ለባዕድ ገዢዎች ፍላጎት ለመንበርከክ ፈቃደኛ አልነበሩም። ይህ "ራስን የመሆን" ጽናት ኢትዮጵያን የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት አደረጋት።
አንድ ሀገር የራሷን ፊደል፣ የቀን አቆጣጠርና ባህል ይዛ መቆሟ ልክ እንደ አንድ ድንቅ ደራሲ የራሷን ኦሪጅናል ታሪክ በአለም መድረክ ላይ እንድታነብ አድርጓታል። ማንነትህን ለሌሎች ስትል አሳልፈህ አለመስጠትህ ነው የራስህ "ባንዲራ" እንዲውለበለብ የሚያደርገው።
4. ለምን ራስን መሆን ይከብዳል? (የውስጥ ትግሉ)
ብዙውን ጊዜ ራሳችንን የምንለውጠው "ተቀባይነት" ለማግኘት ነው። ደራሲያን መጽሐፋቸው እንዲሸጥላቸው ብለው የገበያውን ፍላጎት ብቻ ተከትለው ሲጽፉ፣ ስራቸው ነፍስ የሌለው "ባዶ ቃላት" ይሆናል። ህይወትም እንዲሁ ናት።
የሰዎችን ጭብጨባ ለመስማት ስትል ማንነትህን ስትቀይር፣ ውጫዊ ስኬት ብታገኝ እንኳ ውስጣዊ ሰላምህን ታጣለህ።
ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን እንዲህ ይላል፦
"ሁልጊዜ ሌላ ነገር እንድትሆን በሚገፋፋህ አለም ውስጥ ራስህን ሆነህ መገኘት ትልቁ ስኬት ነው"
ደራሲው ጄምስ ባልድዊን ደግሞ እንዲህ ይላል፦ "ራስህን ማግኘት በጣም ከባድ ነው፣ ምክንያቱም አለም አንተ እንዳትሆን ብዙ ወጥመዶችን ትዘረጋብሃለች።" አንድ ሀገር የራሷን ኢኮኖሚና ፖለቲካ ከሌሎች ብቻ ለመቅዳት ስትሞክር እንደምትወድቅ ሁሉ፣ አንድ ግለሰብም የሌላውን ሰው ስኬት ብቻ እያየ የራሱን መንገድ ከረሳ "የመኖር ትርጉሙ" ይጠፋበታል።
እውነተኛ ስኬት የሚለካው ሌላው በሚሰጥህ ደረጃ (Standard) ሳይሆን፣ አንተ ለራስህ ታማኝ ሆነህ በተጓዝክበት ርቀት ነው።
5. የራስህ ታሪክ ዋና ጸሐፊ ሁን
መጽሐፍ ሲጻፍ መጀመሪያ ረቂቅ (Draft) ነው፤ ከዚያም ይታረማል፣ ይስተካከላል። አንተም ራስህን ስትሆን ፍጹም መሆን አይጠበቅብህም።
ስህተቶችህ፣ ጠባሳዎችህና ድክመቶችህ የታሪክህ ውበት ናቸው።
አለም አንተን የምትፈልገው የሌላ ሰው ጥላ እንድትሆን ሳይሆን፣ የራስህ ብርሃን እንድትሆን ነው። ማንም ሰው ያንተን ሳቅ፣ ያንተን ህመም፣ እና ያንተን ተስፋ ልክ እንደ አንተ አድርጎ ሊገልጠው አይችልም። ስለዚህ ራስህን አትለውጥ። ራስህን "አሻሽል" እንጂ ራስህን "አትቀይር"።
ማጠቃለያ፡ ያንተ ድምፅ፣ ያንተ ውርስ
ታላላቅ ደራሲያን ስራቸውን ሲጨርሱ "ተፈጸመ" ብለው እንደሚፈርሙት ሁሉ፣ አንተም በህይወትህ መጨረሻ ላይ በታሪክህ እንድትኮራ ዛሬ ራስህን መሆን አለብህ።
ከአበበ ቢቂላ ጽናትን ተማር - የራስህ መንገድ፣ የራስህ ባዶ እግር እንኳን ቢሆን ያሸንፋል።
ከሀገርህ ታሪክ ኩራትን ተማር - ኦሪጅናል መሆን ክብርንና ሉዓላዊነትን ያመጣል።
ከኦስካር ዋይልድ ብልሃትን ተማር - የሌላውን ሰው ሚና ለመጫወት መሞከር ትርፉ ድካም ነው።
ያስታውሱ፣ ማንም ሰው የእርስዎን ሚና ከእርስዎ የተሻለ ሊጫወተው አይችልም። ምክንያቱም እርስዎ "የመጀመሪያው" እንጂ "የሌላው ቅጂ" አይደሉም። ያልተደገመና የማይደገም ድንቅ ታሪክ መሆንህን እወቅ። ዛሬም ነገም ራስህን ሁን!

7 months ago
🌹 የፋሽን ዓለም የቁንጮውን "ንጉሠ ነገሥት" ቫለንቲኖን በሀዘን ተሰናበተች!
የታዋቂው ጣሊያናዊ ዲዛይነር ቫለንቲኖ ጋራቫኒ በ93 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት፣ በከፍተኛ የፋሽን ጥበብ (Haute Couture) ታሪክ ውስጥ የአንድ ታላቅ ዘመን ማብቂያ ሆኖ ተመዝግቧል።
📍 የመጨረሻው ጉዞ
ሰኞ ለት በሮም በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ቫለንቲኖ፤ በቅርብ ወዳጆቹና ቤተሰቦቹ ታጅቦ ነበር። "የፋሽን የመጨረሻው ንጉሠ ነገሥት" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ይህ ጥበበኛ፣ ላለፉት 60 ዓመታት የዓለምን የፋሽን መድረክ በውበትና በቅንጦት ሲመራ ቆይቷል።
🔴 "ቫለንቲኖ ቀይ" (Valentino Red)
የቫለንቲኖ ስራዎች በልዩ ጥበባቸውና በዝርዝር አጨራረሳቸው ይታወቃሉ። በተለይም የሴቶችን ውበት የሚያጎላውና የንግሥና ግርማን የሚያጎናጽፈው ደማቅ ቀይ ቀለም (Valentino Red) የእሱ ልዩ መለያ ምልክት ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።
👗 ታዋቂ ደንበኞቹ
ቫለንቲኖ የዓለማችንን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች አልብሷል፦
ጃክሊን ኬኔዲ
ኤልዛቤት ቴይለር
ኦድሪ ሄፕበርን
ሶፊያ ሎረን
ልዕልት ዲያና እና ሌሎችም የሆሊውድ ኮከቦች።
🇮🇹 የጣሊያን ኩራት
ከጥቂት ወራት በፊት (በመስከረም 2025) ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ጆርጂዮ አርማኒ እና ቫለንቲኖ፣ ጣሊያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ምስል በመለወጥ ረገድ ትልቁን ሚና ተጫውተዋል። ጣሊያንን የውበት፣ የጥበብና የባህል ማዕከል በማድረግ ረገድ የእነዚህ ሁለት ሊቃውንት አስተዋጽኦ ታሪካዊ ነው።
✨ የተተወው ቅርስ
ቫለንቲኖ በ1999 ዓ.ም ከስራ ቢገለልም፣ የእሱ የፋሽን ተቋም በፒዬርፓኦሎ ፒቺዮሊ እና በአሁኑ ጊዜ በአሌሳንድሮ ሚሼል አማካኝነት ተተኪዎችን እያፈራ ይገኛል።
ሮም በሚገኘው ስቱዲዮው ውስጥ የሰለጠኑት በርካታ ዲዛይነሮች ዛሬ የዓለምን ፋሽን እየመሩ ይገኛሉ።
"እኔ ሁልጊዜም ውበትን በመፈለግ ላይ ነኝ" — ቫለንቲኖ ጋራቫኒ
የቫለንቲኖ ሞት የአንድን ሊቅ ማጣት ብቻ ሳይሆን፣ የአንድን የሕይወት ፍልስፍና—የጨዋነት፣ የሥነ-ሥርዓትና የዝርዝር ጥበብ ፍቅርን ማጣት ነው። የእሱ ደማቅ ቀይ ቀለም ግን ሁልጊዜም በፋሽን መድረኮች ላይ ሲያበራ ይኖራል።

"የቦሊቫር ምድር ቅዱስ ናት፤ በልጆቹ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት በክብርት አሜሪካችን ልጆች ሁሉ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው!" የኩባው ፕሬዝዳንት ሚጌል ማሪዮ ዲያዝ-ካኔል
የኩባው መሪ የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በአሜሪካ ሀይሎች ከሀገራቸው ተይዘው መወሰዳቸውን ክፉኛ ተችተዋል። የኩባው መሪ በፊደል ካስትሮ መታሰቢያፕ ሮግራም ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር ይህን ይመስለል;
ኢምፔሪያሊዝም ይውደም! (የህዝብ ጩኸት፦ “ይውደም!”)
ኢምፔሪያሊዝም ይውደም! (የህዝብ ጩኸት፦ “ይውደም!”)
የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ፣ ብልሹ እና ፋሽስት የሆነው ኢምፔሪያሊዝም ይውደም! (የህዝብ ጩኸት፦ “ይውደም!”)
የቬንዙዌላ እና የመላው አሜሪካችን ወንድሞች፤
የዓለም ዜጎች፤
ወንድም ማኔይሮ፣ በኩባ የቦሊቫሪያን ቬንዙዌላ ሪፐብሊክ አምባሳደር፤
የሀገሬ ልጆች፦
ዋና አዛዣችን ፊደል ካስትሮ ሩዝ ከሃያ ዓመታት በፊት፣ ኢምፔሪያሊዝም በመካከለኛው ምስራቅ ነፃ ሀገራት ላይ የሚያደርገውን አውዳሚ እንቅስቃሴ ሲተነትኑ እንዲህ ብለው ነበር፦
“የዓለም ሀገራት ሁሉ ፍልስፍናቸው፣ ፖለቲካዊ ሀሳባቸው እና የሥነ-ምግባር እሳቤያቸው ለማንም ለማይታወቅ፣ ወሰን የለሽ የሚመስል ኃይል ላለው ታላቅ መንግስት ገዥዎች ፍላጎትና ስሜት ተገዢ ሆነው አያውቁም። ውሳኔዎቻቸው ሊገመቱ የማይችሉ እና ይግባኝ የማይባልባቸው ናቸው። የማጥፋትና የመግደል አቅማቸው በንግግራቸው ሁሉ ውስጥ በጉልህ ይታያል።”
እነዚህ ቃላት ዛሬ የአሜሪካ ጦር በቬንዙዌላ ላይ የፈጸመውን አረመኔያዊ ጥቃት እና ወንድማችንን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮንና ባለቤታቸውን ሲሊያ ፍሎሬስን ያገቱበትን ተቀባይነት የሌለውና የለየለት አረመኔያዊ ድርጊት ለመግለጽ የተነገሩ ይመስላሉ። (ጭብጨባ)
ኩባ እነዚህን ድርጊቶች እንደ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ታወግዛለች፤ በሰላማዊ ቀጠና በሆነችው አሜሪካችን ላይ የተፈጸመ የወንጀል ጥቃት፣ የነፃነት፣ የክብር እና የአንድነት ተምሳሌት የሆነች ሀገር ሉዓላዊነት መጣስ እና በአለም አቀፍ ህግ ላይ የተፈጸመ ተቀባይነት የሌለው ጥቃት ነው ስትል ትከሳለች።
አይ፣ እናንተ ኢምፔሪያሊስቶች ሆይ! ይህ የእናንተ የጓሮ እርሻ ወይም አከራካሪ ግዛት አይደለም! የሞንሮ መርህን አንቀበልም፣ አንገነዘብምም፤ ጊዜ ያለፈባቸውን ነገሥታትና ንጉሠ ነገሥታትንም አንቀበልም! የቦሊቫር ምድር ቅዱስ ናት፤ በልጆቿ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት በክብርት አሜሪካችን ልጆች ሁሉ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው! (ጭብጨባ)
አቤል እንደጠቀሰው፣ ስለ ቬንዙዌላ እና በእርግጥም ስለ ኩባ ደማችንን አልፎ ተርፎም ህይወታችንን ለመስጠት ዝግጁ ነን፤ ነገር ግን ዋጋው በጣም ውድ ይሆናል! (ጭብጨባ)
በሰላማዊና በክቡር ህዝብ ላይ ንጋት ላይ የተፈጸመ ጥቃት ፈሪነት፣ ወንጀለኛነትና ክህደት ብቻ ሊባል ይችላል። ይህ በውጭ ሀገር መሪ ትዕዛዝ፣ በወታደራዊ የበላይነት በመጠቀም የተፈጸመ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ነው፤ ይህም የፋሽስት ወይም በነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት በመላው የሰው ልጅ ላይ ለመጫን የሚሞከረው የኒዮ-ፋሺዝም ግልጽ መገለጫ ነው።
ስለዚህ ዛቻው ለቬንዙዌላ ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ልጅ ነው። ይህም “ሰላም በኃይል” በሚል የተሳሳተ መርህ ላይ የተመሰረተ ነው።
በቬንዙዌላ የተፈጸመው ይህ የመንግስት ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ የህግ ደንቦችን የጣሰ አሳፋሪ ድርጊት ነው፦ አሜሪካን በምንም መልኩ ስጋት ባልሆነች ሰላማዊ ሀገር ላይ የተፈጸመ ወታደራዊ ወረራ እና በህዝብ የተመረጡ ህጋዊ ፕሬዝዳንት ታግተዋል። ይህ ያስቆጣል፣ እኛም እዚህ የተገኘነው ተቆጥተን ነው!
በጋዛ ሰርጥ የእስራኤል ጽዮናውያን ከሚፈጽሙት በሰው ልጅ ላይ ከሚደረግ ወንጀል ጋር የሚነጻጸር ድርጊት ነው፤ ስለዚህ ዝምታ ሊኖር አይገባም። (ጭብጨባ)
በዚህ ንጋት አንድ የሚያስደነግጥ እውነት አይተናል፦ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው አካል በእውነቱ ለዚህ አህጉር ሰላም ትልቁ ስጋት ነው። (ጭብጨባ) በቬንዙዌላ ላይ የፈጸመው ጥቃት በላቲን አሜሪካ እና በካሪቢያን ቀጠና ለዓመታት የነበረውን መረጋጋት የሚያናጋ ነው።
ይህንን የአሜሪካ ድርጊት የሚያከብሩ ሰዎች ጭንቅላታቸው በጥላቻ የታወረ ብቻ ናቸው። ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው ይህ የወንጀል ድርጊት ለቀጠናው እና ለዓለም ሰላም ያለውን ከባድ አደጋ ሊዘነጋው አይችልም።
ስለዚህ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲንቀሳቀስ እና ይህንን ህገ-ወጥ የፕሬዝዳንት እገታ እንዲያወግዝ እናሳስባለን። የቬንዙዌላ ህዝብ ያልሰጠውን መብት ማንም ሊጠቀምበት አይገባም።
ግቡ ወንድማችን ማዱሮ ወይም የቬንዙዌላ ወታደራዊ ኃይሎች አይደሉም፤ እንደ ማርኮ ሩቢኦ ያሉ ወንጀለኞች ለሳምንታት ሲያናፍሱት የነበረው የዕፅ ዝውውር ወሬም አይደለም። የኢምፔሪያሊስቶች እውነተኛ ፍላጎት የቬንዙዌላ ነዳጅ፣ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ነው።
የቬንዙዌላን ሀብት እንደሚፈልጉ ያለ እፍረት የተናገሩትን የትራምፕንና የተከታዮቹን ንግግር የማይሰሙ ፈሪዎች ብቻ ናቸው።
የቦሊቫሪያን አብዮት ከቻቬዝ ጀምሮ የፀረ-ኢምፔሪያሊስት ትግል ምሽግ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አብዮት ጥልቅ ህዝባዊ መሰረት ያለው መሆኑን አስመስክሯል።
ህዝቡ እንደ 2002ቱ ሁሉ ዛሬም ሉዓላዊነቱንና ፕሬዝዳንቱን ለመከላከል እንደሚነሳ ጥርጥር የለንም። (ጭብጨባ)
አሜሪካ የቬንዙዌላን ፕሬዝዳንት በኃይል ከሀገራቸው ለማውጣት ምንም ዓይነት የሞራልም ሆነ የሕግ ስልጣን የላትም! ነገር ግን ለማዱሮ ደህንነት በአለም ፊት ተጠያቂዋ አሜሪካ ናት! (ጭብጨባ)
ማዱሮ እና ሲሊያ በህይወት መኖራቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እንዲቀርብ ከሚጠይቁት የቬንዙዌላ ባለስልጣናት ጎን እንቆማለን።
ለወራት ያህል በቬንዙዌላ መንግስት ላይ የፈበረኩት የሀሰት ክስ ምንም ማስረጃ የለውም። ማስረጃ የሌለውም እንዲህ ያለ ተግባር ስለሌለ ነው። ይህ ሁሉ የተደረገው የፈጸሙትን የመንግስት ሽብርተኝነት ለማፅደቅ ነው።
በአሜሪካ ያሉ ተንታኞች እንኳ ይህ የዕፅ ሽብርተኝነት ወሬ ሀሰት መሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል። ትራምፕና ሩቢኦ ለእውነት ግድ የማይሰጣቸው መሆኑ ያሳዝናል።
በአለም አቀፍ ፀረ-ፋሽስት ፍርድ ቤት ሊፈረድባቸው የሚገባው እነሱ ናቸው! (ጭብጨባ)
በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ስልጣን ላይ ያሉ ፋሽስቶች "ሺህ ጊዜ የተደጋገመ ውሸት እውነት ይሆናል" የሚለውን የጎብልስን መርህ ከናዚዎች በሚገባ ተምረዋል። ነገር ግን እውነት ያሸንፋል፤ ህዝቡም ቀደም ሲል የሂትለርን ፋሺዝም እንዳሸነፈው ሁሉ ዛሬም እውነትን ይከላከላል።
የቬንዙዌላ ህዝብም ሆነ የአሜሪካ ህዝብ ወይም የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህንን ውሸት አያምንም።
አሁን በሁለት ግራ መጋባት ውስጥ የሚቆምበት ጊዜ አይደለም፤ አሁን ፋሺዝምንና ኢምፔሪያሊዝምን የምንቃወምበት ጊዜ ነው! (ጭብጨባ)
የአሜሪካ ህዝቦች ሆይ፣ አንድነታችንን እናጠናክር! ግዙፉ ጠላት እንዲያልፍ አንፍቀድ!
ከስድስት አስርት ዓመታት በፊት ቼ ጉቬራ “...ኢምፔሪያሊዝምን ቅንጣት ታህል እንኳን አትመኑ” ሲል ያስጠነቀቀውን አንርሳ። (ጭብጨባ)
ኒኮላስ እና ሲሊያ የቬንዙዌላ ናቸው፤ ህዝቡ ወደ መረጣቸውና ወደሚፈልጋቸው ህጋዊ ፕሬዝዳንታቸው ሊመለሱ ይገባል። (ጭብጨባ)

