"የአፍሪካ አንድነት መሐንዲስ"
ከተማ ይፍሩ (1922-1988 ዓ.ም)
ከተማ ይፍሩ በወጣትነታቸው በውጭ አገር ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በኋላ በንጉሠ ነገሥቱ ዘንድ ባላቸው ከፍተኛ የመረዳትና የመግባባት ችሎታ ተለይተው ታወቁ በ1953 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1961) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙንአፍሪካ በታላቅ የመከፋፈል አደጋ ውስጥ ነበረች።
በወቅቱ አፍሪካ በሁለት ጎራዎች ተከፍላ ነበር
* የካዛብላንካ ቡድን፡ አህጉሪቱ በአንድ ጊዜ ወደ አንድ መንግሥትነት (Continental Government) እንድትጠቃለል የሚፈልጉ (በክዋሜ ንክሩማ የሚመሩ)።
* የሞንሮቪያ ቡድን፡ ቀስ በቀስ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ትብብር ማደግን የሚመርጡ።
በነዚህ በሁለቱ ጽንፍ የያዙ ቡድኖች መካከል የነበረው ልዩነት የአፍሪካን አንድነት አደጋ ላይ ጥሎት ነበር በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ከተማ ይፍሩ በንጉሠ ነገሥቱ ትእዛዝ "የሰላም መልዕክተኛ" በመሆን አህጉሪቱን ያቋረጡት።
በአውሮፕላን ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር እየበረሩ መሪዎችን በማነጋገርና ልዩነቶችን በማጥበብ ትልቅ ሥራ ሠሩ ከተማ ይፍሩ የነበረባቸው ዋነኛው ፈተና "ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመሥረት ሁሉም መሪዎች አዲስ አበባ ላይ እንዲገኙ" ማሳመን ነበር።
ከተማ ይፍሩ የአፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ ላይ እንዲሰበሰቡ ያደረገው ጥረት የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ብስለት ለዓለም ያሳየ ክስተት ነበር።
በከተማ ይፍሩ ከፍተኛ ድካም እና በንጉሠ ነገሥቱ ድጋፍ በግንቦት ወር 1955 ዓ.ም (May 1963) 32 የነፃ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ ላይ ተሰበሰቡ። በጉባኤው ወቅት የድርጅቱ "ቻርተር" ወይም መተዳደሪያ ደንብ ሲረቀቅ የከተማ ይፍሩና የቡድናቸው አበርክቶ ከፍተኛ ነበር።
በወቅቱ የነበረውን ውጥረት በማርገብና የሁለቱን ቡድኖች (ካዛብላንካና ሞንሮቪያ) ሃሳብ አቀናጅቶ አንድ የጋራ ሰነድ እንዲወጣ በማድረግ ረገድ የእሳቸው ብልህነት ወሳኝ ነበር በዚህም ምክንያት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) ተመሠረተ መቀመጫውም አዲስ አበባ እንዲሆን ተወሰነ።
ከተማ ይፍሩ ከአአድ መመስረት በኋላም ለአፍሪካ ነፃነትና አንድነትመትጋታቸውን አላቆሙም
በሞሮኮና አልጄሪያ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የነበሩ የድንበር ውጥረቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረዋል።ገና ነፃ ባልወጡ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የነፃነት ታጋዮች የኢትዮጵያ ድጋፍ እንዲጠናከር አድርገዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የፖለቲካ ማዕከል እንድትሆንና የዲፕሎማሲ አውድማ እንድትሆን መሠረት ጥለዋል።
ከተማ ይፍሩ በሥራቸው ትጉ፣በንግግራቸው ረቂቅና በሃሳባቸው አርቆ አሳቢ ዲፕሎማት ነበሩ ዛሬ የአፍሪካ ሕብረት (AU) በአዲስ አበባ በግርማ ሞገስ ሲቆም ከጀርባው የዚህ ታላቅ ሰው የላብና የጥበብ ውጤት አለበት።
ከተማ ይፍሩ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ "የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባት" ተብለው ቢጠሩ የሚገባቸው አህጉሪቱ በጥርጣሬና በልዩነት በታወከችበት ወቅት ድልድይ ሆነው ስላገናኟት ነው።

6 months ago