ዶናልድ ትራምፕ የዓለም ንጉሠ ነገሥት አይደሉም። ከሳቸው ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ሲሉ የብራዚል ፕሬዝዳንት ተናገሩ
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር "ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው" እና በስልክም እንኳ አውርተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ትራምፕ "የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን የዓለም ንጉሠ ነገሥት አይደሉም!" ብለዋል።
ትራምፕ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጄይር ቦልሶናሮ ለፍርድ መቅረባቸው ስላስቆጣቸው በብራዚል ላይ ከባድ ቀረጥ መጣላቸው ይታወሳል።
ሉላ እና ትራምፕ በቅርብ ጊዜ በተደጋጋሚ እርስ በርሳቸው ሲተቹ ቆይተዋል።
ሉላ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመረጡ እኔ ፕሬዝዳንት ስላልነበርኩ ከትራምፕ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም። የእሳቸው ግንኙነት ከቦልሶናሮ ጋር እንጂ ከብራዚል ጋር አይደለም።"
ዶናልድ ትራምፕ በሐምሌ ወር በብራዚል ዕቃዎች ላይ የ50 በመቶ ቀረጥ መጣላቸው ይታወሳል።
ሉላ ቀረጡን "ፖለቲካዊ" ሲሉ ገልጸው፣ "ትራምፕ ከብራዚል ጋር ባላቸው ግንኙነት የሚሠሯቸውን ስህተቶች የአሜሪካ ሕዝብ ዋጋ ያስከፍላሉ" ብለዋል።

11 months ago