8 months ago
✨ እ ም ነ ጽ ዮ ን ▬▬ እ ና ታ ች ን ጽ ዮ ን ✨
“እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ፥ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፤“መዝ ፹፮፥፭።
#ethiopia | በቅዱሳት መጻሕፍት ጽዮን የሚለው ቃል ተደጋግሞ በነቢያቱ ተነግሯል፡፡ ሆኖም የጽዮን ትርጉም እንደተነገረበት ዐውደ ትንቢት እንደተሰበከበት መዋዕለ ትምህርት ምስጢሩ ይለያያል፡፡
በዚህ ጽሑፍ በጥቂቱ የምንመለከተው ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደመጣች፣ ኅዳር 21 ቀን ስለምናከብረው ዓመታዊ በዓል፣ በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ምስጢራዊ ትርጉም ነው፡፡ ታቦት አንቺ ነሽ» ብሏል፡፡
ታቦተ ጽዮን በፈቃደ እግዚአብሔር በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሰው ልጆች ተሰጥታ እስራኤላውያን ሲባረኩባት፣ መሥዋዕታቸውን ሲያቀርቡባት ከእግዚአብሔር ሲታረቁባት ኖረዋል፡፡
ከዐራት ሺሕ ሦስት መቶ ሃያ ሰባት ዓመተ ዓለም ጀምሮ ለዐርባ ዓመታት ያህል እስራኤላውያንን በክህነት ያገለግል የነበረው ካህኑ ዔሊ ዕድሜው ሲገፋ ሁለት ልጆቹን ጠርቶ ምሉዕና ዱግ "ዋናና ምክትል" አድርጎ ሾማቸው፡፡
በደብተራ ኦሪት ታቦተ ጽዮንን እንዲያገለግሉ የተሾሙት ሁለቱ ወጣት ካህናት "አፍኒን እና ፊንሐስ" ፈቃደ እግዚአብሔርን ተላልፈው ሦስት ታላላቅ በደሎችን ፈጸሙ፡፡
የመጀመሪያው በደል፤ በሙሴ ሥርዓት በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት በርታ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት የምትጠፋ መብራት እንድትቀመጥ የተሠራ ሥርዓት ነበር፡፡ ሆኖም አገልግሎት ከሌለ ሲበራ ማደሩ ለምን ? ብለው መቅረዙን አነሡ፤ መብራቱንም አጠፉ፡፡
ሁለተኛ ለራሳቸው ሥጋዊ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተው ለመሥዋዕት እንዲሆን ከመጣው እንስሳ ታርዶ ስቡ ሳይጤስ፣ደሙ ሳይፈስ ሥጋውን እየመረጡ ተመገቡ፡፡
ሦስተኛ ጸሎት እናደርሳለን ሥርዓተ አምልኮ፣ እንፈጽማለን ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጡ ከነበሩት እስራኤላውያን ቆነጃጅት ጋራ በዝሙት ወደቁ፡፡ አባታቸው ካህኑ ዔሊም የልጆቹን በደል እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ ቸል በማለቱ እግዚአብሔርአዘነ፡፡ በዚህም ምክንያት ፍልስጥኤማውያንን አስነሥቶ በጦርነት ቀጣቸው፡፡
ዕብራውያን በጦርነት ውሎ ያለልማዳቸው በአሕዛብ ተሸነፉ፡፡ ሕዝበ እስራኤልም ግራ ቢገባቸው «ድል የተነሣነው ታቦተ ጽዮንን ይዘን ባለመዝመታችን ነው» ብለው አፍኒን እና ፊንሐስ ጽላቱን እንዲሸከሙ አድርገው ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ምሽግ ገሠገሡ፡፡
ሆኖም ያሰቡት ሳይሳካ ታቦተ ጽዮን ተማረከች፣ አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ፤ ዕብራውያንም በጦርነቱ ድል ተደረጉ፡፡ ፍልስጥኤማውያንም ታቦተ ጽዮንን ማርከው ዳጎን ከተባለው ጣዖታቸው ላይ አስቀመጧት፡፡ በማግስቱ ሲመለሱ ዳጎን ተገልብጦ ታቦተ ጽዮን በላይ ተቀምጣ አገኟት፡፡ በማግስቱም ተመሳሳይ ድርጊት ተፈጽሞ ዳጎን ወድቆና ተሰባብሮ አገኙት፡፡ "1ሳሙ 5÷4" ይኽን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል ሰቆቃወ ድንግል በተባለው ድርሰቱ፤
« ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፤
አመ ነገደት ቁስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤
ወድቁ አማልክተ ግብጽ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፡፡
ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ. . .፤
ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡
ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብጽ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብጽ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» በማለት በንጽጽር አስቀምጦታል፡፡ (ኢሳ 19÷1)
ኃይል እና ድል ማድረጉን በዳጎን የጀመረችው ታቦተ ጽዮን የፍልስጥኤማውያንን መንደር በአባርና በቸነፈር በእባጭም መታች፡፡ ሕዝበ ፍልስጥኤምም ታቦተ ጽዮን ወደ እስራኤል ምድር እንድትመለስ አደረጉ፡፡
በእንደዚህ ዓይነት ታላቅ ክብር በሀገረ እስራኤል ትኖር የነበረችው ታቦተ ጽዮን ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷ ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ ሐሴት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡
█══ ▬▬ የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ▬▬ ══█
ከዐርባ ሁለት ጊዜ በላይ ስሟ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ሀገር ቅድስት ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተወደደች ለመሆኗ ነቢያቱ መስክረዋል፡፡ ከነቢያት አንዱ አሞፅም፤ «የእስራኤል ልጆች ሆይ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን ?» ብሎ እግዚአብሔር መናገሩን ጽፏል /9÷7/፡፡
ከሁሉም ከፍ ባለ መልኩ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት፤ «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» ብሎ ሕዝበ ኢትዮጵያ እደ ሕሊናውን እና እደ ልቡናውን ዘወትር በአምልኮተ እግዚአብሔር፣ በጾምና በጸሎት፣ በምጽዋትና በትሩፋት፣ ዘርግቶ በሃይማኖት ጸንቶ፣ በምግባር ቀንቶ የሚኖር በመሆኑ፤ ሕዝቡ ሕዝበ እግዚአብሔር ምድሪቱ ሀገረ እግዚአብሔር ተብለዋል። (መዝ.68÷31)
ለታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ዋናው ምክንያት በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው የሠመረ ግንኙነት ነው፡፡ ይኽም በመሆኑ የንግሥት ሳባ እና የንጉሥ ሰሎሞን ግንኙነት ሰፊውን ታሪክ ይዞ ይገኛል፡፡
የንግሥተ ሳባ ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረው ታምሪን ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ ንጉሥ ሰሎሞን ያሠራውን ቤተ መቅደስ ዓይቶ፣ የሰሎሞንን ጥበባዊ ዝና ሰምቶ በፍጹም መደነቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ ያየውንና የሰማውን ለንግሥቲቱ አጫወታት፡፡ እሷም የሰማችውን ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ የሰሎሞንን መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበብ ተመልክታ እግዚብሔርን አመስግና ተመለሰች፡፡
ከንጉሥ ሰሎሞን ምኒልክን ፀንሳ ከኢየሩሳሌም ተነሥታ ባሕረ ኤርትራን ተሻግራ፣ ሐማሴን አውራጃ ስትደርስ አሥመራ ከተማ በሚገኘው ማይበላ ከተባለው ቦታ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ የሕፃኑንም ስም የንጉሥ ልጅ ስትል «እብነ መለክ» አለችው፡፡ ይኽ ስም በዘመን ሒደት ምኒልክ ተብሎ ተለወጠ፡፡
ምኒልክ ተወልዶ በአእምሮ እያደገ ሲሔድ አባቴ ማን ነው ? አድራሻውስ ወዴት ነው ? እያለ ጥያቄ ቢያበዛባት በሃያ ሁለት ዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ላከችው፡፡ ምኒልክም አባቱ ንጉሥ ሰሎሞንን አግኝቶ ሕገ ኦሪትንና የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲያጠና ከቆየ በኋላ፤ ዐሥራ ሁለት ሺሕ እስራኤላውያንን አስከትሎ ከምድረ እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ጉዞውን አቀና፡፡
ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ለጉዞ የተነሡ ዕብራውያን ከቤተሰቦቻቸው መለየታቸው ሳያሳዝናቸው ከታቦተ ጽዮን መለየታቸው እጅግ ከበዳቸው፡፡ ወዲያው በፈቃደ እግዚአብሔር ታቦተ ጽዮንን ከመንበሯ አንሥተው በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ እና እስራኤላውያን ታቦተ ጽዮንን ይዘው አክሱም የደረሱት ኅዳር 21 ቀን ነበር፡፡ ንግሥተ ሳባም የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በጣም ስላስደሰታት በክብር ተቀበለቻቸው፡፡ «ወአንበርዋ ውስተ ሕፅነ ደብረ ሀገረ ማክዳ» እንዲል
በአክሱም ከተማ መካከል ደብረ ማክዳ (ዛሬ ቤተ ጊዮርጊስ ከሚባለው) ላይ ደብተራ ኦሪት ሠርተው አስቀመጧት፡፡
አሁን ያለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ ዐቅድ የታነፀው የአክሱም ጽዮን ገዳም ቅዳሴ ቤቱ ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ (የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት) እና ልዑል ፊልፕ ከክብር ባለሟሎቻቸው ጋር በተገኙበት ተከብሯል፡፡
█══ ▬▬ ኅዳር ጽዮን በአክሱም ▬▬ ══█
አክሱም ጽዮን ማርያም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መሠረታቸው ስትሆን ከተማዋም የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መነሻ ናት፡፡ አክሱም በሕገ ልቡና የጸናች፣ ሕገ ኦሪትን የፈጸመች፣ በሕገ ወንጌል ያመነች ናት፡፡ ለዚህም ነው «ሕግ ይወጽእ እምጽዮን፤ ከጽዮን ሕግ ይወጣል» የሚለው ጥቅስ የሚነገረው፡፡
በዓለ ልደትን በላሊበላ፣ ጥምቀትን በጎንደር፣ ኅዳር ጽዮንን በአክሱም ጽዮን ሲያከብሩት ልዩ የሆነ ሥርዓት ስለሚቀርብባቸው ምእመናን መንፈሳዊ ደስታ ይሰማቸዋል፡፡
ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፡-
በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ፣
ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ፣
በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት፣
ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት፣
ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት፣
አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት፣
በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን፡፡
ይኽ ሲባል ግን በዓሉ የሚከበረው በአክሱም ጽዮን ማርያም ብቻ ነው ማለት ሳይሆን፤ ታቦተ እግዝእትነ ማርያም ባለችበት ቦታ ሁሉ መከበሩን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ከዚሁ ጋርም የመመኪያችን ዘውድ፣ የመዳናችን ምክንያት፣ የንጽሕናችን መሠረት ስለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያልተነበየ ነቢይ፣ ያልሰበከ ሐዋርያ፣ ያልተቀኘ ባለቅኔ ከቶ የለም፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፣ በቤዛነቱ ዓለምን አዳነ፣ ዳግመኛም በክበበ ትስብእት፣ በግርማ መለኮት ለፍርድ ይመለሳል ብንል ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በመሆኑ ያለ ወላዲተ አምላክ ምስጢረ ሥጋዌን፣ ነገረ ድኅነትን፣ ነገረ ምጽአትን ማሰብ ከቶ የማይቻል ነው፡፡
«ዕግትዋ ለጽዮን፤ ጽዮንን ክበቧት» እንዳለ ነቢዩ፤ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈባትን የእስራኤል አምባና መጠጊያ የሆነችውን ታቦተ ጽዮንን ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ ያቀርቡላት እንደነበረው፤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡
በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምስጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ (ዘፀ. 25÷9-20)
ይህቺ የቃል ኪዳን ታቦት በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች፣
የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች (ኢያ. 3÷14-17)፤
ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች (ኢያ 6÷1-21)፤
ዳጎን የተባለ የፍልስጥኤማውያንን ጣዖት የቆራረጠች (1ሳሙ 5÷1-5)
በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች (1ሳሙ 6÷6) ፤
በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች (2ሳሙ 6÷12)፣
ዳዊት የዘመረላት (2ሳሙ 6÷14)፤
ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት (1ነገ 8÷1)፤ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡
በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለውን ረቂቅ እና ድንቅ ምስጢራዊ ንጽጽር አስመልክቶ ሦርያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም፤
«ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሔ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ፤ ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በው ስጥ በአፍአ በወርቅ የተለበጠ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት በንጽሕናና በቅድስና ጸንታ በኃጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞንም፤ «አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤
ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኃጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» (መኃ 4÷7) ሲል ተናግሯል፡፡
ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች መሆኗን ያጠይቃል፡፡
ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ሆናለች፡፡ ይኽንንም ቅዱስ ኤፍሬም ሲያስረዳ፤
«ኮንኪ ታቦቶ ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ፆርኪዮ በከርስኪ ተሰዓተ አውርኃ አንቲ ማእምንት ለዘኢያገምርዎ ሰማያት ወምድር፤
ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ»
ብሎ ተቀኝቶላታል፡፡
ስለሆነም ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትን የቸርነት በዓል እግዚአብሔር በፈቀደልን ቦታ ሆነን ስናከብር ከእኛ የሚጠበቀውን በጎ ነገር እያሰብን በተግባርም እየገለጥን ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ተሳታፊ እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡
የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እና ምልጃ አክሊልና ጉልላት በሆነው በእናታችን በወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት ሁላችንንም ይማረን
መልካም በዓል ‼
Petros Ashenafi Kebede

ከቡድን 2ዐ ጉባኤ ጋር በተያያዘ እውቅና የተቸራቸው ኢትዮጵያዊው ልዑል
#ethiopia | ልዑል እስጢፋኖስ በፈረንጆቹ 2023 በፓን አፍሪካ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የወጣቶች አምባሳደር ሆኖ መሾሙ ይታወሳል።
ለአፍሪካ አንድነት ተሟጋች የሆኑት ልዑል እስጢፋኖስ ማቴዎስ ባለፈው ሳምንት በጆሃንስበርግ በተካሄደው የቡድን 2ዐ ስብሰባ ላይ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከዓለም አቀፍ መሪዎች እና ተቋማት ከፍተኛ እውቅና አግኝተዋል።
ልዑል አስጢፋኖስ ማቲዮስ የሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥት ዘር የሆኑት የንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ ቀጥተ የዘር ሀረግ ያላቸው ኢትዮጵያዊ ናቸው።
ልዑል እስጢፋኖስ ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው የቡድን 2ዐ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በይፋ ተጋብዘው ስብሰባውን መካፈላቸውም ታውቋል።
በደቡብ አፍሪካ በጆሃንስበርግ ሳንድተን ከተማ ኑሮአቸውን ያደረጉት ልዑል እስጢፋኖስ በወጣቶች ላይ ያተኮሩ ተግባራትን በመደገፍ እንደዚሁም ወጣቶች በአፍሪካ የመሪነት ቦታ ላይ ድርሻቸው የጎላ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትልቅ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው፡፡
ልዑል እስጢፋኖስ በወጣቶች ላይ ያተኮሩ ተግባራትን በመደገፍ እንደዚሁም ወጣቶች በአፍሪካ የመሪነት ቦታ ላይ ድርሻቸው የጎላ እንዲሆን በማድግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
የሞሪታኒያ ስድስተኛ ፕሬዝዳንት አሚናህ ጉሪብ ፋኪም በይፋዊ የኢንስታግራም ገጻቸው እንደጻፉት "በአፍሪካ ህብረት የወጣቶች አምባሳደር ሆኖ እየሰሩ የሚገኙት ልዑል እስጢፋኖስ ኢትዮጵያ በአለም መድረክ ላይ ያላት ተጽዕኖ ፈጣሪነት በጉልህ እያሳዩ" ናቸው ብለዋል።
በጆሃንስበርግ በተካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ ላይ ለቡድናችን ላደረጉት ደግ አቀባበል ልዑል እስጢፋኖስ ማቴዎስን ማመስገን እፈልጋለሁ ብለዋለ።
እርሱ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታላቁ አርክቴክት እና የሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥት ዘር የሆኑት የንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ ቀጥተኛ ዝርያ ናቸው።
ልዑል ማቴዎስ የአፍሪካ አንድነትን እና እድገትን አበረታተዋል እና በ2023 በአፍሪካ ህብረት የፓን አፍሪካ ፓርላማ ለአባል ሀገራት የአፍሪካ ህብረት አምባሳደር ሆነው መሾማቸውም ተቁመዋል።
አሁን ልዑል ያገኙት ዕውቅና ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ላስመዘገበችውና ላበረከተችው አስተዋጽኦ ተምሳሌታዊ ተደርጎ ይወሰዳል ተብሏል።
ልዑል እስጢፋኖስ የኢትዮጵያን ነፃነት ያስጠበቀው የዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ዘር እንደመሆኑ መጠን የአመራር፣ የአንድነት እና የዲፕሎማሲ የዘር ሐረግ አሁንም ድረስ ኢትዮጵያን በጉልህ እየገለጻት እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑን የቸናገሩት የሞሪታኒያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡
አፍሪካ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የምንሰራው ስራ ወደ ፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
በአፍሪካ ወጣቶች በተለያዩ ቦታዎች ላይ ውሳኔ ሰጪ እንዲሆኑ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲያድግ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
ልዑል እሰጢፋኖስ በጂ 20 የመሪዎች ስብሰባ ላይ መገኘት አፍሪካ በአለም አቀፍ መድረክ የውሳኔ ሰጭ ቦታ ላይ ጠንካራ ውክልና እንድታገኝ ያደርጋታል ተብሏል።
አንደዛሁም የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ 2023 የጂ20 ቋሚ አባል ከሆነች በኋላ ተጽዕኖዋ እያደገ መምጣቱን ማሳያ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ልዑል እስጢፋኖስ ማቲዮስ የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ መካፈላቸው እንደዚሁም የደቡብ አፍሪካ መንግስት ለሰጣቸው እውቅና ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን አፍሪካ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የምንሰራው ስራ ወደ ፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
በአፍሪካ ወጣቶች በተለያዩ ቦታዎች ላይ ውሳኔ ሰጪ እንዲሆኑ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲያድግ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩም ነው የገለጹት፡፡
ልዑል እስጢፋኖስ አክለውም የአፍሪካ ሀገራት በአለም አቀፍ ደረጃ ተገቢውን ቦታ እንዲያገኙ ውሳኔ ሰጪም እንዲሆኑ ተግተን እንሰራለን ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

