6 hours ago
ቤተሰብ ለመጠየቅ የሄደችውን ባለትዳር አስገድዶ መድፈር የፈፀመው አጓቷ እና ሌላኛው ተከሳሽ በእስራት ተቀጡ
በካምባ ዙሪያ ወረዳ ኦቶሎ ቀበሌ ከርሼ በተባለ አካባቢ ነው የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው።
ፖሊስ እንዳታወቀው ተበዳይ 22 ዓመቷ ሲሆ ባለትዳር ናት ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ በመንገድ ላይ እየተጓዘች ባለችበት ወቅት ተከሳሾቹ እንዳገኟት ተገልጿል።
በዚህም ከተከሳሾቹ መካከል አንደኛው የተበዳይዋ አጎት ሲሆን ይህንን የቤተሰብ ቅርበት በመጠቀም ተበዳይዋ ሌሊቱን በሌላኛው ተከሳሽ ቤት አድራ በማግስቱ እንድትጓዝ በማሳመን ይዟት ይሄዳል።
ሆኖም በጫካ ውስጥ ከደረሱ በኋላ ተከሳሾቹ ተበዳይዋን በዱላ በመምታት ራሷን መከላከል እንዳትችል ካደረጉ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀማቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በደረሰው ወንጀል ተበዳይዋ ያቀረበችውን አቤቱታ ተከትሎ ፖሊስ ምርመራ በማካሄድ የተበዳይዋን ቃል ጨምሮ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች የተደገፈ መሆኑን በመግለጽ የምርመራ መዝገቡ ለዐቃቤ ህግ ይልካል።
ዐቃቤ ህግም ክስ መስርቶ ጉዳዩን ለካምባ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል።ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎችና የተከራካሪ ወገኖችን አቋም ከመረመረ በኋላ፣ የዋና ወንጀል አድራጊው ከተበዳይዋ ጋር የቅርብ የስጋ ዝምድና ያለው በመሆኑ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ አየለ ባርጋደ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ ጹንዖ ገርሻ ደግሞ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Seledadotio

አቃቢ ህግ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ
በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው እንዲከታተሉ አቃቢ ህግ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ እና በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ብይን ተሰጠ።
አቃቢ ህግ በከፍተኛ የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾች እና ጠበቃቸው፣ የተከሰሱበት የክስ መዝገቡ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ እና በችሎት ውሳኔ ያልተሰጠበት ሆኖ እያለ በሚዲያ ላይ በመቅረብ ከክሱ አውድ ውጪ የሆነ ማብራሪያ በመስጠታቸው የፍትሕ ሂደቱን ተጽዕኖ ውስጥ ለመክተት እና ምስክሮችን ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ሞክረዋል በሚል የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ከማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የሚል አቤቱታ አቅርቦ ነበር።
በተጨማሪም ዘገባው የተጫነበት ሚዲያ ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ቪዲዮውን እንዲያወርድ ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 457 ስር በቀጥታ እንዲቀጡ እንዲወሰን የሚሉ አቤቱታዎችንም አቃቢ ህግ አካቷል።

7 hours ago
በሁለቱ የኢሕአፓ ፖለቲከኞች እና በተቃዋሚዎች ጠበቃው አበራ ንጉሥ ላይ 12 የምርመራ ቀናት ተፈቀደ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት "በሽብር ወንጀል" የተጠረጠሩት ፖለቲከኞቹ አበበ አካሉ እና ይሳቅ ወልዳይ እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉሥ ላይ የ12 የምርመራ ቀናት መፍቀዱን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዛሬ አርብ ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ የተሰየመው ችሎት የመርማሪ ፖሊስን ጥያቄ የተቀበለው፣ ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ለተነሳው ጥርጣሬ በማስረጃነት የቀረቡት ቃለ መጠይቆች ላይ "የሽብር መነሻ ሐሳብ በማግኘታቸው" እንደሆነ ጠበቃው ገልጸዋል።
ሁለቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ፖለቲከኞች እና ለተቃዋሚዎች ጥብቅና በመቆም የሚታወቁት አበራ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰኞ ሐምሌ 27 ነበር። በፌደራል ፖሊስ አባላት በተያዙ ሁለተኛው ቀን ረቡዕ ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።
መርማሪ ፖሊስ ሦስቱ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ "በመንግሥት የፀጥታ ተቋማት እና በመንግሥትት ከፍተኛ አመራሮች ላይ የሽብር ጥቃት" ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለፍርድ ቤት ገልጿል።
ድርጊቱን ሊፈጽሙ የነበሩት "ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ድብቅ ግንኙነት በማድረግ" እንደሆነ የገለጸው ፖሊስ፤ "ጽምዶ [ተ]ብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር በቀናጀት" ምልመላ እና ስለላ ሲያከናውኑ እንደነበር በመጥቀስም ወንጅሏል።
በዚህ ጉዳይ ላይ "ሥራውን አጠናቅቆ መዝገቡን ለሚመለከተው የሕግ አካል ለመላክ" እንዲችልም 14 የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ፣ በሦስቱ ግለሰቦች ላይ የቀረበውን ውንጀላ ለማስረዳት በቀረቡት በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የተደረጉ ቃለ መጠይቆች 'የሽብር ይዘት አላቸው ወይስ የላቸውም' የሚለውን ለመወሰን ለዛሬ አርብ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።
ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት በመርማሪ ፖሊስ ቀረቡትን "የሐሰት ፕሮፓጋንዳ" ቪድዮ ሊንኮች መመልከቱን እንደገለጸ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ዳኞች በቀረቡላቸው የቪዲዮ ሊንኮች ላይ "የሽብር ይዘት" የሚያገኙ ከሆነ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ሊፈቀድ እንደሚችል፤ ካልሆነ ደግሞ በዋስትና ሊወጡ ይችሉ እንደነበር ጠበቃው አስረድተዋል።
እንደ ጠበቃው ገለጻ፣ ቪዲዮዎቹን የተመለከቱን ዳኞች ለፖሊስ ጥርጣሪ "መነሻ የሚሆኑ ይዘቶችን አግኝተናል" ብለዋል።
ዳኞች "በሰማነው ድምፅ ላይ ድርጊቱ የሽብር ሊመስል የሚችል የመነሻ ሀሳብ አግኝተናል። በተወሰነ መልኩ የመነሻ ሀሳብ ስላገኘን ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል" እንዳሉ ጠበቃው አስረድተዋል።
በዚህም መሠረት መርማሪ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ ተጠርጣሪዎቹ "ፍርድ ቤት ከቀረቡበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ የ12 ቀን የምርመራ ጊዜ" መፍቀዳቸውን ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱ በቀጣዩ በሚኖረው ቀጠሮ ላይ "ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ" እንዲቀርብ ትዕዛዝ መሰጠቱንም ጠበቃ ሰለሞን ተናግረዋል።
BBC Amharic

11 hours ago
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ።
የተላለፈው መግለጫ ከዩቲዩብ እንዲወርድ እና ይቅርታ እንዲጠየቅ ፍርድ ቤቱ አዟል።
ዐቃቤ ሕግ አርቲስቶቹ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ በመስጠታቸው የዋስትና መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉና ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።
ዛሬ ነሀሴ 01 2018 ዓ/ም ጠዋት በነበረው ችሎት ተጠርጣሪ አርቲስቶቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ለዐቃቤ ሕግ አቤቱታ በጽሑፍ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ለምን መግለጫ እንደሰጡም ለችሎቱ የቃል ማብራሪያ አቅርበዋል።
አርቲስቶቹ በማብራሪያቸው ድርጊቱን የፈጸሙት በማኅበራዊ ሚዲያ ከሚደርስባቸው ስም ማጥፋትና መልካም ስም ከማጉደፍ ራሳቸውን ለመከላከል አስበው እንደሆነ አስረድተዋል።
ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለከሰዓት 9:00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፤ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠትና ማብራሪያ ማቅረብ ጥፋት መሆኑን አመልክቷል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ለሚጠፋ ስም መልስ ለመስጠት እንኳን ቢሆን ድርጊቱን ፈጽሟል የሚሉትን አካል በሕግ መጠየቅ ሲገባ መግለጫ መስጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ ጠቁሟል።
ሆኖም «በጥቃቅን ጥፋቶች የዋስትና መብትን ማገድ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም» ሲል ዐቃቤ ሕግ የተከሳሾች የዋስትና መብት ተነስቶ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።
በተጨማሪም አርቲስቶቹና ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት ድርጊቱን ሆን ብለው የፈጸሙት በመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 457 መሠረት እንዲቀጡ፣ ወይም በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ እንዲመሠረትባቸው ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም።
በዚህም መሠረት መግለጫ የሰጡት አርቲስቶች ሌላ ጊዜ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጽሙ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በሌላ በኩል «እግረኛው» በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ እንዲተላለፍ ያደረገው አቶ ተክለሃይማኖት አዳነ ቪዲዮውን ከዩቲዩብ (YouTube) ላይ እንዲያወርድና ይቅርታ እንዲጠይቅ ፍርድ ቤቱ አዟል።
የመደበኛው የሕግ ሂደት ቀጠሮ ለጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም የተቀጠረ መሆኑ ታውቋል።
ገዛ ጌታሁን

