2 days ago
መዝሙረ ሄላም ላይ የተደረገ አጭር ኂሳዊ ንባብ
ከቢኒያም አቡራ
#ethiopia | አዳም ረታ ታሪክን ከነገሥታት፣ ከመሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ባበጀው ድልድል ውስጥ ‹ላዕላይ› ከሚባሉት ደረጃዎች አንጻር አያስመለክተንም። ታሪካዊ ከሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተዘነጉትን ጥቃቅን የታሪክ ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ይመርጣል። ይወስዳል መንገድ ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ፍንዳታውን ከሚሞት ዘመድ፣ ከሚደነግጥ ለማኝ፣ ከሚሰነጠቅ የወፍ እንቁላል፣ ከሚፈስ የእናት ወተት ጋር Micro-Macro Connection በመፍጠር የትልቁ ቀዳዳ መፈጠርን ከሚጢጢዬ ሽንቁሮች ጋር ያስተሳስርልናል። እንዲህ ያሉ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕሪያትን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጻሕፍቱ ውስጥ በተለያየ መጠን እናገኛለን።
Adam Reta አዳም ረታ "መዝሙረ ሄላም" በተሰኘው በዐዲሱ መጽሐፉ ላይም በኢትዮጵያ ታሪካዊ-ፖለቲካዊ አጋጣሚ ውስጥ እንደ ዐውራ የሚታዩትን የእድገት በኅብረት ዘመቻን እንደነ-አሮን፣ እንደነቃል … ባሉ ገጸባሕርያት በኩል፣ የሰባ ሰባቱን ድርቅ በሄላም ጡት በኩል፣ “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ” እየተባለ ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጋር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በሡልጣን በኩል፣ የከተማ መሬት ዐዋጅን በተለያዩ ግለሰቦች በኩል … እናያለን። በዚህም የታሪክን ትልቅ ካርታ ለመረዳት የተረሱና የጠለሉ ታሪኮችን ይመረምራል። ስለዚህ ነቁጣዊ ማኅበራዊ ክስተቶችን ወደ ታሪክ ምኩራብ በማምጣት ከትልቁ የታሪክ ምሥል ጎን ያስተያያል። ይህ ደግሞ የኒው ሂስቶሪሲዝም ኹነኛ ማጠንጠኛ ነው።
ልክ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ባለው “የመንግሥቱ ጊዜ” በሚለው ድርሰት ውስጥ፣ ትልቁን “የታኅሣሥ ግርግር”ን እንደ መቼት አምጥቶ የተጻፈውና የተተኮረው ግን ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ላይ ነው። ስለግርማሜ ንዋይ፣ ስለኮሌኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሰለጄነራል ሙልጌታ ቡሊ አይደለም የሚያትተው። ስለአንድ ብላቴና ከእንቅልፍ መነሳት፣ ስለገበጣ ጨዋታ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕፃናትን አሰብስቦ ‹ኪራላይሶን› የሚያስብል ካሕን፣ ስለመንደር ውስጥ ሐሜቶች፣ ስለግለሰቦች ፍርሃት፣ በአጋጣሚ ስላየው አስደናቂ አሞራ … ያወጋል። የታሪክ አጋጣሚ አምጥቶ በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች ላይ ስለሚረብበው የታሪክ መንፈስ ያትታል። ልክ እንደዚሁ መዝሙረ ሄላም ላይም ጽሑፉ ታሪክን አያብራራም፤ ነገር ግን ታሪክ እንዴት በሰው ልብ ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል። በዚህ ኹነተ-ደቂቅ (micro-event) ምክንያት በዘመኑ ላይ ያገነገነውን ባሕላዊ እምነትን፣ የሥልጣን መዋቅርን፣ የወል ግንዛቤን አጨንቁረን እንድንመለከት ያስችለናል።
ከመንግሥት ሼልፍ ላይ ሳይኾን ከግለሰብ ጀርባ ላይ የተወሰደው የአዳም የአጻጻፍ መንገድ ከኒው ሂስቶሪስዝም ጽንሰ-ሐሳቦች ጋር በአንድ መም ላይ የሚሄዱ ናቸው። መዝሙረ ሄላም የተሰኘው ዐዲሱ የአዳም ረታ መጽሐፍ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕርያትን ይጋራል። አንዳንድ ነገሮችን በዓይን መመልከት ባይቻልም በግብሩ (ቁስ ላይ በሚያደርገው ግፊት) ግን ይታወቃል። በመዝሙረ ሄላም መጽሐፍ ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን በቀጥታ ማየት ባንችልም ቅሉ እነርሱን የሚያሳይልንን ነገሮች ግን እንቃኛለን። ዘማች ወጣት ተማሪዎችን እናያለን፤ መንግሥትን፣ ሕግንና ኃይልን ግን በቀጥታ አንመለከትም። የተማከለ ኃይል አናይም ግን የገጸባሕርያቱ የፍርሃት ምንጭ ከተማከለ ኃይል ጋር የተያያዘ ቀጭን መስመር መኖሩን እናያለን። መንግሥትም ቢኾን በቀጥታ አይገባም፤ ነገር ግን ፍርሃት እንደ ሥርዓት ዘዋሪ (system driver) ይኾናል። እንደ ሚሸል ፉኮ አገላለጽ ኃይል ከተማከለ ሥርዓት የሚመነጭ ሳይኾን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በፍርሃት፣ በልማድ፣ በንግግር … ሊከሰት የሚችል ሂደት አይደል?
መዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ “circulation of social energy” ቀርቧል። መዝሙረ ሄላም ላይ መረጃ ከመንግሥት አይመጣም፤ ከግለሰብ እንጂ። የከተማ መሬት ዐዋጅም ኾነ የተማሪዎች ዘመቻ በገጸባሕርያቱ ወሬ ውስጥ ነው የሚንቀረቀበው። ይህ የመረጃ ሥርዓት ኃይል ማን እንዳለው ማን እንደሌለው ያሳያል። እንግዲህ ይህ በፉኮኛ micro-power መኾኑ ነው። በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ ወሬ እንጂ እንደ ሰነድ አይቀርብም።
ወሬ የፍርሃት ቤንዚን ነው … ፍርሃት ደግሞ በዝምታ መሸበብን ይፈጥራል … የዝምታ አፈ-ሙቅ ደግሞ ኃይለኛው እንዳይታይ ያደርጋል … የተደራጀው ኃይል ጥፋትን ሊያደርስ ባሰበ ቁጥር የወሬ ቤንዚን ይጨምራል። ሰዎች በዕቅብተ-ንግግር ራሳቸውን ሲሸብቡ ደርዝ ያለው ሙግት ይኮሰምናል፣ ንግግር ሲጠፋ ያልታወቀ አደጋ ይከሰታል፣ ፍርሃትም ይጨምራል። ያልታወቀ አደጋ ደግሞ ከታወቀ አካል ይመጣል። ስለዚህ ጥንስሱ የሚጀምረው ከወሬ እንደኾነ ያስመለክተናል። አዳም በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክን እንደ “circulation of social energy” ሲያቀርብ ፕሬዝዳንት፣ ጀነራል፣ ፕሮፌሰር የኾኑ ታሪክ ከላዕላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች አያስፈልጉትም። በአንጻሩ ሄላም ለማን እንደሳመችው ተደርጎ ብርሃኔ ያስወራው ወሬ፣ የሄላም አባት ወታደር በመኾኑ ምክንያት በካሱ፣ በሄኖክ እናት የተነዛው ወሬ እና ሄላም ከሄኖክ ጋር የተቆራረጠችበት መንገድ እንዲሁም የሄላምን የጡት ወተት በተመለከተ የተነዛው ወሬን ይጠቀማል።
መዝሙረ ሄላምን ከድኅረ-ቅኝ-አገዛዝ የኂስ መንገድ አንጻር እንመልከተው።
እውን ቅኝ-ግዛት ተረት ኾኖ ቀርቷል? በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነልቦና ረገድ የቅኝ አገዛዝ ዳናው ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል? አዳም በመዝሙረ ሄላም ጽሑፍ ውስጥ ከቅኝ-ግዛት በተወረሰ መዋቅር ምክንያት የተሰናከለን ሕይወት ሊያስመለክተን ይኾን?
“ከተሞች ከቅኝ ግዛት በኋላ ሁለት ዓይነት መልክ ይኖራቸዋል፤ ለጥቂቱ የተድላ፣ ለተቀረው ደግሞ የአሳር መንደር ይኾናሉ” ይላል ፍራንዝ ፋኖን። በመዝሙረ ሄላም ላይ እና “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት” የተሰኘው ድርሰት ላይም ይህንን ነው የምንመለከተው። “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ጽሑፎች መካከል “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላ ሞት” አንዱ ነው። የቢሾፍቱ ልጆች ሆቴሉን ያዩታል፤ ግን አይገቡበትም። ሆቴሉ የሀገራቸው መሬት ላይ ነው፤ እነርሱ ግን ከሆቴሉ ውጭ ናቸው። መናፈሻው ውስጥ አንዲት የፈረንጅ ልጅ ጠግባ ለልጆቹ እንደ ውሻ ዳቦ ትወረውርላቸዋለች። አፈር ላይ የወደቀን ዳቦ አራግፈው ይመገባሉ። በገዛ ሐይቃቸው ዳር ላይ ናቸው፤ ሌሎች ግን በጀልባ እየተንሸራሸሩ ይንፈላሰሳሉ። ለፈረንጆቹ ያደረው ሞገስ የላንድሮቨር ተፈናጣጭ ኾኗል። ሌሎቹ ግን ከመኪናው ውጪ ናቸው። ሞገስ እንደ እነርሱ ሕጻን ቢኾንም ለፈረንጅ በማሸርገዱ የትምህርት ቤቱ ባለቤት ሲመስል ሌሎች ልጆች ግን በገዛ መምህራቸው ይብጠለጠላሉ። የቢሾፍቱ ልጆች፣ ነጻ በተባለች ሀገር እየኖሩ በቅኝ ግዛት ጥላ ይተዳደራሉ። የቢሾፍቱ ልጆች በገዛ መንደራቸው አካሉ በማይታይ የቅኝ ግዛት እጅ ይገፋሉ። ሞገስ አይናገርም፤ የሚናገርለት አለ። ልክ የቢሾፍቱ ልጆች ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንደምናገኘው ሁሉ “የስንብት ቀለማት” ላይም በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንመለከታለን። እንደ ዘድሬክ፣ ሳተርን፣ ከተስፋዬ ወደ አሸናፊ የተቀየሩ የድሎት ምሥሎች እና የእነምትክ ጉልት፣ የእትየ እልልታ የጉርሻ መሸጫ መስኮት ያሉ የእጦት ሥዕል እናገኛለን። መዝሙረ ሄላም ላይም እንዲህ ያለ በአንድ ከተማ ላይ የሁለት ምሥሎች አደባባይ እጀግ ብዙ ቦታ ይገኛል።
በሌላኛው የድኅረ-ቅኝ-ግዛት ኂስ (postcolonial criticism) መዝሙረ ሄላምን ስንመለከት መጀመሪያ ላይ “ፈረንጅ ሲያደንቀኝና ሲገረምብኝ የሰሙ የአገሬ ደነዞች በየተራ “ካላስ የኔ ጎሳ ናት” … እያሉ መሻማት ጀመሩ ትላለች - ሄላም። በኋላ ደግሞ በተነዛባት አጓጉል ወሬ … የሄላምን ጡት ንቀው፣ አንጓጥጠው፣ አባረዋት ሲያበቁ የፈረንጅ የዱቄት ወተትን ይመርጣሉ። ይህ በባሕላዊ ማንነትና በዘመናዊነት መካከል የሚዋልል ማኅበረሰብን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የድኅረ-ቅኝ-ግዛት አካል ነው። በሌሎቹ የአዳም ሥራዎች ውስጥ ድኅረ-ቅኝ-ግዛት አተያይ በቋንቋና በኪነ-ጥበብ ምርጫ ውስጥ እንዴት እንደሚንፀባረቅ ያሳያል። በመዝሙረ ሄላም ላይ ደግሞ ምዕራባዊው ዓለም ለአገር በቀል መፍትኼ-ሥራይ የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ መኾኑንና የኢኮኖሚ ብዝበዛው አሁንም በረቂቅ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል። እዚህ ላይ ሥዕለማርያም የተባለችዋን ገጸባሕርይ እና በውጭ ሀገራት የተነዙ ወሬዎችን ስንጨማምር ደግሞ የበለጠ ብዙ ለማለት ያስችላል።
መዝሙረ ሄላም ላይ እጅግ ብዙ ማኅበረሰባዊ ኂስ እናገኛለን። ለአብነት ያህል አንድ ሁለቱን እንቃኝ።
“መዝሙረ ሄላም” ላይ ማኅበረሰቡ በችላ-ባይነት አልያም በኾን ተብሎነት ልጆቹን ምን ያህል ተጠቂ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መልክ ተንጸባርቆበታል ማለት ይቻላል። ጋሽ ክብካብና ዘመናይ ኾን ብለው ቴዲና ሄላም ላይ የሚያደርሱትን፣ ተክለማርያም የወላጁን(የዘሪቱን) ችላ-ባይነት ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ማኅበረሰቡ ልጆችን “የነገ ተስፋዎች” ይላል፤ ነገር ግን ዛሬያቸው ላይ አይሠራም።
ማኅበረሰብ የመማጸኛ ከተማዎችን ወደ ተጨማሪ ግፍ መሥሪያ ቦታዎች እንደሚቀይር በአዳም መጻሕፍት ላይ በብዛት እንመለከታለን። “ይወስዳል መንገድ …” ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ማርታ ለደበበ በምትሰጠው ፍቅር ሳቢያ የሚሠራበትን ግፍ የምታስረሳ ብትኾንም ማኅበረሰቡ ግን ተጨማሪ ግፍ የሚሠራበት መሣሪያ ኾናለች። የስንብት ቀለማት ላይ ምኒልክ ከዚያ ሁሉ እስርና እንግልት በኋላ፣ “በፊያሜታ አርፋለሁ” ብሎ ቤቷ ሲሄድ ተጨማሪ ሕመም በጆሮው በኩል ጭንቅላቱ ላይ ይሻጥበታል። መዝሙረ ሄላም ላይም፣ ሄላም “ሙዚቃዬን ከሕዝብ ጆሮ ያደርስልኛል … ያሳርፈኛል …” ብላ የተመካችበት ምናሴ እንጦሮጦስ ይጨምራታል። ማኅበረሰባችን የመስቀል ተ ሠላጢን ግብር እንዳለው፣ ከላይ አሳልሞ ከታች በአንካሴው ጉድጓድ እንደሚምስ ያሳያል። ይህም የመልእክትን ወጭት ሰብሮ የወጣ ጥበባዊ አጻጻፍ ነው። በፈጣጣው የቀረበ የትችት ኮሶ አይደለም። ድንቅ ነው!
መዝሙረ ሄላም ላይ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸባሕርያት የተወሰኑት (አሮን፣ ቃል፣ ምናሴ፣ ሄላም) ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ።
auto-fiction ዓይነት አጻጻፍ ባለው የአሮን አተራረክ ውስጥ አሮን “system observer” መኾኑን እንገነዘባለን። ሥርዓቱን ያያል፣ ዘማቹን ያስተውላል፣ ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ችግሩን ይመለከታል፣ ይጽፋል። አሮን የተገፋ ታሪክ ድምፅ ነው፤ ንቃት አለው፣ ግን የታሪክ ሂደትን የሚቀይር ኃይል የለውም፤ ስለዚህም ያ ሁሉ የጻፈውን ጽሑፍን ያጣል። የንቃት ችግር የለበትም፤ የማኅበራዊ ንቃት ድምፅነቱን ከዘመነ አባት ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ ተመልክተናል። ግን ደግሞ ይህ ብቻውን የቆመ ነጠላ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማኅበራዊ ተሳትፎ የለበትም። ቃል የተሰኘችው ገጸባሕርይም እንደ አሮን ናት፤ ንቃት ያላት፣ system observer ናት። ማኅበራዊ ንቃት ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ካላገዘው ግንጥል ጌጥ ነው። ቃልና አሮን ንቃት አላቸው፤ ግን ንቃታቸውን ተግባር አላገዘውም፤ ንቃቱን የሚተገብር አደረጃጀት የላቸውም። ስለዚህ ዕጣ-ፈንታቸው ውድቀት ይኾናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ይህን የድግግሞሽ አዙሪት መዝሙረ ሄላም ላይ ደራሲ አዳም ረታ በሰላ ብዕር አስቀምጧል።
የደራሲና የአርታኢ ትስስር በተንጸባረቀበት በሄላም አተራረክ ውስጥ ምናሴ የተሰኘ ገጸባሕርይ እናገኛለን። ምናሴ የ-false collective consciousness ትእምርት ነው። ምናሴዎች ለሥልጣን ይሠራሉ፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ ያስባሉ፤ ነገር ግን የሥርዓቱ የመጠቀሚያ መሣሪያ (system functionary) ናቸው። ምናሴዎች የኦልቪቴዎች ጥይት ናቸው። ምናሴዎች የሔላምዎች ስኬት ሳይኾን የገዛ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ምናሴ በሌላ መነጽር ብናየው የመንግሥት ቢሮክራት የመካከለኛው መደብ ውክል ነው። ሀገሩ ከንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊ ሥርዓት ቢቀየርም፤ ከወታደራዊ ሥርዓት ወደ ሌላ ሥርዓት ቢለወጥም ምናሴያውያን ግን አይቀየሩም። ሥርዓት ይቀየራል - ምናሴያውያን አይቀየሩም፣ ትእዛዝ ይፈጽማሉ፣ ይከድራሉ። ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካል-ታሪክ ውስጥ የተደጋገመ፣ ግን ደግሞ ያልተስተዋለ እውነት ነው።
ሄላም የወታደር ልጅ ናት፤ እንዲያሳድጋት በአደራ የተሰጠው ቤተሰብ የሚበድላት። የሷ ዓይነት ዕጣ ከደረሰው እንደ ወንድሟ ከምታየው ቴዲ ከሚባል ልጅ ጋር ታድጋለች። መጀመሪያ የሚልዮን፣ የኋላ ኋላ የምናሴ ፍቅረኛ የምትኾን ድምፀ-መረዋ ሴት ናት። ሁሉ ነገሯን ባጣችበት ወቅት ጡቷ ተአምር ያመርታል።
በመዝሙረ ሄላም ላይ የሄላም የጡት ወተት የአንዳች ነገር ውክል ይመስለኛል። ሻዕቢያ ለታጋይ ወጣቶች ማሳደጊያ ፈልጓት ሊሰርቃት መፈለጉ በቀላሉ የሚዘለል ነገር ነው? ወተት እና ጡት በመጀመሪያ እይታ የሕፃናት ትዝታ፣ የእናትነት ምሥል፣ የእምነት እና የጾታ መነሳሳት የተዋሃዱበትም አይደል? ወተት ሕይወት ነው? የመጀመሪያ ምግብ፣ ከእናት ወደ ልጅ የሚፈስም አይደል? በክርስቲያናዊ ምልክት ንጹሕነትን አይወክልም? ወተት ከ“ቅዱስ” ወደ “ሥጋዊ” የሚያስተላልፍ ድልድይ ነው ማለት እንችል ይኾን? የሄላምን ጡት የጠባ ታማሚ ልጅ እንዴት ጤናማ ሊኾን ቻለ? የምን ትእምርት ነው? ሄላም ከብዙ ወንድ ጋር የወጣች እንደመኾኗ ለዚህ ሰናይ ግብር ለምን የሷ ጡት ተመረጠ?
ሌላው፣ መዝሙረ ሄላም ላይ ኦልቬቲን እናገኛታለን። ኦልቬቲ የግራጫ ቃጭልዋ። መዝገቡ ንፋስ መውጫ ሳለ፣ ባልንጀራው ኤልያስ የብልግና ሀሁ ሊያስተምረው እፊቱ ያቆማት ቀይ ሰሌዳ ነበረች ኦልቬቲ። መዝሙረ ሄላም ላይ ምናሴን እና ቤተሰቡን የምታሾር ዐውራ ገጸባሕርይ ኾና ትከሰታለች። መዝሙረ ሄላም እና ግራጫ ቃጭሎች በጋለሞታይቱ በኦልቬቲ ብቻ ሳይኾን በዘመነ እንድርያስ እና በመዝገቡ ዱባለም ይገናኛሉ። ነጋ ዳቦ ጋጋሪውም በ-typological space መዝሙረ ሄላም ላይ እናገኘዋለን።
መዝሙረ ሄላምን ከህላዌነት (Existentialism) አንጻር እንመልከተው። ሄላም ትርጉም በማይሰጥ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደምትኖር እናነባለን። የሀገሯ ዳር ድንበር እንዳይነካ አባት ብታዋጣም አሳዳጊዎቿ ግን የወላጅን ፍቅር አዋጥተው አይለግሷትም። ወርቅ አበድራ ጠጠር ትነፈጋለች። ዕቃ ለማገዝ ቤቷ ድረስ ለመጣው ሚልዮን ልቧን ትሰጣለች። ሀና የሸነቆረችውን ክፍተት ለሞላችበት ውለታዋ ክፍያ ይኾን ዘንድ ሚልዮን ለሄላም የወለፈንዴ ቡጢ ያሳርፍባታል። ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት ባስ ውስጥ ካገኘችው ሄኖክ ጋር ብትሞክርም የበለጠ የሕይወት ትርጉም ይዛባባታል። የወታደር ልጅ መኾኗ ሄላምነቷን በዜሮ ያባዘዋል። የመጨረሻው ስንብትም ከሄኖክ ጓደኛ አፎት በሚወጣ ሰይፍ መቀላት ይኾናል። ከሄኖክ ጓደኛ ጀርባ የሚውለበለበው ባንዲራ ደግሞ የሄኖክ ሸሚዝ መኾኑ ደግሞ ቁስሉን እንደ አቡሰዲቅ ያደርገዋል። ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ያለውን የሙዚቃ ሥራዋን፣ “ትርጉም ወዳለው
ነገር ይቀይርልኛል” ብላ በምትተማመንበት በምናሴ ትነጠቃለች። ተአምር በሚያስብለው በጡት ወተት ምክንያት ለሕይወቷ ትርጉም ለመስጠት ትታትራለች። የጡት ወተቷን ምርምር በማድረግ ለትልቅ ዓለምአቀፍ በጎ ተፅዕኖ ታደርጋለች ተብላ የተቆጠረችው ሥዕለማርያም የዓለም አቀፍ መሳለቂያና ትችት ምንጭ ትኾንባታለች። ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው ድግግሞሽ ነው። ይህ ደግሞ በሳርተር የተገለጸውን “existence without essence”-ን ያሳያል።
የህላዌነት መሠረታዊ ሐሳብ ነጻነት ነው፤ ግን ነጻነት ፍርሃትን ይወልዳል። ሄላም ለአሮን ፍቅሯን መናገር ትችላለች፤ ነገር ግን ዝምታን መርጣለች። የግራጫው መዝገቡ፣ የእንጀራ እናቱ የምታደርስበትን በደል እንደሚያውቀው ሁሉ ሄላምም ክብካብና ዘበናይ የሚያደርሱባትን አድሎ ታውቃለች፤ ግን ለረዥም ጊዜ ዝም ብላለች። ሄላም፣ ሙዚቃዋን ካጣች በኋላ ወደ ባንዱ ሄዳ መጋፈጥ ትችላለች፤ ነገር ግን አትሄድም … ይህ በሳርተርኛ bad faith ነው።
የሄላም ምርጫ ዝምታ ኾነ እንጂ ደካማ ናት ማለት አይደለም። “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል ዝምታ ነው ያላት። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዝምታዋ፣ የለመደችውን ግፍ ከማታውቀው ዐዲስ ግፍ የመምረጥ ኹኔታ ነው። ዐዳዲስ ግፎችን ለመሸሽ በዝምታ አላዋቂነት ዛጎል ውስጥ የመደበቅ ብቃት ነው። የለመደችውን ግፍ የመከላከል አቅም ስላላት ባለመደችው ግፍ እንዳያጠፏት ሠግታ በውስጣዊ ንቃተ ሕሊና የዘየደችው ብልሃት ሊኾን ይችላል። ዝምታዋ የመቆየቷ ምሥጢር ነው። ደበበ ቀዝቃዛ ገለልተኛ ነኝ የሚለው ሰው ለመኖር ሲል ሳይታወቀው ስሜቱን የሚቆጣጠርበት መንገድን ለማስታወስ ነው።
“የስንብት ቀለማት” ገጸባሕርይ የኾነው ዮሴፍም ብዙ ነገር ያውቃል፤ ግን ዝም ይላል … ፊያሜታ ቂል መስሏት ትዘባርቃለች … እሱ ግን “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል የዝምታ መልስ ይመልስላታል። እሷ ግን ዝምታው አይገባትም። የ“ቀዳዳ”ው ደበበ እና “የስንብት …” ዮሴፍ ቀዳዳውን አይሞሉትም፤ እያዩት ይኖራሉ። ዶነሮች ጥሩ ፈንድ ሲለቁ ፊያሜታ ፕሮጀክቱን ለአሳምነው ትሰጠውና ዮሴፍን “ምን ዶነሮች እኮ ጠፉ ትለዋለች” … ዝም ይላል፤ ይታዘባል።
ቃል መሣሪያ ነበር፤ በዘመነ ደበበ፣ በዘመነ ዮሴፍ፣ በዘመነ ሄላም እና በዘመነ መዝገቡ ዱባለ ግን ቃል አደገኛ ኾኗል፤ ዝምታ ኹነኛ መጠጊያ ነው … ይህ ከደርግ በኋላ የተፈጠረ “traumatized literary silence” ማሳያ ነው። ስለኾነም ተራኪዎቹ (ደበበ፣ መዝገቡ፣ ዮሴፍ እና ሄላም) ለምን ዝም አሉ ሳይኾን "ዝምታን የሚያመነጭ ሥርዓት ምን ይኾን?" ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። ግለሰብ ዝም ሲል፤ ሕዝብ በጸጥታ ይዋጣል፤ የዚያኔ የተማከለው ኃይል አፍ ያወጣል።
የአዳምን ዐዲሱን መጽሐፍ "በንባብ ይለቅ" ብለን መርቀናል።
ቢኒያም አቡራ
ሐምሌ 25 / 2018 ዓ.ም

