መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት እለት !
‹‹ … ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል፤ ለደህንነትዎ ሲባልም አስተባባሪው ኮሚቴ ወዳዘጋጀልዎ ቦታ እንዲሄዱ ተወስኗል …››
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም
ከዓለም ስመጥር ነገሥታት መካከል አንዱ የነበሩት፣ የሰለሞናዊ ስርዎ መንግሥት የመጨረሻው ንጉሥ፣ እግራቸው በረገጠበት ምድር ሁሉ የነበረው ሕዝብ የሚሰግድላቸው፣ አንበሳ አጉራሹ … ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የባለቤታቸው የእቴጌ መነን አስፋው፣ የልጆቻቸውና የቅርብ ሰዎቻቸው ሞት፣ የመንግሥታቸው ሹማምንት ንቅዘት፣ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተደማምረው የአስተዳደራቸውን ምሰሶ አናጉት፡፡
በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ሁለተኛው ቀን ልክ በዛሬዋ እለት ፤ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ አፄ ኃይለሥላሴን ከዙፋናቸው አውርዶ ቤተ መንግሥቱን በመቆጣጠር የኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን ያወጀበት እለት።
አጼ ኃይለ ሥላሴ በርግጥም በውጪው በጣም ነበር የሚከበሩት፡፡ የሚናገሩት ቃልም ተሰሚነት ነበረው፡፡ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትንና የገለልተኝነት ንቅናቄ ሀገራት ማህበርን በማቋቋም ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ የአፍሪቃ ሀገራት ነጻነታቸውን እንዲቀዳጁ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል፡፡ በሀገር ቤቱ ጉዳይ ግን ብዙም አልተሳካላቸውም፡፡ በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን ህገ መንግሥት ያረቀቁት እኚሁ መሪ እውነተኛው ስልጣን የህዝብ ይሆን ዘንድ አልፈቀዱም፡፡ የባሪያ ንግድን በማጥፋት የዘመናዊነት ተስፋን የፈነጠቁት ንጉሥ በኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች እንኳ ተወግዶ የነበረውን የገባር ስርዓት እንደገና በህዝብ ላይ ጭነዋል፡፡ ውሳኔዎችን በፓርላማ የማሳለፍ ባህልን ያስተዋወቁት “አጼ” ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ላለማስፈን በብርቱ ታግለዋል፡፡
በአገዛዝ ዘመናቸው የሀገሪቱን “አፈር ገፊ” አርሶ አደር አላንቀሳቅስ ካለው የመደብና የኢኮኖሚ ጭቆና በተጨማሪ የሀይማኖትና የብሔር ጭቆናዎች የሀገሪቷን ቀፍደደው ይዘዋታል፡፡ ሀገሪቷ ወደፊት መንቀሳቀስ አቅቷት ትዋትት ነበር፡፡
ለበርካታ ዘመናት ህዝቡ ጭቆናውንና መከራውን በግላጭ መቃወም ያልቻለው ህዝብ በውስጡ እየነፈረ ኖረ፡፡ ብሶቱ በቁጭት ሲያንተከትከው ከቆየ በኋላ የመጨረሻው ጥግ ደረሰ፡፡ ከ1965 መጨረሻ እስከ 1966 አጋማሽ ድረስ ሲታዩ የነበሩት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥንቅጦች ህዝቡን በስርዓቱ ላይ አነሳሱት፡፡ በየካቲት 1966 አብዮት ፈነዳ፡፡ ስልጣን ከንጉሠ ነገሥቱ እጅ አመለጠች፡፡ ለብዙ ክፍለ ዘመናት ሲወራረስ የቆየው የሰለሞናዊው ስርወ መንግሥት ግብአተ መሬትም ሊፈጸም ተቃረበ፡፡
ከየጦር ክፍሎቹ የተላኩት ተወካዮች በአራተኛ ክፍለ ጦር ተሰባሰቡ፡፡ በሰኔ 21/1966 “የጦር ሀይሎች፣ የፖሊስ ሰራዊትና የብሔራዊ ጦር አስተባባሪ ኮሚቴ” የሚባል 120 አባላት ያሉት ወታደራዊ ሸንጎ መሰረቱ፡፡ ከሶስተኛ ክፍለ ጦር የመጡት ሻለቃ መንግሥቱ ሀይለማሪያም የኮሚቴው ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ የአራተኛ ክፍለ ጦሩ ሻለቃ አጥናፉ አባተ ምክትል ሊቀመንበር ተብለው ተሰየሙ፡፡ በሊቀመንበር መንግሥቱ ጠያቂነትም የሶስተኛ ክፍለ ጦሩ ሻለቃ ገብረየስ ወልደሃና የኮሚቴው ዋና ጸሓፊ ጠያቂነት ሆኑ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ኮሚቴው “ለምን በፈረንጅ ስም እንጠራለን” በሚል ምክንያት “አስተባባሪ ኮሚቴ” የተሰኘውን መጠሪያውን “ደርግ” በማለት ቀየረው (“ደርግ” የሚለውን ስም ያመነጨው የደርጉ የባህል ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበረው ሻለቃ ናደው ዘካሪያስ ነው፤ በደርግ ወገን ሆነው ታሪኩን የጻፉ ወገኖች እንደገለጹት “ደርግ” የግዕዝ ቃል ሲሆን እኛ “ኮሚቴ” ከምንለው ጋር ተቀራራቢ ፍቺ አለው)፡፡