Sponsored by
Surafel
13 hours ago
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች ላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት ቀጠሮ ተሰጠ።
በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ መጠነ ሰፊ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ታዋቂ አርቲስቶች፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
ነገር ግን ተከሳሾቹ "እግረኛው" በተሰኘ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ቀርበው መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ ዐቃቤ ሕግ ባለ 5 ገጽ የክስ አቤቱታ አቅርቦ ስለነበር ጉዳዩ ከሰዓት በኋላ በሌላ ችሎት እንዲታይ ተደርጎ ፣ ለዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።
ጠዋት በነበረው ችሎት ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነን ጨምሮ አርቲስቶቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ዐቃቤ ሕግ ላቀረበው አቤቱታ በጽሑፍ ምላሽ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ለምን መግለጫ እንደሰጡ የቃል ማብራሪያ አቅርበዋል።
ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ፦ "እኛ የኪነ ጥበብ ሰዎች ነን፤ ነገር ግን በመልካም ስማችን ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ስለተከፈተብንና ስማችን በመጥፋቱ ሥራችን ስለተበላሸ ነው ምላሽ ለመስጠት የተገደድነው" ብለዋል።
"ለምሳሌ በዚህ ምክንያት አምስት የሥራ ውሎች ተቋርጠውብኛል፤ እኔና ጓደኛዬ የምንሰራው የቴሌቪዥን ፕሮግራምም እንዲቋረጥ ተደርጓል" ሲል አርቲስት ይገረም ደጀኔ ለችሎቱ አብራርቷል።
በነበረው መግለጫ የፍርድ ቤቱን የሕግ ሂደት እንዳያስተጓጉሉ ጥንቃቄ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።
አርቲስቶቹን በማኅበራዊ ሚዲያ አናግሮ መግለጫቸውን ያስተላለፈው ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ በበኩሉ፦ "እኔ ይህን ፕሮግራም ሳቀርብ የመጀመሪያዬ አይደለም፤ አርቲስቶቹ በሕግ ከመያዛቸው አስቀድሞ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬን በፊንቴክ ዙሪያ ተገልጋዮች ስለሚያነሱት ቅሬታ ጠይቄ ሰርቻለሁ፤ ከዚያ በኋላም አርቲስቶቹን ጥፋተኛ አድርገው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚዘግቡትን መረጃዎች መነሻ በማድረግ የጠየቅኋቸው ሰዎች አሉ። አሁን እነሱን ያናገርኩት ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ የፍትሕ ሂደቱን እንደማይጎዳ የሕግ ባለሙያ አማክሬ ነው" ሲል ለችሎቱ አስረድቷል።
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የተሰጠው መግለጫ ከፍርድ ቤት ውጭ ውሳኔ መስጠት እንደሆነና በሕግ ሂደት ላይ ባለ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት በሕግ ወንጀል መሆኑ መደነገጉን አብራርቷል።
ቀጥሎም "ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ የአርቲስቶችን ጠበቃ ስለ መዝገቡ ጠይቆ ጠበቃው 'በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ አልሰጥም' ሲሉ 'ፈሪ ነህ ማለት ነው?' በማለት ተናግሯል፤ ይህም የተሳሳተ አካሄድ ነው።
ማንም ቢሆን መግለጫ መስጠት በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ አያውቅም ተብሎ አይገመትም፤ “የመጣው ይምጣ” በሚል ስሜት የተሰጠ መግለጫ እንደሆነ ስለምናምን፣ ፍርድ ቤቱ በአቤቱታው ላይ የተጠቀሱትን መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥልን" ሲል ጠይቋል።
ዐቃቤ ሕግ ከትላንት በፊቱ ችሎት በጽሑፍ ባቀረበው አቤቱታ፦
• የተከሳሾች የዋስትና መብት ተነስቶ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ፣
• የወንጀል ድርጊቱን ሆን ብለው የፈጸሙት በመሆኑ፣ ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖትን ጨምሮ ድርጊቱን ለምን እንደፈጸሙ ተጠይቀው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 457 መሠረት እንዲቀጡ፣
• ፍርድ ቤቱ ቀጥታ የማይቀጣቸው ከሆነ፣ ዐቃቤ ሕግ በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ እንዲመሠረትባቸው እንዲያደርግ፣
• በተላለፈው ቪዲዮ ላይ ይቅርታ ተጠይቆ ከማኅበራዊ ሚዲያ እንዲወርድ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት፣ የሚሉ ነጥቦች ይገኙበታል።
ግራ ቀኙን ያደመጠው ችሎቱ የቀረቡትን አቤቱታዎች መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

1 day ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የቀድሞው የኮሮና ቫይረስ ግብረ-ኃይል መሪ የነበሩት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ስለ ኮቪድ-19 መነሻ "እውነቱን ለመናገር" ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለእስር ሊዳረጉ እንደሚችሉ ተዘገበ።
የአሜሪካ ሴኔት የሀገር ውስጥ ደህንነት ኮሚቴ ሐሙስ ዕለት ባካሄደው ድምጽ አሰጣጥ፣ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺን በኮንግረስ ንቀት ጥፋተኛ ብሏቸዋል። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ፋውቺ ባለፈው ሳምንት በነበረው ችሎት ላይ ስለ ኮቪድ-19 መነሻ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸውን ተከትሎ ነው። በሪፐብሊካኖች በሚመራው በዚህ ኮሚቴ ውስጥ፣ ውሳኔው በ8 ለ 7 ድምጽ የጸደቀ ሲሆን፣ ዴሞክራቶች ድምጽ አሰጣጡን ለማስተጓጎል ያቀረቧቸው አምስት የውሳኔ ሃሳቦች በሙሉ በሪፐብሊካን አብላጫ ድምጽ ውድቅ ተደርገዋል።
ፋውቺ ባለፈው ረቡዕ በኮሚቴው ፊት በቀረቡበት ወቅት፣ በቻይና የዉሃን የቫይሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለተካሄደው አደገኛ የ'Gain-of-Function' ምርምር የገንዘብ ድጋፍ በማድረጋቸው፣ ኮቪድ-19 በቤተ-ሙከራ ውስጥ ስለመፈጠሩ በነበራቸው እውቀት፣ ከአሜሪካ የስለላ ተቋማት ጋር በነበራቸው ስራ፣ እንዲሁም ውጤታማ ያልሆኑ ክትባቶችን በማስተዋወቃቸው ዙሪያ ጥብቅ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር። ሆኖም የቀድሞው ባለስልጣን ከ100 ጊዜ በላይ ዝም የማለት ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ለአንዳቸውም ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ፋውቺ ይህን ያደረጉት ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሰፊ ይቅርታ አግኝተው እያለ መሆኑ አስገራሚ ሆኗል። አሜሪካ የምርምር ስራዋን ወደ ቻይና ማውጣት ከጀመረችበት ከጥር 1 ቀን 2014 ጀምሮ እስከ ጥር 20 ቀን 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ለፈጸሙት ማንኛውም ወንጀል ከክስ ነጻ የሚያደርግ ይቅርታ ከባይደን ተሰጥቷቸው ነበር።
የኮሚቴው ሰብሳቢ ሴናተር ራንድ ፖል ከድምጽ አሰጣጡ በፊት ባደረጉት ንግግር የፋውቺን ድርጊት አጥብቀው ወቅሰዋል። "ከአንድ ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን በኮቪድ ሞተዋል፤ ብዙዎቹ ብቻቸውን ነው ያረፉት። ሰራተኞች በስራቸው እና በክትባት ግዴታ መካከል እንዲመርጡ ተገደዋል፤ የንግድ ተቋማት ተዘግተው ዳግም አልተከፈቱም፤ አሜሪካውያን የመስራት፣ የማምለክ እና በሰውነታቸው ውስጥ ምን መግባት እንዳለበት የመወሰን ነጻነታቸውን አጥተዋል" በማለት የጉዳቱን ስፋት አውስተዋል። አክለውም "ዶ/ር ፋውቺ ምንም አይነት የፌደራል ክስ ስጋት አልነበረባቸውም፤ ማድረግ የነበረባቸው እውነቱን መናገር ብቻ ነበር" ብለዋል።
ፋውቺ ከ2014 እስከ 2025 ለፈጸሟቸው ጥፋቶች ከክስ ነጻ ቢሆኑም፣ ይቅርታው በችሎቱ ላይ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ሽፋን አይሰጥም። የኮንግረስ ንቀት በራሱ ወንጀል በመሆኑ፣ ፖል ከድምጽ አሰጣጡ በኋላ ወዲያውኑ የፋውቺን ጉዳይ ለአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር መርተዋል። ሚኒስቴሩ ክስ ለመመስረት ከወሰነ፣ ፋውቺ እስከ 100,000 ዶላር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና እስከ 12 ወራት በሚደርስ እስራት ሊቀጡ ይችላሉ።
ከዚህ ቀደም የዶናልድ ትራምፕ ረዳቶች የነበሩት ፒተር ናቫሮ እና ስቲቭ ባኖን በተመሳሳይ የኮንግረስ ንቀት ወንጀል በባይደን የፍትህ ሚኒስቴር ተከሰው እያንዳንዳቸው አራት ወራትን በእስር እንዳሳለፉ ይታወሳል። ዶ/ር ፋውቺ ከ1984 እስከ 2022 የብሔራዊ የአለርጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር የነበሩ ሲሆን፣ ጆ ባይደን በ2021 ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2022 ጡረታ እስከወጡበት ጊዜ ድረስ የፕሬዝዳንቱ ዋና የህክምና አማካሪ ሆነው በማገልገል የኮቪድ-19ን ከባድ እርምጃዎች በግንባር ቀደምትነት ሲመሩ የነበሩ ግለሰብ ናቸው።

2 days ago
በስለት እያስፈራሩ የሞባይል ስልክ የቀሙ 3 ወንጀል ፈፃሚዎች በእስራት ተቀጡ።
ሳሙኤል ደሳለኝ፣ ዮሴፍ መስፍን እና ዳግም አድነው የተባሉ ወንጀል ፈፃሚዎች ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ ሁለት ሰዎችን በስለት በማስፈራራት ሞባይል ስልካቸውን ቀምተው ይሰወራሉ፡፡
ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አንፎ ሮም ሰፈር ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ ተመሳሳይ ወንጀል ሲፈፅሙ በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡
የቤተል አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ በመላክ ክስ እንዲመሰረትባቸው ያደርጋል፡፡
የወንጀል ፈፃሚዎችን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ፈጣን የወንጀል ችሎት ሳሙኤል ደሳለኝ እና ዮሴፍ መስፍን በ4 አመት ዳግም አድነው በ2 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።
Addis Ababa police

በፃድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን ፀበል በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወቷ ያለፈው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
#ethiopia | በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የህግ ትምህርት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ሀብታሟ በቀለ ለእረፍት ወደ ቤተሰብ ከመሄዷ ቀድማ በፃድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን ፀበል በመከታተል ላይ ሳለች በአካባቢው በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ከዚህ አለም ድካም አርፋለች።
ተማሪ ሀብታሟ በትምህርቷ ካስመዘገበችው ከፍተኛ ውጤት ባሻገር፣ በመልካም ስነ ምግባሯ፣ በታታሪ ተማሪነቷ፣ በክፍል ውስጥ ተሳትፎዋና ተግባቢ ስብዕናዎቿ የምትታወቅ፤ በተለይ በምስለ ችሎት ውድድሮች በምታሳየው የላቀ ችሎታ እና ውጤት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ በሚሰጠው የነፃ ህግ አገልግሎት ድጋፎች ዙሪያ በነበራት ተሳትፎ የምትታወቅ ተማሪያችን ነበረች፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በተማሪ ሀብታሟ በቀለ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለተማሪዋ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪ በድንገተኛ አደጋ ህይወቷ አለፈ
#fastmereja I በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የህግ ትምህርት ተማሪ የሆነችው ሀብታሟ በቀለ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቿ ከመሄዷ አስቀድሞ በፃድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን ፀበል በመከታተል ላይ እያለች በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወቷ ማለፉ ተገለጠ። አደጋው የተከሰተው ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን፣ ተማሪዋ በአካባቢው በነበረችበት ወቅት ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት ህይወቷን ልታጣ ችላለች።
ተማሪ ሀብታሟ በቀለ በትምህርት ገበታዋ ካስመዘገበችው የላቀ ውጤት ባሻገር በመልካም ስነ-ምግባሯ፣ በታታሪነቷ እና በተግባቢነቷ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት የነበራት ተማሪ ነበረች። በተለይም በምስለ ችሎት ውድድሮች በምታሳየው የላቀ የህግ ችሎታ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ በሚሰጠው የነፃ ህግ እርዳታ አገልግሎት ላይ በንቃት በመሳተፍ የጎላ አስተዋጽኦ ስታበረክት እንደነበር ተገልጻለች።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በተማሪ ሀብታሟ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፣ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።

የቲቪ ፕሮግራም አቅራቢዋ እና የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዋ ዳናዊት መክብብ ቀርቦባት በነበረው ክስ በነፃ ተሰናበተች።
ዳናዊት ከ ኤቢኤል ኮንሰልታንሲ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ቤተልሔም ታደሰ፣ ገሊላ በለጠ እና ቤል ተስፋዬ ከተባሉ ሌሎች ተከሳሾች ጋር የፍትሐብሔር ክስ የተመሰረተባት ከወራት በፊት እንደነበረ ይታወቃል።
ቁጥራቸው 13 የሆኑ ከሳሾች «እነ ዳናዊት ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን በማለት ከእያንዳንዳችን 437,000 ብር ከተቀበሉ በኋላ ሳይልኩን ቀርተዋል» በሚል ክስ ለፍርድ ቤት አቅርበውባቸው ነበር።
«የተወሰደብንን ገንዘብ እንዲመለስልን በተለያዩ ጊዜያት የቃል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ብንሰጣቸውም እና ጉዳዩን በጋራ መግባባት ለመፍታት ጥረት ብናደርግም ተከሳሾች ብሩን ለመመለስም ሆነ ለማስመለስ እንቢተኛ ሆነዋል» ሲሉ ባስገቡት የክስ ዝርዝር ላይ አብራርተዋል።
አያይዘውም «እኛ ከሳሾች ወደዚህ ጉዳይ በሙሉ መተማመን የገባነው አምስተኛ ተከሳሽ የሆነችው ዳናዊት መክብብ ለድርጅቱ የሰራችውን ማስታወቂያ በማመን ነው» ሲሉ በክሳቸው ላይ ጠቅሰዋል።
ለወራት ክሱን ሲመለከት የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 4ኛ የፍትሐብሔር ችሎት ትናንት ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት አራቱን ተከሳሾች ጥፋተኛ በመሆናቸው በአንድነት እና በነጠላ ገንዘቡን ሊከፍሉ ይገባል ሲል ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፣ አምስተኛ ተከሳሽ ዳናዊት መክብብ «ሥራን የሠራችው የንግድ ፈቃድ አይታ ነው፤ ስለዚህ ልትጠየቅ አይገባም» ከክሱ በነፃ ተሰናብታለች ሲል እንደወሰነ ሰምተናል።
ዘገባው የኢትዮጲካሊንክ ነው::

ዳናዊት መክብብ በፍትሐብሔር ክስ በነፃ ተሰናበተች
#fastmereja I የታዋቂዋ የቲቪ ፕሮግራም አቅራቢና የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዳናዊት መክብብ ቀርቦባት የነበረው የፍትሐብሔር ክስ ውድቅ ተደርጎ በነፃ የተሰናበተች ሲሆን፣ ከእሷ ጋር በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች አራት ተከሳሾች ግን ጥፋተኛ ተብለው ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አራተኛ ፍትሐብሔር ችሎት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ፣ አምስተኛ ተከሳሽ ሆና የቀረበችው ዳናዊት መክብብ የንግድ ፈቃድ አይታ የማስታወቂያ ሥራ የሰራች በመሆኗ በጉዳዩ ላይ ልትጠየቅ አይገባም በሚል ከክሱ በነፃ አሰናብቷታል።
ጉዳዩ የተጀመረው 13 ከሳሾች «ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን» በሚል ከእያንዳንዳቸው 437 ሺህ ብር የተቀበላቸው የኤቢኤል ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የቤተልሔም ታደሰ፣ ገሊላ በለጠ፣ አቤል ተስፋዬ እና የዳናዊት መክብብ ክስ በመስረታቸው ነው። ከሳሾቹ የተወሰደብን ገንዘብ እንዲመለስልን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ተከሳሾቹ ሊመልሱልን አልቻሉም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አብራርተው ነበር።
እንደ ኢትዮጲካሊንክ ዘገባ ለወራት ክሱን ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ፣ አራቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በነጠላና በአንድነት የተወሰደውን ገንዘብ ለከሳሾቹ እንዲከፍሉ ሲወሰን፣ ዳናዊት መክብብ ግን በነፃ ተሰናብታለች።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ጨምሮ ከፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሶስት ግለሰቦች ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ አሴረዋል በሚል ወንጀል ከሷቸዋል። ፖሊስ በነዚህ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።
ክሱ የቀረበው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ደረጃ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባቀረበው የቅድመ ምርመራ ጥያቄ ላይ ነው። ይህ የሆነው ኢህአፓ የሶስቱን ግለሰቦች መታሰር ካረጋገጠ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። የታሰሩት ግለሰቦች የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ይስሃቅ ወልዳይ፣ ከፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች በህግ ሲወክሉ የነበሩት ጠበቃ አበራ ንጉስ አየነው፣ እና መምህር እንዲሁም የኢህአፓ አባል የሆነው አበበ አካሉ ክብረት ናቸው።
የኢህአፓ ዋና ፀሀፊ ሚስጥረ-ስላሴ ታምራት እስሩ መጀመሩን አረጋግጠው፣ ጠበቃ አበራ ንጉስ እና ይስሃቅ ወልዳይ መጀመሪያ በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ አበበ አካሉ ደግሞ በማግስቱ መታሰሩን ገልፀዋል። ፓርቲው ባወጣው አጭር መግለጫ፣ ግለሰቦቹ በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን በነፃነት በመግለፃቸው ብቻ መታሰራቸውን አውግዞ፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ወንጀል ስላልሆነ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።
በሌላ በኩል የፌደራል ፖሊስ የክስ መዝገብ እንደሚያትተው፣ ግለሰቦቹ የታሰሩት በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሳይሆን በኃይል ስልጣን ለመያዝ በተቀናጀ ሴራ ውስጥ በመሳተፋቸው ነው። የፖሊስ የምርመራ ቢሮ እንዳለው፣ ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊውን የፖለቲካ ፓርቲ እንደ ሽፋን በመጠቀም ከፓርቲው ህገ-ደንብ እና አላማ ውጪ መንግስትን በኃይል ለመገልበጥ ተንቀሳቅሰዋል። ፖሊስ አክሎም ግለሰቦቹ "የሀገር ውስጥ እና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች" ከተባሉት ህወሓት፣ ፅምዶ ከተባለ ቡድን እና ሌሎች ፀረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በቅንጅት ሲሰሩ እንደነበር ወንጅሏል። በአዲስ አበባ አባላትን በመመልመል፣ የፀጥታ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመከታተል እና መረጃዎችን ለታጠቁ ኃይሎች በማስተላለፍ ተሳትፈዋል ተብለዋል።
ፖሊስ በክሱ ላይ እንዳሰፈረው ተጠርጣሪዎቹ የፖለቲካ፣ የወታደራዊ ስልጠና፣ የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የድርጊት መርሃ-ግብር አስፈፃሚ ክንፎችን በማዋቀር ህገ-ወጥ አደረጃጀት ፈጥረዋል። አንከር ሚዲያ፣ ኢትዮ-ፎረም እና ኢትዮ 360 ሚዲያን ጨምሮ በውጭ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር ህዝቡን በመንግስት ላይ ለማነሳሳት የሀሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ እንደነበርም ተጠቅሷል።
ከዚህም ባሻገር ከከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ጋር በሚስጥር በመገናኘት በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግስት የፀጥታ ተቋማት እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት ሲያደርጉ በፀጥታ ኃይሎች ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። ጉዳዩ እጅግ ውስብስብ እና ሀገራዊ አንድነትን የሚያፈርስ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ፣ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢለቀቁ ምስክሮችን ሊያባብሉ ወይም ሊያስፈራሩ ይችላሉ በሚል ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