3 days ago
ፋሻ ላውንጅ ሀዋሳ
– የመዝናኛዎ አዲሱ መዳረሻ!
ሀዋሳን በልዩ መንገድ ለመዝናናት ይፈልጋሉ?
ፋሻ ላውንጅ ሀዋሳ ለከተማው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ከየትኛውም ስፍራ ለሚመጡ እንግዶች የተለየ የመዝናኛ ልምድ ያቀርባል።
🌴 ነፋሻማና ዘመናዊ አካባቢ
🎧 በምርጥ ዲጄዎች የተሞላ አስደሳች ሙዚቃ
🍽️ ጣፋጭ ምግቦችና የተለያዩ መጠጦች
🤝 ፈጣንና ሙያዊ አገልግሎት
✨ ለወዳጅ ስብሰባ፣ ለቤተሰብ መዝናኛ እና ለልዩ ዝግጅቶች ተስማሚ
ደማቅ ቀንም ሆነ አስደሳች ምሽት በሀዋሳ ማሳለፍ ከፈለጉ፣ ፋሻ ላውንጅ የመጀመሪያ ምርጫዎ ነው።
አድራሻ: ሀዋሳ 05፣ ከጉዱማሌ ፊት ለፊት
ስልክ +251-916-860330
ፋሻ ላውንጅ ሀዋሳ
ይምጡ... ይዝናኑ... የማይረሳ ትዝታ ይዘው ይመለሱ!

4 days ago
“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

ብዕሩም እንደ አንደበቱ የሰላ ነው
#ethiopia | የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በተለየ የጽሁፍ ዘይቤአቸው እና ጥልቅ በሆነ ሃሳባቸው ይታወቃሉ።
ከጻፏቸው መጻሕፍት መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አድናቆት ያገኙት እና ከፍተኛ ተነባቢ ከሚባሉት መካከል እነዚህ ተጠቃሽ ናቸው።
በፈረንጆቹ 2020 ላይ ተፅፎ ለንባብ የበቃው A promised Land ወይም የተስፋይቱ ምድር የተሰኘው መፅሐፋቸው እጅግ ተነባቢ ከሆኑት መካከል ይጠቀሳል።
ይህ መጽሐፍ የአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ትዝታዎች የመጀመሪያ ክፍል ሲሆን የኦባማ በጣም ታዋቂው እና በስፋት የተነበበው ሥራ ነው።
መፅሐፉ ከለጋ የፖለቲካ ህይወቱ ጀምሮ በ2008 የነበረውን ታሪካዊ የምርጫ ድል እና የመጀመሪያውን የስልጣን ዘመን እስከ ኦሳማ ቢን ላደን መገደል ይተርካል።
በተጨማሪም ከዋና ዋና ታሪካዊ ውሳኔዎች ጀርባ የነበረውን ውስጣዊ ስሜት የፖለቲካ ውጥረቶች እና የስልጣን ፈተናዎችን ግልጽ በሆነ መንገድ ያቀርባል።
ሌላው ኦባማ ወደ ፖለቲካው ዓለም ከመግባታቸው በፊት የጻፉት እና የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ግላዊ ታሪካቸው የሆነው መፅፍ ደግሞ "Dreams from my Father"ይሰኛል።
መፅሐፉ በዋናነት ማንነትን ፍለጋ ስለ ዘር ሐረጋቸው እና ስለ አባታቸው ታሪክ ለመረዳት ያደረጉትን ጉዞ ያብራራል።
ስሜት ቀስቃሽ እና ፍልስፍናዊ በሆነ የጽሁፍ ውበት የተዋቀረ በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ ከምርጥ ግላዊ ታሪክ መጻሕፍት መካከል ተመራጭ አድርጎታል።
ሶስተኛው የኦባማ ተመራጭ መፅሐፍ
The Audacity of Hope ይሰኛል።
ይህ መጽሐፋቸው የአሜሪካ ፖለቲካዊ ክፍፍል እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል የፖለቲካ እሴቶች እና ለወደፊት አሜሪካ ያለውን ተስፋና ራዕይ ያቀርባል።
የኦባማን የፖለቲካ ፍልስፍና እና የኋለኛውን የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው መሪ ሃሳብ በጥሩ ሁኔታ የሚያሳይ መፅሐፍ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #barackobama #apromisedland #theaudacityofhope #dreamsfrommyfather

