Logo
Getu Temesgen
ኢኳኢተስ

ዓባይ እና አዲሱ የፍትሕ ዓውድ

ፕ/ር ምዋንጊ ሳምሶን ኪመኒ እና ፕ/ር ጆን ሙከም ምባኩ

ትርጉም:- ሰለሞን በጋሻው
#ethiopia | በዘመኑ የነበሩት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሀገራቸው ለምትመኘው ብሔራዊ ልማትና ብልጽግና የሙህ ሀብቷን መጠቀም እንደሚያስፈልጋት ጠንቅቀው ይገነዘቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ዶ/ር ዳንኤል ክንዴ አንዳቀረበው የመከራከሪያ ሀላብ በብሪታኒያና በኢትዮጵያ መካከል በ1902 ተፈጽሟል የተባለውን የሁለትዮሽ ስምምነት እርባና ቢስ የሚያደርጉ እና ተጨባጭ የሆኑ ኹነት ገላጭ መረጃዎች አሉ።

ተፈጸመ የተባለው የሁለትዮሽ ስምምነት በብሪታኒያ ፓርላማም ሆነ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና የንጉሠ ነገሥቱ አማካሪ ባለሟሎች ምክር ቤት ዘንድ ቀርቦ፤ በመጽደቅ ወደ ሕግነት የተለወጠበት አጋጣሚ አለመከሰቱ ስምምነቱን ወረቀት ላይ ብቻ የቀረ ባዶ ደንብ እንዲሆን አድርጎታል። ሁለቱም ሀገራት ይህንን በማድረግ ስምምነቱን ወደ ሕግነት አጽድቀው አላሳለፉትም። ኢትዮጵያ በስምምነቱ ታሳሪ አለመሆኗን ለማስረዳት የሚገልጽ ከዚህ የበለጠ ጭብጥ የለም፡፡ ክንዴ 1999,p.146) "

በመሆኑም ኢትዮጵያ ከብሪታኒያ ጋር ፈጸመች በተባለው ስምምነት መሠረት ታሳሪ አለመሆኗን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ከርክር ማድረግ ወይም ጭብጥ ማቅረብ አያስፈልጋትም።

****

"በደቡብ የአሜሪካ ግዛት ይመረት ከነበረው የጥጥ ምርት አብዝሐኛው የሚላከው ወደ ታላቋ ብሪታንያ ላንክሻየር የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ነበር (ቤከርት 2004) ። በ1861 አሜሪካ ውስጥ ተከስቶ የነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ሲነሳ በደቡብ ግዛት በሰፊው ይመረት የነበረው የጥጥ ምርት ተስተጓጎለ ። ……"

" እንግሊዞች ሰፊ የሆነው የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪያቸው የገጠመውን የግብዓት እጥረት ለመታደግ ግብፅ ውስጥ ጥጥ ላይ ብቻ ያተኮረ የመስኖ ልማት እንዲከወን ማድረግ ነበረባቸው ።"

ከአሜሪካኖች የእርስ በርስ ጦርነት ውጤት እስከ የኤርትራ መገንጠል የዓባይ ጉዳይ ኢትዮጲያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ ውስጥ የከተታት የመልክዓ ፖለቲካ ጉዳይ እጅጉን ብዙ ነው ።
#ኢኳኢተስ እነዚህን ውስብስብ የብሔራዊ ጥቅማችን የሚመለከቱ ጉዳዮች ከሌሎች በርካታ ጉዳዮች ጋር ከከዲቭ እስማዔል እስከ አብዱል ፈታህ አልሲሲ ዘመን ድረስ በሰፊው ታስቃኘናለች ።

በሁሉም የጃዓፈር መጽሐፍት መደብር ያገኙታል ።

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.