በትግራይ በዘውዱ ሀፍቱ ግድያ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው የነበሩ ግለሰቦች ከእስር መፈታታቸውን 'ይኾኖ' ማህበር አስታወቀ
በትግራይ ክልል ወጣት ዘውዱ ሀፍቱን በመግደል ወንጀል በእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ከእስር መፈታታቸውን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅት 'ይኾኖ' (Yikhono) አስታወቀ።
እንደ ማህበሩ ገለፃ፣ ሁለቱ ግለሰቦች በፈጸሙት ዘግናኝ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው የጽኑ እስራት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ገና አንድ ወር ያህል እንኳ ሳይሞላው ነው ከእስር ነፃ የወጡት።
ዕድሜዋ 32 የነበረችው ዘውዱ ሀፍቱ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በታቀደ ጥቃት በህዝብ ፊት በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ እና በመኪና በመጨፈለቋ ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።
ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ በቆየባቸው ሁለት ዓመታት ውስጥ፦
በዳኞች ላይ ይደርስ የነበረ ዛቻ እና በችሎት ውስጥ የተፈጠሩ ረብሻዎች ሂደቱን ሲያስተጓጉሉት መቆየታቸው ተገልጿል።
ፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነታቸውን በማረጋገጥ ያለ ምንም ይቅርታ (ይግባኝ) የዕድሜ ልክ እስራት ውሳኔ አሳልፎ ነበር።
ከእስር ተፈተዋል የተባሉት ተከሳሾች ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ሲሆኑ፣ ያሬድ በወቅቱ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የ22ኛ ሰራዊት አዛዥ ሆነው የሚያገለግሉት የኮሚሽነር ገብረሥላሴ በላይ ልጅ እንደሆነ ተገልጿል።
የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ቤተሰቦች እንደሚያስረዱት፣ በምርመራው እና በፍትህ ሂደቱ ወቅት የባለስልጣናት ተፅዕኖ እና ጣልቃ ገብነት እንደነበር ጠቁመዋል።
የግለሰቦቹ ከእስር መፈታት በክልሉ የፍትህ ስርዓት እና በሕግ የበላይነት ላይ ትልቅ ጥያቄ ማስነሳቱን የጠቆመው 'ይቅኖ' ማህበር፣ ውሳኔው የሴቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ #justiceforzewdu በሚሉ ሃሽታጎች ለወጣት ዘውዱ ሀፍቱ ፍትህ እንዲረጋገጥ፣ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ጣልቃ በሚገቡ ባለስልጣናት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ጥሪዎች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ።
Via ጉርሻ page

3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በፌንቴክ የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በዋስትና ላይ የሚገኙት እነ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ጉዳይ አሁን ወደ ሌላ አሳሳቢ ደረጃ ተሸጋግሯል! አርቲስቶቹ በእጃቸው ላይ ያለውን የፍርድ ቤት ሂደት ወደ ሚዲያ በማውጣታቸው ያልታሰበ አደጋ አንዣቦባቸዋል።
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሚስጥራዊ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደጠቆሙት፣ አቃቤ ህግ ይህንን የሚዲያ ላይ ቃለ-ምልልስ ተከትሎ ነገ ረቡዕ (ሐምሌ 29 ቀን) በሚኖረው ችሎት "የተሰጣቸው የዋስትና መብት ይነሳልኝ" የሚል ከባድ አቤቱታ ያቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ይህ ማለት ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ አርቲስቶቹ ዳግም ወደ እስር ቤት ሊመለሱ ይችላሉ ማለት ነው።
ነገሩ በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ቃለ-ምልልሱ ወደ አየር ከመውጣቱ አስቀድሞ፣ ተጠርጣሪዎቹ "በከፍተኛው ፍርድ ቤት የታገደብን የባንክ ሂሳብ ይለቀቅልን" የሚል ጥያቄ ለችሎቱ አቅርበው ነበር። ፍርድ ቤቱም ጥያቄውን ከተመለከተ በኋላ፣ አቃቤ ህግ በዚህ የገንዘብ መለቀቅ አቤቱታ ላይ የራሱን አስተያየት ይዞ ሐምሌ 29 ቀን ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አርቲስቶቹ የታገደባቸውን ገንዘብ አስለቅቀው በነጻነት መንቀሳቀሳቸውን ይቀጥላሉ? ወይስ የሚዲያ ላይ ቆይታቸው ዋጋ አስከፍሏቸው ዋስትናቸው ተነጥቆ ከባድ ኪሳራ ውስጥ ይገባሉ? ነገ ረቡዕ የሚሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ የጉዳዩን የመጨረሻ እልባት የሚያሳይ ይሆናል!

#እንድታውቁት
በየዓመቱ የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ለ2 ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ መሆኑ ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዝግ ሆኖ በሚቆይበት የክረምት ወራት በተረኛ ችሎት የሚያስተናግዳቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች አሳውቋል።
ፍርድ ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳመለከተው፣ አገልግሎቱ የሚሰጠው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መሠረት ነው።
ይህም መሰረታዊ የመብት ጥሰት እንዳይከሰት እና አፋጣኝ ውሳኔ ካልተሰጠባቸው ሊካስ የማይችል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመፍታት የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁ መሠረት በክረምቱ የተረኛ ችሎት የሚታዩ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዝርዝር፦
• አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች እና የልጅ ቀለብ ጥያቄዎች፣
• አካል ነጻ ለማውጣት እና እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀረቡ አቤቱታዎች፣
• የሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ አፈጻጸም ጉዳዮች፣
• ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዞች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ አስቸኳይ የማኅተም አገልግሎት ጥያቄዎች፣
• እንዲሁም ሌሎች መደበኛ የሥራ ጊዜን መጠበቅ የማይችሉ አጣዳፊ ጉዳዮች በዳኛው ውሳኔ የሚስተናገዱ ይሆናል።
በወንጀል ጉዳዮች በኩል ደግሞ የሚከተሉት ነጥቦች ተለይተዋል፦
• የዋስትና እና የአምክሮ ጥያቄዎች፣
• እስረኛ ያለባቸው የክስ መዛግብት፣
• የጊዜ ቀጠሮ ጉዳዮች (በአራዳ ምድብ ችሎት)፣
• በተሰብሮ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እና ለመሰየም የሚቀርቡ ጥያቄዎች፣
• ሌሎች ጊዜ የማይሰጡ አንገብጋቢ የወንጀል ጉዳዮች ይስተናገዳሉ።
ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ በሆነባቸው በእነዚህ ሁለት ወራት፣ ለዳኞች ተራ ወጥቶ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን፤ የፍርድ ቤቱ ማኅበረሰብም ሆነ ተገልጋዩ ለሥራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።

4 days ago
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በክረምት ተረኛ ችሎት የሚያስተናግዳቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች ይፋ አደረገ
*******************
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት፤ ከመደበኛ የፍርድ ቤት የሥራ ጊዜ ውጭ አስቸኳይ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት አሰራር ተዘርግቶ ሲሠራ ቆይቷል።
በዚሁ መሠረት መሠረታዊ የመብት ጥሰት የሚያስከትሉ በባሕሪያቸው ጊዜ የማይሰጡ እና አፋጣኝ ውሳኔ ካልተሰጠባቸው ሊካስ የማይችል ጉዳት የሚያስከትሉ አጣዳፊ ጉዳዮችን አይቶ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑበት ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ በተረኛ ችሎት አገልግሎት ይሰጣል።
በፍትሐ ብሔር በኩል በሚታዩ ጉዳዮች፡ አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች፣ የልጅ ቀለብ፣ አካል ነጻ የማውጣት አቤቱታዎች፣ እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች፣ ሠራተኞች በአሠሪዎቻቸው ላይ የሚያቀርቧቸው የደመወዝ ክፍያ አፈጻጸሞች፣ ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዝ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ አስቸኳይ የማኅተም አገልግሎት ጥያቄዎች እንዲሁም ሌሎች ጊዜ የማይሰጡ ጉዳዮች በተረኛ ችሎት ይስተናገዳሉ።
በወንጀል በኩል ደግሞ፡ የዋስትና፣ የአመክሮ፣ የአርቲዲ (እስረኛ ያላቸው የወንጀል መዛግብት)፣ በሰበር የሚቀርቡ አቤቱታዎች፣ የአራዳ ምድብ ችሎት ጊዜ ቀጠሮ፣ ለመሰየም የሚቀርብ አቤቱታ እና ሌሎች መደበኛ የሥራ ጊዜን መጠበቅ የማይችሉ አጣዳፊ የወንጀል ጉዳዮች የሚታዩ ይሆናል።
በመሆኑም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑበት በዚህ ወቅት ተገልጋዮች እና የፍርድ ቤቱ ማኅበረሰብ አሠራሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥሪ አቅርቧል።
#ethiopia #ebc #ethiopiancourts #fdrejudiciary #justiceethiopia #legalnotice

ደህንነት ነኝ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ
በአምቦ ከተማ ውስጥ ደህንነት ነኝ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ መቀጣቱ ተገልጿል ።የአምቦ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አቡሽ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ተከሳሽ ዘሪሁን ጉርሙ የሰላሳ ዓመት ግለሰብ ነው።
በከተማዋ ውስጥ በመዘዋወር " እኔ ደህንነት ነኝ " በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን አስፈታለሁ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ፈፅሟል።ተከሳሹ አንዲት የአምቦ ከተማ ነዋሪ የሆነች ግለሰብን ባለቤትሽን ከተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊት ነፃ እንዲወጣ አደርጋለሁ በማለት ከግለሰቧ ላይ 120 ሺህ ብር ሲቀበል በቁጥጥር ስር ውሏል ።
ፖሊስም በተከሳሹ ላይ አስፈላጊውን የምርመራ መዝገብ በተገቢው ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቤህግ ልኳል። አቃቤ ህግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በአታላይነት ወንጀል ክስ መስርቶበታል።ክሱን የተመለከተው የአምቦ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ዘሪሁን ጉርሙ የራሱን ማንነትና ሁኔታ በመሰወር፣ አሳሳች ነገሮችን በመናገር እና ደህንነት ነኝ በማለት በፈፀመው የማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ።
በዚህም መሰረት በሁለት ዓመት ከ9ወር እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ፣ እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር አቡሽ ማሞ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።