9 months ago
🇺🇸 በዳላስ፣ ቴክሳስ መንገድ ላይ ...
«ድል አባቷ ብዙ ነው" - ጆኔፍ ኬኔዲ
🌎 እኔም ሀገር አለኝ የሚታይ በሩቁ ...
የጉዞ ማስታወሻ ✈️🇺🇸
#ethiopia | በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
የቀድሞው ዝነኛና ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በቴክሳስ ግዛት፣ ዳላስ ከተማ፣ በክፍት መኪና፤ በጉብኝት ሳሉ ነበር እኤአ በኅዳር 22፣ 1963 ቀትር ላይ በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት። ፕሬዚደንት ኬኔዲ ስልጣን ላይ ከወጡ ሦስተኛ ዓመታቸን ሊይዙ ትንሽ ወራት ይቀራቸው ነበር።
ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ሰውየውን ( ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ) ማን ገደላቸው? ... ለምን ተገደሉ? ... በሚለው ዙርያ ሺህ ምርመራዎች ተደርገዋል።
እነዚህ የምርመራ ሂደቱን የያዙ ዶሴዎችም በምሥጢር ሲከማቹ ነው የኖሩት።
የ1964 የእውነት አፈላላጊው ‘ዋረን ኮሚሽን’ ፕሬዝዳንት ኬኔዲ የተገደሉት ሊ ሐርቬይ ኦስዋልድ በተባለ ግለሰብ ነው ብሎ ነበር።
ሊ ሐርቬይ ቀደም ሲል በሶቭየት ኅብረት ለአጭር ጊዜ የኖረ አሜሪካዊ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸመውም በግሉ ነው ተብሎ ነበር።
በቁጥጥር ሥር በዋለ በሁለተኛው ቀን ግን ብዙም ግልጽ ባልሆነ መንገድ በዳላስ ፖሊስ ምድር ቤት ውስጥ ተገድሏል።
ይሁንና የኬኔዲ አገዳደል፣ ገዳያቸው ነበር የተባለው ሰው በፖሊስ ምድር ቤት መገደል ምሥጢርና ተያያዥ ጉዳዮች ለዐሥርታት ለብዙ መላምቶች ክፍት ሆኖ ቆይቷል።
የሴራ ፖለቲካ ተንታኞች ደግሞ ግድያውንና ግድያውን ተከትሎ የሆነውን ነገር ሁሉ የተለያዩ ትርጉም ሲሰጡት ኖረዋል። ዛሬም ድረስ ...
አንዳንዶች ወጣቱን ፕሬዝዳንት ኬኔዲን የገደላቸው ሴአይኤ ራሱ ነው፤ ለዚያም ነው ገዳያቸው ነው የተባለውን ሰው ፈጥነው የገደሉት ብለው ያምናሉ።
ሲአይኤ ግን "የኔ እጅ የለበትም!" ይላል።
ገዳያቸው ነው የተባለው ኦስዋልድ በሜክሲኮ አገር ከኬጂቢ ሰላይ ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ወደ በኋላ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የመጀመርያው የሮማን ካቶሊክ እምነት ተከታይ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጊዜያቸው ገናና የነበሩ 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸውም ባሻገር በንግግር አዋቂነታቸው ይደነቃሉ።
ከንግግራቸው አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ እንደ ጥቅስ ይወሳሉ፤ ከነዚህም መሀል ‘አገሬ ለኔ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን እኔ ለአገሬ ምን አደረኩላት ብለን እንጠይቅ’ የሚለው የበዓለ ሲመት ንግግራቸው በይበልጥ ይታወሳል።
***
እንደምታውቁት የፕሬዝዳንት ኬኔዲን ግድያ የተመለከተ የምርመራ ዶሴ ከ60 ዓመት በኋላ ይፋ ሆኗል።
ይህ ዶሴ ለሕዝብ ይፋ እየሆነ ያለው ከ60 ዓመታት ጥብቅ ምሥጢርነት በኋላ ነው።
ብዛቱ ከ10ሺህ በላይ ይሆናል የተባለው ይህ ሰነድ ይፋ እንዲሆን የወሰኑት ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ናቸው።
ይሁንና አንዳንድ ሰነዶች አሁንም በምሥጢር የሚቆዩ ይኖራሉ። ይህም ለአንዳንድ ሰዎች ደኀንነት ሲባል ነው።
ምንም እንኳ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ግድያ ለዐሥርታት እያወዛገበ ቢቆይም በዚህ ሰነድ የሚገለጥ አንዳች ታላቅ ምሥጢር ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።
ይሁንና ዶሴው በፕሬዝዳንቱ ግድያ ዙርያ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ግን ልዩ ዕድል ነው ተብሏል።
የ1992 የአሜሪካ ሕግ ዶሴዎቹ በጥቅምት 2017 ለሕዝብ ይፋ እንዲደረጉ አስገዳጅ አድርጎ ነበር።
የአሜሪካ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት ለሕዝብ ይፋ የማይደረጉት ሰነዶች ብዛት 515 ነው ብሏል።
ከጠቅላላው ሰነድ 2ሺህ 545 ሰነዶች ደግሞ ይፋ የሚሆኑት በከፊል ናቸው።
***
ታሪክን የኋሊት 🇺🇸
ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸዉ። በተለይ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸዉ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን መጎብኘታቸዉ ይነገራል።
ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ጥሩ የወዳጅ ነት ግንኙነት እንደነበራት ቢታወቅም ጆኔፍ ኬኔዲ በተለይ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
«ድል አባቷ ብዙ ነው" እንዲል ጆኔፍ ኬኔዲ ብዙ የታሪክ ምዕራፍ ለመሰነቅ ወደ ሙዚየሙ ገባሁ።
The joy and excitement of John Fitzgerald Kennedy's life belonged to all men.
So did the pain and sorrow of his death.
When he died on November 22, 1963, shock and agony touched human conscience throughout the world. In Dallas, Texas, there was a special sorrow.
The young President died in Dallas. The death bullets were fired 200 yards west of this site.
by Philip Johnson, This memorial, designed by was erected by the people by the people of Dallas. Thousands of citizens contributed support, money and effort.
It is not a memorial to the pain and sorrow of death, but stands as a permanent tribute to the joy and excitement of one man's life.
Pohn Fitzgerald Kennedy's life.
***
የዓይን ነገር በዳላስ 🇺🇸
ዓይን በአሜሪካዊው አርቲስት ቶኒ ታሴት የሁለት ቅርፃ ቅርጾች ርዕስ ነው። ትላልቅ ዓይኖች ሰማያዊ አይሪስ ያላቸው እና ከፋይበርግላስ፣ ሙጫ እና ከብረት በዘይት ቀለም የተዘረዘሩ ናቸው። የዓይን ሐውልት የመጀመሪያው በ2007 የተሰራው በ12 ጫማ (3.7 ሜትር) ዲያሜትር ሲሆን በሴንት ሉዊስ፣ ሚዙሪ ውስጥ በላሜየር ቅርፃ ቅርፅ ፓርክ ይገኛል። ሁለተኛው እ.ኤ.አ. በ 2010 በ 30 ጫማ (9.1 ሜትር) ዲያሜትር የተሰራ እና በአሁኑ ጊዜ በዳላስ ፣ ቴክሳስ ውስጥ በThe Joule ሆቴል ባለቤትነት ይተዳደራል።
እኔና መንጌ ( በዳላስ - የክብር ስፖንሰሬ) ጉብኝቱን አቋርጠን የ“ቶክ ዳላስ “(talk Dallas) 🇺🇸 አዘጋጆችን (ጋዜጠኞች እና ተዋናይት) ፍፁም አስፋዉ፣ ቃልኪዳን ግርማ፣ ዋለልኝ አስማረ እና አዚዛ አህመድ ( ተዋናይት) ለማግኘት ወደ addison አዲሰን ከነፍን።
***
ጋዜጠኛና ደራሲ መሐመድ ሰልማን ‹‹ፒያሳ መሓሙድ ጋ ጠቢቅኝ›› (2004) "ትዝታዋ የቀረው የፒያሳዋ ዳላስ" ጣፋጭ ሥራው ትዝ አለችኝ።
ፍቅረኛህን "ማሀሙድ ጋር ጠብቂኝ" ስትላት ተሳስታ ማዶ ተሻግራ ከጠበቀችህ እድለኛ ናት፡፡ ካንተ በላይ የሚያስደስቷትን ሙዚቃዎች እየሰማች ነው ማለት ነው፡፡ ከዳላስ ሙዚቃ ቤት፡፡ ይህ ቤት የየመን ዝርያ ባላቸው ሐበሾች የተያዘ ነው፡፡ ከፒያሳ ፍቅር እንዲይዝህ ከሚያስችሉ አዚሞች አንዱ ነው፤ ዳላስ፡፡
በማለዳ ፒያሳ ከመጣህ በነ‹‹ያኒ›› ዜማ ትታደሳለህ፡፡ በሩቅ ምሥራቅ ረቂቅ ሙዚቃዎች ትፈወሳለህ፡፡ ረፋድ ላይ ፒያሳ ከደረስክ በነ መሀመድ ወርዲ፣ በነ አህመድ ሙስጠፋ፣ በነ ከማል ተርባስ በነ ሳይድ ከሊፋ ሱዳንኛ ዜማ ትደንሳለህ፡፡ በሱዳን ዜማ ለመደነስ አትሽኮርመም እንኳን አንተ ጠቅላይሚኒስትርህም ደንሰዋል፡፡
ከቀትር በኋላ ፒያሳን ከረገጥክ ደግሞ ዳላስ በብሉይየእንግሊዝኛ ሙዚቃዎች አቅልህን ያስትሃል፡፡ በነ ሳም ኩክ፣ በነ ሬይ ቻርለስ፣ በነ ኢታ ጀምስ፣ በነ ዶና ሰመር፣ በነ ዳያና ሮዝ፣ በነ ማርቪንጌ፣ በነ ቲና ቻርለስ፣ በነ ሮድ ስቴዋርት ዜማዎች ትሰክራለህ፤ ትሳከራለህ፡፡ ደግሞ ማምሻ ላይ እነ ዶን ዊሊያምስ፣ እነ አለን ጃክሰን፣ እነ ሩኒ ሚልሳፕ፣ እነ ዶሊ ፓርተን፣ እነ ኬኒ ሮጀርስ በአገረ-ሰብ ሙዚቃ አለምህን ያስቀጩኻል፡፡
ዳላስ ብሉይ በኾኑ ነገር ግን በሚጣፍጡ ሙዚቃዎች የፒያሳን ዜጎች የማዝናናት ተግባር ላይ የተሰማራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ይመስለኛል፡፡ ዛሬም ድረስ ሳይታክት ጆሮ ገብ ሙዚቃዎችን ያስኮመኩማል፡፡ በነፃ!
ከዚህ ቤት የሚደመጡ ሙዚቃዎች ዘፋኞቹ በሕይወት የሌሉ ወይም ደግሞ ዘፋኞቹ ራሳቸው የረሷቸው ሙዚቃዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ‹‹ኦልዲስ-በት-ጉዲስ››፡፡ ታዲያ በቲቪ የምታውቀው ጥቃቅንና አነስተኛ ጀማሪ ዘፋኝ እዚህ ዳላስ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ሲያንዣብብ ካየኽው አንድ ነገር ጠርጥር፡፡ ሊከትፍ ወይ ሊመነትፍ ነው፡፡
ዳላስ በብሉይ ሙዚቃዎች በይበልጥ ይታወቅ እንጂ በዓለም ላይ ዝናው ከፍ ያለ የሮክ፣ የጃዝ፣ የብሉዝ ወዘተ ሙዚቀኛን ሲዲ በመያዝም ይታወቃል፡፡ ዳላስ ገብተህ በትክክል የዘፈን ስም ከጠራህ ሲዲው ያለምንም ጥርጥር ይሰጥኻል፡፡ ድንገት እንኳ ሲዲው አልቆ ቢኾን ስለ አቀንቃኙ አንዳንድ ማብራሪያዎች ተሰጥቶህ ሌላ ጊዜ ብትመለስ ግን ሲዲው ከነልባሱ እንደሚዘጋጅልህ ተነግሮህ ነው የምትሰናበተው፡፡ ዳላስ ከተወለደ ጀምሮ ሙዚቃ አድናቂን አስቀይሞ አያውቅም፡፡ ሙዚቃ በእውቀት የሚነገድበት ቤት ነው፡፡
በነገርህ ላይ እዚያ አካባቢ የሚሠሩ የታክሲ ወያላዎች ዳላስ ሙዚቃ ቤት ተፅዕኖ ስላሳደረባቸው ይመስለኛል ተሳፋሪ ሲጠሩ ራሱ በዜማ ነው፡፡ የወያላዎቹን ድምፅ በደንብ አስተውህ ካዳመጥከው ሙዚቃዊ ቅላፄ አለው፡፡ ይስረቀረቃል፡፡ ‹‹22 ካዛንቺስ…መገናኛ!!!...መገናኛ ካዛንቺስ 22!!፣ አምስት ኪሎ..…ቅድስት ማርያም...አምስት ኪሎ!!!››
ፒያሳ ከመጣህ እንደ ወይን እያደር የሚጣፍጥ ዘፈኖችን ከዳላስ ሙዚቃ ዘወትር ትኮመኩማለህ፡፡ አምስት ሳንቲም ሳትከፍል፡፡ በዚህ ዘመን አንድን ሙዚቃ ሦስት ታክሲ ውስጥ ተከፍቶ ከሰማኸው እጅ እጅ ማለት እንደሚጀመር አንተም ሳትገነዘብ የቀረህ አይመስለኝም፡፡ የድሮ ሙዚቃ ግን ውብ ነው፡፡ ሄዶ ልብህ ላይ ነው የሚቀመጠው፡፡ አይጎረብጥህም፡፡ ካላመንከኝ ፒያሳ ዳላስ ሙዚቃ ቤት ደጅ ላይ ተሰየም፡፡
አንድ ድረ-ገጽ አንባቢዬ ዳላስ ሙዚቃ ቤትን እንዴት ገለጸው
A "The soundtrack of Piassa"
***
የደራሲና ዳይሬክተር ዮሐንስ ፈለቀ ( Yoni Cash ) እና ተገኔ ( እንደስሙ ተገን✈️🇺🇸) የሆኑኝን ወዳጆቼን ጨዋታ ተነጠቅሁ።
በእዝነ ልቦና ሀገር ቤት ገብቼ ነበር።
የተወዳጇ፤ የሶል ንግሥቷ አስቴር አወቀ "ሀገሬ" አልበም ከፍ ብሎ ይሰማኝ ነበር።
"ይሄም ሀገር ሀገር ይላል ሀገር ይሄ ሀገረ ብርቁ
እኔም ሀገር ሀገር ሀገር አለኝ ሀገር የሚታይ በሩቁ....❣️

ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም.
የግርማዊ ቀዳማዊ የዘውድ በዓል ሲዘከር።
"በክብር የነገሡት፤ በግርማ የታጀቡት"
► #በአበው ሥርዓት በግርማ ነግሠዋል፤ በአበው ሕግ ተገዝተዋል፤ ሀገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ በሕያው አምላክ ፊት ቃል ኪዳን ገብተዋል፤ ቃል ኪዳናቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ታትረዋል።
#ከአበው የተቀበሏት፤ በዓምላክ ፈቃድ ዙፋን ተቀምጠው የሚመሯት፤ በበትረ መንግሥታቸው መንገዷን የሚጠርጉላት ሀገራቸው ከፍ ከፍ ትል ዘንድ ሠርተዋል።
#ተናግረው ይሰማሉ፤ መክረው ይመልሳሉ፤ ገስጸው ያስተካክላሉ፤ ዘምተው ያሸንፋሉ፤ አስበው ያደርጋሉ፤ ጀምረው አምላካቸውን ይዘው ይፈጽማሉ።
#አበው ስለ ጠበቋት ሀገራቸው በጽናት ቆመዋል፤ ከአበው ስለተቀበሏት የከበረችው ሠንደቅ ዓላማቸው በጀግንነት ተፋልመዋል፤ ነጻነቷን እንዳታጣ ከጠላቶቿ ጋር ተጋጥመዋል፤ ዓለም ሁሉ ፊቱን ባዞረባቸው ጊዜ እውነትን፣ ቃል ኪዳንን እና ተስፋን ይዘው ብቻቸውን ቆመዋል።
#ሃሰተኞች በሚፈርዱበት፣ ሀሰተኞች በሚመሰክሩበት፣ ሀሰተኞች የፍርዱን ውሳኔ በሚያጸኑበት፣ የፍርድ ሚዛን ሁሉ ወደ ቅኝ ገዢዎች በምታዘነብልበት በዚያ ጊዜ በተስፋ ቆመዋል፤ ከእውነት ጋር ቆመው የእውነት፣ በእውነት፣ ስለ እውነት ለሀገራቸው ነጻነት ታግለዋል።
#እውነትን ይዘው ሀሰተኞችን በፍርድ ዓደባባይ አሸንፈዋል፤ ቅኝ ገዢዎችም በጦር ሜዳ ድል መትተዋል፤ በድል አድራጊነትም በግርማ እና በከፍታ በዓደባባይ ታይተዋል፤ በዙፋን ላይ እንደ ጫካ አንበሳ በአስፈሪ ክብር ተቀምጠዋል ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ።
#በቅኝ ገዢዎች የተበተኑትን ሰብስበዋል፤ መለያየትን አውግዘው አንድነትን አምጥተዋል፤ የአንድነቱን መሠረት አጥብቀዋል፤ የተረሱትን አስታውሰዋል፤ አንገታቸውን የደፉትን ቀና እንዲሉ አድርገዋል፤ የተገፉትን ደግፈዋል፤ ስለ ራሳቸው በራሳቸው የማይመክሩትን ስለ ራሳቸው እንዲመክሩ፣ መፍትሔም እንዲያበጁ አድርገዋል።
#በቅኝ ገዢዎች የተበተኑትን በአንድነት ሰብስበው አቅማቸውን አደርጅተዋል፤ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲናገሩ መንገዱን አሳይተዋል፤ ስለ እነርሱ ከእነርሱ በላይ እንደሌለ አሳይተዋቸዋል፤ በቅኝ ገዢዎች ምክንያት የጨለመችባቸውን የነጻነት ጀንበር እንዲመለከቱ አድርገዋል፤ በነጻነት ጀንበር በብርሃን ይመላለሱ ዘንድ አድርገዋል ጃንሆይ።
#እኒህ አያሌ ታሪክ የሚነገርላቸው፤ አፍሪካውያን የአንድነታችን አባት የሚሏቸው ንጉሠ ነገሥት ዘውድ የጫኑት፣ በከበረው ዙፋን ላይ የተቀመጡት፣ በትረ መንግሥቱን የጨበጡት፤ ቅብዓ መንግሥቱን የተቀቡት፤ የአበውን አደራ ይሸከሙ ዘንድ እጃቸውን ከፍ አድርገው ቃል ኪዳን የገቡት በዛሬዋ ቀን ነበር፤ ጥቅምት 23/1923 ዓ.ም።
#የነገሡበት ቀን በሃያ ሦስት፣ የነገሡበት ዓመተ ምኅረት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሦስት፣ የነገሡበት ደብርም ክብረ በዓሉ የሚከበረው በሃያ ሦስት ነው። ሃያ ሦስት የተገጣጠመላቸው ባለ ግርማው ንጉሥ።
#ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሕይዎቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ በተሰኘው መጽሐፋቸው ስለ ንግሥናቸው ሲጽፉ መስከረም 17/1909 ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ ሲነግሡ እኔም ለአልጋ ወራሽነቱ እና ለእንደራሴነቱ ስለተመረጥሁ በባለ ሙሉ ሥልጣን እንደራሴነቴ የመንግሥቱን ሥራ እየሠራሁ 14 ዓመታት ቆየሁ።
#ንግሥት ዘውዲቱ መጋቢት 24/1922 ዓ.ም ስላረፉ በማግሥቱ የንጉሠ ነገሥቱ ዐዋጅ ተነግሮ በዙፋኑ ተቀመጥሁ።
#ወደ ፊት ያለው ወራቱ ክረምት ስለነበረ የዘውድ በዓላችን ሰባት ወራት እንዲቆይ አደረግን። በኢትዮጵያ ያሉ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ፣ ባላባቶችም ሁሉ፣ በየገዳማቱ ያሉ አባቶች፣ የየአድባራቱ አለቆች፣ መጥተው የደስታችን ተካፋዮች እንዲኾኑ የጥሪ ደብዳቤ ተላከላቸው። ለዘውድ በዓሉም ዝግጅት ተደረገ ብለዋል።
#ልብሠ መንግሥቱ፣ ዘውዱ እና ሉሉ፣ በትረ መንግሥቱ እና ሰይፉ፣ ቀለበቱ ይህንም የመሰለው ሁሉ በተለየ በወርቅ እና በአልማዝ እየኾነ ተሠራ። ለመሳፍንቱ፣ ለመኳንንቱ፣ ለጦር አበጋዞች ሁሉ እንደየ ክብራቸው የክብር ልብስ ተዘጋጀላቸው።
#በዘውድ በዓሉ ዋዜማ በጅሮንዱ የንጉሠ ነገሥቱን ልብሰ መንግሥት እና ዘውዱን፣ ሉሉን፣ በትረ መንግሥቱን፣ ሰይፉን፣ የአልማዝ ቀለበቱን፣ የእቴጌይቱንም ልበሰ መንግሥት እና ዘውድ፣ የአልማዝ ቀለበት በሠረገላ አስገብቶ በታላቅ ሰልፍ ወስዶ በመናገሻው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ለሊቀ ጳጳሳቱ አስረክቦ ሌሊቱን ሙሉ ሲጸለይበት አደረ ይላሉ።
#ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱ በሌሊት ወደ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አቀኑ። ጸሎቱም ማካሄዱን ቀጠለ።
#ጃንሆይ ሲጽፉ ሥርዓተ ንግሡ ከመጀመሩ አስቀድሞ ሊቀ ጳጳሳቱ አቡ ቄርሎስ ገበታው የወርቅ የኾነ ወንጌል ይዘው ቀርበው የመሐላ ቃል እንድንፈጽም አደረጉ ብለዋል።
#ብላቴ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተሰኘው መጽሐፋቸው ሲጽፉ የዘውዱ ዋና በዓል ጥቅምት 23/1923 ዓ.ም እሑድ ነበር። ቅዳሜ ማታ የመናገሻ ጊዮርጊስ ካህናት እና ከየአድባራቱ ተመርጠው የመጡ መዘምራን ከማታው ጀምረው ማኅሌት ቆመው አደሩ።
#እኩሌቶቹ መወድስ ሲቆሙ እኩሌቶቹ ክስተት አርያም ያደርሱ ነበር እና ማኅሌቱ ደምቆ አደረ።
#ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱም በሌሊት በመሳፍንቱ እና በመኳንንቱ ታጅበው ወደ ቤተክርስቲያን መጥተው ለዚህ ማዕረግ ላበቃቸው ከዚህ ዕለት ላደረሳቸው አምላክ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ወደ ማረፊያ ድንኳን ሄደው ጸሎተ ሕሊና ሲያደርሱ አደሩ።
#ጠዋት ሲነጋ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ ሙሉ የማዕረግ ልብሳቸውን ከኒሻን ጋር ለብሰው የራስ ሉል እና የራስ ወርቅ ደፍተው በአዳራሹ ውስጥ በተሰናዳላቸው ስፍራ በየማዕረጋቸው ተቀመጡ። ጳጳሳት እና መምህራን ለሥርዓቱ ተዘጋጁ።
#ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓተ ንግሥ ወደሚፈጸምበት ገቡ። በመንበሩ አጠገብ ተሳልመው ጸሎት አደረሱ። ጸሎታቸው እንደጨረሱ በተሰናዳው ዙፋን ላይ ተቀመጡ።
#በዚህም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ አቡነ ቄርሎስ ፊታቸውን ወደ መሳፍንቱ እና ወደ መኳንንቱ አዙረው እንዲህ አሉ።
"እናንት የኢትዮጵያ መሳፍንት እና መኳንንት፣ የጦር አለቆች ወታደሮች እና ሠራዊቶች፣ በቤተ ክህነትም ያላችሁ ሊቃውንት እና አለቆች መምህራን እና ቀሳውስት ሁሉ ንጉሠ ነገሥታችን ግርማዊ ኃይለ ሥላሴ ከሰሎሞን እና ከንግሥተ ሳባ ከተወለደው ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ሳይቋረጥ ከመጣው መኾኑን ታውቃላችሁ።
#አሁን በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ቸርነት ዘውድ ጭኖ እንዲነግሥ ልቀባው ነው እና በሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሥራው ሁሉ ሀገርም በማሠልጠን ሃይማኖትም በማጽናት በዘመኑም ኢትዮጵያ በዕውቀት እና በትምህርት በጥበብም ከፍ ከፍ እንድትል በመትጋት ከወሰን እስከ ወንሰን የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲዘረጋ በማድረግ ይህንንም በመሰለው በመልካም ሥራው ሁሉ እንድትገዙለት እና እንድትረዱት አደራ እላችኋለሁ" አሉ።
#ሕዝቡም በዕልልታ አጀባቸው።
#ከዚያም ልብሰ መንግሥቱን አለበሷቸው፤ ቤተ መንግሥቱን አስጨበጧቸው፤ ሉሉንም ሰጧቸው፤ የአልማዙን ቀለበቱንም አጠለቁላቸው፤ የንግሥና ወግ እና ማዕረግ የኾነው ሰይፉን እና ጦሩንም ሰጧቸው፤ ቅብዓ መንግሥቱንም ቀቧቸው፤ ዘውዱንም ባርከው ደፉላቸው፤ በዚህም ጊዜ እልልታው አስተገባ፤ ታላቅ ደስታም ኾነ።
#ንጉሡም በግርማ ኾነው ከዙፋናቸው ላይ ተቀመጡ። የእተጌዋም በሥርዓቱ መሠረት ተፈጸመ። የአልጋ ወራሹም ከዙፋኑ ግርጌ ኾነው ቃል ኪዳን አሠሩ። እልልታውና ጭብጨው ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ። ንጉሡና እና ንግሥቷ ከፍ ባለ ሥፍራ ኾነው በታዩ ጊዜ እልልታው ቀለጠ።
#በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተፈጸመው ሥርዓት በተጠናቀቀ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱና እቴጌይቱ በስድስት ፈረሶች በሚሳብ በወርቅ ሠረገላ ተቀምጠው፣ ከፊትም ከኋላም በመሳፍንት እና በመኳንንት ታጅበው፣ በሠራዊት ሰልፍ መካከል አልፈው ወደ ቤተ መንግሥታቸው ተመለሱ።
#መሳፍንት እና መኳንንት የመንግሥታት መልእክተኞችም በየማዕረጋቸው በሠረገላ እና በአውቶሞቢል ኾነው አጀቡ። እምቢልታውና መለከቱ ሲንካለል፣ ነጋሪቱ እየተጎሰመ ገብር ገብር ሲል እጅግ ደስ ያሰኝ ነበር።
#በመንገድ ዳር ኾኖ ለማየት የተሰበሰበውም ሕዝብ ሰላምታ እየሰጠና እጅ እየነሳ ሺህ ዓመት ያንግሥዎ እያለ አጨበጨበ። ከቤተ መንግሥት በደረሱ ጊዜም ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱ ለመሰናበቻ በተሰናዳው ሥፍራ ቆመው ሲያዩት ሕዝቡ ሁሉ እንደገና እያጨበጨበ ሺህ ዓመት ያንግሥዎ እያለ እየመረቀ ተሰናበተ። የዘውዱ በዓል ግብርም ተገባ ተብሎ ተመዝግቧል።
#አምባሳደር ዘወዴ ረታ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት በተሰኘው መጽሐፋቸው ንጉሠ ነገሥቱ እና ንግሥቲቱ በወርቅ ሰረገላ ኾነው ወደ ቤተ መንግሥታቸው ሲያመሩ ከሕዝቡ የጎረፈላቸው የደስታ መግለጫ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው እየተባለ ይነገራል ብለው ጽፈዋል።
#ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እስከ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ድረስ በተደረገው የአንድ ሰዓት የእርጋታ ጉዞ ላይ እምቢልታው እና መለከቱ ሲነፋ፣ ነጋሪቱ ሲጎሸም፣ ካህናቱ ሲዘምሩ፣ ወታደሩ ሲሸልል፣ ከዚህ ሁሉ ጋር የሴቶች እልዕልታ እና የወንዱ ጭብጨባ ሲያስተጋባ፣ የአዲስ አበባን የጥቅምት ፀሐይ እጅግ ያጋላው ይመስል ነበር።
#በዋዜማው ቅዳሜ ከማታው በአራት ሰዓት የተጀመረው ጸሎተ ቅዳሴ እና የንግሥ በዓል ሥርዓት የተፈጸመው በማግሥቱ እሑድ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲኾን ነው።
#ለአሥራ አራት ሰዓታት ያለማቋረጥ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ንጉሠ ነገሥቱ እና ንግሥቲቱ ያሳዩትን ጥንካሬ እና የመንፈስ ጽናት ያላደነቀ አልነበረም።
#በተለይም በበዓሉ ተካፋይ ለመኾን ከአውሮፓ፣ ከእስያ እና ከአሜሪካ የመጡት የአሥራ አንድ ሀገራት እንደራሴዎች ከዚህ ቀደም በየትኛውም ዓለም ያላዩትን ይህን እጅግ ረጅም እና ከፍተኛ የኾነ ሥነ ሥርዓት ሲመለከቱ ኢትዮጵያ ያላት ጥንታዊ ባሕል ምን ያህል የሚደንቅ እና የሚከበር መኾኑን መገንዘብ የሚያስችላቸው ነው ብለው ጽፈዋል።
#ዘውድ በጫኑበት ዕለት በእርስዎ መሪነት ኢትዮጵያ ዘመናችን ያፈለቀውን ሥልጣኔ አግኝታ በዓለም ላይ የክብር ቦታ እንድትይዝ የሚያደርጉት ጥረት የተባረከ ይኹን ተብለው እንደተመረቁ ሁሉ ንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ በነጻነት የተቀበሏት ሀገራቸውን ታላቅ እና ገናና ትኾን ዘንድ አቅማቸው የፈቀደውን ሳይሰስቱ ሰጥተዋል።
#የኢትዮጵያን ክብር እና ጥቅም አስከብረዋል፤ ገናናቷን በአፍሪካ እና በቀረው ዓለም ደጋግመው አስመስክረዋል። የአፍሪካውያንን የአንድነት መሠረት ጥለው አልፈዋል።
#ኢትዮጵያን ስላገለገሉ እናመሰግንዎታለን፤ ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት፣ ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ስለታተሩ እናከብረዋታል።
✍️በታርቆ ክንዴ(አሚኮ)
#ethiopianhisoryandtourism #ethiopianhistoryandtourism #enkssm

10 months ago
የቴሌግራም መስራቹ ዱሮቭ ከፈረንሳይ የተሰረቁትን ጌጣጌጦች ለመግዛት ፈቃደኛ መሆኑን አስታወቀ
በላዩር ሙዚየም የተሰረቁ ውድ ቅርሶችን ገዝቶ ወደ አቡ ዳቢ ለመላክ ፍቃደኛ መሆኑን ፓቬል ዱሮቭ ገልፇል።
የቴሌግራም መስራች ፓቬል ዱሮቭ በፓሪስ ከሚገኘው ሉቭር ሙዚየም የተሰረቁትን ጌጣጌጦች ለመግዛት እና ለአቡ ዳቢ ለሚገኘው ሉቭር ሙዚየም ለመለገስ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል።
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚገኘው ሙዚየም ከስርቆት እና ተመሳሳይ ክስተቶች በተሻለ ሁኔታ የተጠበቀ ነው የሚል እሳቤ እንዳለውም ተናግሯል።
ዝርፊያው የተፈጸመው እሁድ 19 ነው። ሌቦች የንጉሠ ነገሥትነት ዘመን፣ የህዳሴ ዘመን፣ ናፖሊዮን III እና ፕሪንሲስ ዩጂኒ ጌጣጌጦች የሚታዩበትን «አፖሎ ጋለሪ» ሰብረው ገብተዋል።
በጠቅላላው ዘጠኝ የጌጣጌጥ ቁርጥራጮች ተሰርቀዋል።
ዱሮቭ ክስተቱ እንዳላስገረመው ፅፏል።
«ይህ በአንድ ወቅት ታላቅ የነበረች ሀገር እያሽቆለቆለች መምጣቷን የሚያሳይ ሌላ አሳዛኝ ምልክት ነው፤ መንግሥት እውነተኛ ስጋቶችን ከመጋፈጥ ይልቅ ሰዎችን በምናባዊ ማስፈራሪያዎች የማዘናጋት ጥበብን የተካነበት ነው» ሲሉ ጽፈዋል።
ከዚህ ቀደም ዱሮቭ የአውሮፓ ህብረት የዜጎችን የግላዊነት መብት ሊያግድ መቃረቡን ተችተው ነበር። በተጨማሪም ፈረንሳይ የመልእክት መላኪያ መተግበሪያዎች የተጠቃሚዎችን የግል መልዕክቶች እንዲቃኙ የሚጠይቅ ህግ ለማውጣት እየሞከረች ነው ሲሉ ከሰዋል።
እንደ ዱሮቭ ገለጻ፣ በጀርመን በመጨረሻው ደቂቃ ላይ የተደረገው ጣልቃ ገብነት ህጉ እንዳይጸድቅ አድርጓል።
seledadotio