ከባንኮክ እስከ ፉኬትና ፓታያ ( በወፍ በረር ... )
* ታይላንድ በዓይኔ ያየኋት፣ በእጄ የነካኋት፣ በልቤ የቀረች የባሕር ነፍስ…!
በገብረማርያም ይርጋ [ የጉዞ ማስታወሻ ]
#ethiopia | እውነተኛ ጉዞ የሚጀምረው ሰው ከራሱ ጋር ሲገናኝ ነው። እውነተኛ ጉዞ አውሮፕላኑ ሲያርፍ አያበቃም፤ ትዝታ በልብ ውስጥ ሲቀጥል እንጂ።
ዓለም አቀፍ የባህልና ጥበባት ልማት ሙያዊ ሽልማቴን ለመቀበል ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያዋ እንቁ — ታይላንድ — ስጓዝ፣ አእምሮዬን የሞላው የጉዞው ዓላማ ብቻ ነበር።
ነገር ግን እግሬ የታይላንድን ምድር ሲረግጥ የተቀበለኝ የከተማዋ የሲሚንቶና የአስፋልት ግለት ወይም የዘመናዊነት ጫጫታ አልነበረም፤ ከሩቅ የባሕር ጥልቀት እየነፈሰ በፊቴ ላይ እንደ አሮጌ ወዳጅ ቀስ ብሎ የተራመደው ቀዝቃዛ የባሕር ነፋስ እንጂ።
ደቡባዊቷ እንቁ — ፉኬትና የፓታያ ሞገዶች
በውሃው ላይ የተበተኑት ባህላዊ የረጅም ጅራት (Long-tail) ጀልባዎች፣ የፀሐይ ወርቃማ ብርሃን በውሃው ላይ ሲያርፍ የሚፈጥረው ብልጭታ፣ የሰማዩና የባሕሩ አድማስ ላይ መገናኘት… እነዚህ ሁሉ ተደምረው እንደ ተአምራዊ ሕልም ይታዩ ነበር። በዚያ ቅጽበት እኔ ባሕሩን አልተመለከትኩትም፤ ባሕሩ እኔን በጥልቀቱ እየተመለከተኝ ነበር።
በጄትስኪ (Jet Ski) አየርና ውሃውን ሰንጥቄ ስነጥቅ፣ የነጭ አረፋ መስመር ከኋላዬ እንደ ግጥም ይሰመር ነበር። በወቅቱ የተረዳሁት ነገር ቢኖር—ፍጥነት ሰውን ከምድር አያርቀውም፤ ይልቁንም በውስጡ የተሸሸገውን እውነተኛ ደስታ ቅርብ ያደርገዋል!
የሰማይ ላይ በረራ (Parasailing)፦ገመዱ ተለቆ ሰማይ ሲከፈትልኝ፣ ከላይ ሆኜ ስመለከት ባሕሩ እንደ ታላቅ ሰማያዊ መስታወት ተንጣሎ ታየኝ።
በዚያ ከፍታ ላይ ዓለም ትንሽ ስትሆን፣ ሰውን የሚያስጨንቀው የዕለት ተዕለት ጭነቷም አብሮ ትንሽ ይሆናል። እንደ ልጅ ሆኜ የነፋሱን ሹክሹክታ ብቻ እሰማ ነበር… ወጣሁ፣ ተነጠቅሁ!
በፉኬት ነጭ አሸዋው በእግር ስር ሲለሰልስ፣ ግልጽና ሰማያዊው ውሃ እስከ ጉልበት ሲደርስ፣ ፀሐይ በቆዳ ላይ ወርቃማ ሙቀቷን ስትረጭ ዓለምና ጭንቋ ሙሉ በሙሉ የተረሱ ይመስላሉ።
የባንኮክ ድቅቅ ያለ ውበትና የሌሊት ከዋክብት
ባንኮክ በቀን በገዥና ሻጭ፣ በበዛ እንቅስቃሴና ህይወት ስትደምቅ፤ ሌሊት ደግሞ በምድር ላይ እንደወረዱ ከዋክብት የሚያበሩ መብራቶች ያሏት አስማተኛ ከተማ ትሆናለች። የከተማዋ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች መብራት በውሃው ላይ ሲሰበር፣ ወርቅና አልማዝ በውሃ ላይ የተበተነ ይመስላል።
በቻኦ ፕራያ (Chao Phraya) ወንዝ ላይ ያለ ምሽት
ከጉዞዬ ሁሉ በላይ በልቤ የተቀረፀው በመርከብ ላይ ያሳለፍኩት ምሽት ነው።
የምስራቃዊው የሙዚቃ ዜማ፣ የሰዎች ወዳጃዊ ሳቅ፣ ጣፋጭ እራት…
በወንዙ ላይ እያለፈች ባለው መርከብ ላይ ሆነን በከተማዋ መብራቶች መካከል ስንሳፈፍ፣ በአንድ ቅጽበት ውስጥ ዓለም በሙሉ የተሰበሰበች ያህል ተሰማኝ።
በዚያ ምሽት አንድ ታላቅ እውነት ተረዳሁ—ደስታ ታላቅና ውስብስብ ነገር አይፈልግም፤ በሙሉ ልብ የሚኖር አንድ ቅጽበት ብቻ ይበቃዋል።
በሻንጣ ያልተያዘ፣ በልብ የተያዘ ሀብት
ታይላንድ ከዚህ በኋላ ከእኔ አትጠፋም፤ በውስጤ ዘላለማዊ ቦታዋን ይዛለች። የፓታያ ነፋስ አሁንም በፊቴ ላይ ይነፍሳል፣ የፉኬት ሞገድ በልቤ ይመታል፣ የባንኮክ የሌሊት መብራት በዓይኔ ላይ ይበራል።
ከዚህ ጉዞ ስመለስ በሻንጣዬ ውስጥ ያሸግኩት ያበደሩኝን ልብስ ብቻ አይደለም፤
የሞገዱን ዘላለማዊ ድምፅ፣ ...
የፀሐይዋን አፍቃሪ ሙቀት፣ ...
የአሸዋውን ልስላሴ፣ ...
የሌሊት መብራቶቿን ብሩህነት፣ ...
እና ...
የልቤን ሙሉ ደስታ ነው።
እውነተኛ ጉዞ አውሮፕላኑ ሲያርፍ አይጨርስም፤ ትዝታው በልባችን ውስጥ መኖር ሲቀጥል እንጂ!
ታይላንድ በዓይኔ ያየኋት፣ በእጄ የነካኋት፣ በልቤ የቀረች የባሕር ነፍስ…!
6 days ago
ነገ ሁለቱ ተጓዦች ይመጣሉ!”
ለጥበብ እና ለጉዞ ወዳጆች -ታላቅ የምስራች!
በዓመታዊው የንባብ ለሕይወት የመጻሕፍት አውደርዕይ ላይ፣ መድረኩን ለየት ባለ ጥበባዊ ድምቀት ሊያነዝሩት የተዘጋጁ ሁለት ታላላቅ ስሞች በአንድ መድረክ ይከሰታሉ!
የሀገራችንን ውበት በቃላትና በምስል እየቀመረ የጉዞን ጥበብ ያስተማረን ሄኖክ ስዩም...ከአንደበተ ርቱዑ እና ተወዳጁ የይዘት አዘጋጅ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) ጋር በመሆን “ንባብና ቱሪዝም”ን በጥበብ መነጽር ያሳዩናል።እነዚህ ሁለቱ ተጓዦች ነገ ምን ይዘውልን ይከሰቱ ይሆን?በንባብ ዓለም ውስጥ የሚደረግ ረጅም ጉዞ፣የኢትዮጵያን ውበት በጥበብ የመቃኘት ጥልቅ እይታ፣የአእምሮ ስንቅ እና የማይረሱ ውብ ትዝታዎች!ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018፣ የዕውቀት እና የጥበብ ማዕድ ተካፋይ ለመሆን ቀጠሮዎን ከእኛ ጋር ያድርጉ። ይህ ድንቅ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ!
ቦታው ኤግዚቢሽን ማዕከል
ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018

Sponsored by
Surafel
7 days ago
የፒያሳ ትዝታዎችን በዲጂታል ጥበብ ያስመለሰው “Echoes of Piassa” ኤግዚቢሽን በፈንዲቃ ተከፈተ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ታሪካዊ የከተማ ማዕከል የሆነችውን ፒያሳን ትዝታ፣ ታሪክና የባህል ውበት በዘመናዊ የዲጂታል ጥበብ መልክ ያቀረበው “Echoes of Piassa” የተሰኘ የጥበብ ኤግዚቢሽን በሃያት ሬጀንሲ በሚገኘው ፈንዲቃ የሥነ-ጥበብ ጋለሪ በይፋ ተከፍቷል።
ኤግዚቢሽኑ በአርቲስት ዳዊት ክፍሌ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የቀድሞዋን ፒያሳ የንግድ፣ የማህበራዊ ኑሮ፣ የሕንፃ ቅርስና የሰዎች ትዝታ በዲጂታል ምስሎች እና በዘመናዊ የጥበብ ቋንቋ ለተመልካቾች አቅርቧል።
ፒያሳ፤ ከሕንፃዎች በላይ የሕዝብ ትውስታ
በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ የፈንዲቃ ጋለሪ መስራች መላኩ እንደገለጹት፣ የአንድ ከተማ ባህል በሕንፃዎች ብቻ የሚለካ አይደለም።
“የሕንፃዎች መፍረስ የባሕል ሞት አይደለም፤ ባሕል የሚኖረው በሕዝቡ ልብ ውስጥ ነው”
በማለት ጥበብ ታሪክን ለመጠበቅ ያለውን ሚና አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፒያሳ በኢትዮጵያ የከተማ ታሪክ ውስጥ ልዩ ስፍራ ያላት ሲሆን፣ የንግድ፣ የሙዚቃ፣ የስነ-ጥበብና የማህበራዊ ትስስር ማዕከል በመሆን ለብዙ ትውልዶች የማይረሳ ትዝታ ጥላለች።
ዲጂታል ጥበብ የተረሱ ታሪኮችን እንደገና ማስታወሻ
“Echoes of Piassa” የተለመደ የሥዕል አቀራረብ ብቻ ሳይሆን፣ የታሪክ ቅርሶችን ከቴክኖሎጂ ጋር ያጣመረ የጥበብ ሙከራ ነው።
የዲጂታል ጥበብ በመጠቀም ያለፉ የከተማ ገጽታዎችን፣ የሰዎችን የግል ትዝታዎችና የአካባቢውን ማንነት ለአዲሱ ትውልድ ማቅረብ የኤግዚቢሽኑ ዋና ዓላማ ነው።
የጥበብ ትብብር
ኤግዚቢሽኑ በኃይሉ ክፍሌ እና ዮሴፍ ሰቦቅሳ አሰናጅነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሃያት ሬጀንሲ እና የፈንዲቃ ቡድን አባላት ለዝግጅቱ ድጋፍ አድርገዋል።
የፈንዲቃ ጋለሪ የኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን ሥራዎች ለማስተዋወቅ የሚሰራ ማዕከል ሲሆን፣ በቀንም ሆነ በሌሊት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ጥበብ፣ ትውስታና የከተማ ማንነት
“Echoes of Piassa” የሚያስተላልፈው መልዕክት አንድ ከተማ በመንገዶቿና በሕንፃዎቿ ብቻ እንዳልተገነባች፣ በሰዎቿ ትዝታ፣ በባህሏና በጥበቧ እንደምትኖር ነው።
ይህ ኤግዚቢሽን ያለፈውን የፒያሳ ዘመን ከዛሬው የዲጂታል ዓለም ጋር በማገናኘት ታሪክን ለነገው ትውልድ ለማስተላለፍ የተደረገ የጥበብ ምስክርነት ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

8 days ago
በየመንገዱ ቆመው ብዙዎቻችንን ያቀራረቡ፣ ወረፋ እስኪደርሰን ትዕግስትን ያለማመዱን፣ የሳንቲም ድምፅ እየሰማን የተነጋገርንባቸው #የሕዝብ_ስልኮች 🤩
🙋♂️🙋♀️ በእነዚህ የሕዝብ ስልኮች የተጠቀማችሁ
✍️ ከትዝታዎቻችሁ የማትረሱትን አጋሩን
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

''ልክ እንደቆዳው ባህሪውንም ቀየረው''
#ethiopia | የታዋቂው ድምጻዊ ማይክል ጃክሰን የቅርብ ወዳጅ የሆነው ኮሜዲያን እና ተዋናይ ክሪስ ታከር ስለ ማይክል ልዩ ባህሪ የሚያስታውሰውን ገጠመኝ ወደኋላ በትዝታ ሄዶ ያወሳል።
ማይክል ሰዎች በእጁ የሚገኙ ውድ ቁሳቁሶችን ሲያደንቁለት በስጦታ የመስጠት ልምድ ነበረው ታድያ ይሄን ነገር አጅሬ በቅርብ ርቀት ሲከታተል ቆይቷል፤ ክሪስ ታከር ከዕለታት በአንዱ ቀን የማይክል የክት መኪና ሮልስ ሮይን አደነቀለት ሆኖም የሆነው የተጠበቀው አልነበረም።
ማይክል መኪናውን በስጦታ ከመስጠት ይልቅ ለታከር “አንተ በጣም ቀልደኛ ነህ፤ ሄደህ የራስህን ግዛ” የሚል ምላሽ ሰጥቶ ሙሽሽ አደረገው።
በ “You Rock My World” የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ አብረው ከሠሩ በኋላ የጠበቀ ወዳጅነት የመሰረቱት ሁለቱ አርቲስቶች በመካከላቸው የነበረው ግንኙነት ፍቅርና መከባበር የተሞላበት ነበር።
ክሪስ ታከር ማይክልን ሁልጊዜም በትሕትናውና በሰው አክባሪነቱ የሚያስታውሰው ሲሆን የ''ሮልስ ሮይስ'' መኪናው ነገር ግን አሁንም እንደሚከነክነው አልሸሸገም።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