6 days ago
ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ ከጠዋቱ 2፡00-11፡00
👉ቀጨኔ ሰብስቴሽን፣ችሎት አደባበይ፣ ሰሜን ማዘጋጃ፣ ሸገር መናፈሻ፣ ዕንቁላል ፋብሪካ፣
👉አባዲና፣ ሩፋኤል ቤ/ክ፣ ሚኒሊክ ሆስፒታል፣ ጀርመን ድልድይ፣ እና አካባቢው፣
👉 ጋርመንት፣ በግ ተራ፣ ጎፋ ካምፕ ኮንዶሚኒየም፣ ጀርመን አደባባይ፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 2፡00 - 10፡00
👉 ሳሪስ ነጋ ቦንገር፣ ጀሶ ፋብሪካ፣ ብሔረፅጌ፣ ቆዳ ፋብሪካ ፣ ፓስታና መኮረኒ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 2፡00 - 10፡00
👉በወልዲያ ሪጅን አዳጎ፣ ውድሜን፣ ሰዋሜዳ፣ ውርጌሳ፣ጊራና እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ከጋብቻ ውጭ የወለደችውን ልጅ በወላጆቿ ግቢ ውስጥ በድብቅ የቀበረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ውስጥ ከጋብቻ ውጭ በጤና ተቋም በሰላም የተገላገለችውን ልጅ ወላጆቿ ግቢ ውስጥ በድብቅ የቀበረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጥታለች።
የጮራ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር በለጠ ጉታ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ተከሳሽ ሙሚሻ ሱልጣን የአስራ ዘጠኝ አመት ታዳጊ ወጣት መሆኗን ገልጸዋል።
ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ በሰላም ከጤና ጣቢያ ልጇን ተገላግላ ወደ ቤት ስትገባ ወላጆቿ ከጋብቻ ውጭ በመውለዷ ባደረሱባት ቁጣ ተፅዕኖ ስር ወድቃ በነጋታው አስር ሰዓት ላይ የወለደችውን ጨቅላ ወንድ ልጅ አፍና ገድላዋለች። አስክሬኑን ካርቶን ውስጥ ሸሽጋ በማቆየት ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ማንም ሳያያት ልትቀብር ስትል በአካባቢው ማህረሰብ ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች።
የአራስ ልጇን አስክሬን ወደ ደልቢ ጤና ጣቢያ በመላክ ተከሳሿ ላይ አስፈላጊውን የምርመራ መዝገብ በሰውና በሕክምና ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ተላልፏል። አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን መዝገብ ተመልክቶ በህፃን መግደል ወንጀል ክስ መስርቶባታል።
በአቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው የቡኖ በደሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሿ አስባ የፈፀመችው የወንጀል ድርጊት በመሆኑ በአስራ አምስት አመት እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን ኢንስፔክተር በለጠ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

7 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በ'ፊንቴክ' (የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ቲክቶከሩ መንሱር ጀማል፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የ800 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቀደለት።
ተጠርጣሪው በተጠረጠረበት ጉዳይ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ሁለቱም ፍርድ ቤቶች የዋስትና መብቱን ከልክለውት በማረሚያ ቤት ቆይቷል። ይሁን እንጂ መንሱር ጀማል "ዋስትና ልከለከል አይገባም፤ የህግ ስህተት ተፈጽሞብኛል" በማለት አቤቱታውን ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርቦ ነበር።
አቤቱታውን የመረመረው ሰበር ሰሚ ችሎት፣ ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ባዋለው ችሎት ግለሰቡ በ800 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ውሳኔ አሳልፏል። ከገንዘብ ዋስትናው በተጨማሪም ተጠርጣሪው ከሀገር እንዳይወጣ ፍርድ ቤቱ እግድ ጥሎበታል።
ምንም እንኳን ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን ቢፈቅድለትም፣ የዋስትና ማረጋገጫ የማስያዝና ተያያዥ ህጋዊ ሂደቶች እስካሁን ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት፣ አቶ መንሱር እስከ ቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ድረስ በማረሚያ ቤት በእስር ሊቆይ እንደሚችል የቤተሰብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) 'እግረኛው' በተሰኘው የዩቲዩብ ቻናል የተለያዩ ግለሰቦችን ቃለ ምልልስ በማድረግ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ተክለሀይማኖት አዳነ፣ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ በመልበስ አከራካሪ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ የነበረው አበባየሁ ደሜ (አለማየሁ) በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።
የፌዴራል ፖሊስ ጋዜጠኛ ተክለሀይማኖትን ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ የወንጀል ችሎት ያቀረበው ሲሆን፣ "ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨትና ፍትህን ለማዛባት በመሞከር" ወንጀል እንደጠረጠረው ለችሎቱ አስታውቋል። ፍርድ ቤቱም የፖሊስን የክስ መዝገብ ከመረመረ በኋላ፣ የቀረበለትን የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ በመቀበል ለሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በመሆኑም አቶ ተክለሀይማኖት እስከ ቀጠሮው ዕለት ድረስ በማረሚያ ቤት በእስር የሚቆይ ይሆናል።
የጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር መዋል መነሻ ምክንያት በውል ባይታወቅም፣ በቅርቡ ከ'ፊንቴክ' (Fintech) የመኪና ማጭበርበር ጉዳይ ጋር በተያያዘ ክስ ከተመሰረተባቸው አርቲስቶች ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ በሚዲያው በሁለት ክፍሎች ማሰራጨቱ ይታወሳል። በተጨማሪም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ልብስ ለብሶ ከቀረበው ግለሰብ ጋር ያደረገው አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ ለዚህ እስር መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ቢገመትም፣ ጉዳዩ ከነዚሁ ስርጭቶች ጋር ይያያዝ አይያያዝ ዘ-ሐበሻ ማረጋገጥ አልቻለም።
በተያያዘ ዜና፣ በጋዜጠኛው ሚዲያ ላይ ቃለ ምልልስ የሰጠው ግለሰብም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት አልባሳትን ያለአግባብ በመጠቀም በየማህበራዊ ሚዲያው የአንድነትና የፍቅር ሀሳብ ከማስተላለፍ ይልቅ የመከፋፈል ንግግሮችን እና አላስፈላጊ መልእክቶችን ሲያሰራጭ የነበረው አበባየሁ ደሜ በፖሊስ ተይዟል።

8 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአማራ ክልል በቀጠለው አውዳሚ ግጭት እና አለመረጋጋት መዋቅር ውስጥ ሕጻናት ላይ የሚፈጸመው ሰብዓዊ ጥቃት ወደ አሰቃቂ ምዕራፍ መሸጋገሩ ይፋ ሆነ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት፣ በግጭቱ እና በወቅታዊው ሁኔታ ውስጥ በርካታ ሕጻናት መደፈራቸውን እና የ900 ሕጻናት የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ጉዳይ በችሎት መታየቱን በይፋ አረጋግጠዋል።
ይህ ይፋዊ መግለጫ የግጭቱን አስከፊ ሰብዓዊ ዋጋ እና በተለይም አቅመ ደካማ የሆኑ ሕጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ እጅግ አሳሳቢነት ያሳያል። ይሁን እንጂ ርዕሰ መስተዳድሩ ከቀረቡት አጠቃላይ አሃዞች መካከል በግጭቱ አውድ እና በቀጥተኛ ጦርነት ተጽዕኖ ብቻ ስንት ሕጻናት የጥቃቱ ሰለባ እንደሆኑ በግልጽ አለመናገራቸው፣ ችግሩ ከተገለጸው በላይ የሰፋ እና የከፋ ሊሆን እንደሚችል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ስጋት አባብሶታል። በግጭት ቀጠናዎች ውስጥ የሚፈጸሙ የፆታዊ እና የጾታ-ተኮር ጥቃት ወንጀሎች ሪፖርት ሳይደረጉ የሚቀሩት ጉዳዮች እጅግ እልፍ መሆናቸው ይታወቃል።
በሌላ በኩል በባህር ዳር፣ በጎንደር እና በደሴ ከተሞች የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ሕጻናት ማገገሚያ የተቋቋሙ ማዕከላት በበቂ ሁኔታ መደራጀታቸውን እና ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። ቢሆንም፣ የደረሰውን ጥልቅ ማህበራዊ፣ የጤና እና የሥነ-ልቦና ጉዳት ለመቋቋም የተዘረጋው መዋቅር አሁን ባለው የሀገሪቱ እና የክልሉ አስቸጋሪ የጸጥታ ሁኔታ ውስጥ ምን ያህል አቅም አለው የሚለው ጥያቄ በብዙዎች ዘንድ ይነሳል።
በግጭት ውስጥ የሚገኙ ሕጻናትን ከእንዲህ ዓይነቱ ዘግናኝ ጥቃት መጠበቅ፣ አጥፊዎችን ለህግ ማቅረብ እና ሰለባዎችን በዘላቂነት ማቋቋም የመንግስት ቀዳሚ ኃላፊነት ቢሆንም፤ የህግ የበላይነት በተሸረሸረበት እና ተቋማት ፈተና ውስጥ በወደቁበት አካባቢ የፍትህ ሂደቱ ፍጥነት እና አጋዥነቱ ጥያቄ ውስጥ ወድቋል። ይህ ሪፖርት የግጭቱ ሰለባዎች ዋነኛ ተጠቂዎች ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን በድጋሚ ያረጋገጠ እና አፋጣኝ የመንግስትና የህብረተሰብ ጣልቃ ገብነትን የሚጠይቅ ብሔራዊ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል።