የሀርቫርድ ምሩቁ የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በ97 ዓመታቸው አረፉ
ዕዝራ እጅጉ-(ተወዳጅ ሚድያ)
ታሕሣስ 24 ቀን 1920 ዓም - ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም
ቀብራቸው ሐሙስ ጥቅምት 13 በለንደን ይፈፀማል
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል። ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ቅፅ 3 መዝገበ አእምሮ ከ20 በላይ ዘርፎች ይኖሩታል። እዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ የአገር ባለውለታዎችን መሰነዳችን ይቀጥላል። የባንክ፣ የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ በሚለው ዘርፍ ውስጥ ታሪካቸው የሚሰነደው ልጅ የወንድወሰን መንገሻ ሲሆኑ ታሪካቸውንም ዕዝራ እጅጉ ሰንዶታል።
የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የግራጅዌት ቢዝነስ ትምህርት ቤት የታላቅ አገልግሎት እና ለቀድሞ ተማሪዎች የሥራ ስኬት ተብሎ የተሰየመውን ሽልማት ለልጅ የወንድወሰን መንገሻ እ ኤ አ በ1996 ዓ.ም ሲሰጣቸው በመጀመሪያ የእርሳቸውን ማንነት መገለጫ ያደረገው “ሰብዓዊነትን የረዱ” በማለት እና በምስጋናው መዝጊያ ላይ ደግሞ “ለዓለም ደህንነት የታቻላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ” ሲል ዩኒቨርሲቲው አድናቆቱን በሚገባ ገልጿል።
የተከበሩ አባታቸው አባ መንገሻ ገነሜ (ቀደም ሲል ፊታውራሪ) የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመድ ነበሩ። እናታቸው ወይዘሮ ተዋበች ዛማኑኤል በወራሪው ፋሽስት በግፍ ታስረው በተወሰዱበት ኢጣልያ አገር ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል። አክስታቸው ወ/ሮ ሉልአደይ ዛማኑኤል ልጅ የወንደሰንን እና ታናሽ እህቶቻቸውን ወ/ሪት ኮከቤ መንገሻን እና ወ/ሮ እግዚሐርያ መንገሻን እንደ ልጆቻቸው በፍቅር አሳድገዋቸዋል። ልጅ ከበደ ኃይሌ ታላቅ ወንድማቸው ነበሩ።
ልጅ የወንድወሰን የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተፈሪ መኮንን እና በፕሪንቺፔ ዲ ፒያሞንቴ ትምህርት ቤቶች ከተማሩ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አቃቂ በሚገኘው የአድቬንቲስት ሚሲዮን እና አዲስ አበባ በሚገኘው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተምረው አጠናቅቀዋል። ቀጥሎም፣ በጊዜው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ አካል የነበረው ሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተቀብሏቸው በኢትዮጵያ መንግሥት የነፃ ትምህርት ዕድል ድጋፍ ተምረው እ ኤ አ በ1954 ዓ.ም በኢኮኖሚክስ እና አካውንቲንግ በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቁ። ኮሌጅ የተማረ የመጀመሪያው የቤተሰቡ አባል እንደመሆናቸው መጠን ወደ እናት አገራቸው ሲመለሱ ሌሎችን ለመርዳት ይጓጉ ነበር። እውቀታቸውን እና ተሞክሯቸውን ለማስፋት ወደ አሜሪካ ሲጓዙ አስፈላጊው ገንዘብ ስላልነበራቸው ቦስተን ለመድረስ ወደካናዳ በሚጓዝ አንስተኛ የውቅያኖስ መስመር ላይ በአስተናጋጅነት በመሥራት ሀሳባቸውን አሳክተዋል። ከእዚያም እ ኤ አ በ1956 ዓ.ም ከሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በኤም ቢ ኤ (MBA) ዲግሪ ተመረቁ።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ ፣ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት ዶክተር አልበርት ሸቫይጸርን ለማግኘት ምዕራብ መካከለኛው አፍሪቃ ውስጥ ሩቅ ሥፍራ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተጓዙ። ሆስፒታሉ ውስጥ ሁለት ሳምንታት ከቆዩ በኋላ ዶክተር ሸቫይጸርን የመሰለ ሌሎችን ለመርዳት የወሰኑ ሰውን መተዋወቅ ለወጣቱ ምሩቅ ታላቅ ክብር ነበር። በሆስፒታሉ ያጋጠማቸው ተሞክሮ በአገራቸው ሕዝብ ሕይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት እራሳቸውም በቁርጠኝነት እንዲሰለፉ አድርጓቸዋል።
ወደ የሚወዷት አገራቸው ከተመለሱ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ምድባቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የከፍተኛ ማኔጅመንት ኃላፊነት ነበር። ቀጥሎም በገንዘብ ሚንስቴር የዳይሬክተርነት ሹመት አገኙ። በዚሁ ሥራቸው ላይ እንዳሉም በወቅቱ በልዑል ራሥ መንገሻ ሥዩም በሚመራው የኢትዮዽያ የአየር መንገድ ቦርድ አባል በመሆን አየር መንገዱ በተለይ አፍሪቃ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ የተለያዩ የብሪያ መስመሮችን እንዲዘረጋ የአባልነታቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዎል። የመጀመሪያዎቹን ቦይንግ ጄት ኤሮፕላኖች ለመግዛት በተደረገው ወሳኝ ድርድር ውስጥ ቁልፍ ሚና ነበራቸው።
በ1960 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሆነው ተሾሙ። ይህንን የተከበረ ቦታ ለመያዝ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ነበሩ። የባንኩን ተቋም ለማዘመን ጠቃሚ ተነሳሽነቶችን በመምራት እና በማስተባበር ለአሥራ አራት ዓመታት በዚያ ሥራ ላይ ቆይተዋል። ከብዙ ትሩፋቶቻቸው አንዱ የብሔራዊ ባንክ ሠራተኞችን ለተጨማሪ ሥልጠና ወደ ውጭ አገር ለመላክ ያደረጉት ብርቱ ጥረት እና ስኬታማ ተነሳሽነት ነበር። ይህ በአርቆ አሳቢነት ላይ የተመሠረተ ጥረት ቁጥራቸው እየጨመረ ለመጣው ልዩ የባንክ ሥራ መደቦች በሙያው የሠለጠኑ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያትን መመደብ አስችሏል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክለው ከሌሎች ሀገሮች የገንዘብ ሚኒስትሮች ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ የባንክ ማኅበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል። በተለይም ልጅ የወንድወሰን መንገሻ የአፍሪቃን ኤኮኖሚ ለማሳደግ እና ድህነትን ለመቀነስ የታለመውን የአፍሪቃ ልማት ባንክን (AfDB) በሚመሠረትበት ጊዜ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። ኢትዮጵያ መሥራች ባለአክሲዮን እንደመሆኗ መጠን ባንኩን በማቋቋም ረገድ ግንባር ቀደም እና ስኬታማ መሪነት አሳይታለች። ብዙዎች ይህንን ስኬት የብሔራዊ ባንክ ገዥ የአቶ ምናሴ ለማ እና ምክትል ገዥ የልጅ የወንድወሰን መንገሻ አርቆ አስተዋይነት እና አመራር ውጤት ነው ብለው ይመለከቱታል። በዓለም አቀፍ ፋይናንስ ላይ በነበራቸው ዕውቀት እና ባለራዕይ አመራር በ1980 ዎቹ ዓመታት አፍሪቃ ልማት ባንክ ካፒታሉን ለማሳደግ ክልላዊ ያልሆኑ ሀገራትም
(non-regional countries) እንዲሳተፉ መንገድ ከፍተዋል። ይህም ዛሬ የባንኩ የስኬት ታሪክ ነው።
ትጉህ እና ድንቅ አትዮጵያዊው ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በባልደረቦቻቸው እና በመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ሰፊ ክብር ያሰጡዋቸው አዕምሯዊ ችሎታቸው፣ የሀገራቸውን እድገት ለማፋጠን ያሳዩት ቁርጠኝነት እና ከሌሎች ጋር ተስማምቶ የመሥራት ችሎታቸው። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት የልጅ የወንድወሰን መንገሻን የአመራር ችሎታቸውን እና ለፍትሃዊነት ያላቸውን ጥልቀት በመመዘን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት አምስት ባለአደራዎች ውስጥ አንዱ አድርገው ሾመዋቸዋል። በዚህም ኃላፊነት ከ10 ዓመታት በላይ አገልግለዋል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ እ ኤ አ 1974 ዓም በሚያዝያ ወር ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የአይ ኤም ኤፍ (IMF) ስብሰባ በመሳተፍ ላይ እንዳሉ በኢትዮጵያ የነበረው ሁኔታ አደገኛ እየሆነ መጣ። ሁኔታው እርሳቸውንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከሚወዷት ሀገራቸው የለያቸው እና ማለቂያ የሌለው የመሰለው አሳዛኝ የግዳጅ ግዞት ዘመን መጀመሪያ ነበር። ባለቤታቸው እና ሦስቱም ልጆቻቸው ከእርሳቸው ጋር ለመሆን ወደ አሜሪካ መጓዝ ቻሉ። ልጅ የወንድወሰን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ጥሩ አማራጭ እንዳልሆነ ከተረዱ በኋላ ቅድሚያ የሰጡት ቤተሰቡን የሚያስተዳድሩበት በተለይም ልጆቻቸውን ለማስተማር የሚያስችል ሥራ መፈለጉን ነበር።
በዓለም አቀፍ ፋይናንስ መስክ በነበራቸው ሰፊ ዕውቀት እና ችሎታ ለንደን በሚገኘው First Boston Corporation (ፈርስት ቦስተን ኮርፖሬሽን) ሥራ ለማግኘት በቁ። ቀጥሎም በታማኝነታቸው እና በልዩ ችሎታቸው ወደ ማኔጂንግ ዳይሬክተርነት (Managing Director)
ደረጃ ዕድገት አገኙ። በኩባንያው ውስጥ ለብዙ ዓመታት በጥሩ መሪነት ከአገለገሉ በኃላ Associated African Financial Services (አሶሽየትድ አፍሪካን ፋይናንሽያል ሰርቪስስ) የሚባል የአማካሪ ድርጅት አቌቁመው በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉልህ በሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ ከአሥር አመታት በላይ ሠርተዋል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በቀሪው ሕይወታቸውም እንደሁልጊዜው ሌሎችን ለመርዳት፣ ሀገራቸው እና ሕዝቡ ላደረገላቸው ውለታ ለመመለስ ትኩረት በማድረጋቸው ብዙ የበጎ አድራጎት ቡድኖችን፣ ቤተክርስቲያናትን እና ግለ ሰቦችን ከመርዳት ተቆጥበው አያውቁም። ቤቱ ይቁጠረው እንደሚባለው ሰው የማያውቀው አምላክ ግን የሚያየው ብዙ ችግረኛችን ደግፈዋል። በተለይ ኅብረተሰቡን ለመርዳት ካቋቋሙዎቸው ቅርሶች አንዱ ለውድ አባታቸው መታሰቢያ እንዲሆን ባሕር ዳር ውስጥ የከፈቱት “አባ መንገሻ ገነሜ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል” ነው።
ወጣቶች ትምህርታቸውን በትጋት እንዲቀጥሉ እና በሙሉ አቅማቸው ዓላማቸውን ለማሳካት እንዲጥሩ ለማበረታታት እና ለመደገፍ በምንም ዓይነት ወደኃላ አዩሉም ነበር። በተለይም ለከፍተኛ ትምህርት እድሎችን ለማስፋት ከነበራቸው ጽኑ ፍላጎት በራሳቸው እና በባለቤታቸው ወይዘሮ ሕይወት ስም በሃርቫርድ ቢዝነስ ትምህርት ቤት የትምህርት ብቃት ላላቸው የአፍሪቃውያን ተማሪዎች ስኮላርሺፕ አቋቀቁመው ብዙ ተማሪዋች ሊጠቅሙ ችለዎል።
በፍቅር ወንድዬ ተብለው የሚጠሩትን ልጅ የወንድወሰን መንገሻን የማወቅ ዕድል ያገኙ ሁሉ ተንከባካቢነታቸውን፣ ትሁትነታቸውን እና ለጋሥነታቸውን ይመሰክራሉ። ዘመዶችን፣ ጓደኞችን እንዲሁም ሌሎች ሰዎች መርዳት እና ምክር በመለገስ ረገድ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። እንዲሁም ታዳጊ እና ወጣት የሆኑት ዘመዶቻቸው እንደአባት እና አማካሪ ያዩዋቸው ነበር። የቤተሰብ አባላት ታማኝነታቸውን እና ጥበባዊ ምክራቸውን ከፍ አድርገው ይመለከቷቸው ነበር። በተለይም የቅርብ ዘመዶቻቸው ከሆኑት ከራሥ አንዳርጋቸው መሳይ እና ከልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለ ሥላሴ ፍቅር እና አክብሮት ምንግዜም አልተላያቸውም።
ልጅ የወንድወሰን እ ኤ አ ጥቅምት 12 ቀን 2025 በለንደን በሚገኘው ቤታቸው በቤተሰብ ተከበው በሰላም በማረፍ ከዚህ አለም ተለይተዋል።
በነሐሴ 23 ቀን 1UG4 ዓም እኤአ በትዳር ካገቡዋቸው ከውድ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ሕይወት ጋር በፍቅር፣ በመከባበር እና በተድላ የዕድሜ ባለፀጋ ሆነው ያሬድ፣ ያድዋ እና የአደይን አፍርተዋል። የሰባት የልጅ ልጆች አያት ለመሆን በቅተዋል - ካሌብ፣ ሶፊያ፣ ሉላዴይ (ሊሊ)፣ ጌሊላ፣ አሸር፣ ፀጋ እና ኢያሱ ። ቤተሰቡ መሪ አባት የነበሩትን በሞት በማጣታቸው በታላቅ ሀዘን ላይ ቢወድቁም አምላክ ረጅም ዕድሜ ስለሰጣቸው እና ቤተሰቡን ፍቅር በተሞላበት አርአያነት በመምራታቸው በምስጋና ተሞልተዋል።
እኚህ ትሁት የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 13 ላይ እንዳስተማረው የፍቅር ምሳሌ ሆነው ኖረዋል።
“ፍቅር ታጋሽ ነው፣ ፍቅር ደግ ነው፣ ፍቅር አይመቀኝም፣ ፍቅር አይታበይም፣ ፍቅር አይኰራም፣ ፍቅር ስነስርዓተቢስ አይደለም፣ ፍቅር የራሱን ጥቅም ብቻ ፈላጊ አይደለም፣ ፍቅር አይበሳጭም፣ ፍቅር ቢበደልም እንኳ በደልን እንደበደል አይቆጥርም፣ ፍቅር እውነት በሆነ ነገር ይደሰታል እንጂ ክፋት በሆነ ነገር አይደሰትም፣ ፍቅር ሁሉን ችሎ ይታገሳል፣ ፍቅር በሁሉም ላይ ተስፋ የደርጋል፣ ፍቅር በሁሉም ነገር ይጸናል”
ቸሩ አምላክ ነፍሳቸውን የዘላለም እረፍት ይስጥልን።
ቤተሰቡ ጓደኞቻቸው እና ዘመዶቻቸው ለላኩት አጽናኝ መልእክቶች እና የሀዘን መግለጫዎች ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።ልጅ የወንድወሰን መንገሻ
ታሕሣስ 24 ቀን 1U20 ዓም - ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓም
የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የግራጅዌት ቢዝነስ ትምህርት ቤት የታላቅ አገልግሎት እና ለቀድሞ ተማሪዎች የሥራ ስኬት ተብሎ የተሰየመውን ሽልማት ለልጅ የወንድወሰን መንገሻ እ ኤ አ በ1UUG ዓም ሲሰጣቸው በመጀመሪያ የሳቸውን ማንነት መገለጫ ያደረገው “ሰብዓዊነትን የረዱ” በማለት እና በምስጋናው መዝጊያ ላይ ደግሞ “ለዓለም ደህንነት የታቻላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ” ሲል ዩኒቨርስቲው አድናቆቱን በሚገባ ገልጿል።
የተከበሩ አባታቸው አባ መንገሻ ገነሜ (ቀደም ሲል ፊታውራሪ) የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመድ ነበሩ። እናታቸው ወይዘሮ ተዋበች ዛማኑኤል በወራሪው ፋሽስት በግፍ ታሥረው በተወሰዱበት ኢጣልያ አገር ውስጥ ሕይወታቸው አለፏል።
አክስታቸው ወ/ሮ ሉልአደይ ዛማኑኤል ልጅ የወንደሰንን እና ታናሽ እህቶቻቸውን ወ/ሪት ኮከቤ መንገሻን እና ወ/ሮ እግዚሐርያ መንገሻን እንደ ልጆቻቸው በፍቅር አሳድገዋቸዋል። ልጅ ከበደ ኃይሌ ታላቅ ወንድማቸው ነበሩ።
ልጅ የወንድወሰን የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተፈሪ መኮንን እና በፕሪንቺፔ ዲ ፒያሞንቴ ትምህርት ቤቶች ከተማሩ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አቃቂ በሚገኘው የአድቬንቲስት ሚሲዮን እና አዲስ አበባ በሚገኘው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተምረው አጠናቅቀዋል። ቀጥሎም፣ በጊዜው የላንደን ዩኒቨርሲቲ አካል የነበረው ሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተቀብሏቸው በኢትዮጵያ መንግሥት የነፃ ትምህርት ዕድል ድጋፍ ተምረው እ ኤ አ በ 1U54 ዓም በኢኮኖሚክስ እና አካውንቲንግ በከፍተኛ ማዕርግ ተመረቁ። ኮሌጅ የተማረ የመጀመሪያው የቤተሰቡ አባል እንደመሆናቸው መጠን ወደ እናት አገራቸው ሲመለሱ ሌሎችን ለመርዳት ይጓጉ ነበር። እውቀታቸውን እና ተሞክሯቸውን ለማስፋት ወደ አሜሪካ ሲጓዙ አስፈላጊው ገንዘብ ስላልነበራቸው ቦስተን ለመድረስ ወደካናዳ በሚጓዝ አንስተኛ የውቅያኖስ መስመር ላይ በአስተናጋጅነት በመሥራት ሃሳባቸውን አሳክተዋል። ከእዚያም እ ኤ አ በ1U5G ዓም ከሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በኤም ቢ ኤ (MBA) ዲግሪ ተመረቁ።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት ዶክተር አልበርት ሸቫይጸርን ለማግኘት ምዕራብ መካከለኛው አፍሪቃ ውስጥ ሩቅ ሥፍራ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተጓዙ። ሆስፒታሉ ውስጥ ሁለት ሳምንታት ከቆዩ በኋላ ዶክተር ሸቫይጸርን የመሰለ ሌሎችን ለመርዳት የወሰኑ ሰውን መተዋወቅ ለወጣቱ ምሩቅ ታላቅ ክብር ነበር። በሆስፒታሉ ያጋጠማቸው ተሞክሮ በአገራቸው ሕዝብ ሕይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት እራሳቸውም በቁርጠኝነት እንዲሰለፉ አድርጓቸዋል።
ወደ የሚወዷት አገራቸው ከተመለሱ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ምድባቸው በኢትዮጵያ አየር
መንገድ የከፍተኛ ማኔጅመንት ኃላፊነት ነበር። ቀጥሎም በገንዘብ ሚንስቴር የዳይሬክተርነት ሹመት አገኙ። በዚሁ ሥራቸው ላይ እንዳሉም በወቅቱ በልዑል ራሥ መንገሻ ሥዩም በሚመራው የኢትዮዽያ የአየር መንገድ ቦርድ አባል በመሆን አየር መንገዱ በተለይ አፍሪቃ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ የተለያዩ የብሪያ መስመሮችን እንዲዘረጋ የአባልነታቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዎል። የመጀመሪያዎቹን ቦይንግ ጄት አኤሮፕላኖች ለመግዛት በተደረገው ወሳኝ ድርድር ውስጥ ቁልፍ ሚና ነበራቸው።
በ1UG0 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሆነው ተሾሙ
ይህንን የተከበረ ቦታ ለመያዝ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ነበሩ። የባንኩን ተቋም ለማዘመን ጠቃሚ ተነሳሽነቶችን በመምራት እና በማስተባበር ለአሥራ አራት ዓመታት በዚያ ሥራ ላይ ቆይተዋል።
ከብዙ ትሩፋቶቻቸው አንዱ የብሔራዊ ባንክ ሠራተኞችን ለተጨማሪ ሥልጠና ወደ ውጭ አገር ለመላክ ያደረጉት ብርቱ ጥረት እና ስኬታማ ተነሳሽነት ነበር።
ይህ በአርቆ አሳቢነት ላይ የተመሠረተ ጥረት ቁጥራቸው እየጨመረ ለመጣው ልዩ የባንክ ሥራ መደቦች በሙያው የሠለጠኑ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያትን መመደብ አስችሏል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክለው ከሌሎች ሀገሮች የገንዘብ ሚኒስትሮች ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ የባንክ ማኅበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል።
በተለይም ልጅ የወንድወሰን መንገሻ የአፍሪቃን ኤኮኖሚ ለማሳደግ እና ድህነትን ለመቀነስ የታለመውን የአፍሪቃ ልማት ባንክን (AfDB) በሚመሠረትበት ጊዜ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል።
ኢትዮጵያ መሥራች ባለአክሲዮን እንደመሆኗ መጠን ባንኩን በማቋቋም ረገድ ግንባር ቀደም እና ስኬታማ መሪነት አሳይታለች። ብዙዎች ይህንን ስኬት የብሔራዊ ባንክ ገዥ የአቶ ምናሴ ለማ እና ምክትል ገዥ የልጅ የወንድወሰን መንገሻ አርቆ አስተዋይነት እና አመራር ውጤት ነው ብለው ይመለከቱታል።
በዓለም አቀፍ ፋይናንስ ላይ በነበራቸው ዕውቀት እና ባለራዕይ አመራር በ1U80ዎቹ ዓመታት አፍሪቃ ልማት ባንክ ካፒታሉን ለማሳደግ ክልላዊ ያልሆኑ ሀገራትም

ትጉህ እና ድንቅ አትዮጵያዊው ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በባልደረቦቻቸው እና በመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ሰፊ ክብር ያሰጡዋቸው አዕምሯዊ ችሎታቸው፣ የሀገራቸውን እድገት ለማፋጠን ያሳዩት ቁርጠኝነት እና ከሌሎች ጋር ተስማምቶ የመሥራት ችሎታቸው። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት የልጅ የወንድወሰን መንገሻን የአመራር ችሎታቸውን እና ለፍትሃዊነት ያላቸውን ጥልቀት በመመዘን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት አምስት ባለአደራዎች ውስጥ አንዱ አድርገው ሾመዋቸዋል። በዚህም ኃላፊነት ከአስር ዓመታት በላይ አገልግለዋል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ እ ኤ አ 1U74 ዓም በሚያዝያ ወር ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የአይ ኤም ኤፍ (IMF) ስብሰባ በመሳተፍ ላይ እንዳሉ በኢትዮጵያ የነበረው ሁኔታ አደገኛ እየሆነ መጣ። ሁኔታው እርሳቸውንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከሚወዷት ሀገራቸው የለያቸው እና ማለቂያ የሌለው የመሰለው አሳዛኝ የግዳጅ ግዞት ዘመን መጀመሪያ ነበር።
ባለቤታቸው እና ሦስቱም ልጆቻቸው ከእርሳቸው ጋር ለመሆን ወደ አሜሪካ መጓዝ ቻሉ። ልጅ የወንድወሰን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ጥሩ አማራጭ እንዳልሆነ ከተረዱ በኋላ ቅድሚያ የሰጡት ቤተሰቡን የሚያስተዳድሩበት በተለይም ልጆቻቸውን ለማስተማር የሚያስችል ሥራ መፈለጉን ነበር።
በዓለም አቀፍ ፋይናንስ መስክ በነበራቸው ሰፊ ዕውቀት እና ችሎታ ለንደን በሚገኘው First Boston Corporation (ፈርስት ቦስተን ኮርፖሬሽን) ሥራ ለማግኘት በቁ። ቀጥሎም በታማኝነታቸው እና በልዩ ችሎታቸው ወደ ማኔጂንግ ዳይሬክተርነት (Managing Director) ደረጃ ዕድገት አገኙ።
በኩባንያው ውስጥ ለብዙ ዓመታት በጥሩ መሪነት ከአገለገሉ በኃላ Associated African Financial Services (አሶሽየትድ አፍሪካን ፋይናንሽያል ሰርቪስስ) የሚባል የአማካሪ ድርጅት አቌቁመው በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉልህ በሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ ከአሥር አመታት በላይ ሠርተዋል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በቀሪው ሕይወታቸውም እንደሁልጊዜው ሌሎችን ለመርዳት፣ ሀገራቸው እና ሕዝቡ ላደረገላቸው ውለታ ለመመለስ ትኩረት በማድረጋቸው ብዙ የበጎ አድራጎት ቡድኖችን፣ ቤተክርስቲያናትን እና ግለ ሰቦችን ከመርዳት ተቆጥበው አያውቁም። ቤቱ ይቁጠረው እንደሚባለው ሰው የማያውቀው አምላክ ግን የሚያየው ብዙ ችግረኛችን ደግፈዋል።
በተለይ ኅብረተሰቡን ለመርዳት ካቋቋሙዎቸው ቅርሶች አንዱ ለውድ አባታቸው መታሰቢያ እንዲሆን ባሕር ዳር ውስጥ የከፈቱት “አባ መንገሻ ገነሜ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል” ነው።
ወጣቶች ትምህርታቸውን በትጋት እንዲቀጥሉ እና በሙሉ አቅማቸው ዓላማቸውን ለማሳካት እንዲጥሩ ለማበረታታት እና ለመደገፍ በምንም ዓይነት ወደኃላ አዩሉም ነበር።
በተለይም ለከፍተኛ ትምህርት እድሎችን ለማስፋት ከነበራቸው ጽኑ ፍላጎት በራሳቸው እና በባለቤታቸው ወይዘሮ ሕይወት ስም በሃርቫርድ ቢዝነስ ትምህርት ቤት የትምህርት ብቃት ላላቸው የአፍሪቃውያን ተማሪዎች ስኮላርሺፕ አቋቀቁመው ብዙ ተማሪዋች ሊጠቅሙ ችለዎል።
በፍቅር ወንድዬ ተብለው የሚጠሩትን ልጅ የወንድወሰን መንገሻን የማወቅ ዕድል ያገኙ ሁሉ ተንከባካቢነታቸውን፣ ትሁትነታቸውን እና ለጋሥነታቸውን ይመሰክራሉ። ዘመዶችን፣ ጓደኞችን እንዲሁም ሌሎች ሰዎች መርዳት እና ምክር በመለገስ ረገድ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። እንዲሁም ታዳጊ እና ወጣት የሆኑት ዘመዶቻቸው እንደአባት እና አማካሪ ያዩዋቸው ነበር።
የቤተሰብ አባላት ታማኝነታቸውን እና ጥበባዊ ምክራቸውን ከፍ አድርገው ይመለከቷቸው ነበር። በተለይም የቅርብ ዘመዶቻቸው ከሆኑት ከራሥ አንዳርጋቸው መሳይ እና ከልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለ ሥላሴ ፍቅር እና አክብሮት ምንግዜም አልተላያቸውም።
ልጅ የወንድወሰን እ ኤ አ ጥቅምት 12 ቀን 2025 በሎንዶን በሚገኘው ቤታቸው በቤተሰብ ተከበው በሰላም በማረፍ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
በነሐሴ 23 ቀን 1964 ዓም እኤአ በትዳር ካገቧቸው ከውድ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ሕይወት ግሬታ መንገሻ ጋር በፍቅር፣ በመከባበር እና በተድላ የዕድሜ ባለፀጋ ሆነው ያሬድ፣ ያድዋ እና የአደይን አፍርተዋል።
የሰባት የልጅ ልጆች አያት ለመሆን በቅተዋል - ካሌብ፣ ሶፊያ፣ ሉላዴይ (ሊሊ)፣ ጌሊላ፣ አሸር፣ ፀጋ እና ኢያሱ ። ቤተሰቡ መሪ አባት የነበሩትን በሞት በማጣታቸው በታላቅ ሀዘን ላይ ቢወድቁም አምላክ ረጅም ዕድሜ ስለሰጣቸው እና ቤተሰቡን ፍቅር በተሞላበት አርአያነት በመምራታቸው በምስጋና ተሞልተዋል።