9 days ago
በሆነ በዘመን የቀረውን እኔን የመለሰ አልበም!
የአህመድ ተሸመ (ዲንቢ) “ጊዜ አይሄድም”!
ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕሮፌሰር)
#ethiopia | መቸም የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ድንቅ የዜማ ደራሲነት ሰብዕና ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ ለራሱ የሠራቸውን ዘግየት እናድርግና ለሌሎች የሙያ አጋሮቹ ሠርቶላቸው በብዙኋን አድማጮች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነትን ያገኙትን የዜማ ድርሰቶቹን እንዘርዝር ብንል ጊዜም ሥፍራም አይበቃንም፡፡
እንደው ከግምታችን በላይ ስለሆነው ስለዲንቢ የላቀ የዜማ ደራሲነት ሰብዕና መሠረታዊ ግንዛቤ ሊያስጨብጠን ቢችል ግን ጥቂቱን ብቻ ከዚህ እንደሚከተለው እዘረዝርላችኋለሁ፡—
ለአሊ ቢራና ሄለን በርሄ - “ሲያዴ”፤ ለፀሀዬ ዮሐንስ - “ማን ልበልሽ”፤ ለማዲንጎ አፈወርቅ - “ላላተርፍ”፤ ለብዙአየሁ ደምሴ - “የህልሜ ንግስት”፤ ለዘቢባ ግርማ - “ገራገር”፤ ለኢሳያስ ታምራት - “እያዳነ ያማል”፤ ለታረቀኝ ሙሉ - “ስሚያቸው”፤ ለሚኪያስ ቸርነት - “ግርማ ሞገሴ”፤ ለሃይማኖት ግርማ - “ከዚራ ቁ-2”፤ ለግርማ ተፈራ - “ልዩ”፤ ለሀመልማል አባተ - “ሀሴት”፤ እና የመሳሰሉቱን የአህመድ ዲንቢን የዜማ ፈጠራዎች ከብዙ በጥቂቱ ማስታወስ ይቻላል፡፡
አንዳንድ ሙዚቃዎች ለጆሮ ብቻ አይሰሩም፤ ለስሜት ይደርሳሉ፤ ዛሬ ተሰርተው ግን ትዝታችንን ይመልሱልናል፡፡
አንዳንድ ዜማዎች፣ በውስጣችን የተከረቸሙ የጊዜ በሮችን ያንኳኳሉ፤ ይከፍታሉምም፡፡ በሮቹ ሲከፈቱ ደግሞ የተዘነጉ ፊቶች፣ የተለየናቸው ጓደኞች፣ የተራመድንባቸውን ጎዳናዎች… ብቻ ምኑ ቅጡ ትላንታችንን እንደ መጽሀፍ ይገልጡልናል፡፡ በሆነ ዘመን የቀረውን ማንነታችንን እንደገና ይመልሱልናል።
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ከ14 ዓመታት በኋላ በአዲስ አልበሙ ሲመለስ፣ እኔ የሰማሁት የአዳዲስ ዜማዎች ስብስብን አይደለም። አንድ በሆነ ዘመን የነበረ የዜማ ሰዋሰውና በዚሁ ዜማ ምክንያት የተሰፋ፣ የምናፍቀውን ዘመን የመለሰልኝ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡
ያ የኔ ዘመን የምለው “ዘጠናዎቹ”ን ነው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆኜ የገባሁት በ1997 ዓ.ም. ነው። አይ፣ ተማሪነት! እንዴት ያለ ጣፋጭ፣ እንዴት ያለ የማይደገም ዘመን ነበር! ያ ዘመን ለእኔ የወጣትነት ወርቃማ ጠዋት ነበር። ዓለምን እንደ አዲስ ማየት የጀመርኩበት፤ ከተማዋን፣ ሕይወትን፣ ፍቅርን፣ ሐሳብንና ነፃነትን ለመጀመሪያ ጊዜ በሙሉ ልብ ያጣጣምኩበት ዘመን ነበር።
ያ ዘመን ከጓደኞቸ ጋር እንደፈለግን የኖርንበት ዘመን ነበር። በአደባባይ የተከራከርንበት፣ አለምን የጠየቅንበት፣ መንግሥትን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃወምንበት፣ ነፃነትን ያየንበት፣ ዜማን ያጣጣምንበት ወቅት ነበር። ያ ዘመን “ዘጠናዎቹ” ነበር፡፡
ያንን ዘመን ሁሌም እናፍቀዋለሁ፤ ምናልባትም የምናፍቀው ዘመኑን ራሱን አይደለም፤ በዚያ ዘመን ውስጥ የነበርነውን እሱን፣ እሷን፣እኔን፣እኛን ነው። እንደገና እንዲመጣም እመኛለሁ።
ማርሴል ፕሩስት የተባለ ፈረንሳያዊ የልብ ወለድ ጸሀፊና ሀያሲ ጥልቅ የሆነን ትዝታ አስበን ለማስታወስ በምናደርገው ጥረት አይመለስም፤ ነገር ግን የስሜት ሕዋሳችን በሚነካ አንድ ድንገተኛ ልምድ ሊቀሰቀስ ይችላል ይላል፡፡ ሙዚቃም ከእነዚህ የትዝታ ቀስቃሾች መካከል እጅግ ኃይለኛው ሳይሆን አይቀርም።
በዚህ ረገድ እንደ አህመድ ተሾመ ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራ ዜማ የተረሳ ግን ተደበቀ ስሜትን ይቀሰቅሳል፤ የጠፋ የሚመስለውን የዜማ ስልተ ምት ይመልሳል፤ በዘመን ጥላ ሥር ተደብቆ የኖረ ማንነት እንደገና ያነቃቃል።
በ1990ዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የራሱ የሆነ የዜማ ሰዋሰው፣ ቀለምና የአወራረድ ለዛ ነበረው። ያ ዘመን ለእኔ ሙዚቃን ከመስማት ወደ ማዳመጥ የተሸጋገርኩበት ጊዜ ነው። ስለዚህ የዚያ ዘመን ዜማዎች በጆሮዬ ብቻ ተደምጠው አልቀሩም፤ በማንነቴ ውስጥ ህያው ናቸው።
እኔ የሙዚቃ ባለሙያ አይደለሁም፤ ሙዚቃን ግን በልቤ አዳምጠዋለሁ። በእኔ የዜማ አረዳድ፣ የዚያ ዘመን የዜማ አሠራሮች በቀላሉ የሚደገሙ አይደሉም። ምክንያቱም ዜማው የተፈጠረው በድምፅ ብቻ ሳይሆን፣ በዘመኑ መንፈስም ጭምር ነው። ከዚያ በኋላ የመጡት ዘመናት የራሳቸውን የሙዚቃ ቋንቋ ፈጥረዋል።
ያው ዘመን ሲለወጥ የዜማ ሰዋሰውም የሚለወጥ ይመስለኛል፡፡ ይህም የሥነ ጥበብ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው፤ ዋናው ጉዳይ ግን በ1990ዎቹና ከዚያ በኋላ በመጡት ዜማዎች መካከል የተቋረጠ ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ መቆራረጡ ለሙዚቃ ባለሙያዎች ትልቅ የጥናት ርዕስ የሚሆንም ነው፡፡
ታዲያ የአህመድ ተሾመ አዲስ አልበም፣ የ1990ዎቹን የዜማ መንፈስ አገኘሁበት፤ የቀድሞውን በቀጥታ ሳይደግም፣ ያንን ለዛ በአዲስ ስልተ ምት የቀነበበ ዜማ ሆኖ አዳመጥኩት። ጉዳዩን ሳይንቲፊካሊ መግለጽ ባልችልም ልቤ ግን አልበሙ በዚያን ጊዜና በዛሬው የሙዚቃ ዘመን መካከል የተዘረጋ የዜማ ድልድይ እንደሆነ ይነግረኛል።
በአጠቃላይ ለእኔ፣ የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ጊዜ አይሄድም አዲስ አልበም የአዳዲስ ዜማዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ካለፈ ጊዜና ትዝታ ጋር የተደረገ ውይይት ነው፤ ትናንትን ከዛሬ ጋር ያስታረቀ የዜማ ድልድይ ነው፤ በዘጠናዎቹ የቀረውን እኔን የመለሰ አልበም ነው። ይመችሽ ዲንቢ!!
ካላመናችሁኝ ደግሞ ከአዲስ አልበሙ መካከል "ጊዜ አይሄድም"፣"አይሽና"፣ "ይረፍዳል" እና "ህልም ነው" አድመጣችሁ ፍረዱኝ፤ ካጠፋሁ እኔ ሳልሆን ዲንቢ ይቀጣል፡፡

12 days ago
በህይወት እያሉ ተመሰገኑ
(በዕዝራ እጅጉ)
.የመዲናዋ ጤና ቢሮ ነፃ ህክምና እንዲያገኙ ወሰነ
#ethiopia | አንጋፋ የሚድያ ባለሙያዎች አዲስ አለም ሓድጉና በልሁ ተረፈ ዛሬ ጋቢ በተደረበላቸው ዕለት ደስታቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ነበር።
በኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክ የማይረሳ አሻራ ያኖሩት እነዚህ ጉምቱ ባለሙያዎች ከ 35 አመት በላይ በትጋት ያገለገሉ ሲሆን በሙያ አጋሮቻቸው ተከበው አድናቆት ሲቸራቸው ውለዋል።
ቅዳሜ ሐምሌ 18 2018 ዓ.ም ከ 4 ሰዓት ጀምሮ በወመዘክር መርስኤሀዘን አዳራሽ በተደረገው መርሀ ግብር የሚድያ ባለሙያዎች እና ወዳጆቻቸው ተገኝተው እኛም አመስጋኞቻችሁ ነን በማለት ለመርሀ ግብሩ ድምቀት ሰጥተዋል።
ባለሙያዎቹን ለማመስገን ራሱን የቻለ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን ይህም ኮሚቴ ባለሙያዎቹ በዘለቄታዊነት የሚታገዙበት መንገድ ያመቻቸ ነው።
ለዝግጅቱ መሳካት በተከፈተው የwhat is up ገፅ ኮሚቴው ውስጥ ተግባራቸውን የተወጡት ጥላሁን ካሣ ፣ሀብታሙ ድረስ ፣ሰለሞን ሀይለኢየሱስ፣ዕዝራ እጅጉ (ተወዳጅ ሚድያ)፣ አለም ታደሰ፣ሠናይት ሀይሌ፣እሸቱ ገለቱ፣ ጌጡ ተመስገን እና ግደይ ገብረ ሲሆኑ እነርሱም በዕለቱ እንደተናገሩት ሥራው በአጭር ጊዜ ታስቦ ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ለአንጋፋ ባለሙያዎቹ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ነፃ ህክምና የሚያገኙበት መንገድ ያመቻቸ ሲሆን ይህ የመረዳዳት ባህል ወደፊትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተነግሯል።
አዲስ አለም ሓድጉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በትግርኛ ክፍል በኤዲተርነት እና በጋዜጠኝነት የሠራ ሲሆን ላለፉት 35 አመታትም ሙያውን ወዶና አክብሮ በመሥራት ይታወቃል።
የሚድያ ሰው በልሁ ተረፈ ደግሞ በኢትዮጵያ ሬድዮ ከሳይንስ ማህደር፣ ማንነት ሲፈተሽ እና ዝክረ ሰንበት በተባሉ ፕሮግራሞች ከ30 አመት በላይ የሠራ ሲሆን ሌሎችንም በማብቃት የማይዘነጋ አሻራ ለማኖር የቻለ ነው።
"ሰውን በሕይወት ሳለ እናመስግን "የሚል መርህ ያነገበው ይህ መሰናዶ የሚድያ ባለሙያዎችን በኑሯቸው የማገዝ ፣ በችግራቸው ጊዜ አብሯቸው የመሆን ግብ የሰነቀ ነው። እንዲህ አይነቱ ተግባር ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
ሁለቱም ባለሙያዎች አገር የጣለችባቸውን አደራ የተወጡ ብርቱ ባለሙያዎች እንደነበሩ በዕለቱ ምስክርነት የሰጡ ባልደረቦቻቸው የተናገሩ ሲሆን የምስጋና ቀን መዘጋጀቱ አዲስ የሚመጣውንም ባለሙያ የሚያበረታታ ነው ሲሉ ሀሣብ ሰንዝረዋል።
በዕለቱ የሚድያ ሥራን ከ1950ዎቹ ጀምሮ ያስቃኘ አጭር የትዝታ ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን ተመስጋኞቹ ከዚህ ቀደም አየር ላይ ያዋሏቸው ሥራዎችም በዕለቱ ለታደሙት እንግዶች ቀርበዋል።
በባልደረቦቻቸው የምስጋና ዝግጅት የተደረገላቸው አዲስአለም ሓድጉና በልሁ ተረፈ እንደዛሬ ደስ ብሎንም አያውቅ ፣ ይህን መርሀ ግብር በተሳካ መንገድ ዕውን እንዲሆን የጣራችሁ ሁሉ ፈጣሪ መንገዳችሁን ያቃና ሲሉ መርቀዋል።
የአዘጋጅ ኮሚቴው አባል እሸቱ ገለቱ እንዳለው በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን የሚሠሩ ባልደረቦች የመጠያየቅ ባህልን ከጀመሩ ሁለት አመት እንደሆናቸው ጠቅሰው ይህ የምስጋና መርሀ ግብር የዚያ መጠያየቅ አካል እንደሆነ ጠቁሟል።
ባለሙያዎች ጡረታ ሲወጡ የሚደገፉበት፣ በተለይም በኢኮኖሚ እገዛ የሚያገኙበት ስልት መነደፍ እንዳለበትም ጋዜጠኛ እሸቱ ጥቆማ ሰጥቷል። በተጨማሪም የጤና ሁኔታቸውን፣ የሚከታተሉበት መንገድ መፈጠር እንዳለበትም ተናግሯል።
ከጡረታ በኃላ ምክር በመስጠት ባለሙያዎቹ ልምዳቸውን ማጋራት አለባቸውም ብሏል።ይህንኑ ትልቅ ርዕይ ለማሳካት መንግሥትና የሚመለከታቸው የሚድያ ማህበራት ሊተባበሩ ይገባልም ሲል ሀሣብ አንስቷል።
የእለቱን የምስጋና መሰናዶ እንዲሳካ አቶ ሠርፀፍሬ ስብሓት አዳራሽ በመስጠት ፣ ጋዜጠኛ ማህደረ ታሪኩ ፕሮጀክተር በመለገስ እንዲሁም አልፋ ውሃ፣ ለታዳሚዎች የመስተንግዶ ውሃ በማቅረብ መርሀ ግብሩ የተሳካ እንዲሆን አድርገዋል።