ወታደሮቹ ያቋቋሙት “ደርግ” እንቅስቃሴውን ጀመረ፡፡ ከሁሉም በፊት ህጋዊነትን ማግኘት አስፈላጊው ስለነበረ ከንጉሠ ነገሥቱ ዘንድ ቀርቦ ታማኝነቱን ገለጸላቸው፡፡ አጼውም ደርጉን በይሁንታ ተቀበሉት፡፡ በዚህ መሰረት ወታደራዊው ደርግ ከሲቪሉ የልጅ እንዳልካቸው ካቢኔ ጎን ለጎን ሆኖ አመራር መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጣናቸው ባልገዋል የተባሉ ባለስልጣናትንም አሰረ፡፡ ይሁንና ሁለቱ የአመራር አካላት በሚወስዷቸው የተቃረኑ እርምጃዎች ሊጣጣሙ ባለመቻላቸው አብረው መቀጠል ተሳናቸው፡፡ ይባስ ብሎም በሐምሌ መገባደጃ ላይ ወታደራዊው ደርግ የልጅ እንዳልካቸውን ካቢኔ አፈረሰው፡፡ ከሚኒስትሮቹም መካከል በርካቶቹ ታሰሩ፡፡
የወታደሮቹ ደርግ የንጉሠ ነገሥቱን ስልጣን ቀስ በቀስ መገዝገዝ ጀመረ፡፡ እንደ ዘውድ ምክር ቤት፣ የዙፋን ችሎትና የጸጥታ ካቢኔ (ልዩ ካቢኔ) የመሳሰሉ ተቋማትን አፈረሰ፡፡ በጥናት ላይ የነበረው አዲሱ ህገ መንግስትም እንዲታገድ ወሰነ፡፡ ፓርላሜንቱም ዳግመኛ ላይሰበሰብ ተበተነ፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ደርግ የህዝቡን ስነ-ልቦና ለራሱ አመራር ዘመን የማዘጋጀቱን ተግባር ተያያዘው፡፡ የንጉሡንና የዘውዳዊውን ስርዓት ገመና ማጋለጥ ጀመረ፡፡ ንጉሡ ከጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካና ከከተማ አውቶቡስ አገልገሎት ከፍተኛ ገቢ እንደሚዝቁ የሚገልጹ ፕሮግራሞችን በመገናኛ ብዙሀን አስተላለፈ፡፡ በመጨረሻው ላይ ግን መላውን ህዝብ ያስለቀሰውንና የ1965ቱን የወሎ ረሐብ የሚዘግበውን ዶክመንተሪ ፊልም አሳየ፡፡ በዚህም ህዝቡ ለስርዓቱ ያለውን ገደብ የለሽ ጥላቻ አሳየ፡፡
መስከረም ሁለት/1967….. ከጧቱ 3፡00 ሰዓት… በብሔራዊ ቤተ መንግሥት…..
በደርጉ ውስጥ የአስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆነው የተሰየሙት ሻለቃ ደበላ ዲንሳ ንጉሠ ነገሥቱ ከስልጣን መውረዳቸውን እንዲያረዳቸው የተመረጠውን አስራ ሶስት አባላት ያሉትን ቡድን እየመሩ ከቤተ መንግሥት ደርሰዋል፡፡ ነገር ግን ቡድኑ ንጉሡ ፊት ቀርቦ መልዕክቱን የሚነግርበትን ድፍረት አጣ፡፡ ጥቂት ካሰቡ በኋላ ግን ሻለቃ ደበላ አንድ ዘዴ ብልጭ አለችባቸው፡፡ የንጉሡ የቅርብ የስጋ ዘመድ የሆኑት ልዑል ራስ እምሩ ሀይሥ ስላሴ “ለደሃው ገበሬ የሚቆረቆሩ ተራማጅ መስፍን ናቸው” ማለትን ስለሰሙ እርሳቸው ባሉበት ንጉሡ መልዕክቱን እንዲሰሙት ቢደረግ ግዳጃቸውን ያለ አንዳች ችግር መፈጸም የሚችሉ ሆኖ ታያቸው፡፡ በዚህም መሰረት ጉዳዩን ለራስ እምሩ አስረዱ፡፡ ራስ እምሩም ይሁንታቸውን ገለጹላቸው፡፡ በቀጣይ የሆነውን ሻለቃ ደበላ ዲንሳ እንደሚከተለው ተናግረውታል፡፡
“የደርጉ መልዕክተኞች ሆነን የመጣነው አስራ ሶስታችንም ስድስት በአንድ በኩል፣ ስድስት በሌላ በኩል ተሰልፈው፣ እኔ መሀከላቸው ሆኜ ነበር የቆምኩት፡፡ ትንሽ ከጠበቅን ኋላ ጃንሆይ ከፎቅ እየወረዱ መሆናቸው ተነገረንና በተጠንቀቅ ቆምን፡፡ ትልቁ የዙፋን አዳራሽ ውስጥ ነበርን፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ ገብተው ወንበራቸው ላይ እንደተቀመጡ አንድ እርምጃ ወደፊት ሄጄ በመቅረብ ወታደራዊ ሰላምታ ግጥም ካደረግኩ በኋላ በደርጉ ተዘጋጅቶ የተሰጠኝን ጽሑፍ አነበብኩና እንደገና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጥቼ አንድ እርምጃ ወደኋላ በመራመድ ከጓደኞቼ ጋር ተቀላቅዬ ቆምኩ፡፡ ከስልጣን መውረዳቸውን የሚገለጽ ከሁለት፣ ሶስት መስመር ያልበለጠ አጭር ጽሑፍ ነበር፡፡”

11 months ago