(ዘ-ሐበሻ ዜና) 'እግረኛው' በተሰኘው የዩቲዩብ ቻናል የተለያዩ ግለሰቦችን ቃለ ምልልስ በማድረግ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ተክለሀይማኖት አዳነ፣ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ በመልበስ አከራካሪ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ የነበረው አበባየሁ ደሜ (አለማየሁ) በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።
የፌዴራል ፖሊስ ጋዜጠኛ ተክለሀይማኖትን ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ የወንጀል ችሎት ያቀረበው ሲሆን፣ "ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨትና ፍትህን ለማዛባት በመሞከር" ወንጀል እንደጠረጠረው ለችሎቱ አስታውቋል። ፍርድ ቤቱም የፖሊስን የክስ መዝገብ ከመረመረ በኋላ፣ የቀረበለትን የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ በመቀበል ለሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በመሆኑም አቶ ተክለሀይማኖት እስከ ቀጠሮው ዕለት ድረስ በማረሚያ ቤት በእስር የሚቆይ ይሆናል።
የጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር መዋል መነሻ ምክንያት በውል ባይታወቅም፣ በቅርቡ ከ'ፊንቴክ' (Fintech) የመኪና ማጭበርበር ጉዳይ ጋር በተያያዘ ክስ ከተመሰረተባቸው አርቲስቶች ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ በሚዲያው በሁለት ክፍሎች ማሰራጨቱ ይታወሳል። በተጨማሪም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ልብስ ለብሶ ከቀረበው ግለሰብ ጋር ያደረገው አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ ለዚህ እስር መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ቢገመትም፣ ጉዳዩ ከነዚሁ ስርጭቶች ጋር ይያያዝ አይያያዝ ዘ-ሐበሻ ማረጋገጥ አልቻለም።
በተያያዘ ዜና፣ በጋዜጠኛው ሚዲያ ላይ ቃለ ምልልስ የሰጠው ግለሰብም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት አልባሳትን ያለአግባብ በመጠቀም በየማህበራዊ ሚዲያው የአንድነትና የፍቅር ሀሳብ ከማስተላለፍ ይልቅ የመከፋፈል ንግግሮችን እና አላስፈላጊ መልእክቶችን ሲያሰራጭ የነበረው አበባየሁ ደሜ በፖሊስ ተይዟል።

2 months ago