16 days ago
የአቤን አንጀት የምታርሰው ሙዚቃ
#ethiopia | ሁለገቡ የጥበብ ሰው አበበ ብርሃኔ ግጥምና ዜማቸው በሌሎች ከተሰሩ የሙዚቃ ስራዎች መካከል የሚወደው አንድ ሙዚቃ አለ።
አቤ እጅግ ከሚወዳቸው የሙዚቃ ስራዎች መካከል የቴዎድሮስ ታደሰን "ሰርካለም" የተሰኘው ሙዚቃ ሙዚቃ እንደሆነ በአንድ ወቅት ከጋዜጠኛ ሔኖክ ወ/ገብርኤል ጋር በሙዚቀኞች ብፌ ፕሮግራም ላይ በነበረው ቆይታ ተናግሮ ነበር።
ይህ ሙዚቃ ለአቤ ሁሉ ነገሩ ነው።
የጥበብ ሰው አበበ ብርሃኔ የቴዎድሮስ ታደሰን "ሰርካለም" ሲያዳምጥ ልክ በውስጡ የተደበቀ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ጥልቅ ስሜት የሚቀሰቀስበት ይመስላል።
አበበ ብርሃኔ በሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከ800 በላይ የግጥምና የዜማ ስራዎች የሰራ ታላቅ የጥበብ ሰው ነው።
በይልማ ገ/አብ እና በዜማ ደራሲው አበበ መለሰ የተሰራው ይህ ሰርካለም ሙዚቃ ስራ ግን ለአበበ ብርሀኔ ቀዳሚ የሙዚቃ ምርጫ ነው።
የቴዎድሮስ ታደሰን "ሰርካለም" ሲሰማ ምርጫው መሆኑን ከመመስከር ወደ ኋላ አይልም።
ለእርሱ ይህ ሙዚቃ ከአድማጭነት አልፎ የህይወት አጋሩ ሆኗል።
አበበ ለዚህ ሙዚቃ ያለው ክብር እንደ ተራ አድናቂ አይደለም።
ሙዚቃው ሲጀምር አበበ ወደ ትዝታው ጥግ ይጓዛል።
"ሰርካለም" ለእርሱ እንደ አንድ ታሪካዊ መጽሐፍ ገጾች ያለፉትን ጣፋጭና መራራ የህይወት ምዕራፎች ሁሉ እያገላበጠ የሚያስታውሰው ነው።
የሙዚቃው ዜማና የቴዎድሮስ ታደሰ ድምፅ በአበበ ልብ ውስጥ ልዩ የሆነ የመረጋጋት ስሜት ይፈጥራል የአንጀቱ መታረሻም ይኸው ነው።
"ሰርካለም" የጥበብ ጥግ ነው። በሙዚቃው ውስጥ የሚሰማው የፍቅር የናፍቆትና የህይወት ትርጉም ከአበበ የጥበብ እይታ ጋር ይዋሃዳል።
አበበ በግርምት ሲናገር እንዲህ ይላል
እንዴት እንዲህ አይነት ሙዚቃ ይሰራል የሚል።
የግጥሙ ጥልቀት የዜማው ጥራት እና ውበት ይደንቀኛልም ይላል።
"ሰርካለም" ለእርሱ የትላንት ናፍቆቱ የዛሬ ኩራቱ እና የነገ ተስፋው የሆነ ሙዚቃ ይመስላል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ኢትዮጵያሙዚቃሰርካለም #አበበብርሀኔቴዎድሮስታደሰ #ይልማገብረአብአበበመለሰ

18 days ago
ለሜሲ ያማል!
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኒውዮርክ ሰማይ ስር የእግር ኳስ ታሪክ አዲስ ንጉስ መውለዱን ለዓለም አውጇል።
የሊዮኔል ሜሲን የመጨረሻ ዳንስ ለመመልከት በተሰበሰበው የዓለም ሕዝብ ፊት ሳይጠበቅ የመጣው የስፔን የአዳጊዎች ስብስብ የክብር ዘውዱን ነጥቋል።
ይህ ድል የስፔን ብቻ አይደለም፤ በሜሲ እጅ ገላውን ታጥቦ ያደገው የላሚን ያማል የንግስና ዘመን ይፋዊ ማብሰሪያ ጭምር እንጂ፡፡
ታሪካዊው ፍልሚያ ከመጀመሩ በፊት ዓለም ሁሉ ትኩረቱን በሜሲና በአዳጊው ያማል የ2007 ድንቅ የፎቶ ትዝታ ላይ አድርጎ ነበር።
ሜሲ በበጎ አድራጎት መርሐ ግብር ላይ ገላውን ያጠበው የያኔው ሕፃኑ ያማል፥ ዛሬ በ19 ዓመቱ ድንቅ ጥበብ እያሳየ ለአርጀንቲና ፈተና ሆኖ ቀረበ።
በኒውዮርክ ስታዲየም የታየው ትዕይንት ድንቅ ነበር፤ ሜሲ ዘውዱን ለተተኪው አስረክቦ የዓለም ዋንጫውን ሲያጠናቅቅ ያማል ደግሞ አዲሱ የዓለም እግር ኳስ መሪ መሆኑን አረጋግጧል።
ይህ የስፔን ወጣት ስብስብ በውድድሩ ጉዞው ቀላል አልነበረም።
ገና ከጅምሩ በጥንካሬና በማይበገረው የኬፕ ቨርዴ ስብስብ ብርቱ ፈተና ገጥሞት የነበረ ቢሆንም፤ ያንን አስቸጋሪ ውቅያኖስ በፅናት ተሻግሯል።
ሜሲ እና የአርጀንቲናው ወርቃማ ትውልድ የስፔንን የወጣቶች ስብስብ የዋንጫ ጥማት ግን ሊገቱት አልቻሉም።
ቫሞስ! አዲሱ ዘመን ጀምሯል።
"ለሜሲ ያማል" የሚለው ድምጽ አሁን በስታዲየሙ ውስጥ ያስተጋባል።
በአንድ በኩል ለታላቁ ንጉስ ሜሲ የመጨረሻ ጉዞ የተሰማ ቁጭት ሲሆን፥ በሌላ በኩል ደግሞ በላሚን ያማል መነሳት የተፈጠረ አዲስ እምቅ ስሜት ነው።
የስፔን ከዋክብት "ቫሞስ" እያሉ ዋንጫውን ወደ ሰማይ ሲያነሱ፥ እግር ኳስ አዲስ ምዕራፍ መጀመሯን አረጋግጣለች።
ታሪኩ ተፈጽሟል፤ ንጉሱ ሜሲ በታላቅ ክብር ተሰናብቷል፤ አዲሱ ንጉስ ያማል ደግሞ በኒውዮርክ ሰማይ ስር ዘውዱን ደፍቷል፡፡
በኃይለኢየሱስ መኮንን

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የኳታር መንግሥት ለአሜሪካ መሪዎች የሥራ ጉዞ በስጦታ ያበረከተውና በአሁኑ ወቅት እንደ ዋናው ፕሬዝደንታዊ አውሮፕላን እያገለገለ ያለው ጃምቦ ጄት፣ የደኅንነት ገፅታዎቹን በተመለከተ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ተከትሎ በቅርቡ ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንዲደረጉበት እንደሚላክ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ ባለፈው ዓመት በስጦታነት የተቀበሉትን ይህንን ቦይንግ 747-8 አውሮፕላን ለፕሬዝደንታዊ አገልግሎት እንዲውል በፍጥነት የማደስ ሥራ ከተከናወነ በኋላ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ጁላይ 1፣ 2026 (እ.ኤ.አ.) በሜሪላንድ ከሚገኘው ጆይንት ቤዝ አንድሪውስ ወደ ሰሜን ዳኮታ ለቴዎዶር ሩዝቬልት ፕሬዝደንታዊ ላይብረሪ ምረቃ ስነ-ስርዓት ለመጓዝ ተጠቅመውበታል።
ይሁን እንጂ ጁላይ 8 ቀን ከአሜሪካ ጋር በነበረው ከፍተኛ የኢራን ውጥረት መባባስ ምክንያት፣ ትራምፕ ከቱርክ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) በሚያደርጉት በረራ ላይ ይህንን አዲስ አውሮፕላን ባልተጠበቀ ሁኔታ ትተውት ነበር። በወቅቱ ወደ ለንደን የተጓዙት በአሮጌው ኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን ሲሆን፣ ድርጊቱንም “ለቀድሞው ትዝታ ሲባል” ያደረጉት እንደሆነ ገልጸዋል። ነገር ግን በኋላ ላይ ወደ አሜሪካ ለመመለስ በአዲሱ አውሮፕላን ተሳፍረዋል።
ትራምፕ በኒው ጀርሲ ከተካሄደው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ አዲስ የታደሰው አውሮፕላን የሚሳይል መከላከያ ሥርዓት ይጎድለዋል ወይ ተብለው በጋዜጠኞች ተጠይቀው ነበር።
ትራምፕ ስለ አውሮፕላኑ ሲናገሩ “ከፍተኛ የሆነ የመከላከልና የአገልግሎት አቅም አለው” ካሉ በኋላ፣ “ነገር ግን እኔ እንደተረዳሁት፣ በሚቀጥለው አንድ ወር ገደማ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሙሉዕ እንዲሆን እና ከፍተኛ ማሻሻያ እንዲደረግበት ይልኩታል። ይህም አንድ ወር ገደማ ይወስዳል” ብለዋል።
የአሜሪካ አየር ኃይል በዚህ ጉዳይ ላይ በይፋ አስተያየት ለመስጠት የቀረበለትን ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።

24 days ago
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) «ጊዜ አይሄድም» የተሰኘውን 3ኛ አልበሙን ሊለቅ ነው!
#fastmereja :-ታዋቂው ድምፃዊና የዜማ ደራሲ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) «ጊዜ አይሄድም» የተሰኘውን 3ኛ ሙሉ የሙዚቃ አልበሙን የፊታችን ሐምሌ 10 ቀን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
በናሆም ሪከርድስ (Nahom Records) አማካኝነት በተለያዩ የሙዚቃ ማሰራጫዎችና በዩቲዩብ የሚለቀቀው ይህ አልበም፣ በአጠቃላይ 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን የሀገር ፍቅርን፣ ማህበራዊ ህይወትንና ፍቅርን የሚዳስሱ ይዘቶች እንዳሉት ተገልጿል። አልበሙ «ጊዜ አይገድም» እና «ይረፍዳል» የሚሉ ተቃራኒ እውነታዎችን ያጣመረ ልዩ ፍልስፍናዊ ጭብጥም እንዳለዉ ነዉ የተገለፀዉ።
ይህም ተስፋ ላለው ሰው ጊዜ እንደማይሄድና ሁሌም ብርሃን እንዳለ የሚያሳይ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜ የማይጠብቅ መሆኑንና «ይረፍዳል» የሚለውን ተቃራኒ የህይወት እውነታ በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ልዩ ፍልስፍናዊ ስራ ስለመሆኑም ነዉ የተገለፀዉ።
በአልበሙ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረገው ድምፃዊና የግጥም ደራሲ ካድር አሊ «እሳሳታለሁ» እና «ከፍ በል» የተሰኙ ሁለት ስራዎችን በግጥምና በድምፅ ያበረከተ ሲሆን፣ ስራው ዘመን ተሻጋሪና በጥራት የተሰራ መሆኑን ገልጿል።
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ከዚህ ቀደም «እዮሪካ» እና «ኦሜርታ» የተሰኙ እጅግ ተወዳጅና ስኬታማ አልበሞችን ለአድማጮች ያበረከተ ሲሆን፤ «ዲንቢ ለዲንቢ»፣ «ተጠየቂ ናዝሬት»፣ «አውራአምባ»፣ «በትዝታው ፈረስ» እና «አይ መሬት ያለ ሰው» የተሰኙ በርካታ የራሱ ተወዳጅ ሙዚቃዎች አሉት።
ከዚህ ቀደም «እዮሪካ» እና «ኦሜርታ» የተሰኙ ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጮች ያበረከተው አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፤ ለማዲንጎ አፈወርቅ፣ ለፀሀዬ ዮሀንስ፣ ለብዙአየሁ ደምሴ እና ለዘቢባ ግርማ በርካታ ተወዳጅ ዜማዎችን በመስራት የሚታወቅ ስኬታማ ባለሙያ ነው።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የዓለም ዋንጫው ግለት ጣሪያ ነክቷል! ረቡዕ ዕለት በአትላንታ ስታዲየም (ቢትዮጵያ አቆጣጠር ምሽት) በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ታላቅ ፍጥጫ፣ የአምናዋ ሻምፒዮኗ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ጋር ስትፋጠጥ ታዋቂውን ጥቁር ሰማያዊ የሜዳ ውጪ ማልያዋን አጥልቃ ወደ ሜዳ እንደምትገባ ታውቋል። በበኩሏ እንግሊዝ ሙሉ ነጭ የሆነውን የሜዳዋን ማልያ ለብሳ ለዚህ ትልቅ ጦርነት ትቀርባለች።
አርጀንቲና በዘንድሮው ውድድር ይህንን ማልያ የተጠቀመችው በምድብ ድልድሉ ጆርዳንን 3 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ ብቻ ነው። ይሁን እንጂ... ይህ የማልያ ምርጫ ከፊፋ የደንብ አሰራር ባሻገር ትልቅ የስነ-ልቦና እና የ"እምነት" ሚስጥር እንዳለው በአርጀንቲና ሚዲያዎች በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ምክንያቱም ይህ ጠቆር ያለ ሰማያዊ ማልያ፣ አርጀንቲናውያን በእንግሊዝ ላይ ታሪካዊ ድል ለተቀዳጁባቸው የ1986ቱ እና የ1998ቱ የዓለም ዋንጫዎች ትልቅ ትዝታ ያለው በመሆኑ ነው!
በተለይም በ1986ቱ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በታሪካዊቷ "የአምላክ እጅ" ጎል እንግሊዝን 2 ለ 1 ሲያሸንፉ፣ እንዲሁም በ1998ቱ የፈረንሳይ ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ (Last-16) ጨዋታ በፔናሊቲ መለያ ምት የሶስቱን አናብስት ስብስብ ሲያሸንፉ ያጠለቁት ይሄንኑ ማልያ ነበር።
በተቃራኒው ግን በ2002ቱ በጃፓን በተካሄደው የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ እንግሊዝ ቀይ ማልያ ለብሳ፣ አርጀንቲና ደግሞ ባህላዊውን ባለ መስመር ማልያዋን ለብሳ በተገናኙበት ጨዋታ እንግሊዝ 1 ለ 0 ማሸነፏ የማይዘነጋ ነው።
የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) አሰራር እያንዳንዱ ቡድን የሜዳውን የመጀመሪያ ምርጫ ማልያ እንዲለብስ ቅድሚያ የሚሰጥ ቢሆንም፣ የማልያ ቀለም መመሳሰል ካጋጠመ ግን የለቀቀ እና የደመቀ ቀለም እንዲኖር እርምጃ ይወስዳል። ይህም በተለይ colour blindness ችግር ላለባቸው ደጋፊዎች ጨዋታውን በቀላሉ እንዲከታተሉ ታስቦ የሚደረግ ጥንቃቄ ነው።
ወደዚህ ግዙፍ የግማሽ ፍጻሜ ጦርነት ለመድረስ ሁለቱም ቡድኖች ፈታኝ መንገድ አልፈዋል። እንግሊዝ ባለፈው ቅዳሜ ኖርዌይን በጭማሪ ሰዓት 2 ለ 1 ስታሸንፍ፤ አርጀንቲና ደግሞ እሁድ ዕለት 10 ተጫዋቾች ብቻ ቀርተውባት ከነበረችው ስዊዘርላንድ ጋር ባደረገችው እጅግ አጓጊ ጨዋታ በጭማሪ ሰዓት 3 ለ 1 አሸንፋ ማለፏ ይታወቃል። አሁን የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪዎች ዓይን በአትላንታው የረቡዕ ምሽት ፍልሚያ ላይ አርፏል!

