ደህንነት ነኝ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ
በአምቦ ከተማ ውስጥ ደህንነት ነኝ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ መቀጣቱ ተገልጿል ።የአምቦ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አቡሽ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ተከሳሽ ዘሪሁን ጉርሙ የሰላሳ ዓመት ግለሰብ ነው።
በከተማዋ ውስጥ በመዘዋወር " እኔ ደህንነት ነኝ " በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን አስፈታለሁ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ፈፅሟል።ተከሳሹ አንዲት የአምቦ ከተማ ነዋሪ የሆነች ግለሰብን ባለቤትሽን ከተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊት ነፃ እንዲወጣ አደርጋለሁ በማለት ከግለሰቧ ላይ 120 ሺህ ብር ሲቀበል በቁጥጥር ስር ውሏል ።
ፖሊስም በተከሳሹ ላይ አስፈላጊውን የምርመራ መዝገብ በተገቢው ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቤህግ ልኳል። አቃቤ ህግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በአታላይነት ወንጀል ክስ መስርቶበታል።ክሱን የተመለከተው የአምቦ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ዘሪሁን ጉርሙ የራሱን ማንነትና ሁኔታ በመሰወር፣ አሳሳች ነገሮችን በመናገር እና ደህንነት ነኝ በማለት በፈፀመው የማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ።
በዚህም መሰረት በሁለት ዓመት ከ9ወር እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ፣ እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር አቡሽ ማሞ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።
Seledadotio

1 day ago