9 days ago
''አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡'' ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፳፰ ፤ ፭፡፲፭ ሰዓት
#ethiopia | ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸው ጠየም ያለ፣ አዋቂነታቸው እና ትህትናቸው ከገፃቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብስ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር ፡፡
በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድም የተሰየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም የጣሊያኖች የጦር ሹማምንት ናቸው፡፡ የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ እራስዎም ዐምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም “ካህናቱም ሆኑ የቤተ-ክህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የኢጣሊያንን መንግሥት ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን ዐመፁ? ለምን ብቻዋን አፈንጋጭ ሆኑ?” ሲል ጠየቃቸው፡፡
አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መለሱ፡፡ “አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ሐላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ” አሉ፡፡
“ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲያይ ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእክት አስተላለፉ “አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተ-ክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ ለመሥራት እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ፡፡ ነፃነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን፡፡”
ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣልያ የእጅ ሰላምታ ዓይነት እጁን እንዲያነሳ ታዘዘ ፡፡ በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ ፡፡ሐምሌ 22 ሰዓቱም 5፡15 ነበር ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር ፡፡ ታላቅ ፍርሃትም በፊቱ ላይ ይታይ ነበር፡፡
(ከታሪክ ማህደር አጠር ተደርጎ የቀረበ)
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የቀድሞው የአሜሪካ ከፍተኛ የኢንፌክሽን በሽታዎች ኤክስፐርት ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ፣ ረቡዕ ዕለት በሴኔት ሀገር ውስጥ ደኅንነት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ከኮሚቴው ሰብሳቢ ሪፐብሊካኑ ሴናተር ራንድ ፖል ጋር የከረረ ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል። ዶክተር ፋውቺ በችሎቱ ላይ የቀረቡት በሴናተር ፖል መጥሪያ አዛዥነት ሲሆን፣ ውጥረት በነገሰበት በዚህ ችሎት ላይ ማንኛውንም ጥያቄ ላለመመለስ አምስተኛውን የሕገ-መንግስት ማሻሻያ መብታቸውን እንደሚጠቀሙ ይፋ አድርገዋል።
ዶክተር ፋውቺ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ሴናተር ራንድ ፖል በቅርቡ የግል ማስታወሻ ደብተራቸውን ይፋ ማድረጋቸውን በመኮነን ጥብቅ መግለጫ ሰጥተዋል። "ሴናተር ፖል እኔን ለፍርድ ለማቅረብ ካለው ግልጽ እብደት፣ ስለ እኔ ከተናገራቸው ስም አጥፊ ንግግሮች እና እኔን ለማሳፈርና ለማስፈራራት ሲል ይፋ ካደረገው የግል ማስታወሻ ደብተሬ በመነሳት፤ እኔ ልደርስበት የምችለው አንድ መደምደሚያ ብቻ ነው። እሱ እኔን ወደዚህ ኮሚቴ የጠራበት ብቸኛ ምክንያት እስር ቤት እንድገባ የገባውን ቃል የሚያረጋግጥልኝን ማንኛውንም ቃል ከእኔ አፍ ለማውጣት ነው" ብለዋል። አክለውም በህግ አማካሪዎቻቸው ምክር መሰረት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሙሉ ምላሽ ከመስጠት እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል።
በችሎቱ ወቅት ሴናተር ራንድ ፖል እና ሌሎች ሪፐብሊካን ሴናተሮች በቻይና ውሃን ላቦራቶሪ ስለተደረገው የቫይረስ ምርምር፣ ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች እና በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስለተሰጣቸው የፕሬዝዳንታዊ ምህረት ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ቢያቀርቡም፣ ዶክተር ፋውቺ "በጠበቃዬ ምክር መሰረት በአምስተኛው ማሻሻያ መብቴ በመጠቀም ምላሽ ከመስጠት እቆጠባለሁ" የሚለውን አቋማቸውን አልቀየሩም።
በችሎቱ መሀል ድባቡ ይበልጥ የከረረው ሴናተር ራንድ ፖል የዶክተር ፋውቺን ጠበቃ "ያለ ፈቃድ ተናግረሃል" በሚል ከችሎት ክፍሉ በደኅንነት አባላት አስወጥተው እንዲባረሩ ሲያደርጉ ነው። ይህንን ተከትሎ የፋውቺ ጠበቃ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ደንበኛቸው ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን የመጠቀም ሙሉ ህጋዊ መብት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሴናተር ራንድ ፖል፣ ዶክተር ፋውቺ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ባይደን ሙሉ የፕሬዝዳንት ምህረት የተሰጣቸው በመሆኑ ይህንን የምስክርነት መብት የመቃወም መብት የላቸውም ሲሉ ሞግተዋል። ፋውቺ ጥያቄዎችን ባለመመለሳቸው ምክንያት ኮሚቴው በሚቀጥለው ሳምንት በዶክተር ፋውቺ ላይ "የኮንግረስ ንቀት" ውሳኔ ለማስተላለፍ ድምፅ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል በኮሚቴው ውስጥ የሚገኙት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት እና የኮሚቴው ከፍተኛ አባል ሴናተር ጋሪ ፒተርስ፣ ሴናተር ፖል የምርጫ እና የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም ያለፈውን ታሪክ እየቆፈሩ የምርመራ ሂደቱን ለፓርቲ ጥቅም እያዋሉት ነው ሲሉ አጥብቀው ተችተዋል።
ለሶስት ሰዓታት የቆየውን ይህንን ችሎት ያጠናቀቁት ሴናተር ራንድ ፖል "ዛሬ የፋውቺ የ40 ዓመት የቁጥጥር እና የስልጣን አጠቃቀም ማጠቃለያ ነው" ካሉ በኋላ፣ የፋውቺ ውሳኔዎች በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ሰው ሰራሽ ወረርሽኝ እንዲከሰት ምክንያት ሆነው እንደሆነ አሁንም በህሊናቸው ሊጠየቁ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሳዳም በስቅላት!
በኢራቅ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች አልተገኙም!
#ethiopia | እ.ኤ.አ. መጋቢት 20 ቀን 2003 አሜሪካ ከብሪታንያ እና ከሌሎች አጋሮቿ ጋር በመሆን በኢራቅ ላይ ድንገተኛ ወረራ ፈጸመች።
የወረራው ዋነኛ ምክንያት ሳዳም ሁሴን የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎች ባለቤት ናቸው ለዓለምም ስጋት ደቅነዋል የሚል ነበረ።
ይህንን ተከትሎ በባግዳድ ሰማይ ስር የተካሄደው ከባድ የቦምብ ድብደባ የብዙ ንጹሃንን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን መኖሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና መሠረተ ልማቶች እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል።
በርካታ ቤተሰቦች ሲፈናቀሉ፣ ሕፃናት ተቀብረዋል አገሪቱም እስከዛሬ ድረስ ወደማያበቃ መከራና ውዥንብር ውስጥ ገብታለች።
ከወራት መሸሸግ በኋላ በታህሳስ 13 ቀን 2003 ሳዳም ሁሴን በተክሪት አቅራቢያ በአሜሪካ ጦር ከተያዙ በኋላ በጥቅምት 19 ቀን 2005 በባግዳድ በከፍተኛ ጥበቃ ሥር በሚገኘው የኢራቅ ከፍተኛ ችሎት ፍርድ ቤት ቀረቡ።
በሕዳር 5 ቀን 2006 በ1982 በዱጃይል ከተፈጸመው የሰዎች ግድያ ጋር ተያይዞ በሰብአዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው በሞት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው ሲሆን፣ በታህሳስ 30 ቀን 2006 ቅጣታቸው ስቅላት ሆኗል።
ሆኖም ለወረራውና ለተከተለው የሃያ ዓመታት መከራ መነሻ የተደረጉት የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎች በኢራቅ ምድር በጭራሽ ሳይገኙ ቀርተዋል።

በርካታ አካባቢዎች መብራት ይቋረጣል‼️
የጥገና ሥራ ምክንያት ነገ በበርካታ አካባቢዎች የመብራት አቅርቦት ይቋረጣል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ሥራ ለማከናወን ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ለተወሰነ ሰዓት እንደሚቋረጥ አስታውቋል።
ከጠዋቱ 4፡00 – 10፡00
• ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ችሎት አደባባይ፣ ዘበኛ ሰፈር፣ ሾላ፣ ሰሜን ሆቴል ጫፍ፣ ቀለመወርቅ ት/ቤት፣ ዶሮ ተራ፣ ራስ ደስታ፣ አርበኞች ት/ቤት እና አካባቢያቸው።
• ዕንቁላል ፋብሪካ፣ ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን፣ ዳትሰን ሰፈር፣ ሰን ሆቴል እና አካባቢያቸው።
• 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ፣ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን፣ አትክልት ተራ፣ ጣሊያን ሰፈር፣ ፒያሳ (በከፊል)፣ ማዘጋጃ ቤት፣ አውቶብስ ተራ እና አካባቢያቸው።
• ማርቆስ መጋዘን፣ ቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞሪያ፣ ቀጨኔ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ መንገድ፣ ይመር ውኃ፣ መቀጠያ፣ 19 ታቦት ማደሪያ፣ መታፈሪ ሰፈር፣ ጴጥሮስ ሆስፒታል፣ ሽሮ ሜዳ እና አካባቢያቸው።
ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00
• አያት ለገጣፎ ሰብስቴሽን ፊትለፊት ያሉ ኮንዶሚኒየሞች፣ ክቡርደመና፣ ሰላም ቪሌጅ፣ ጣፎ ገብርኤል፣ ጋሪ ተራ፣ ባጃጅ ተራ እና አካባቢያቸው።
ከጠዋቱ 3፡00 – 10፡30
• ገላን፣ አራብሳ፣ እንጀራ ማምረቻ ፋብሪካ፣ ፕሮጀክት 13 አራብሳ ወታደር ሰፈር፣ ነጋ ቦንገር፣ ጀሶ ፋብሪካ፣ ብሔረፅጌ ቆዳ ፋብሪካ፣ ፓስታና መኮረኒ ፋብሪካ እና አካባቢያቸው።
• አባ ሳሙኤል፣ አቡሴራ፣ ሉግና፣ ዱፍና፣ ደበራ ጢኖ፣ ሻሸመኔ፣ ዱከም፣ በላይነህ ክንዴ፣ በስተቀኝ ያሉ ኢንዱስትሪዎች፣ ካፍ ማደያ እና አካባቢያቸው።
ከጠዋቱ 4፡30 – 11፡00
• መቐለ (ላቺ በከፊል)፣ ሀምዲያ ኢንዱስትሪ ዞን፣ ቀበሌ 03፣ ባህርዳር (አዲስ ዓለም)፣ ኦቪድ፣ ሰማኤታ፣ ሚሊኒየም ት/ቤት እና አካባቢያቸው።
ከጠዋቱ 1፡00 – 6፡00
• ወልዲያ፣ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቢልባላ፣ ቂርቆስ፣ ሳሬዜና፣ ሶርባ፣ ላሊበላ፣ ገነተ ማርያም፣ ዘሃ፣ ሙቅ ውኃ፣ ተከዜ ገዳሜ፣ ኢርፋ ገለሶቴ እና አካባቢያቸው።
• ቅዱስ አርቢ፣ ዳቦ ከተማ፣ ቡርኮ፣ አይና ሚካኤል፣ ጭሮ፣ ሜኤሶ፣ አሰቦት እና አካባቢያቸው።
በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ደንበኞች የጥገና ሥራው እስኪጠናቀቅ እና የኃይል አቅርቦቱ ወደ መደበኛ ሁኔታው እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጠይቋል።

የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ከጠዋቱ 4፡00 – 10፡00
👉ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ችሎት አደባባይ፣ዘበኛ ሰፈር፣ ሾላ፣ ሰሜን ሆቴል ጫፍ፣ ቀለመወርቅ ት/ቤት፣ ዶሮ ተራ፣ ራስ ደስታ አካባቢ፣ አርበኞች ት/ቤት እና አካባቢው፣
👉ዕንቁላል ፋብሪካ፣ ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፣ ዳትሰን ሰፈር፣ ሰን ሆቴልእና አካባቢው ፣
👉3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ፣ተ/ሃይማኖት ቤ/ክ፣ አትክልት ተራ፣ ጣሊያን ሰፈር፣ ፒያሳ በከፊል፣ ማዘጋጃ ቤት፣ አውቶብስ ተራ እና አካባቢው ፣
👉ማርቆስ መጋዘን ፣ ቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞሪያ፣ ቀጨኔ 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ መንገድ ፣ ይመር ውኃ ፣ መቀጠያ፣ 19 ታቦት ማደሪያ፣ መታፈሪ ሰፈር፣ ጴጥሮስ ሆስፒታል፣ ሽሮ ሜዳ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00
👉አያት ለገጣፎ ሰብስቴሽን ፊትለፊት ያሉ ኮንዶሚኒየሞች፣ ክቡርደመና፣ ሰላም ቪሌጅ፣ ጣፎ ገብርኤል፣ ጋሪ ተራ፣ ባጃጅ ተራ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 3፡00 – 10፡30
👉ገላን አካበቢ፣ አራብሳ፣ እንጀራ ማምረቻ ፋብሪካ፣ ፕሮጀክት 13 አራብሳ ወታደር ሰፈር፣ ነጋ ቦንገር ዝቅ ብሎ፣ ጀሶ ፋብሪካ፣ ብሔረፅጌ ቆዳ ፋብሪካ ፣ ፓስታና መኮረኒ እና አካባቢው፣
👉አባ ሳሙኤል፣ አቡሴራ፣ ሉግና ፣ ዱፍና፣ ደበራ ጢኖ፣ ሻሸመኔ፣ ዱከም፣በላይነህ ክንዴ፣ በስተቀኝ ያሉ ኢንዱስትሪዎች፣ ካፍ ማደያ እና አካባቢው ፣
✅ከጠዋቱ 4፡30 – 11፡00
👉መቐለ- መቐለ ላቺ በከፊል፣ ሀምዲያ ኢንዱስትሪ ዞን፣ ቀበሌ 03 ፣ ባህርዳር - አዲስ ዓለም፣ ኦቪድ፣ ሰማኤታ፣ሚሊኒየም ት/ቤት እና አካባቢው ፣
✅ከጠዋቱ 1፡00 – 6፡00
👉ወልዲያ - ይምርሃነ-ክርስቶስ፣ ቢልባላ፣ ቂርቆስ፣ ሳሬዜና፣ ሶርባ፣ ላሊይበላ ከተማ፣ ገነተማርያም፣ ዘሃ፣ ሙቅውኃ፣ ተከዜ ገዳሜ፣ ኢርፋ ገለሶቴ እና አካባቢው ፣
👉ቅዱስ አርቢ፣ ዳቦከተማ፣ ቡርኮ፣ አይና ሚኬል እና አካባቢው፣ጭሮ፣ ሜኤሶ፣ አሰቦት እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግሰት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡

10 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የ9 ዓመቷን ሜሊና ፍራቶሊንን ገድሎ አስከሬኗን ደብቋል ተብሎ የተከሰሰው ኢትዮ-ጣሊያናዊ ካናዳዊው የሉቺያኖ ፍራቶሊን የፍርድ ሂደት ማክሰኞ ዕለት ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ የሟች እናት የሆነችውን ካሊ ጋላኒስን ጨምሮ በርካታ ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል። ችሎቱ የሟች ቤተሰቦች በተገኙበት በሀዘን ድባብ ታጅቦ ውሏል።
ካሊ ጋላኒስ ስለ ልጇ ሞት በአደባባይ ስትናገር ማክሰኞ የፍርድ ቤት ውሎ የመጀመሪያዋ ነበር። ፍርድ ቤት ቀርባ ቃል ስትሰጥ፣ ከተከሳሹ ሉቺያኖ ጋር ስለነበራት የ10 ዓመታት ግንኙነት ተናግራለች። ጋላኒስ እና ሉቺያኖ እ.ኤ.አ. በ2009 በኢትዮጵያ ውስጥ እንደተገናኙ እና የርቀት ፍቅር እንደነበራቸው ገልጻለች። ሜሊና በ2016 የተወለደች ሲሆን፣ ጋላኒስ የልጇ ብቸኛ አሳዳጊ እንደነበረች መስክራለች።
ሉቺያኖ በሀምሌ 2025 ሜሊናን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ይዟት ለመሄድ ፍላጎት እንዳለው አሳውቆ እንደነበር ጋላኒስ መስክራለች። ነገር ግን፣ "ተከሳሹ ለሜሊና የነገራትን አንዳንድ አሳሳቢ ነገሮች በመስማቴ ምቾት አልተሰማኝም" ስትል ለፍርድ ቤቱ አስረድታለች። በዚህም ምክንያት የጉዞ መዳረሻቸውን ወደ ኒውዮርክ ለመቀየር መስማማታቸውን ተናግራለች። ሉቺያኖ እና ሜሊና ሀምሌ 11 ቀን 2025 ወደ ኒውዮርክ ያቀኑ ሲሆን፣ ሀምሌ 19 ከምሽቱ 12 ሰዓት ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። በዚያች ምሽት ሲዘገዩ በተደጋጋሚ ስልክ እንደደወለች እና አጭር የጽሁፍ መልእክት እንደላከች፣ እንዲሁም ልጇን ማናገር እንደምትፈልግ ስትጠይቀው "ተኝታለች" የሚል ምላሽ እንደሰጣት እናትየው በምስክርነቷ ገልጻለች።
ጋላኒስ ስለ ሁኔታው ያወቀችው በማግስቱ ሀምሌ 20 ቀን 2025፣ ሌሊት 7፡30 አካባቢ የሞንትሪያል ፖሊሶች ቤቷ መጥተው "ስለ ልጅሽ ሁኔታ የሰማሽው ነገር አለ?" ብለው እስኪጠይቋት ድረስ ምንም እንደማታውቅ ተናግራለች። ለ12 ሰዓታት ያህል ከፖሊሶች ጋር በቆይታ ጥያቄዎችን ስትመልስ ካሳለፈች በኋላ፣ በማግስቱ ቀትር ላይ የልጇ አስከሬን መገኘቱን ሲነግሯት እጅግ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባቷን አስረድታለች።
በእለቱ ከሟች እናት በተጨማሪ አራት ሌሎች ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል። መርማሪ ዲጄ ሞሸር፣ የኤሴክስ ካውንቲ አስከሬን መርማሪ ኬሊ ቫለንታይን፣ የአስከሬን ምርመራ ያደረጉት የፎረንሲክ ፓቶሎጂስት ዶ/ር ማይክል ሲኪሪካ፣ እንዲሁም ፍለጋውን የመሩት የደን ጠባቂ ሎጋን ኩዊን ይገኙበታል። ኩዊን በሰጡት ምስክርነት፣ 14 የደን ጠባቂዎች እና ከ50 በላይ የህግ አስከባሪዎች በተሳተፉበት ፍለጋ፣ አስከሬኗን ሾርት ስዊንግ ትሬይል በተባለ ስፍራ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ማክሰኞ በዋለው ችሎት በርካታ ማስረጃዎች ቀርበዋል። የመጀመሪያው ሉቺያኖ ከመርማሪ ሞሸር ጋር በነበረው የ10 ሰዓታት ቆይታ የተወሰደ የቪዲዮ ማስረጃ ነው። በቪዲዮው ላይ ሉቺያኖ ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲናገር እና ሲያለቅስ፣ እንዲሁም "የት እንዳለች አላውቅም" ሲል ታይቷል። ሁለተኛው ማስረጃ ደግሞ ሜሊና ከመጥፋቷ በፊት ሀምሌ 19 ቀን በመኪና ጀርባ ተቀምጣ ለእናቷ የላከቻት ፎቶግራፍ ሲሆን፣ ይህ ፎቶ በኋላ ላይ ልጇን ለመፈለግ በወጣው የማንቂያ መልእክት ላይ ጥቅም ላይ ውሏል። በተጨማሪም የሟች አስከሬን ፎቶዎች፣ የሞት የምስክር ወረቀት እና የአስከሬን ምርመራ ውጤቶች ለዳኞች ቀርበዋል።
የአስከሬን ምርመራውን ያደረጉት ዶ/ር ሲኪሪካ፣ ሜሊና የሞተችው ውሃ ውስጥ ሰጥማ መተንፈስ በማቃቷ መሆኑን አረጋግጠው፣ አሟሟቷም ግድያ መሆኑን የሚያሳዩ "አሳማኝ ማስረጃዎች" መገኘታቸውን ገልጸዋል። የሞተችበት ትክክለኛ ሰዓት በሪፖርቱ ላይ ባይሰፍርም፣ የመጨረሻ ምግብ ከተመገበች ከ4 እስከ 6 ሰዓታት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደተገደለች ዶክተሩ ገምተዋል። መርማሪዎች እንዳረጋገጡት ሜሊና የመጨረሻ ምግቧን የበላችው ሀምሌ 19 ቀን ከቀኑ 11፡30 ላይ በሳራቶጋ ስፕሪንግስ በሚገኝ ማክዶናልድስ ውስጥ ነበር።
ሉቺያኖ በሁለተኛ ደረጃ ግድያ እና የሰው አስከሬን በመደበቅ ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብሎ የካደ ሲሆን፣ የፍርድ ሂደቱ እስከ ሶስት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ዳኛ ታቲያና ኮፊንገር ጠቁመዋል። ችሎቱም ዛሬ ረቡዕ ጠዋት ይቀጥላል።