25 days ago
"ገላ ገላ" አስቱካን እካችሁ
የሰው ልጅ ነፍስ የምትተነፍስበት ጥልቅ ውቅያኖስ "ሙዚቃ"
"ሙዚቃ" እና "ፍቅር" ደግሞ ተነጣጥለው የማይታዩ፣ አንዱ ለአንዱ የተፈጠሩ፣ የሰማይ እና የምድር ያህል የተሳሰሩ የነፍስ ቋንቋዎች ናቸው።
ከትላንት እስከ ዛሬ... ከካሴት ክር እስከ ዲጂታል ዘመን፣ ቴክኖሎጂው ቢለዋወጥም፣ ትውልድ ቢተካካም እነዚህን ሁለት መለኮታዊ ጸጋዎች በአንድ ልብ አዋህዳ፣ ስሜትን በዜማ ሸምና ያቀረበችልን የዘመናቶች ፈርጥ—እሷ አስቴር አወቀ ናት!
የትውልድን ልብ ያንኳኳች፣ ማዕበል እና ጸጥታን በድምጿ ያስማማች የኢትዮጵያ የሙዚቃ ጸጋ! አስቴር የ"ሶል" (Soul)
የፍቅር ንግሥት በድምጿ ጅረት ውስጥ የሰውን ልጅ ጥልቅ የልብ ጓዳ የምትፈትሽ፣ ስንከፋ አባባይ፣ ስንደሰት አጀብ ባይ የሆነች የዘመን ሀብት ናት።
ትዝታን ብቻ አይቀሰቅሱም፤ ገና ሳንኖረው የናፈቀንን፣ በቃላት የማይገለጸውን ያንን ጥልቅ ናፍቆት (መናፍቅነት) በውስጣችን ይፈጥራሉ። "ፍቅር" የሚለውን ቃል ስታዜመው፣ የፍቅርን ፊደል ያልቆጠረው እንኳ በፍቅር ይነድፋል፤ ገና ያላየነውን የፍቅር ብስራት በሙዚቃዋ እንድንኖረው፣ ያላጣጣመነውን ስሜት በምናባችን እንድንስለው ታደርገናለች። ድምጿ ሲሰማ የሌለብን ትዝታ ይጭንብናል፣ የሌለ ስንብት ያስለቅሰናል፣ ገና ያልመጣ ተስፋ ያስፈነድቀናል።
ትላንት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ያደመጧትን፣ ዛሬ እኛ በፍቅር እንሰማታለን፤ ነገም ልጆቻችን ይወርሷታል። ጊዜ የማይሽራት፣ ዘመን የማያልፍባት ተወዳጅ አርቲስት!
እስኪ አንድ ሁለቲቱን እንምልክት
"ለመድክ ወይ" የተሰኘውን ይህን ልብ ሰባሪ እና ስሜት አንጀት ሰርስሮ የሚገባ የሙዚቃ ስራ ስናዳምጥ፣ የሰውን ልጅ የፍቅር ስነ-ልቦና፣ የልብ ስብራትን (Heartbreak) እና የመለየትን መራር እውነት በሚያስገርም ጥልቀት ስትፈትሸው እናገኛለን።
ይህ ዘፈን ተራ የሙዚቃ ዜማ አይደለም፤ ይልቁንም አንዲት በፍቅር የተከዳች፣ ማመን ያቃታት እና በትዝታ እስር ቤት ውስጥ የቀረች ነፍስ የምታሰማው የውስጥ ጩኸት ነው።
የዚህን ድንቅ ዘፈን ጥልቅ መልእክት በበሰለ የኪነ-ጥበብ መነጽር ስንተነትነው የሚከተሉትን ህያው እውነታዎች እናገኛለን
1. "ለመድክ ወይ?" ይህ ጥያቄ ተራ መጠይቅ አይደለም። የድንጋጤ እና የመገረም ጩኸት
ያለኔ መኖርን ቻልከው? እኔ ገና የትላንቱን አብሮነታችንን መርሳት አቅቶኝ በትዝታ እሳት እየነደድኩ፣ አንተ ግን እንዴት ያለምንም ህመም የክህደት እና የመገረም ስሜት ነው አንድ ሰው የነፍሱን ግማሽ አድርጎ ያሰበው አካል አዲስ ህይወት በአንድ ጀንበር የሚፈጠረውን የአእምሮ ንዝረት ያሳያል
አስቴር ይህንን ሚዛን የሳተ ፍቅር በጉልህ ታሳያለች።
በፍቅር መለያየት ውስጥ እጅግ አሳማሚው ነገር የህመሙ አለመመጣጠን ነው።
ለአንዱ (ለአፍቃሪዋ) ፍቅር የህይወት መሰረት፣ እስትንፋስ እና አለም ሲሆን፤ ለሌላኛው (ለተፈቃሪው) ግን ፍቅር ጊዜያዊ ማረፊያ፣ በቀላሉ ሊተካ እና ሊረሳ የሚችል ተራ ክስተት ሆኖ እናገኘዋለን። "እኔ እንዲህ ሆኜ፣ አንተ እንዴት ሆንክ?" የሚለው የዘፈኑ የጀርባ አጥንት ይህንን የስሜት መራራቅ ያጋልጣል።ያ የለመደችው ድምፅ፣ ያ የለመደችው መዓዛ በድንገት ሲቋረጥ ነፍስ ባዶ ትቀራለች። አስቴር በዚህ ዘፈኗ፣ መለየቱን አምና ለመቀበል የሚደረገውን የውስጥ ትግል እና የትዝታን አረመኔነት በቃላቷ ትስላለች። "ልመዳ" እንዴት ከባድ እንደሆነና ያንን ማቋረጥ ደግሞ ሞት መሆኑን ልክ አንዲት ሴት ብቻዋን ክፍሏ ውስጥ ሆና የምታነባውን፣ የምታቃስተውን እና ከራሷ ጋር የምታደርገውን ሙግት በዜማ ልክ ሰፍታ ታለብሰናለች።
የናፍቆትን እሳት እና የልብን መታለል ያለምንም ማለዘቢያ ፊት ለፊት
ለመድክ ወይ" የፍቅርን የጨለመ ገፅ ሚያዳምጣት ሁሉ የተወሳሰበ የሰው ልጅ ስሜት ወስዳ
የቆሰለ ልብ ያለው ሁሉ፣ በዚህ ዘፈን ውስጥ የራሱን እንባ ያገኛል!
"ገላ ገላ" በረቂቅ ቃላት የተሳለበት የፍቅር ጸሎት ።
ይህ ዘፈን ተራ የቃላት ድርደራ ሳይሆን፣ አንዲት የሰው ልጅ ነፍስ በፍቅር ስትገዛ፣ ስትማረክ እና ራሷን አሳልፋ ስትሰጥ የሚኖራትን ጥልቅ ስነ-ልቦናዊ እና ስጋዊ ውህደት የሚያሳይ ህያው ማሳያ ነው።
ገላ—የነፍስ ማረፊያ፣ የስሜት መግለጫ እና የፍቅር ቤተ-መቅደስ ነው።
አስቴር "ገላ" ስትል፣ መነካካትን ብቻ ሳይሆን፣ ሁለት ነፍሶች አንድ የሚሆኑበትን፣ መለያየት የሌለበትን ያንን የመጨረሻውን የፍቅር ልዕልና (Intimacy) እየጠራች ነው። ለእሷ ህይወት የሚዘራ፣ ግን ደግሞ ናፍቆትን የሚያባብስ ጣፋጭ እስር ቤት ነው።
አንድ የምታውቀው ፍጹም እውነት ቢኖር የራሷን የልብ ትርታ ነው።
የሷ "ሆድ" (ውስጧ/ነፍሷ) ለእሱ መገዛቱን አምና መቀበሏ፣ በፍቅር ውስጥ ያለውን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ራስን አሳልፎ የመስጠት ጀግንነት ያሳያል።ፍቅር ከስሜት አልፎ ወደ "መኖር እና አለመኖር" ትርጉም ይሸጋገራል። ፍቅር የልብ ምት ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ሳንባ ገብቶ የሚያኖራት ኦክስጅኗ ሆኗል።
የነፍስ ኑዛዜ ነው ገና ያላፈቀረውን "እንዲህ ያለ ጥልቅ ፍቅር ባገኘሁ" ብሎ እንዲመኝ ሲያደርግ፤ ያፈቀረውን ደግሞ የልቡን ቋንቋ አግኝቶለታል።የሰውን ልጅ ድብቅ እና ጥልቅ የልብ ጓዳ ገብታ፣ ትበረብራልች
በሥራ መክበርን" በተግባር በማሳየቷ እንጂ! 40የልማሳ ዓመታት ሙሉ በመድረክ ላይ መቆየት፣ 28 አልበሞችን ማበርከት... ይህ ቁጥር ብቻ አይደለም፤ የትጋት፣ ለጥበብ የመገዛት እና የተሰጥኦ ጥግ ነው። አስቴር ጥበብን ከትጋት ጋር አጣምራ፣ የሰራችው ስራ ሁሉ ወርቅ ሆኖላት፣ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለዘላለም የነገሰች የጥበብ ጀግና ናት። "ሙዚቃ" ፍቅር ነው፤ "ፍቅርም" ሙዚቃ ነው። ሁለቱም ደግሞ በአንድነት ሲጣመሩ "አስቴር አወቀ" የሚል ትርጉም ይሰጡናል።
ክብር በሥራዋ ለከበረችው...
ክብር ጥበብን አክብራ ላስከበረችን...
ክብር ትውልድን በዜማ እና በፍቅር ላዋሃደችው...ክብርም በስራሽ ሁሉ እድንወድሽ ላደረጉት በስራዎችሽ አሻራቸውን ላኖሩ ከቴዎድሮስ መኩሪያ ላስቱካ

29 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ምሽት ከቱርክ ሲነሱ ወደ ስፍራው ባመጣቸው እና በኳታር በተበረከተው አዲሱ አውሮፕላን ፈንታ ባልተጠበቀ ሁኔታ በአሮጌው 'ኤር ፎርስ ዋን' አውሮፕላን መጓዛቸው ተሰማ። 'ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ' እንደዘገበው፣ ይህ ውሳኔ የተላለፈው የደህንነት ጥንቃቄን ታሳቢ በማድረግ በአሜሪካ ሚስጥራዊ የደህንነት አገልግሎት የውሳኔ ሃሳብ መሰረት ነው።
ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኋላ ላይ በብሪታንያ ወደ አዲሱ አውሮፕላን በመቀየር ጉዟቸውን ወደ ዋሽንግተን አድርገዋል።
ለኔቶ ጉባኤ ወደ ቱርክ የተደረገው ይህ ጉዞ ለአዲሱ አውሮፕላን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ በረራ ሲሆን፣ ጉዞው የተካሄደው ቱርክን ከምታዋስነው ኢራን ጋር ወታደራዊ ውጥረት ባየለበት ወቅት ነው።
ይህ ያልተጠበቀ የአውሮፕላን ቅያሬ የተከሰተው፣ ቦይንግ ኩባንያ ዘመናዊዎቹን የ'ኤር ፎርስ ዋን' አውሮፕላኖች ርክክብ ባዘገየበት በዚህ ወቅት፣ እንደ ጊዜያዊ መተኪያ እንዲያገለግል በተበረከተው በዚህ የቅንጦት ስጦታ ላይ ለወራት የዘለቀ ክትትል እና ትችት ሲቀርብበት ከቆየ በኋላ ነው። ተቺዎች የአውሮፕላኑን እድሳት ወጪ፣ ደህንነት እና ፍጥነት በተመለከተ ጥያቄዎችን ሲያነሱ ቆይተዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ'ትሩዝ ሶሻል' ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት፣ ከአንካራ ወደ ብሪታንያው 'አር.ኤ.ኤፍ ሚልደንሆል' የጦር ሰፈር ለመብረር አሮጌውን ሰማያዊ 'ኤር ፎርስ ዋን' አውሮፕላን የተጠቀሙት "ለድሮው ጊዜ ትዝታ" ሲሉ መሆኑን ገልጸዋል። በዚሁ ወቅት አዲሱ አውሮፕላን በዚያው የጦር ሰፈር በማረፍ፣ በስፍራው የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች አውሮፕላኑን እንዲጎበኙት መደረጉን አመልክተዋል።
ትራምፕ በመረጡት ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር ሰማያዊ እና ወርቃማ ቀለማት ያሸበረቀው ይህ አዲሱ ቦይንግ 747 አውሮፕላን፣ ባለፈው ዓመት ከኳታር ለአሜሪካ በስጦታ የተበረከተ እና በ'ኤል3ሀሪስ ቴክኖሎጂስ' የመከላከያ ተቋራጭ ድርጅት የታደሰ ነው።
ትራምፕ በአንካራ በነበሩበት ወቅት፣ አውሮፕላን ለመቀየር የወሰኑት የግድያ ሙከራ ስጋት ኖሮ ስለመሆኑ ተጠይቀው ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ቢቆጠቡም፣ ስጋቱ ሊኖር እንደሚችል ግን አምነዋል። የኔቶ ጉባኤ ሲጠናቀቅ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ "በኢራን የግድያ ኢላማ ዝርዝር ውስጥ አንደኛ ደረጃ ላይ ነኝ፤ አላውቅም፣ ይህንን ልነግራችሁ አልችልም፤ ነገር ግን ያን ያህልም አልጨነቅም" ብለዋል።
ከኳታር ለተበረከተው አውሮፕላን የተደረገው እድሳት እጅግ በፍጥነት በመጠናቀቁ፣ አንዳንድ ባለሙያዎች አውሮፕላኑ እንደ ነባሮቹ የ'ኤር ፎርስ ዋን' አውሮፕላኖች አስተማማኝ ደህንነት ላይኖረው ይችላል የሚል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የ'ኒው ዮርክ ታይምስ' ዘገባ ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጮችን ጠቅሶ እንዳብራራው፣ የአውሮፕላን ቅያሬው ጥንቃቄን ታሳቢ ያደረገ እንጂ የተለየ ተጨባጭ የደህንነት ስጋት ኖሮ አይደለም። ጋዜጣው የዋይት ሃውስ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ስቲቨን ቼንግን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ "ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ እንዳሉት፣ አሜሪካ እሳቸውን ኢላማ ያደረጉ በርካታ ጠላቶች አሏት፤ እኛም እነዚህን ስጋቶች ለመቋቋም ትኩረትን ማሳሳት እና አቅጣጫን ማስቀየርን ጨምሮ በእጃችን ያሉትን አማራጮች ሁሉ እንጠቀማለን" ብለዋል።