“ፍቅር ታጋሽ ነው፣ ፍቅር ደግ ነው፣ ፍቅር አይመቀኝም፣ ፍቅር አይታበይም፣ ፍቅር አይኰራም፣
ፍቅር ስነስርዓተቢስ አይደለም፣ ፍቅር የራሱን ጥቅም ብቻ ፈላጊ አይደለም፣ ፍቅር አይበሳጭም፣ ፍቅር ቢበደልም እንኳ በደልን እንደበደል አይቆጥርም፣ ፍቅር እውነት በሆነ ነገር ይደሰታል እንጂ ክፋት በሆነ ነገር አይደሰትም፣ ፍቅር ሁሉን ችሎ ይታገሳል፣ ፍቅር በሁሉም ላይ ተስፋ የደርጋል፣ ፍቅር በሁሉም ነገር ይጸናል”

በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ የሚገኘው ሉቭር ሙዚየም ተዘረፈ
ትናንት ሦስት ጭምብል ያደረጉ ወንጀለኞች የጭነት ማጓጓዣ ሊፍት በመጠቀም ወደ ህንፃው ገብተው፣ መስኮቶችን ሰብረው የአፖሎ ጋለሪ ውስጥ ገብተው ነበር።
ከናፖሊዮን ዘመን የተውጣጡ ዘጠኝ የጌጣጌጥ እቃዎችን እንደሰረቁ ይታመናል፤ ከእነዚህም መካከል ብሩክ ፣ የአንገት ሐብል፣ ቲያራ እና ሌሎች እቃዎች ይገኙበታል። የጠፉት ኤግዚቢሽኖች ትክክለኛ ዝርዝር በሚስጥር ተይዟል።
ዘራፊዎቹ በመኪና አምልጠዋል እየተፈለጉም ነው። ከዝርፊያው በኋላ የንጉሠ ነገሥት ናፖሊዮን ሣልሳዊ ሚስት የተሰበረ ዘውድ ከሉቭር ሙዚየሙ አቅራቢያ ተገኝቷል።
የዝርፊያው ተግባር ሰባት ደቂቃ የወሰደ እንደነበረ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ሆኖም ዘራፊዎቹ ከናፖሊዮን የጌጣጌጥ ስብስብ ውስጥ ትልቁን አልማዝ—140 ካራት የሚመዝነው ሪጀንት አልወሰዱም።
ቪዲዮው እንደሚያሳየው ዘራፊዎቹ ከሴይን ወንዝ በኩል ወደ ሉቭር መስኮት እንዲወጡ ያስቻላቸው ሊፍት እንደነበረ ይታመናል።

"አገሬ ለኔ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን እኔ ለአገሬ ምን አደረኩላት ብለን እንጠይቅ?!" 🇺🇸
#ethiopia | በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
የቀድሞው ዝነኛና ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በቴክሳስ ግዛት፣ ዳላስ ከተማ፣ በክፍት መኪና፤ በጉብኝት ሳሉ ነበር እኤአ በኅዳር 22፣ 1963 ቀትር ላይ በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት። ፕሬዚደንት ኬኔዲ ስልጣን ላይ ከወጡ ሦስተኛ ዓመታቸን ሊይዙ ትንሽ ወራት ይቀራቸው ነበር።
ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ሰውየውን ( ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ) ማን ገደላቸው? ... ለምን ተገደሉ? ... በሚለው ዙርያ ሺህ ምርመራዎች ተደርገዋል።
እነዚህ የምርመራ ሂደቱን የያዙ ዶሴዎችም በምሥጢር ሲከማቹ ነው የኖሩት።
የ1964 የእውነት አፈላላጊው ‘ዋረን ኮሚሽን’ ፕሬዝዳንት ኬኔዲ የተገደሉት ሊ ሐርቬይ ኦስዋልድ በተባለ ግለሰብ ነው ብሎ ነበር።
ሊ ሐርቬይ ቀደም ሲል በሶቭየት ኅብረት ለአጭር ጊዜ የኖረ አሜሪካዊ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸመውም በግሉ ነው ተብሎ ነበር።
በቁጥጥር ሥር በዋለ በሁለተኛው ቀን ግን ብዙም ግልጽ ባልሆነ መንገድ በዳላስ ፖሊስ ምድር ቤት ውስጥ ተገድሏል።
ይሁንና የኬኔዲ አገዳደል፣ ገዳያቸው ነበር የተባለው ሰው በፖሊስ ምድር ቤት መገደል ምሥጢርና ተያያዥ ጉዳዮች ለዐሥርታት ለብዙ መላምቶች ክፍት ሆኖ ቆይቷል።
የሴራ ፖለቲካ ተንታኞች ደግሞ ግድያውንና ግድያውን ተከትሎ የሆነውን ነገር ሁሉ የተለያዩ ትርጉም ሲሰጡት ኖረዋል። ዛሬም ድረስ ...
አንዳንዶች ወጣቱን ፕሬዝዳንት ኬኔዲን የገደላቸው ሴአይኤ ራሱ ነው፤ ለዚያም ነው ገዳያቸው ነው የተባለውን ሰው ፈጥነው የገደሉት ብለው ያምናሉ።
ሲአይኤ ግን "የኔ እጅ የለበትም!" ይላል።
ገዳያቸው ነው የተባለው ኦስዋልድ በሜክሲኮ አገር ከኬጂቢ ሰላይ ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ወደ በኋላ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የመጀመርያው የሮማን ካቶሊክ እምነት ተከታይ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጊዜያቸው ገናና የነበሩ 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸውም ባሻገር በንግግር አዋቂነታቸው ይደነቃሉ።
ከንግግራቸው አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ እንደ ጥቅስ ይወሳሉ፤ ከነዚህም መሀል ‘አገሬ ለኔ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን እኔ ለአገሬ ምን አደረኩላት ብለን እንጠይቅ’ የሚለው የበዓለ ሲመት ንግግራቸው በይበልጥ ይታወሳል።
***
እንደምታውቁት የፕሬዝዳንት ኬኔዲን ግድያ የተመለከተ የምርመራ ዶሴ ከ60 ዓመት በኋላ ይፋ ሆኗል።
ይህ ዶሴ ለሕዝብ ይፋ እየሆነ ያለው ከ60 ዓመታት ጥብቅ ምሥጢርነት በኋላ ነው።
ብዛቱ ከ10ሺህ በላይ ይሆናል የተባለው ይህ ሰነድ ይፋ እንዲሆን የወሰኑት ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ናቸው።
ይሁንና አንዳንድ ሰነዶች አሁንም በምሥጢር የሚቆዩ ይኖራሉ። ይህም ለአንዳንድ ሰዎች ደኀንነት ሲባል ነው።
ምንም እንኳ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ግድያ ለዐሥርታት እያወዛገበ ቢቆይም በዚህ ሰነድ የሚገለጥ አንዳች ታላቅ ምሥጢር ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።
ይሁንና ዶሴው በፕሬዝዳንቱ ግድያ ዙርያ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ግን ልዩ ዕድል ነው ተብሏል።
የ1992 የአሜሪካ ሕግ ዶሴዎቹ በጥቅምት 2017 ለሕዝብ ይፋ እንዲደረጉ አስገዳጅ አድርጎ ነበር።
የአሜሪካ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት ለሕዝብ ይፋ የማይደረጉት ሰነዶች ብዛት 515 ነው ብሏል።
ከጠቅላላው ሰነድ 2ሺህ 545 ሰነዶች ደግሞ ይፋ የሚሆኑት በከፊል ናቸው።
***
ታሪክን የኋሊት
ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸዉ። በተለይ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸዉ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን መጎብኘታቸዉ ይነገራል።
ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ጥሩ የወዳጅ ነት ግንኙነት እንደነበራት ቢታወቅም ጆኔፍ ኬኔዲ በተለይ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
«ድል አባቷ ብዙ ነው" እንዲል ጆኔፍ ኬኔዲ ብዙ የታሪክ ምዕራፍ ለመሰነቅ ወደ ሙዚየሙ ገባሁ።
The joy and excitement of John Fitzgerald Kennedy's life belonged to all men.
So did the pain and sorrow of his death.
When he died on November 22, 1963, shock and agony touched human conscience throughout the world. In Dallas, Texas, there was a special sorrow.
The young President died in Dallas. The death bullets were fired 200 yards west of this site.
by Philip Johnson, This memorial, designed by was erected by the people by the people of Dallas. Thousands of citizens contributed support, money and effort.
It is not a memorial to the pain and sorrow of death, but stands as a permanent tribute to the joy and excitement of one man's life.
Pohn Fitzgerald Kennedy's life.
#ethiopia | በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
የቀድሞው ዝነኛና ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በቴክሳስ ግዛት፣ ዳላስ ከተማ፣ በክፍት መኪና፤ በጉብኝት ሳሉ ነበር እኤአ በኅዳር 22፣ 1963 ቀትር ላይ በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት። ፕሬዚደንት ኬኔዲ ስልጣን ላይ ከወጡ ሦስተኛ ዓመታቸን ሊይዙ ትንሽ ወራት ይቀራቸው ነበር።
ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ሰውየውን ( ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ) ማን ገደላቸው? ... ለምን ተገደሉ? ... በሚለው ዙርያ ሺህ ምርመራዎች ተደርገዋል።
እነዚህ የምርመራ ሂደቱን የያዙ ዶሴዎችም በምሥጢር ሲከማቹ ነው የኖሩት።
የ1964 የእውነት አፈላላጊው ‘ዋረን ኮሚሽን’ ፕሬዝዳንት ኬኔዲ የተገደሉት ሊ ሐርቬይ ኦስዋልድ በተባለ ግለሰብ ነው ብሎ ነበር።
ሊ ሐርቬይ ቀደም ሲል በሶቭየት ኅብረት ለአጭር ጊዜ የኖረ አሜሪካዊ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸመውም በግሉ ነው ተብሎ ነበር።
በቁጥጥር ሥር በዋለ በሁለተኛው ቀን ግን ብዙም ግልጽ ባልሆነ መንገድ በዳላስ ፖሊስ ምድር ቤት ውስጥ ተገድሏል።
ይሁንና የኬኔዲ አገዳደል፣ ገዳያቸው ነበር የተባለው ሰው በፖሊስ ምድር ቤት መገደል ምሥጢርና ተያያዥ ጉዳዮች ለዐሥርታት ለብዙ መላምቶች ክፍት ሆኖ ቆይቷል።
የሴራ ፖለቲካ ተንታኞች ደግሞ ግድያውንና ግድያውን ተከትሎ የሆነውን ነገር ሁሉ የተለያዩ ትርጉም ሲሰጡት ኖረዋል። ዛሬም ድረስ ...
አንዳንዶች ወጣቱን ፕሬዝዳንት ኬኔዲን የገደላቸው ሴአይኤ ራሱ ነው፤ ለዚያም ነው ገዳያቸው ነው የተባለውን ሰው ፈጥነው የገደሉት ብለው ያምናሉ።
ሲአይኤ ግን "የኔ እጅ የለበትም!" ይላል።
ገዳያቸው ነው የተባለው ኦስዋልድ በሜክሲኮ አገር ከኬጂቢ ሰላይ ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ወደ በኋላ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የመጀመርያው የሮማን ካቶሊክ እምነት ተከታይ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጊዜያቸው ገናና የነበሩ 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸውም ባሻገር በንግግር አዋቂነታቸው ይደነቃሉ።
ከንግግራቸው አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ እንደ ጥቅስ ይወሳሉ፤ ከነዚህም መሀል ‘አገሬ ለኔ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን እኔ ለአገሬ ምን አደረኩላት ብለን እንጠይቅ’ የሚለው የበዓለ ሲመት ንግግራቸው በይበልጥ ይታወሳል።
***
እንደምታውቁት የፕሬዝዳንት ኬኔዲን ግድያ የተመለከተ የምርመራ ዶሴ ከ60 ዓመት በኋላ ይፋ ሆኗል።
ይህ ዶሴ ለሕዝብ ይፋ እየሆነ ያለው ከ60 ዓመታት ጥብቅ ምሥጢርነት በኋላ ነው።
ብዛቱ ከ10ሺህ በላይ ይሆናል የተባለው ይህ ሰነድ ይፋ እንዲሆን የወሰኑት ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ናቸው።
ይሁንና አንዳንድ ሰነዶች አሁንም በምሥጢር የሚቆዩ ይኖራሉ። ይህም ለአንዳንድ ሰዎች ደኀንነት ሲባል ነው።
ምንም እንኳ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ግድያ ለዐሥርታት እያወዛገበ ቢቆይም በዚህ ሰነድ የሚገለጥ አንዳች ታላቅ ምሥጢር ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።
ይሁንና ዶሴው በፕሬዝዳንቱ ግድያ ዙርያ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ግን ልዩ ዕድል ነው ተብሏል።
የ1992 የአሜሪካ ሕግ ዶሴዎቹ በጥቅምት 2017 ለሕዝብ ይፋ እንዲደረጉ አስገዳጅ አድርጎ ነበር።
የአሜሪካ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት ለሕዝብ ይፋ የማይደረጉት ሰነዶች ብዛት 515 ነው ብሏል።
ከጠቅላላው ሰነድ 2ሺህ 545 ሰነዶች ደግሞ ይፋ የሚሆኑት በከፊል ናቸው።
***
ታሪክን የኋሊት
ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸዉ። በተለይ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸዉ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን መጎብኘታቸዉ ይነገራል።
ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ጥሩ የወዳጅ ነት ግንኙነት እንደነበራት ቢታወቅም ጆኔፍ ኬኔዲ በተለይ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
«ድል አባቷ ብዙ ነው" እንዲል ጆኔፍ ኬኔዲ ብዙ የታሪክ ምዕራፍ ለመሰነቅ ወደ ሙዚየሙ ገባሁ።
The joy and excitement of John Fitzgerald Kennedy's life belonged to all men.
So did the pain and sorrow of his death.
When he died on November 22, 1963, shock and agony touched human conscience throughout the world. In Dallas, Texas, there was a special sorrow.
The young President died in Dallas. The death bullets were fired 200 yards west of this site.
by Philip Johnson, This memorial, designed by was erected by the people by the people of Dallas. Thousands of citizens contributed support, money and effort.
It is not a memorial to the pain and sorrow of death, but stands as a permanent tribute to the joy and excitement of one man's life.
Pohn Fitzgerald Kennedy's life.
10 months ago
ኢኳኢተስ
ዓባይ እና አዲሱ የፍትሕ ዓውድ
ፕ/ር ምዋንጊ ሳምሶን ኪመኒ እና ፕ/ር ጆን ሙከም ምባኩ
ትርጉም:- ሰለሞን በጋሻው
#ethiopia | በዘመኑ የነበሩት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሀገራቸው ለምትመኘው ብሔራዊ ልማትና ብልጽግና የሙህ ሀብቷን መጠቀም እንደሚያስፈልጋት ጠንቅቀው ይገነዘቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ዶ/ር ዳንኤል ክንዴ አንዳቀረበው የመከራከሪያ ሀላብ በብሪታኒያና በኢትዮጵያ መካከል በ1902 ተፈጽሟል የተባለውን የሁለትዮሽ ስምምነት እርባና ቢስ የሚያደርጉ እና ተጨባጭ የሆኑ ኹነት ገላጭ መረጃዎች አሉ።
ተፈጸመ የተባለው የሁለትዮሽ ስምምነት በብሪታኒያ ፓርላማም ሆነ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና የንጉሠ ነገሥቱ አማካሪ ባለሟሎች ምክር ቤት ዘንድ ቀርቦ፤ በመጽደቅ ወደ ሕግነት የተለወጠበት አጋጣሚ አለመከሰቱ ስምምነቱን ወረቀት ላይ ብቻ የቀረ ባዶ ደንብ እንዲሆን አድርጎታል። ሁለቱም ሀገራት ይህንን በማድረግ ስምምነቱን ወደ ሕግነት አጽድቀው አላሳለፉትም። ኢትዮጵያ በስምምነቱ ታሳሪ አለመሆኗን ለማስረዳት የሚገልጽ ከዚህ የበለጠ ጭብጥ የለም፡፡ ክንዴ 1999,p.146) "
በመሆኑም ኢትዮጵያ ከብሪታኒያ ጋር ፈጸመች በተባለው ስምምነት መሠረት ታሳሪ አለመሆኗን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ከርክር ማድረግ ወይም ጭብጥ ማቅረብ አያስፈልጋትም።
****
"በደቡብ የአሜሪካ ግዛት ይመረት ከነበረው የጥጥ ምርት አብዝሐኛው የሚላከው ወደ ታላቋ ብሪታንያ ላንክሻየር የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ነበር (ቤከርት 2004) ። በ1861 አሜሪካ ውስጥ ተከስቶ የነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ሲነሳ በደቡብ ግዛት በሰፊው ይመረት የነበረው የጥጥ ምርት ተስተጓጎለ ። ……"
" እንግሊዞች ሰፊ የሆነው የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪያቸው የገጠመውን የግብዓት እጥረት ለመታደግ ግብፅ ውስጥ ጥጥ ላይ ብቻ ያተኮረ የመስኖ ልማት እንዲከወን ማድረግ ነበረባቸው ።"
ከአሜሪካኖች የእርስ በርስ ጦርነት ውጤት እስከ የኤርትራ መገንጠል የዓባይ ጉዳይ ኢትዮጲያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ ውስጥ የከተታት የመልክዓ ፖለቲካ ጉዳይ እጅጉን ብዙ ነው ።
#ኢኳኢተስ እነዚህን ውስብስብ የብሔራዊ ጥቅማችን የሚመለከቱ ጉዳዮች ከሌሎች በርካታ ጉዳዮች ጋር ከከዲቭ እስማዔል እስከ አብዱል ፈታህ አልሲሲ ዘመን ድረስ በሰፊው ታስቃኘናለች ።
በሁሉም የጃዓፈር መጽሐፍት መደብር ያገኙታል ።

11 months ago
የግብፅ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሐሙስ ዕለት እንዳስታወቀው፣ ከዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከካይሮ ሙዚየም የጠፋው የ3,000 ዓመት ዕድሜ ያለው የፈርዖን የወርቅ አምባር ተሰርቆ ቀልጦአል ሲል ሬውተርስ ዘግቧል።
እከዚህ ቀደም የግብፅ የጥንታዊ ቅርሶችና ቱሪዝም ሚኒስቴር የዋጋ የማይተመነው አምባር መሰወሩን አስታውቆ ነበር። አምባሩ የሦስተኛው መካከለኛ ዘመን የግብፅ ፈርዖን (የጥንቷ ግብፅ ንጉሠ ነገሥት) የነበረው እና ግብጽን በ1000 ከክርስቶስ ልደት በፊት አካባቢ ያስተዳደረው የአሜንሞፕ ነው።

ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ (ከ1922-2018)
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል። ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ቅፅ 3 መዝገበ አእምሮ ከ20 በላይ ዘርፎች ይኖሩታል። እዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ የአገር ባለውለታዎችን መሰነዳችን ይቀጥላል። ዲፕሎማሲና የመንግስት ኃላፊነት በሚለው መደብ ታሪካቸውን የምንሰንድላቸው ዶክተር ምናሴ ኃይሌ ሲሆኑ ታሪካቸውንም ዕዝራ እጅጉና ሲሳይ ገብረማሪያም እንደሚከተለው አጠናክረውታል
ህልፈታቸው በዩናይትድስቴትስ ኒውጀርሲ እ.ኤ.አ መስከረም 2025 (ጳጉሜ 5, 2017 ዓ.ም) ነበር።እንደ አንድ የመንግስት ኃላፊ ፣ዲፕሎማት ፣የህግ ምሁር ለማይታረቁና ለተለያዩ የዓለም አስተሳሰቦች የሚጋሩትን ድልድይ በመገንባት ይህን ዓለም ተሠናብዋል። ከልጅነት እስከዕውቀት ዶ/ር ምናሴ ህይወትን እንዴት ኖሯት?
ልደት፣ ዕድገትና ትምህርት
ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ ከእናታቸው ከወይዘሮ እሌኒ ኃይሌ እና ከአባታቸው ከአቶ ኃይሌ ድብነህ በ1922 ዓ.ም በሐረር ተወለዱ። የልጅነት ዘመናቸውን በሐረር ያሳለፉት የያኔው አዳጊው ምናሴ ቤተሰባቸው ኑሮውን በአዲስ አበባ ሲከትም የእርሳቸው የትምህርት ህይወት በኮተቤ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቀጠለ። በኮተቤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ሳሉ በሀገረ- አሜሪካ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸውን እድል አገኙ።
በአሜሪካ በቀጠለው ትምህርታቸው እ.ኤ.አ በ1950 ከዊስኮንሲን ማዲሰን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አገኙ። እ.ኤ.አ በ1954 ደግሞ በኒውዮርክ ወደሚገኘው ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ በማቅናት የህግ ትምህርት ለማጥናት ጥርጊያውን ያመቻቸላቸውን ለህግ ትምህርት ቅድመ ዝግጅት ብቁ የሚያደርገውን የ (Juris Doctor) ወረቀት አገኙ። ባልተገታው የትምህርት ጉዟቸው እ.ኤ.አ በ1957 ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሲጎናፀፉ ከ4 አመት በኋላ በ1961 ሦስተኛው ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) ያዙ።
ሀገራዊ ኃላፊነት እና ሙያዊ አበርክቶ
በዛው ትምህርታቸውን ባጠናቀቁበት ዓመት ምቾት ይበልጥብኛል ሳይሉ እ.ኤ.አ በ1961 ወደ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመለሱ።
በተመለሱበት ቅፅበትም የኢትዮጵያን ፒስ ኮርፐስ ከአሜሪካ ጋር በጋራ እንዲሠሩ ሁለቱን ሀገራት ያፈራረሙት ዶክተር ምናሴ ነበሩ። በጊዜውም እርሳቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የህግ አማካሪ ሆነው በተቀጠሩበት ጊዜ ነው። ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ በተመደቡበት የውጭ ጉዳይ ስራ ሳይታጠሩ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ደንብ የሚል ረቂቅ በማዘጋጀት በረቂቅ ደንቡ አማካይነት የኢትዮጵያ ፐርሶኔል አስተዳደራዊ ኤጀንሲ ተብሎ የሚጠራውን ተቋም አቋቋሙ ።
ከዚህ መንግስታዊ ኃላፊነት በኋላ እ.ኤ.አ በ1962 ዶ/ር ምናሴ የንጉሠ ነገስቱ የግል ካቢኔ አባል ተደርገው ተሾሙ። በዚሁ ኃላፊነታቸው የውጭ ፣የፍትህ ፣የኢኮኖሚ ፣የውጭ ደህንነት እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ቅኝት እንዲያደርጉ እና ስትራቴጂካዊ በሆኑ ሀሣቦች ዙሪያ እንዲያማክሩ በንጉሡ የግል ካቢኔ አባል ሆነው ሥራቸውን ቀጠሉ።
ከተሠጣቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችን ማማከር እና ቅኝት የማድረግ ኃላፊነት ባሻገር እ.ኤ.አ በ1964 ሌላ ድርብ ኃላፊነት ተጣለባቸው። የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። በዚህ ኃላፊነታቸው በሃገሪቱ በወቅቱ በነበሩት ሚዲያ ዎች ማለትም በኢትዮጵያ ሬድዬ ፣ቴሌቪዥን እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላይ ስርነቀል ለውጥ እንዲመጣ በማድረግ በእርሳቸው መሪነት ተቋማቱ የተሻለ ሙያዊ ነፃነት እንዲጎናፀፉ አድርገዋል።በተመሣሣይ ጊዜም በሀገሪቱ በተነባቢነት ሁለተኛ ደረጃነት ይዞ የነበረው የዛሬይቱን ኢትዮጵያ ጋዜጣን መስርተዋል።
እ.ኤ.አ ከ1969 እስከ 1971 የነበረው ወቅት የአሜሪካ ትኩረት በቬትናም ጦርነት እና የቀዝቃዛው ጦርነት ትኩረት ያየለበት ጊዜ ነበር።ለዶ/ር ምናሴ ይኸው ወቅት ቀጣይ የሙያ ማረፊያቸው ሆኖ በአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉበት ጊዜ ነበር።
ከአሜሪካ አምባሳደርነት መልስ እ.ኤ.አ በ1971 ዶ/ር ምናሴ ዳግም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ሆነው ተሾሙ።በዚህ የውጭ ጉዳይ ቆይታቸው ቦታው የሚጠይቀውን ታላላቅ የዲፕሎማሲ ስራዎችን ያከናወኑ ሲሆን በዚሁ ጊዜ የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ልዑክ በተባበሩት መንግስታት ፣በአፍሪካ አንድነት፣ በወቅቱ የዓለም ገለልተኛ አባል ሃገራት ንቅናቄ እየተባለ ከሚጠራው ተቋምና እና በሌሎች የሁለትዮሽ ትብብር መድረኮች ኢትዮጵያ እንድትከብር አድርገዋል።
እ.ኤ.አ ከ1971 -1972 ባለው ጊዜም ሀገርን በሌላ ሙያዊ አቅም ወደሚያገለግሉበት ወደአፍሪካ አንድነት ድርጅት በማቅናት በድርጅቱ ውስጥ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል አገልግሎታቸውን ቀጠሉ። እርሳቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል በነበሩት ዘመንም አህጉሪቱ በታላቅ ተስፋ እና ስጋት ውስጥ ነበረች። ዶ/ር ምናሴም በድርጅቱ በነበራቸው ቆይታ ስጋትን ወደተስፋ በመቀየር ካሳኳቸው ተግባራት መካከል እ.ኤ.አ በ1972 በአዲስ አበባ የተካሄደው ስምምነት ሲሆን ስምምነቱም የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቋጭ ያደረገ ነበር። ከዚሁ ጎን ለጎን ለረዥም ጊዜ አጨቃጫቂ የነበረው የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር እንዲካለል አድርገዋል። በተመሳሳይ ወቅት ከንጉሰ ነገስቱ ጋር ወደቻይና ተጉዘው ጉብኝት አድርገው ከወቅቱ የቻይና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዞ ኔሊያ እና ከሊቀመንበሩ ማኦ ዜዱንግ ጋር ተገናኝተው ሁለቱ ሃገራት በጋራ ስለሚሠሩባቸው ጉዳዮች መክረዋል።
የጋራ እሳቤ መስራቹ ምናሴ ሀይሌ!
ሀሙስ ግንቦት 16 1965 ዓ.ም ፡፡ የአፍሪካ ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና ርዕሳነ መንግስታት የወቅቱን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ 10ኛ አመት በአል ለማክበር በአዲስ አበባ ታድመዋል፡፡
ለአዲስ አበባ ይህ ክብረ በአል የድርጅቱ ጉዞ 10 ዓመት ላይ መድረሱ ብቻ አይደለም ትርጉሙ።ዕለቱን ልዩ ያደረገው በዚህ ቀን የተፃፈው አይረሴ ታሪክ ነው።
በአፍሪካ አንድነት ምስረታ 10ኛ ዓመት ላይ
ቅዳሜ ግንቦት 18 1965 ዓ.ም የድርጅቱን ምስረታ በማስመልከት የሚደረጉ ንግግሮች ቀጥለዋል፡፡በወቅቱ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ከሚሉ መልዕክቶች ባሻገር የበዓሉን ዐውድ የሚለውጡ ንግግሮች መደመጥ ጀመሩ፡፡ ቀዳሚው ደግሞ ከሶማሌያው ተወካይ የተደመጠው ንግግር ነበር፡፡በአፍሪካ አንድነት 10ኛ አመት በዓል ላይ የወቅቱ የሀገራቸውን ፕሬዚዳንት የሆነትን ዚያድ ባሬን ወክለው የተገኙት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ኮለኔል ኢስማኤል አቡበከር ሲሆኑ ንግግራቸው ኢትዮጵያን በመክሰስ ጀመረ ፡፡በሶማሊያው ፕሬዚዳንት ዚያድ ባሬ ተፅፎ በምክትሉ በቀረበው ንግግር ኢትዮጵያ ሶማሊያን ልትወር ነው የሚል ሀሜት ያዘለ ዲስኩርን አሰሙ፡፡ የሶማሌውን ምክትል ፕሬዚዳንት ተከትሎ መድረኩን ቀጥለው የተረከቡት ደግሞ የወቅቱ የሊቢያ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት አቡ ዘይድ ነበሩ፡፡ አቡዘይድ “ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጥቂት ነጭ ገዢዎች ስርዓት እንዲሰፍን ትፈልጋለች፡፡” በማለት ለሰደድ እሳቱ ክብሪቱን በመጫር
ንግግራቸውን ጀመሩ፡፡ በማስከተልም “ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጥቂት ነጭ ገዢዎች ስርዓት እንዲሰፍን የምታደርገው እስራኤልን በመርዳት ነው፡፡” ሲሉ ክሳቸውን አጠናከሩ፡፡በዚህ ያልተገታው ተንኳሽ ንግግራቸው “ኢትዮጵያ ለአሜሪካ የጦር ሰፈር ፈቅዳለች፡፡ለሰሜን ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶም ትሰልላለች፡፡ይኸው የስለላ ሥራዋ በደቡብ አፍሪካ እና በሮዴዥያ ያለውን ሥርአት የሚመግብ ነው፡፡ይህ የኢትዮጵያ ተግባር ከአፍሪካ አንድነት ዓላማ ጋር የማይሄድ በመሆኑ ፤ በዚህ በዓል ላይ የታደማችሁ የአንድነት ድርጅቱ አባላት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቀመጫ ከአዲስ አበባ እንዲነሳ” የሚል ክስ አቀረቡ፡፡ ይኸው ንግግር በአዳራሹ የነበረውን አውድ ቀየረው፡፡ ክብረ-በዓሉ ወደሃሣብ ጦርሜዳነት ተቀየረ። በወቅቱ ንጉሰ ነገስቱን ወክለው ለሶማሌ ፕሬዚዳንት እና ለሊቢያው ፕሬዚዳንትተወካዮች የወቅቱ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አክሊሉ ሀብተወልድ በፈረንሳይኛ መልስ ሰጡ።ነገሩ ግን በዚህ አልተቋጨም መሠል ጥያቄን በታሪክ ሲነሣም ሁሌም መልስ ሊሆን የሚችል ንግግር በሌላኛው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ተሰማ፡፡
ስለሁኔታው በማግስቱ ጉዳዩን ለዓለም አንባብያን ያደረሠው “The New York Times” በዘጋቢ ቶማስ ጆንሰን ፅሁፍ እንዲህ ሲል ገለፀው። “AFRICAN NATIONS CLASH AT PARLEY” ወይም “በሰርግ መሀል የቀለጠው ጦርነት” የሚል ስሜት ያለው ፅሁፍ ፃፈ፡፡በዚሁ ግንቦት 19 1965 ዓ.ም ለንባብ ባዋለው ፅሁፍ በአፍሪካ አንድነት 10ኛ ዓመት ክብረ-በአል ላይ የኢትዮጵያ እና ሊቢያ ዱላ ቀረሽ ፀብ ማስተናገዳቸውን፡፡
የፀቡ ፊትአውራሪ የሊቢያው ተወካይ አቦዙድ ዱዋርዳ በአረበኛ ባደረገው ንግግር የኢትዮጵያን መሪዎች “ፅዮናውያን እና ቅኝ ገዢዎች” ብሎ መዝለፉን። “ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ከአሜሪካ እና ከፅዮናውያን ጋር ጥብቅ ቁርኝት” ያላቸው መሆኑን ይህን ተከትሎም “የአፍሪካ አንድነት ዋና መዲናነት ወደሌላ ሥፍራ ይዘዋወር” ብሎ መጠየቁ መሆኑን አትቷል፡፡
አፀፋዊ ምላሹ በጣም ትዕግስተኛ እና ሆደሰፊ እንደመሆናቸወ ከሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን የማይገመት ነበር ያለው "ዘ ኒውዮርከ ታይምስ" በወቅቱ መብረቃዊ የሆነ አፀፋዊ ምላሽ የሰጡትን የኢትዮጵያው የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ምናሴ ሀኃይሌ ምላሽ 'No Dictation From Libya' ብለው ጀመሩ ይላል፡፡
“ቀድሞ ዲስኩር ያሰማው ሰው ንግግሩ የፈላስፋ መስሏችሁ ከቁብ እንዳትቆጥሩ፡፡…የአንድ የዞረበት እና ግራ የገባው ሰው ንግግር ነው፡፡” ሲሉ ቀጠሉ “በዚህ አዳራሽ ያላችሁ የአፍረካ ርዕሳነ ብሔራት እና ርዕሳነ መንግስታት፤በተነሣው ርዕስ ላይ ማናችሁም በሊቢያ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ትቀበላላችሁ ብዬ አላምንም፡፡ሊቢያ የቱን ያህል አማላይና የተትረፈረፈ ሀብት ቢኖራትም አፍሪካ ለሽያጭ የቀረበች ቁስ አይደለችም። የሊቢያ ሀብት ለአፍሪካውያን ምናቸውም ነው፡፡ ” ሲሉ ጠንካራ ቅስም ሰባሪ ምላሽ ሰጡ፡፡አዳራሹ በጭብጨባና ጩኸት ተሞላ።
አክለውም የኢትዮጵያን አቋም በግልፅ እንዲህ በድፍረት አስቀመጡ “ሊቢያ ከነዳጅ የምታገኘው 13 ቢሊየን ዶላር ዓለምን ለመቀየር በቂ ይመስላታል።” በማለት የኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲናነት መለወጥ እንደማይችል የወቅቱ ደፋር እና የአድዋ ልጅ መሆናቸውን ያስመሰከሩበትን ንግግር አደረጉ። ይህንኑ ታሪክም ዘ ኒውዮርከ ታይምስ ለታሪክ እንዲቀመጥ አድርጎታል።
ይህ የዶክተር ምናሴ መርህ አዘል ንግግር በመድረኩ ብቻ ተቀብሮ አልቀረም።የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ እንደሚባለው ኢትዮጵያ ዛሬም ድረስ በአፍሪካና በዓለም ጭቁን ህዝቦች ፊት በአርአያነት ለመታየትና ለአፍሪካውያንም የቁርጥ ቀን ቤታቸው ልትሆን የቻለችው ትናንት በተከፈለው ዋጋ ነው። የትናንቱ ዋጋ ለዛሬ መሰረት ሆኖ ነገ እንዲገነባባት አድርጓል፡፡ የአፍሪካ ህብረት መዲና መሆንም እንዲሁ በዋዛ ያልተገኘ እና በየጊዜው እጅግ የከበረ ዋጋ የሚከፈልበት መሆኑ በታሪክ አጋጣሚ የሚከሰቱ ክስተቶች ማሳያ ሆነው አልፈዋል፡፡ እዚህ ላይ ትናንት የህብረቱ መቀመጫ በኢትዮጵያ እንዲሆን ለማድረግ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ እና ጓዶቻቸው ገጥሟቸው የነበረው ፈተና ራሱን በታሪክ የደገመበትን አጋጣሚ እናንሳ፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቶጎ ሎሜ በ1991 ዓ.ም ለህብረቱ ስብሰባ ታድመዋል። ይኸው በትውልድ መፈራረቅ ያልተገታው ጥያቄ በቶጎ ሎሜ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ከመቃብር ተነስቶ ብቅ አለ። ለውይይት ከቀረቡ አጀንዳዎች በ24 ኛ ደረጃ ላይ የአፍሪካ ህብረት መዲናነትን ከአዲስ አበባ እንዲነሳ በወቅቱ አንድ ጉዳይ ሆኖ መጣ። ኢትዮጵያን ወክለው በመድረኩ የተገኙትት አቶ መለስም ለአጀንዳው መልሳቸው የእነዶክተር ምናሴ ኃይሌ አርአያነትን የተከተለ ነበር፡፡ “….በአፍሪካ ጉዳይ መንግስቱ ኃይለማርያም ልክ እንደቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሁሉ የፀና አቋም ነበረው፡፡ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያላት ቁርጠኝነት መንግስታት በተለዋወጡ ቁጥር የሚቀየር አይደለም፡፡” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው መድረኩ ላይ ተናገሩ።
ይህን የመለስ አባባል ከባለታሪኩ ዶ/ር ምናሴ ሀይሌ ስም ትርጉም ጋር ስናሰናኘው ስምና ግብራቸው የገጠመላቸው ሰው ያስብላቸዋል፡፡ በቅዱስ መፅሀፍ ምናሴ፦ማስረሻ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ለዘመናት እኛ ኢትዮጵያውያን ስርአት መጥቶ ስርአት ሲተከል በውስጥ ጉዳያቸው መለያየታችን ያለና የኖረ ቢሆንም በአፍሪካ ጉዳይ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌና ባልደረቦቻቸው በዘመናቸው ለሀገራቸው የከፈሉት ዋጋ በዓለም መድረክ የውስጥ ልዩነታችንን ያስረሳ ተብለው ቢገለፁ የሚያንስባቸው አይሆንም፡፡ ህያው ሥራቸው በርዕዮትም በግብርም በማይመስሏቸው የኢትዮጵያ መሪዎች መመስከሩም ይህንኑ ያስረዳል፡፡
ይህ ሁሉ ሀገራዊ አበርክቶ ግን በምስጋና አልተቋጨም። ጊዜ ሲለወጥ ነገሮችም አብረው ተቀየሩ። አንዱ ሾተል የሆነው የታሪክ አካልም በ1966 አብዮት ብቅ አለ። በወቅቱ በሀገራችን የተካሄደውን የ1966 ቱ አብዮት ተከትሎ ዶ/ር ምናሴ ከስልጣን ለቀቁ።
ከስልጣን በኋላ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ ስለነበሩበት ሁኔታ ቤተሰቡን በቅርበት የሚያውቁት ዶ/ር ጌታቸው ተድላ እንዲህ ያስታውሱታል።"በወቅቱ ዶ/ር ምናሴና ቤተሰባቸው ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ትምባሆ ሞኖፖል በታች ቪላ ተከራይተው ይኖሩ ነበር።እኔ ስለቤተሰቡ የማስታውሰው ልጅ እያለን ወ/ሮ አይሬስ ሀይሌ እሁድ እሁድ በራቸው ላይ ብስኩት ይሰጡን ነበር። ወይዘሮ አይሬስ መልከ መልካም ጥቁር አሜሪካዊት እናት ነበሩ።ሁለት መንታ ወንድ ፣አንድ ሴት እና ሌላ አንድ ወንድ ልጅ ነበራቸው።መንቶቹ ዴቪድ እና ዳንኤል ሲባሉ።ሴቷ ሱዛን የመጨረሻው ወንድ ልጅ ስም ማይክ ነው።ሶስቱም ወንዶች ፕሮፌሽናል ዶክተሮች ናቸው ።ሴት ልጃቸው ሱዛን የአባቷን ፈለግ በመከተል የጥብቅና ሙያ ላይ ታገለግላለች። ዶ/ር ምናሴን ደርግ አንድ አመት ከሁለት ወር አስሯቸዋል።ልክ መስከረም 1ቀን ተፈቱ።ኮሎኔል ዳንኤል አስፋው ከ4ኛ ክፍለጦር ወደቤተ-መንግስት ወሰዳቸው።ከዚያም ተፈቱ። እንደተፈቱም ኒውዮርክ መሄድ እፈልጋለሁ ሲሉ ልቀቋቸው ይሂዱ የተከበሩ ሰው ናቸው አለ።ወደአሜሪካ ሄዱ ።" በማለት ዶክተር ጌታቸው መስክረዋል።
ከእስር እንደተፈቱ ህይወታቸውን በስደት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መምራት ቀጠሉ። በስደት እያሉ ህይወታቸውን በአላማ መምራታቸውን አላቆሙም።በተግባር የቀሰሙትን እውቀት በትምህርት ማካፈል ጀመሩ። በቀዳሚነት የማስተማር ስራ የጀመሩት ደግሞ በቪላኖቫ ዩንቨርስቲ ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ ወደኒውዮርክ በማቅናት ካርዶዝ ዩኒቨርሲቲ ለ26 ዓመታት በማስተማር እና በተለያዩ የህግ፣በዲፕሎማሲ እና የአፍሪካ ሉአላዊነት ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን ሲያሳትሙ ቆይተዋል።
ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ እንዳሰቡት የኖሩ፣በታላቅ ክብር ፣በማይናወፅ ትጋት እና በኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር እንደተነደፉ በ95 ዓመታቸው የህይወታቸው ጉዞ ተፈፅሟል።ዶ/ር ምናሴ ከወ/ሮ አይሪስ ሀይሌ ጋር 71 አመት የትዳር ህይወት ነበራቸው።ከትዳር አጋራቸውም አራት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን ጠቃና የህግ ምሩቅ የሆነችው ሱዛን ሀይሌን ፣ዶ/ር ዳዊት ፣ዶ/ርዳንኤል ፣ዶ/ር ሚካኤል ሀይሌ እና 8 የልጅ ልጅ እና የአንድ የልጅ ልጅ ልጅ ቅድም አያት ነበሩ።
የአሁን ዲፕሎማቶች ከዶ/ር ምናሴ ሀይሌ ምን ይማሩ?
ክቡር አምባሳደር ነብዩ ተድላ
"አንድ ዲፕሎማት በየትኛውም ጊዜና ወቅት የሃገሩን ጥቅም ከማስከበር አኳያ ስትራቴጂክ የሆነ ትዕግስት ባለቤት ሊሆን ይገባል ተብሎ ይታሰባል። በዲፕሎማሲ አንዳንድ ጊዜ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች በአጭር ጊዜ የማይገለፅ ውጤት ላይኖራቸው ይችላል።ስለዚህ በዲፕሎማሲ ረዥሙን ጨዋታ መጫወት የሚችል ስትራቴጂክ ትዕግስት እንዲኖረው ከአንድ ዲፕሎማት ይጠበቃል።በዚህ ሂደት መቼ የወደፊት ርምጃ ማድረግ ያስፈልገኛል።
መቼስ ወደኋላ ልመለስ ያስፈልጋል።እርምጃ ማድረግ አለብኝ የለብኝም የሚለውን ማወቅ አስፈላጊ ነው ።
ሁለተኛ የታሪክና የባህል ጥልቅ ግንዛቤ ሊኖረውም ይገባል። ይህ ሲሆን አንድ ዲፕሎማት ውጤታማ ዲፕሎማሲ ይሰራል ተብሎ ይታመናል።
ሶስተኛው ከቋንቋ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ያሉ ክህሎቶችን መረዳት ነው።ዶ/ር ምናሴም ባየነው የድርድር መድረክ ላይ በአጭር አገላለፅ በተመጠነ ቋንቋ የሀገራቸውን ጥቅም ያስጠበቁበትን ሁኔታ ማየት ይችላሉ።
በመሠል የድርድር እና ምክክር መድረኮች የሀገርን ጥቅም ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ።ችግሮች ሲከሰቱ መደናገጥና ስሜታው መሆን ሳይሆን በተረጋጋ ሁኔታ ለተነሣ ጉዳይ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።አስፈላጊ ሲሆን ተግሳጽ መስጠት ጭምር እንደሚያስፈልግ መማር ይቻላል።ይህን ከቀደሙ በሳል ዲፕሎማቶች መማር የምንችለው ነው።"ብለዋል
አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት "ስለ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ ብዙ የምናነሳውቸው ነገሮች አሉ።በእርሳቸው ዘመን በነበረው ዲፕሎማሲ እና የውጭ ጉዳይ ሥራ አመራርነት ሁሉንም አንስቶ መጨረስ አይቻልም።የ10ኛውን የአፍሪካ አንድነት ክስተት መነሻ አድርገን ትውልድ ሊማር የሚችለው ከምንም ነገር በፊት የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ ሀገርን ሊጎዳ የሚችል ነገር ሲገጥም ለሀገር ቆፍጠን ብሎ መቆምን አስተምረዋል።
በአሁኑ ጊዜ የሚነገር ነገር አለ። በሀገር ጉዳይ የሀገር ጥቅምን ቆፍጠን ብሎ መናገር እና ማስከበርን ብዙ እንማራለን ።ሌላው የሚፈጥረው ስሜት አለ መለስ ብሎ እንዲህ አይነት ጉዳይ ሲታይና ሲነበብ የሚፈጥረው ስሜትና የሀገር ፍቅር የበለጠ ይቀሰቅሳል።ትውልድም ከዶ/ር ምናሴ ይህን ይማራል ብዬ አምናለሁ።" ብለዋል አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት።