11 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የ9 ዓመቷን ልጁን ሜሊናን በውሃ ውስጥ አፍኖ ገድሏል በሚል የተከሰሰው ካናዳዊው የቡና ንግድ ፈጣሪ ኢትዮ ጣሊያናዊው ሉቺያን ፍራቶሊን፣ በፖሊስ ምርመራ ወቅት ልጁን ከአሜሪካ ውጭ መግደል "በጣም ቀላል ይሆን ነበር" ሲል የሰጠው ዘግናኝ ቃል በኤሴክስ ካውንቲ ፍርድ ቤት ሰኞ ዕለት በነበረው የችሎት ውሎ ላይ ተሰምቷል።
ተከሳሹ የ9 ዓመት ልጁን አግቶ እንደገደለ ቢጠረጠርም፣ መጀመሪያ ላይ "ልጄ ታፍና ተወሰደች" የሚል የውሸት ሪፖርት ለፖሊስ አቅርቦ ነበር። የኒውዮርክ ስቴት ፖሊስ መርማሪዎች ባደረጉት ምርመራ፣ የልጅቷ አስከሬን በታይኮንዴሮጋ በሚገኝ ኩሬ ውስጥ ከግንድ ስር ተደብቆ ተገኝቷል። ተከሳሹ ዜግነት ባላቸው ኢትዮጵያ ወይም ጣሊያን ውስጥ ቢሆን ኖሮ ግድያውን መፈጸም በእጅጉ ቀላል ይሆንለት እንደነበር ለፖሊስ መናገሩም በችሎት ተገልጿል።
የ46 ዓመቱ ተከሳሽ ሉቺያን ፍራቶሊን፣ ሀምሌ 19፣ 2025 (እ.ኤ.አ.) ልጁ ሜሊና እንደታፈነች ሪፖርት ካደረገ በኋላ በማግስቱ በፖሊስ የሰዓታት ምርመራ ሲደረግበት ነበር። የኒውዮርክ ስቴት ፖሊስ መርማሪ ዳንኤል ማውሮ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ ተከሳሹ ልጁ ስለመታፈኗ የሚያወራው ታሪክ እየተምታታበት ሲመጣ፣ የገዛ ልጁን ለመግደል የሚያበቃ ምክንያት እንዳለው ተጠይቆ ነበር። ተከሳሹም ምንም ዓይነት ስሜት በማያሳይ ሁኔታ፣ ይህንን ወንጀል በአሜሪካ ውስጥ እንደማያደርገውና ነገር ግን ድርብ ዜግነት ባለው ሀገራት (በኢትዮጵያ ወይም በጣሊያን) ቢሆን ኖሮ "በጣም ቀላል ይሆን ነበር" ሲል መመለሱን መርማሪው ለችሎቱ አብራርተዋል።
በካናዳ ሞንትሪያል ከተማ 'ጋምቤላ ኮፊ' የተሰኘ የቡና ኩባንያ መስርቶ የነበረውና አሁን ላይ በከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ኢትዮ ጣሊያናዊው ተከሳሹ፣ የፖሊስን ትኩረት ለማሳት በማሰብ ጥፋቱን ወደ ቀድሞ ሚስቱ እና የልጅቷ እናት ወደሆነችው ካሊ ጋላኒስ ለማዞር ሞክሯል።
እናቲቱ የስነ-ልቦና እክል (schizophrenia) እንዳለባትና በ9 ዓመቷ ልጃቸው ላይ ጥቃት ታደርስ እንደነበር በምርመራው ወቅት ተናግሯል። ልጁ ታፍናለች የሚለውን የፈጠራ ታሪክ እውነት ለማስመሰልም፣ "ይህን እገታ ያቀነባበረችው እሷ ከሆነች፣ እኔን መጥፎ ሰው አድርጋ ለማሳየት ብላ ነው" ሲል በድምጽ በተቀረጸው የምርመራ መዝገብ ላይ ተደምጧል።
ዐቃብያነ ህግ እንዳስረዱት ፍራቶሊን ልጁ የአእምሮ ህመም እንዳለባት በማሰብ ህይወቷን ለማጥፋት ከ2025 መጀመሪያ አንስቶ ሲያቅድ ነበር። በሌክ ጆርጅ ጉዞ ላይ እያሉም በውሃ አፍኖ ከገደላት በኋላ "ታፍናለች" የሚል የውሸት ሪፖርት አቅርቧል።
መርማሪ ዴቪድ ሞሸር እንደመሰከሩት፣ ፖሊሶች የሞባይል ስልኩን እና የመኪና ሰሌዳውን የጉዞ መስመር በቴክኖሎጂ እንደሚመረምሩ ሲነግሩት ተከሳሹ በከፍተኛ ሁኔታ መደናገጡን አሳይቷል። በወቅቱ በነበረው የመኪና ውስጥ ቆይታም፣ ተከሳሹ በድንጋጤ እጆቹን እና ሰውነቱን ከመኪናው በር ጋር ሲያጋጭ እንደነበር በድምጽ ማስረጃ ቀርቧል። ከጥቂት ሰዓታት በኋላም፣ የሜሊና አስከሬን በኩሬ ውስጥ ተደብቆ የተገኘ ሲሆን፤ የሞት መንስኤዋም በውሃ ውስጥ በመታፈን መሆኑ ተረጋግጧል።
ሉቺያን ፍራቶሊን በሁለተኛ ደረጃ ግድያ እና የሰው አስከሬን በመደበቅ ወንጀሎች የተከሰሰ ሲሆን፣ በሁሉም ክሶች ላይ "ጥፋተኛ አይደለሁም" ሲል ክዷል። የተከሳሹ ጠበቃ ብራያን ፒላትዝኬ የዐቃቤ ህግን ማስረጃ "ደካማ ነው" በማለት ደንበኛቸው ያቀረበውን የ"እገታ" ታሪክ እንደሚደግፉ ተናግረዋል። ተከሳሹ በሁለተኛ ደረጃ ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቀዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከ'ፊንቴክ' ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው፣ ታስረው በዋስ የተለቀቁት እነ ሰራዊት ፍቅሬ ጉዳያቸውን ከእስር ቤት ውጪ ሆነው እየተከታተሉ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ ከሰሞኑ ክሳቸውን በተመለከተ በሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ የፊንቴክ ተበዳዮች በተለያዩ መንገዶች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በተጨማሪም ይህ የሰጡት መግለጫ "ትልቅ ስህተት ነው" ሲሉ ከአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው የሕግ ባለሙያዎች አቋማቸውን አንጸባርቀዋል። ለመሆኑ እነ ሰራዊት ፍቅሬ በፍርድ ቤት የተያዘን ጉዳይ በሚዲያ ላይ ወጥተው ማብራሪያ መስጠት ይችላሉ ወይ? የሕግ ባለሙያዎቹ የኢትዮጵያን ሕግ መሠረት በማድረግ ጉዳዩን በዝርዝር ተንትነውታል።
የመጀመሪያው ጉዳይ ንጹህ ሆኖ የመገመት እና ሐሳብን የመግለጽ መብት ነው። የኢትዮጵያ ሕግ ከዓለም አቀፍ የሕግ መርሆች ጋር ተመሣሣይ የሆነ አቋም ሲኖረው፣ የሕጉ መሠረታዊ ዓላማ የግለሰብን መብት ማስጠበቅ እና የፍርድ ቤቶችን ነጻነት ማረጋገጥ ነው። በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ በግልጽ እንደሰፈረው፣ ማንኛውም የተከሰሰ ሰው ጥፋተኛነቱ በሕግ መሠረት በፍርድ ቤት እስኪረጋገጥ ድረስ ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት አለው። በተጨማሪም በአንቀጽ 29 ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ሕገ-መንግሥቱ ያረጋግጣል። በመሆኑም አንድ ተከሳሽ ይህንን መብቱን ተጠቅሞ ለቀረበበት ክስ "ንጹህ ነኝ" ብሎ መናገሩ የዚሁ መብት አካል ስለሆነ በሕግ አያስጠይቅም። ነገር ግን ይህ መብት በፍርድ ቤቶች ሥራ ጣልቃ እስካልገባ ድረስ ብቻ የሚያገለግል ነው።
ሁለተኛው እና ዋነኛው ነጥብ በፍርድ ቤቶች ሥራ ጣልቃ አለመግባት ነው። በ2004 ዓ.ም. በወጣው የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ፣ የፍርድ ቤቶችን ነጻነት እና የፍትሕ አሰጣጥ ሂደትን መጠበቅ ላይ ጥብቅ ክልከላዎች አሉ። ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ወይም በክርክር ላይ እያለ፣ ተከሳሹ በሚዲያ ወጥቶ የክሱን ዝርዝር በመተንተን ሕዝባዊ ጫና ለመፍጠር ከሞከረ፣ ምስክሮችን ካሸማቀቀ፣ ወይም ማስረጃዎችን በሚዲያ ለማቅረብ ከሞከረ የፍትሕ ሂደቱን እንዳስተጓጎለ ተቆጥሮ በወንጀል ይጠየቃል።
እንዲሁም ተከሳሾቹ በሚሰጡት መግለጫ ውስጥ የዳኞችን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት፣ ፍርድ ቤቱን የሚያንኳስስ፣ ወይም የፍርድ አቅጣጫን ለማስያዝ የሚሞክር ሐሳብ ከተንጸባረቀ የፍርድ ቤትን ክብር በመንካት (Contempt of Court) ወንጀል ሊከሰሱ ይችላሉ።
በሌላ በኩል የሕግ ባለሙያዎቹ የሚዲያዎችን ሕጋዊ ኃላፊነት በተመለከተም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ መሠረትም ቢሆን፣ የፍርድ ቤትን ነጻነት ሊጋፋ የሚችልን ጉዳይ ሚዲያዎች ማስተናገድ አይፈቀድላቸውም። አንድ ሚዲያ በፍርድ ቤት የተያዘን ጉዳይ የራሱን "የሚዲያ ችሎት" በመክፈት የተከሳሹን ማስረጃዎች ቢመረምርና ቢያስተላልፍ ሕጋዊ ተጠያቂነትን ያስከትልበታል።
በኢትዮጵያ ሕግ አንድ ግለሰብ ክስ ከቀረበበት በኋላ በሚዲያም ሆነ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች "በተከሰስኩበት ጉዳይ ንጹህ ነኝ፤ እውነቱ በፍርድ ቤት ይረጋገጣል" የሚል አጠቃላይ መግለጫ መስጠቱ መብቱ ነው። ነገር ግን ከዚህ ባለፈ የክሱን ዝርዝር መተንተን፣ ማስረጃን ማቅረብ፣ እንዲሁም በዐቃቤ ሕግ፣ በምስክሮች ወይም በዳኞች ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥር የሚችል ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠት የፍርድ ሂደትን በማስተጓጎል ወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር ነው።

Comments