"በሰርጌ ትዝታ" የህዝቡ ስሜት ለምን ተነካ?
የጥበብ ስራዎችን እንደ ቁስ ሳይሆን እንደ የጋራ ትዝታችን ማየት ሲቻል እንደዚህ ያሉ ውዝግቦች ይቀንሳሉ።
አሁን የተፈጠረው የህዝብ ብስጭትም የጥበብን ክብር ከመጠበቅ የመነጨ ነው።
የጥበብ ስራዎች የትዝታችን ካርታዎች ናቸው እነርሱን በዘፈቀደ መቀየር ወይም ማዛባት ትዝታችንን እንደመንጠቅ ይቆጠራል።
ጥበብ በውሳኔ ሰጪዎች ፍላጎት ብቻ የሚመራ ሳይሆን ጥልቀት ባለው መረዳት ሊቃኝ ይገባል።
ትኩረታችንን ከአርቲስቶቹ ላይ እናንሳና ይህንን ሃሳብ ወደ ፊት ያመጡትና የመወሰን ስልጣን በነበራቸው አካላት ላይ እናድርግ።
የዚህ ስራ ዳግም መሰራትን የጠነሰሱት ሰዎች ለሙዚቃችን እና ለአድማጩ ስሜት ምን ያህል ክብር ሰጥተው ነው የወሰኑት?
ጥበብ በውሳኔ ሰጪዎች ፍላጎት ብቻ የሚመራ ሳይሆን ጥልቀት ባለው የባህል መረዳት ሊቃኝ ይገባል።
በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የማይረሱና በህዝብ ልብ ውስጥ ጥልቅ ቦታ ያላቸው ስራዎች የጋራ ቅርሶች ናቸው።
በአስቴር አወቀ እና በያየራድ አላምረው ተሰርቶ የነበረው ሰሞኑ ዳግም በተሰራው "የሰርጌ ትዝታ" የብዙዎችን ትኩረት በመሳብ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰፊ ክርክር ፈጥሯል።
ይህ ጉዳይ በአንድ የጥበብ ስራ ላይ የሚሰነዘር ተራ ትችት ብቻ ሳይሆን የኪነ ጥበብ ባለቤትነት እና የጥበብ ክብር ጥያቄ ጭምር ነው።
ኦርጂናሉ የሰርጌ ትዝታ ምን ጎሎት ነው ዳግም እንዲሰራ የተፈለገው?
አድማጩ የዚህን ጥያቄ መልስ መፈለጉ ተገቢ ነው።
ቀድሞ የተሰራው የሰርጌ ትዝታ በቅንብር ፣ የቅጂ ጥራቱ በከድማጩ የሚፈጥረው አጠቃላይ ስሜቱ ለዘመናት የቆየና የብዙዎችን ደስታ አስጠብቆ የነበረ ሙዚቃ ነበር።
አንድ ሙዚቃ በድጋሚ ሲሰራ አዲስ ነገር የመጨመር ወይም የጥበብ ደረጃን የማሻሻል ዓላማ ሊኖረው ይገባል።
ሆኖም አድማጩ በዚህ ዳግም በተሰራው ስራ ላይ የተሰማው ስሜት በመጀመሪያ ስራ የነበረውን ውበት በዚህኛው ላይ ማግኘት አልቻለም።
ስራው የላቀ የኪነ ጥበብ ፈጠራን ይዞ ከመቅረብ ይልቅ በሌሎች ውሳኔ የተገደደ ወይም የንግድ ዓላማ የተጫነው መስሏል።
ለዚህም ነው አድማጩ ስሜቱ እንዲረበሽ ያደረገው።
ይህ ሙዚቃ የአስቴር አወቀ ወይም የያየራድ አላምረው የግል ንብረት ብቻ አይደለም።
ጥበብ ለህዝብ ሲቀርብ የህዝብ ቅርስ ይሆናል።
አንድ ስራ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ያ ህዝብ ስራው እንዴት እየተስተናገደ እንደሆነ ለምን እንደተቀየረ ወይም ለምን አላማ እየዋለ እንደሆነ የመጠየቅ ሙሉ መብት አለው።
በየትኛውም ዘርፍ አንድ ነገር ሲበላሽ ህዝብ "ለምን ተነካ?" ብሎ መጠየቁ መብቱ ነው።
የጥበብ ስራዎች ሲሰሩ ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ቁርኝት እንደ አንድ ውል ይቆጠራል።
ስለዚህ የጥበብ ባለቤቱ ህዝብ በመሆኑ ስራዎቹን የመጠበቅና የመጠየቅ መብቱን ተገቢ ነው።
በዚህ ስራ የተሳተፉ ሰዎችም ህዝብ ለምን እንደተበሳጨ ከመንቀፍ ይልቅ የሰጠውን ትችት እንደ ታላቅ የኪነ ጥበብ ትምህርት ሊወስዱት ይገባል።
በጋዜጠኛ ሔኖክ ወ/ገብርኤል

30 days ago
ተወዳጇ አርቲስት አስቴር አወቀ የድሮ ሙዚቃዎችን በአዲስ መልክ የሰራችውን አልበም አስመልክቶ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ በተለይ “የሰርጌ ትዝታ” የተሰኘው ሙዚቃ ከብዙዎች ትችት እየቀረበበት ይገኛል።
በዩቲዩብ ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል አንዱ የሙዚቃ አድማጭ ይህን ብሏል “ይሄ ሙዚቃ የእውቁ ሙዚቀኛ የግራሚ ሽልማትን የወሰደው የደረጄ መኮንን አሻራ በትልቁ ያረፈበት ነው:: ይሄንን ሙዘቃ ለዚህን ያህል ዘመን ሕያው አድርገው ያቆዩት ዐራት ባለሞያዎች ናቸው:: የድምጻዊቷ አስቱ ዜማና እና ውብ ድምጽ፣ አቀናባሪው ደረጄ መኮንን፣ ገጣሚው ያየህይራድ አላምረው እና የእኛ የአድማጮቹ ትዝታ፡፡ የዚህ ቅንብር ላይ ሁለቱ ነገራት ተዘንግተዋል፡፡ የደረጄ መኮንን የአሬንጅመንት ጥልቅ ፍልስፍና እና የእኛ ትዝታ፡፡ ስለሆነም ይህንን ዘፈን በዚህ መልኩ መስማት ያናድዳል፡፡ ለአድማጭ ስሜት ያልተጨነቀ ትዝታችንን የጨፈለቀ ሙዚቃ ነው።” ብሏል።

1 month ago
የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
*******************
በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያሳረፈችው የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር፤ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቿና በርካታ የሙያ አድናቂዎቿ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ በተለየ የድምፅ ቀለምና በባህል ዜማዎቿ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈች ሲሆን፣ በኪነ-ጥበብ ዘመኗ 13 የሙዚቃ አልበሞችን ለሕዝብ አበርክታለች።
ከዚህም ባለፈ ከተለያዩ ዕውቅ ድምፃውያን ጋር በመጣመር በርካታ ዘመን አይሽሬና ተወዳጅ ሥራዎችን ለአድማጮች አድርሳለች።
ከያኒዋ ካበረከተቻቸው በርካታ የሙዚቃ ሥራዎቿ መካከል "ኢትዮጵያ"፣ "አራዳ"፣ "እንደ ኢየሩሳሌም"፣ "ትዝታ"፣ "አንቺ ባለድሪ" እና "አየር ኃይላችን" የሚሉት ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ እነዚህ ዜማዎች ዛሬም ድረስ በሕዝብ ልብ ውስጥ የታተሙና ተወዳጅነታቸው የማይደበዝዝ ድንቅ የጥበብ ሥራዎቿ ናቸው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ለአንጋፋዋ አርቲስት ራሔል ዮሐንስ ቤተሰቦች፣ የጥበብ ባልደረቦችና ለመላው አድናቂዎቿ መጽናናትን ይመኛል።

ተወዳጇ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
በበርካታ የባህል ሙዚቃ ዜማዎቿ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘችው ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
ድምፃዊቷ ያጋጠማትን የጤና እክል ተከትሎ በሕክምና ስትረዳ ቆይታለች።
ራሔል ዮሐንስ በግሏ እናከተለያዩ ድምፃውያን ጋር በመሆን በርካታ ተወዳጅነት ያገኙ ሙዚቃዎችን ሠርታለች።
በሙዚቃዎቿ ከድምፃዊነቷ ባለፈ፣ በአንዳንዶቹ ላይ በግጥም እና በዜማ ድርሰትም አስተዋፅኦ ታደርግ ነበር።
ራሔል ዮሐንስ ከሠራቻቸው ሙዚቃዎቿ መካከል እንደ "ኢትዮጵያ"፣ "አራዳ"፣ "እንደ ኢየሩሳሌም"፣ "ትዝታ"፣ "አንቺ ባለድሪ"እና "አየር ኃይላችን" የመሳሰሉት ተወዳጅነት አግኝተውላታል።
Seledadotio

አንጋፋዋ ድምፃዊት ራሄል ዮሐንስ
ከግራውንድ ሆስተስ እስከ ታዋቂ ድምፃዊነት ከመቀጠር ወደ መቅጠር ፣ ከሰራተኝነት ወደ ጀኔራል ማናጀርነት ተሸጋግራም አገልግላለች፡፡ ራስ ሆቴል ፣ ጊዮን ሆቴል ፣ አርጀንቲና ፣ ታንዛኒያ እና ፊሊፕስ ኢምባሲ ፣ ሸበሌ ሆቴል ፣ ሂልተን ሆቴል ፎርሺፕ ትራቭል ፣ አነስ ያለች ሆቴል (በግሏ ከፍታ) ሰርታለች፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ቀስ በቀስ ወደ ድምፃዊነቱ አምርት በርካታ ስራዎቿን ለአድናቂዎቿ ያደረሰችው። የወይን ስፔሳሊስቷ አርቲስት ራሄል ዮሀንስ።
መዲናችን አዲስ አበባ ካዛንቺስ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ሚያዚያ 27 ቀን 1939 ዓ.ም ነው የተወለደችው፡፡ ለቤተሰቦቿ የበኩር ልጅ የሆነችው ራሄል ዮሀንስ ከታናሽ ወንድሟ ድምፃዊ ሰይፉ ዮሀንስ ጋር የቄስ ትምህርትን እስከ ዳዊት ቆጥራለች፡፡ አንጋፋው ድምፃዊ ሰይፉ ዮሀንስን “ሀና ሀና” በተሰኘ ስራው ታስታውሱታላችሁ፡፡
ራሄል የ 1ኛ ደረጃ ትምህርቷን በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት ተከታትላለች፡፡ ወደ ሆቴል ሙያ ያዘነበለችው ራሄል ዮሀንስ በራስ ሆቴል ለ 3ወር አጠቃላይ የመስተንግዶ ስነ ስርዓት ተምራለች፡፡ በመቀጠልም በምርጫዋ በጊዮን ሆቴል የወይን መስተንግዶ ትምህርትን ለሁለት አመታት ተከታትላ ዲፕሎማ አግኝታለች፡፡
ድምፃዊት ራሔል በሆቴል ቆይታዋም ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ባለስልጣናትን እና የአፍሪካ እንዲሁም ሌሎች ሀገራት መሪዎችን አስተናግዳለች፡፡ እነ ጋማል አብዱል ናስር ፣ ሴኩ ቱሬ ፣ ክዋሚ ንኩርማ እና ሌሎችንም፡፡ ገና በልጅነቷ ሆስተስ (የበረራ አስተናጋጅ) የመሆን ህልም የነበራት በኋላ ግን ግራውንድ ሆስተስ (የሆቴል አስተናጋጅ) የሆነች ራሄል ዮሀንስ በሆቴሎቹ ባገለገለችባቸው ጊዜያት ውስጥ ከ 80 እስከ 200 ብር ይከፈላት ነበር፡፡ ቲፕ ተሰብበስቦ ለሁላችንም እንደ የደረጃችን በፐርሰንት ይከፈለን ነበርና ከደሞዛችን ይልቅ ይኸ ሻል ያለ ነበር ትላለች ራሔል ያንን ጊዜ ስታስታውሰው፡፡
አንድ ቀን ድምፃዊ ከተማ መኮንን እና ሌሎች አንጋፋ ሰዎች በቤቷ ተገኝተው ምግብ ከተመገቡ በኋላ በጋሽ ከተማ አጋፋሪነት ጨዋታው ደራ፡፡ እሱ ማሲንቆ ሲጫወት እሷም ማንጎራጎሯን ቀጠለች በድምጧ የተደነቁት ሰዎች ምግብ ቤቱን ትታ ዘፋኝ አንድትሆን ይገፋፏታል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ወደ ድምፃዊነት ሙያ ገባች፡፡
ከዚያም ከጥቂት አመታት በኋላ በ 70ዎቹ (1973/74ዓ.ም) የመጀመሪያ ስራዋን “አንቺ ባለድሪ” የተሰኘ አለበም ከሻምበል በላይነህ ጋር አወጣች፡፡ በወቅቱም ለዚህ ስራ አምባሳል ሙዚቃ ቤት 10,000 ብር ከፍሏታል፡፡ በዚህ ካሴት ውስጥ በግጥም – ይልማ ገብረአብ እና በዜማ – አበበ መለሰ ተሳትፈዋል፡፡ ከዚያ በኋላ በ 1983 ዓ.ም ከታዋቂዎቹ የሀገር ባህል ተጨዋቾች ከባህሩ ቀኜ እና ከይርጋ ዱባለ ጋር የሰራቻቸው ዘፈኖችም በህዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ናቸው፡፡
አራዳ ፣ ትዝታ ፣ ምኒልክ እና ሀገሬ ኢትዮጵያ ያሉት ደግሞ በግሏ ከሰራቻቸው ተወዳጅ ዜማዎቿ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ አርቲስት ራሄል ዮሀንስ ሙዚቃ እስካቆመችበት ጊዜ ድረስ ወደ 13 የሚጠጉ አልበሞችን ሰርታለች፡፡ በነገራችን ላይ ድምፃዊት ራሄል ዮሀንስ ከዘፋኝነቷ ባሻገር የዜማ ደራሲም ጭምር ናት፡፡
ለአብነትም ምኒልክ ፣ ጀግናው ሰራዊት ፣ እንደ እየሩሳሌም (የአስናቀች ወርቁን በድጋሚ በራሷ ዜማ የሰራችው) እና ሌሎችንም ዜማ ደርሳለች፡፡ የመጨረሻ ስራዋ “ዘናበል” የሚል አልበሟ ሲሆን በያሬድ ተፈራ የተቀናበረ አልበም ነበር፡፡
በአንድ ወቅት እንዲህ ተብሎም ተገጥሞላት ነበር፡-
“አዝማሪ ይሏታል ራሄል ሆዴን
አዝማሪ ይሏታል ጭንቄ ራሄልን
ልጆች ለማሳደግ ያደረገችውን፡፡” በማለት ……..
የሁለት ወንድ እና አራት ሴት ልጆችን ያፈራቸው ድምፃዊ ራሔል አሁን ላይ አያት የሆነችው ራሄል በርከት ያሉ የልጅ ልጆችንም አይታለች፡፡
Ⓒ EthiopiaAnything

“አረጋዊው እና ባህሩ”
#ethiopia | በፈረንሳይ ሞርሌ ከተማ “ኤሮ” በተሰኘው የጥበብ ባለሙያ የተሳለውና “አረጋዊው እና ባህሩ ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲስ የግድግዳ ላይ ሥዕል የበርካቶችን ቀልብ እየሳበ ይገኛል።
ይህ በጥቁርና ነጭ ቀለማት ብቻ ያሸበረቀው ማራኪ የጥበብ ሥራ፤ አረጋዊ ባህረኛን የባህር ላይ ወፍን፣ የመብራት ማማን፣ አለቶችን፣ ጉምና ማዕበሎችን በአንድ ያረጀ ግድግዳ ላይ አዋህዶ በማቅረብ የከተማዋን ጥንታዊ የወደብ ላይ ትዝታዎች በሚያስደምም ሁኔታ ሕያው አድርጎታል።
የዚህ ድንቅ የጥበብ ሥራ ርዕስ ዓለም አቀፍ ሥነ-ጽሑፍንና የአካባቢውን ታሪክ በአንድ ላይ ያሰናሰለ መሆኑ ይበልጥ ልዩ ያደርገዋል።
በስያሜው ላይ የተጠቀሰው ሐረግ እ.ኤ.አ. በ1953 በልብወለድ ዘርፍ የፑሊትዘር ሽልማትን ያሸነፈውን ታዋቂውን የኧርነስት ሄሚንግዌይ ታሪክ የሚያስታውስ ሲሆን ሥዕሉ የሞርሌ ከተማ ከዚህ ቀደም የነበራትን ታላቅ የባህር ላይ ንግድ ማዕከልነት ታሪክ በሚገባ የሚዘክር መሆኑ ተገልጿል።

