3 days ago
በትግራይ በዘውዱ ሀፍቱ ግድያ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው የነበሩ ግለሰቦች ከእስር መፈታታቸውን 'ይኾኖ' ማህበር አስታወቀ
በትግራይ ክልል ወጣት ዘውዱ ሀፍቱን በመግደል ወንጀል በእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ከእስር መፈታታቸውን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅት 'ይኾኖ' (Yikhono) አስታወቀ።
እንደ ማህበሩ ገለፃ፣ ሁለቱ ግለሰቦች በፈጸሙት ዘግናኝ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው የጽኑ እስራት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ገና አንድ ወር ያህል እንኳ ሳይሞላው ነው ከእስር ነፃ የወጡት።
ዕድሜዋ 32 የነበረችው ዘውዱ ሀፍቱ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በታቀደ ጥቃት በህዝብ ፊት በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ እና በመኪና በመጨፈለቋ ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።
ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ በቆየባቸው ሁለት ዓመታት ውስጥ፦
በዳኞች ላይ ይደርስ የነበረ ዛቻ እና በችሎት ውስጥ የተፈጠሩ ረብሻዎች ሂደቱን ሲያስተጓጉሉት መቆየታቸው ተገልጿል።
ፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነታቸውን በማረጋገጥ ያለ ምንም ይቅርታ (ይግባኝ) የዕድሜ ልክ እስራት ውሳኔ አሳልፎ ነበር።
ከእስር ተፈተዋል የተባሉት ተከሳሾች ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ሲሆኑ፣ ያሬድ በወቅቱ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የ22ኛ ሰራዊት አዛዥ ሆነው የሚያገለግሉት የኮሚሽነር ገብረሥላሴ በላይ ልጅ እንደሆነ ተገልጿል።
የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ቤተሰቦች እንደሚያስረዱት፣ በምርመራው እና በፍትህ ሂደቱ ወቅት የባለስልጣናት ተፅዕኖ እና ጣልቃ ገብነት እንደነበር ጠቁመዋል።
የግለሰቦቹ ከእስር መፈታት በክልሉ የፍትህ ስርዓት እና በሕግ የበላይነት ላይ ትልቅ ጥያቄ ማስነሳቱን የጠቆመው 'ይቅኖ' ማህበር፣ ውሳኔው የሴቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ #justiceforzewdu በሚሉ ሃሽታጎች ለወጣት ዘውዱ ሀፍቱ ፍትህ እንዲረጋገጥ፣ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ጣልቃ በሚገቡ ባለስልጣናት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ጥሪዎች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ።
Via ጉርሻ page

Comments