ዶናልድ ትራምፕ የዓለም ንጉሠ ነገሥት አይደሉም። ከሳቸው ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ሲሉ የብራዚል ፕሬዝዳንት ተናገሩ
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር "ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው" እና በስልክም እንኳ አውርተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ትራምፕ "የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን የዓለም ንጉሠ ነገሥት አይደሉም!" ብለዋል።
ትራምፕ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጄይር ቦልሶናሮ ለፍርድ መቅረባቸው ስላስቆጣቸው በብራዚል ላይ ከባድ ቀረጥ መጣላቸው ይታወሳል።
ሉላ እና ትራምፕ በቅርብ ጊዜ በተደጋጋሚ እርስ በርሳቸው ሲተቹ ቆይተዋል።
ሉላ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመረጡ እኔ ፕሬዝዳንት ስላልነበርኩ ከትራምፕ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም። የእሳቸው ግንኙነት ከቦልሶናሮ ጋር እንጂ ከብራዚል ጋር አይደለም።"
ዶናልድ ትራምፕ በሐምሌ ወር በብራዚል ዕቃዎች ላይ የ50 በመቶ ቀረጥ መጣላቸው ይታወሳል።
ሉላ ቀረጡን "ፖለቲካዊ" ሲሉ ገልጸው፣ "ትራምፕ ከብራዚል ጋር ባላቸው ግንኙነት የሚሠሯቸውን ስህተቶች የአሜሪካ ሕዝብ ዋጋ ያስከፍላሉ" ብለዋል።

#ethiopia | የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር "ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው" እና በስልክም እንኳ አውርተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።

#yederaw #fidelpost #luiz_inácio Lula_da_Silva

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ዶክተር ምናሴ ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ አገራቸውን ብሎም አሕጉራቸውን አፍሪካን ያገለገሉት ዶክተር ምናሴ ኃይሌ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚኖሩበት አገረ አሜሪካ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ታውቋል።
ዶክተር ምናሴ ኃይሌ ከአባታቸው ከባላምባራስ ኃይሌ ድብነህ ከእናታቸው ወይዘሮ ኢሌኒ ኃይሌ ታኅሣሥ 24 ቀን 1922 ዓ.ም. ሐረር ከተማ የተወለዱት ሲሆን ከማንም በላይ የለፋላትን አገራቸውን ከኀምሳ አመታት በላይ ሳያዩ በስደት እንዳሉ በአሜሪካን አገር በኒውጀርሲ ጠቅላይ ግዛት ሕይዎታቸው አልፏል።
በንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን ሀገራቸው ኢትዮጵያን በማስታወቂያ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ታላቁ ዲፕሎማት ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በ95 ዓመታቸው ማረፋቸውን ተሰምቷል።
እኚህ አንጋፋ ዲፕሎማት ብዙዎቻችን የምናውቃቸው በዘመነ ቀኃሥ የሊቢያው ተወካይ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና መዲናውን ከአዲስ አበባ ወደ ሌላ የአፍሪካ ከተማ እንዲዘዋወር ትእቢትና ንቀት በታከለበት ሁኔታ ለጠየቀው ጥያቄ በሰጡት አስደናቂ መልስ ነበር።
ዶ/ር ምናሴ በ1922 ዓ.ም(እኢአ)የተወለዱ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርታቸውን የመጀመሪያ ዲግሪያቸው እ.አ.አ 1946 - 1950 በአሜሪካ በሚገኘው ዊስኮሲን ማዲሰን ዩኒቨርሲቲ ካገኙ በኋላ በተጨማሪም ዶክትሬታቸዉን እ.አ.አ 1954 - 1961 ድረስ በኮሎምቢያ የህግ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።
ዶ/ር ምናሴ በግርማዊ ሃይለስላሴ አስተዳደር ዉስጥ ከ 1971 - 1973 ዓ.ም(እኢአ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በደርግ አብዮት ዘመን በህይወት ከተረፉ ጥቂት የቀ.ኃ.ስ ባለስልጣናት አንዱ ናቸው።
ዶ/ር ምናሴ በሙሉ የፕሮፌሰር ማዕረግ በተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የህግ መምህር ሆነዉ አገልግለዋል ሲል ባላገሩ ቴለቪዥን ዘግቧል።

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት እለት !
‹‹ … ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል፤ ለደህንነትዎ ሲባልም አስተባባሪው ኮሚቴ ወዳዘጋጀልዎ ቦታ እንዲሄዱ ተወስኗል …››
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም
ከዓለም ስመጥር ነገሥታት መካከል አንዱ የነበሩት፣ የሰለሞናዊ ስርዎ መንግሥት የመጨረሻው ንጉሥ፣ እግራቸው በረገጠበት ምድር ሁሉ የነበረው ሕዝብ የሚሰግድላቸው፣ አንበሳ አጉራሹ … ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የባለቤታቸው የእቴጌ መነን አስፋው፣ የልጆቻቸውና የቅርብ ሰዎቻቸው ሞት፣ የመንግሥታቸው ሹማምንት ንቅዘት፣ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተደማምረው የአስተዳደራቸውን ምሰሶ አናጉት፡፡
በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ሁለተኛው ቀን ልክ በዛሬዋ እለት ፤ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ አፄ ኃይለሥላሴን ከዙፋናቸው አውርዶ ቤተ መንግሥቱን በመቆጣጠር የኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን ያወጀበት እለት።
አጼ ኃይለ ሥላሴ በርግጥም በውጪው በጣም ነበር የሚከበሩት፡፡ የሚናገሩት ቃልም ተሰሚነት ነበረው፡፡ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትንና የገለልተኝነት ንቅናቄ ሀገራት ማህበርን በማቋቋም ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ የአፍሪቃ ሀገራት ነጻነታቸውን እንዲቀዳጁ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል፡፡ በሀገር ቤቱ ጉዳይ ግን ብዙም አልተሳካላቸውም፡፡ በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን ህገ መንግሥት ያረቀቁት እኚሁ መሪ እውነተኛው ስልጣን የህዝብ ይሆን ዘንድ አልፈቀዱም፡፡ የባሪያ ንግድን በማጥፋት የዘመናዊነት ተስፋን የፈነጠቁት ንጉሥ በኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች እንኳ ተወግዶ የነበረውን የገባር ስርዓት እንደገና በህዝብ ላይ ጭነዋል፡፡ ውሳኔዎችን በፓርላማ የማሳለፍ ባህልን ያስተዋወቁት “አጼ” ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ላለማስፈን በብርቱ ታግለዋል፡፡
በአገዛዝ ዘመናቸው የሀገሪቱን “አፈር ገፊ” አርሶ አደር አላንቀሳቅስ ካለው የመደብና የኢኮኖሚ ጭቆና በተጨማሪ የሀይማኖትና የብሔር ጭቆናዎች የሀገሪቷን ቀፍደደው ይዘዋታል፡፡ ሀገሪቷ ወደፊት መንቀሳቀስ አቅቷት ትዋትት ነበር፡፡
ለበርካታ ዘመናት ህዝቡ ጭቆናውንና መከራውን በግላጭ መቃወም ያልቻለው ህዝብ በውስጡ እየነፈረ ኖረ፡፡ ብሶቱ በቁጭት ሲያንተከትከው ከቆየ በኋላ የመጨረሻው ጥግ ደረሰ፡፡ ከ1965 መጨረሻ እስከ 1966 አጋማሽ ድረስ ሲታዩ የነበሩት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥንቅጦች ህዝቡን በስርዓቱ ላይ አነሳሱት፡፡ በየካቲት 1966 አብዮት ፈነዳ፡፡ ስልጣን ከንጉሠ ነገሥቱ እጅ አመለጠች፡፡ ለብዙ ክፍለ ዘመናት ሲወራረስ የቆየው የሰለሞናዊው ስርወ መንግሥት ግብአተ መሬትም ሊፈጸም ተቃረበ፡፡
ከየጦር ክፍሎቹ የተላኩት ተወካዮች በአራተኛ ክፍለ ጦር ተሰባሰቡ፡፡ በሰኔ 21/1966 “የጦር ሀይሎች፣ የፖሊስ ሰራዊትና የብሔራዊ ጦር አስተባባሪ ኮሚቴ” የሚባል 120 አባላት ያሉት ወታደራዊ ሸንጎ መሰረቱ፡፡ ከሶስተኛ ክፍለ ጦር የመጡት ሻለቃ መንግሥቱ ሀይለማሪያም የኮሚቴው ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ የአራተኛ ክፍለ ጦሩ ሻለቃ አጥናፉ አባተ ምክትል ሊቀመንበር ተብለው ተሰየሙ፡፡ በሊቀመንበር መንግሥቱ ጠያቂነትም የሶስተኛ ክፍለ ጦሩ ሻለቃ ገብረየስ ወልደሃና የኮሚቴው ዋና ጸሓፊ ጠያቂነት ሆኑ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ኮሚቴው “ለምን በፈረንጅ ስም እንጠራለን” በሚል ምክንያት “አስተባባሪ ኮሚቴ” የተሰኘውን መጠሪያውን “ደርግ” በማለት ቀየረው (“ደርግ” የሚለውን ስም ያመነጨው የደርጉ የባህል ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበረው ሻለቃ ናደው ዘካሪያስ ነው፤ በደርግ ወገን ሆነው ታሪኩን የጻፉ ወገኖች እንደገለጹት “ደርግ” የግዕዝ ቃል ሲሆን እኛ “ኮሚቴ” ከምንለው ጋር ተቀራራቢ ፍቺ አለው)፡፡
ወታደሮቹ ያቋቋሙት “ደርግ” እንቅስቃሴውን ጀመረ፡፡ ከሁሉም በፊት ህጋዊነትን ማግኘት አስፈላጊው ስለነበረ ከንጉሠ ነገሥቱ ዘንድ ቀርቦ ታማኝነቱን ገለጸላቸው፡፡ አጼውም ደርጉን በይሁንታ ተቀበሉት፡፡ በዚህ መሰረት ወታደራዊው ደርግ ከሲቪሉ የልጅ እንዳልካቸው ካቢኔ ጎን ለጎን ሆኖ አመራር መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጣናቸው ባልገዋል የተባሉ ባለስልጣናትንም አሰረ፡፡ ይሁንና ሁለቱ የአመራር አካላት በሚወስዷቸው የተቃረኑ እርምጃዎች ሊጣጣሙ ባለመቻላቸው አብረው መቀጠል ተሳናቸው፡፡ ይባስ ብሎም በሐምሌ መገባደጃ ላይ ወታደራዊው ደርግ የልጅ እንዳልካቸውን ካቢኔ አፈረሰው፡፡ ከሚኒስትሮቹም መካከል በርካቶቹ ታሰሩ፡፡
የወታደሮቹ ደርግ የንጉሠ ነገሥቱን ስልጣን ቀስ በቀስ መገዝገዝ ጀመረ፡፡ እንደ ዘውድ ምክር ቤት፣ የዙፋን ችሎትና የጸጥታ ካቢኔ (ልዩ ካቢኔ) የመሳሰሉ ተቋማትን አፈረሰ፡፡ በጥናት ላይ የነበረው አዲሱ ህገ መንግስትም እንዲታገድ ወሰነ፡፡ ፓርላሜንቱም ዳግመኛ ላይሰበሰብ ተበተነ፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ደርግ የህዝቡን ስነ-ልቦና ለራሱ አመራር ዘመን የማዘጋጀቱን ተግባር ተያያዘው፡፡ የንጉሡንና የዘውዳዊውን ስርዓት ገመና ማጋለጥ ጀመረ፡፡ ንጉሡ ከጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካና ከከተማ አውቶቡስ አገልገሎት ከፍተኛ ገቢ እንደሚዝቁ የሚገልጹ ፕሮግራሞችን በመገናኛ ብዙሀን አስተላለፈ፡፡ በመጨረሻው ላይ ግን መላውን ህዝብ ያስለቀሰውንና የ1965ቱን የወሎ ረሐብ የሚዘግበውን ዶክመንተሪ ፊልም አሳየ፡፡ በዚህም ህዝቡ ለስርዓቱ ያለውን ገደብ የለሽ ጥላቻ አሳየ፡፡
መስከረም ሁለት/1967….. ከጧቱ 3፡00 ሰዓት… በብሔራዊ ቤተ መንግሥት…..
በደርጉ ውስጥ የአስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆነው የተሰየሙት ሻለቃ ደበላ ዲንሳ ንጉሠ ነገሥቱ ከስልጣን መውረዳቸውን እንዲያረዳቸው የተመረጠውን አስራ ሶስት አባላት ያሉትን ቡድን እየመሩ ከቤተ መንግሥት ደርሰዋል፡፡ ነገር ግን ቡድኑ ንጉሡ ፊት ቀርቦ መልዕክቱን የሚነግርበትን ድፍረት አጣ፡፡ ጥቂት ካሰቡ በኋላ ግን ሻለቃ ደበላ አንድ ዘዴ ብልጭ አለችባቸው፡፡ የንጉሡ የቅርብ የስጋ ዘመድ የሆኑት ልዑል ራስ እምሩ ሀይሥ ስላሴ “ለደሃው ገበሬ የሚቆረቆሩ ተራማጅ መስፍን ናቸው” ማለትን ስለሰሙ እርሳቸው ባሉበት ንጉሡ መልዕክቱን እንዲሰሙት ቢደረግ ግዳጃቸውን ያለ አንዳች ችግር መፈጸም የሚችሉ ሆኖ ታያቸው፡፡ በዚህም መሰረት ጉዳዩን ለራስ እምሩ አስረዱ፡፡ ራስ እምሩም ይሁንታቸውን ገለጹላቸው፡፡ በቀጣይ የሆነውን ሻለቃ ደበላ ዲንሳ እንደሚከተለው ተናግረውታል፡፡
“የደርጉ መልዕክተኞች ሆነን የመጣነው አስራ ሶስታችንም ስድስት በአንድ በኩል፣ ስድስት በሌላ በኩል ተሰልፈው፣ እኔ መሀከላቸው ሆኜ ነበር የቆምኩት፡፡ ትንሽ ከጠበቅን ኋላ ጃንሆይ ከፎቅ እየወረዱ መሆናቸው ተነገረንና በተጠንቀቅ ቆምን፡፡ ትልቁ የዙፋን አዳራሽ ውስጥ ነበርን፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ ገብተው ወንበራቸው ላይ እንደተቀመጡ አንድ እርምጃ ወደፊት ሄጄ በመቅረብ ወታደራዊ ሰላምታ ግጥም ካደረግኩ በኋላ በደርጉ ተዘጋጅቶ የተሰጠኝን ጽሑፍ አነበብኩና እንደገና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጥቼ አንድ እርምጃ ወደኋላ በመራመድ ከጓደኞቼ ጋር ተቀላቅዬ ቆምኩ፡፡ ከስልጣን መውረዳቸውን የሚገለጽ ከሁለት፣ ሶስት መስመር ያልበለጠ አጭር ጽሑፍ ነበር፡፡”

Comments