(ዘ-ሐበሻ ዜና) በ'ፊንቴክ' (የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ቲክቶከሩ መንሱር ጀማል፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የ800 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቀደለት።
ተጠርጣሪው በተጠረጠረበት ጉዳይ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ሁለቱም ፍርድ ቤቶች የዋስትና መብቱን ከልክለውት በማረሚያ ቤት ቆይቷል። ይሁን እንጂ መንሱር ጀማል "ዋስትና ልከለከል አይገባም፤ የህግ ስህተት ተፈጽሞብኛል" በማለት አቤቱታውን ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርቦ ነበር።
አቤቱታውን የመረመረው ሰበር ሰሚ ችሎት፣ ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ባዋለው ችሎት ግለሰቡ በ800 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ውሳኔ አሳልፏል። ከገንዘብ ዋስትናው በተጨማሪም ተጠርጣሪው ከሀገር እንዳይወጣ ፍርድ ቤቱ እግድ ጥሎበታል።
ምንም እንኳን ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን ቢፈቅድለትም፣ የዋስትና ማረጋገጫ የማስያዝና ተያያዥ ህጋዊ ሂደቶች እስካሁን ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት፣ አቶ መንሱር እስከ ቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ድረስ በማረሚያ ቤት በእስር ሊቆይ እንደሚችል የቤተሰብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል።

8 days ago