እንደገና የተወለደው ቀበና…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
በ87 ነጥብ 6 ሔክታር መሬት ያረፈው እና 10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ፕሮጀክቱ የወንዝ መከላከያ ግንቦችን፣ ዘመናዊ ድልድዮችን እና ሰፊ አረንጓዴ ሥፍራዎችን ይዟል።
ይህ ቀበናን ውብ ገጽታ ያለበሰው እና የትውልድ ዐሻራ ያረፈበት ፕሮጀክት ነዋሪዎቿን አስደስቷል።
የቀበና ነዋሪዎቹ አቶ አለማየሁ፣ አቶ አወቀ እና ወ/ሮ መሰሉ ስለ ቀበና ልማት ድሮና ዘንድሮን እያነሱ ከፋና ፖድካስት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
አቶ አወቀ÷ የነዋሪው ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ንጹህ የነበረው የቀበና ወንዝ እየተበከለ እና የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ እየተለቀቀበት ቀድሞ የነበረውን ውበትና ገፅታውን እንዳጣ ያስታውሳሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለነዋሪው የማይመች እና ጤናን የሚነሳ ሆነ ይላሉ፡፡
ቀበና አካባቢ ተወልደው ላለፉት 49 ዓመታት የኖሩት ወ/ሮ መሰሉ በበኩላቸው÷ የቀበና የቀድሞ ገፅታ በጫካ የተሸፈነ መሆኑን ይናገራሉ። በቀበና ወንዝ ቅዳሜ እና እሑድ ልጆች ጊዜያቸውን በዋና እና ሌሎች ጨዋታዎች የሚያሳልፉበት እንደነበር ያስታውሳሉ።
በሒደትም ቦታው መበከሉንና ለመዋኘት ቀርቶ ለማየት ደስ ወደማይል ገጽታ መቀየሩን ነው የሚያስረዱት፡፡
ሌላው የቀበና ነዋሪ አቶ አለማየሁ በ1959 ዓ.ም ነው በቀበና የተወለዱት፡፡ ስለአከባቢውም ብዙ ትዝታ አላቸው፡፡ መንገዱ አስቸጋሪ ስለነበር እና በአንድ ወቅት አዳልጧቸው ቀበና ወንዝ ውስጥ በመግባታቸው ከስራ እንደቀሩ ያስታውሳሉ፡፡ አሁን ያ ሁሉ ተለውጦ እንዲህ ተውቦ በማየታቸው "ራሴን እንደ እድለኛ እቆጥረዋለሁ" ይላሉ፡፡
"ቀደምት ሰዎች እኔ ያየሁትን ቢያዩ" ሲሉ ቁጭታቸውን የገለፁት ነዋሪው በተወለዱበት ቦታ ላይ በአሁኑ ወቅት ውብ የህጻናት መጫወቻ መሰራቱን በማየታቸው እንደተደሰቱ ተናግረዋል። አቶ አለማየሁ በዚህ ምክንያት "አባቴ እዛ ቦታ ላይ ሐውልት እንደተሰራለት እቆጥረዋለሁ" ሲሉም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ መሰሉ በተሰራው ልማት የቀበና ገጽታ ተለውጦ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸው÷ ልጆች እና ወጣቶች ምቹና ጤናማ በሆነ አካባቢ እንዲያድጉ ያስችላል ብለዋል፡፡
በልማቱ ቀበና ውበት መላበሷ እንዳስደሰታቸው የሚናገሩት አቶ አወቀ÷ የአካባቢው ማሕበረሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ በመሆኑ ሊጠብቀውና ሊንከባከበው ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ቀበና ድምጻዊ ጸሀዬ ዮሐንስ የተወለደባት፣ የቦረቀባት፣ የዋኘባትና ያዜመላት መሆኗን የገለጹት አቶ አወቀ÷ "ጸሐዬ ቀበና ላይ የሙዚቃ ድግስ አዘጋጅቶ ቀበናን ቀበና ማሰኘት አለበት" ነው ያሉት፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ
የቀበና ነዋሪዎች ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://youtube.com/watch?...

የትውልዱ የቱሪዝም ዘርፍ አለኝታ ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እልፍ በሆኑ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች የተሞላች ነች፤ ነገር ግን ቀደም ሲል ለዘርፉ በተሰጠው አነስተኛ ግምትና አስተዳደራዊ ችግሮች ሳቢያ እነዚህ ሀብቶች ለዐይን የማይሞሉ፣ ጎብኚዎችን የማይስቡ፣ ከገቢም አንጻር ይህ ነው የማይባል አስተዋፅኦ ሳይኖራቸው ዘመናት ተቆጥረዋል።
ከሀገራዊ ለውጥ በኋላ ቱሪዝም እንደ ሀገሪቷ የብልጽግና ምሰሶነት ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ችሏል።
በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ተጠንስሰው ለፍሬ በቅተዋል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች የሀገርን እምቅ ውበት ከመግለጥ አንጻር ከፍተኛ እመርታን እያሳዩ ሁለንተናዊ እድገትንም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ርምጃ ሆነው ውጤታቸው መታየት ጀምሯል።
ከገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው በስሙ የሚጠራ ከተማ የተሰየመለት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በተሁለደሬ ወረዳ የሚገኘው የሎጎ ሐይቅ አንዱ ነው፡፡
ይህ ሐይቅ ከአዲስ አበባ በ430 ኪሎ ሜትር፤ ከደቡብ ወሎ ዞን መቀመጫ ደሴ ከተማ ደግሞ በ30 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከሐይቅ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ከ23 እስከ 88 ሜትር ጥልቀት ያለው ሐይቁ ከባህር ወለል በላይ 1 ሺህ 950 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የሚሸፍነው የመሬት አካል ደግሞ 35 ስኩዌር ኪሎ ሜትር በላይ ነው።
ይህ ሐይቅ የተንሰራፋበት መልክዓ ምድር በሰንሰለታማ ተራሮች የተከበበ፣ ለዕይታ ማራኪ፣ የበርካታ ጎብኚዎችን ቀልብ መሳብ የሚችል ሃብቱ ያለተነካ ድንቅ የመስህብ ስፍራ ነው፡፡
ሐይቅ ከተማ ኢትዮጵያውያን የሚታወቁበት የአብሮነት እሴት በተጨባጭ የሚታይበት ስፍራ እንደሆነ በርካቶች ይስማሙበታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቦታውን እንዲህ ሲሉ ገልጸውት ነበር፤ "ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ገራገርና ቅን የሆነውን የወሎ ሕዝብ ውብ ባህልና እሴት ለማስተዋወቅ ያስችላል፤ ክርስትና እና እስልምና ተዋደው እና ተከባብረው የሚኖሩበት ድንቅ አከባቢ፤ የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ደግሞ የስፍራው ታላቅ ሃብት ነው"፡፡
በዚህ ከተማ የሚገኘው ትልቅ ውበት ነው ታድያ፤ ከትኩረት ማጣት አንጻር ከተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ብሎም ከዓለም ዕይታ ተሸሽጎ የቆየው።
በገበታ ለትውልድ ውጥን ፕሮጀክቶች ስር በመታቀፍ ቀን ከሌት ስራው በጥራትና በፍጥነት ተከናውኖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጥር ወር 2018 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።
በሐይቁ ላይ የተገነባው ሪዞርት በመደመር እሳቤ መንግሥትንና የግሉን ዘርፍ በአንድነት በማሳተፍ የተገኘውን ውጤት ጽኑ መሰረት እንዲኖረው አስችሏል፡፡
በ13 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምግብ ቤቶችን፣ የመዋኛ ገንዳዎችን፣ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገዶችን እና የሄሊኮፕተር ማረፊያን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት አገልግሎቶችን በአንድነት ይዟል፡፡
ልዩ ልዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ስፍራዎች፣ ለዕይታ የሚማርኩ አረንጓዴ አካባቢዎችን አቅፎ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገራት ጎብኚዎች የማይረሳ ትዝታን የሚፈጥር ውብ ቦታ ነው፡፡
የቱሪዝም ልማትን ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ ከዘላቂ እና ከአካታች ሁለንተናዊ እድገት ጋር በማቀናጀት፣ ሪዞርቱ የወሎ ሕዝብ ያለውን ታላቅ ባህላዊና ተፈጥሯዊ እሴት ለተቀረው ዓለም ማኅበረሰብ ማስተዋወቅ የሚቻልበት ሰፊ ገበታ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ለማህበረሰቡ የስራ ዕድልን ከመፍጠር ባሻገር የአካባቢውን ቱሪዝም፣ የትራንስፖርት እንዲሁም የግብርና ዘርፎች የሚያነቃቃ በተጨማሪም ለአምራቾችና ስራ ፈጣሪዎች አዲስ የገበያ ትስስርን በመፍጠር ለኢኮኖሚ እድገትና ብልጽግና አለኝታ ሆኖ ያገለግላል።
በመልካም ፍቃዱ

ደስተኛ - የድምፃዊት ቤተልሄም ሸረፈዲን
በኩራ ስትሪም ተለቀቀ
ስሜትን የሚነካ፣ ፍቅርን የሚያወሳ እና በዜማ ውበት የተሞላ አዲስ የሙዚቃ ሥራ ይዘን መጥተናል።
💫 የልብን ትዝታ፣
💫 የፍቅርን ስሜት፣
💫 የሕይወትን ውብ ትርጓሜ በሚያንጸባርቅ ዜማ፣
"ደስተኛ" አሁን ለአድማጮች ቀርቧል!
🎧 በተለያዩ የሙዚቃ መድረኮች ያዳምጡት፤
📺 የሙዚቃ ቪዲዮውንም በይፋዊ ቻናሎች ይከታተሉ።
በኩራ ስትሪም— የልብ ቃል፣ የስሜት ዜማ ይበላችሁ መጥቷል! 🎵✨
https://youtube.com/kura_...
#ደስተኛ #ቤተልሄም_ሸረፈዲን #አዲስ_ሙዚቃ #ethiopianmusic #musicrelease

"የ10 ደቂቃ ዋጋ"
።።።።።።።።
አንድ ትንሽ ልጅ የአባቱን አይን እያየ፦
"አባዬ... በአንድ ሰዓት ስንት ብር ታገኛለህ?"
አባቱም በስራ የደከመ ሰውነቱን ለማሳረፍ ወደ ሶፋ ጠጋ እያለ "ለምን ትጠይቀኛለህ?" አለው።
ልጁ በቀስታ፣ "እባክህ ንገረኝ..." አለ።
"500 ብር።"
ልጁ እንደገና ጠየቀ፦
"250 ብር ልታበድረኝ ትችላለህ?"
አባቱ ተናደደ። "መጫወቻ ልትገዛ ከሆነ አኹን ቀጥ ብለህ ወደ ክፍልህ ሂድ!"
ልጁ ዝም ብሎ ገባ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባቱ ተረጋጋ። ወደ ክፍሉ ገብቶ 250 ብሩን ሰጠው።
ልጁም ከትራሱ ስር ያለውን ገንዘብ አወጣ። ሁሉንም ቆጠረ።
አባቱም "ምን እያደረክ ነው?" አለው።
ነገር ግን ልጁ ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፦
"አባዬ... አሁን 500 ብር ሞልቶኛል። ነገ ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት ታሳልፋለህ?" አለው።
🕰 Quality Time ውድ ስጦታዎችን አይፈልግም። የወላጅን መገኘት ብቻ ይፈልጋል። በዋናነት አጭር የደቂቃዎች ቆይታ አስር ደቂቃ ሊኾን ይችላል ግን ደግሞ ተከታታይነት የሚፈልግ ሲኾን ሃሳብን ከሚበትን ስክሪን መራቅን ይጠይቃል። በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ ተአምራዊ ለውጥ የማምጣት አቅም አለው።
ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚያስታውሱት የገዛህላቸውን ነገር ሳይሆን፣ ከእነሱ ጋር ያሳለፍከውን ጊዜ ነው።
💡 ስለዚህ ዛሬ ለልጆቻችን በመገኘት አይረሴ ትዝታዎች ይኑሩን መልዕክቴ ነው።
✍️ ብርሃኑ በላቸው አሰፋ
የክቡር ልጆች ደራሲ ( የ2025 ሕንጸት ተሸላሚ መጽሐፍ)
https://t.me/childdevtnetw...

ብራዚል ያነባች ዕለት - የጀርመኑ ዓለም ዋንጫ ትዝታዎች
****************
ያኔ ብራዚል እንዲህ ትሆናለች፣ በመሰል ደረጃ ላይ ትገኛለች ብለው ብዙዎች አልጠበቁም። ሁለት አስርት ዓመታት አልፈው ወደ ኋላ መለስ ብለው ሲያስታውሱት የሆነው ግን እንደዚያ ነው። የ2006 ዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ የቀደመውን አሸናፊ ፈረንሳይ እና የወቅቱን ሻምፒዮን ብራዚልን አገናኝቷል።
የ21ኛው ክፍለ ዘመን የብራዚል ወርቃማ ትውልድ፣ ኳስ የጥበብ አውድማ መሆኑን ዳግም ያስመሰከሩት ጥበበኞች ስብስብ ጀርመን ምድር ለዓለም ዋንጫው ሲዘልቁ ለ6ኛ የመድረኩ አሸናፊነት፣ ለተከታታይ ሻፒዮንነት ነው የታጩት።
ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማ፣ ሮናልዲንሆ ጎቾ፣ ካካ፣ ካፉ፣ ሮቤርቶ ካርሎስ፣ አድሪያኖ እና ዚ ሮቤርቶን የመሰሉ ክዋክብት እንደ ምን ይዘነጋሉ? የሰው አዕምሮ ሊዘነጋቸው ቢፈቅድ እንኳ የእግር ኳስ ታሪክ ሊረሳቸው አይቻለውም። ትዝታቸው ርቆ ያልራቀ፣ ደብዝዞ ያልጠፋ፣ ቀጥኖ ያልተበጠሰ ህልው ነው። ከመዘንጋት የራቀ ታሪክ!
የዚያች ዕለት ግን ቀን ከነርሱ በተቃራኒ የቆመች መሰለች። የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በተለይም ዚነዲን ዚዳን በዚያች ቀን ስል፣ አስፈሪ እና ባለ ግርማ ሞገስ ሆነው ነው የቀረቡት።
ዚዳን ፀጉሩ እንደከዳው፣ የጎልማሳነት ደጃፉ ላይ እንደቆመ፣ ከእግር ኳስ የመሰናበቻ ቀናቱ እንደደረሰ ሳይሆን የ20ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሚገኝ ወጣት ነበር ይቦርቅ የነበረው።
በዚያ ጨዋታ ዚዳን የነበረው እንቅስቃሴ በዓለም ዋንጫ ታሪክ በግለሰብ ደረጃ ከተደረጉ እንቅስቃሴዎች ምርጡ እንደሆነ የብዙዎች እምነት ነው። የዘመን ተጋሪው ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማም ያን ጨዋታ አስመልክቶ በሰጠው ቃለ-መጠይቅ “በዚያ ጨዋታ ዚዳን ያደረገው እንቅስቃሴ ያለማወላዳት በዓለም ዋንጫው ታሪክ ከታዩ ምርጥ ብቃቶች እንደ አንዱ ሊመደብ የተገባ ነው” ነበር ያለው።
ፈረንሳይ በቴሪ ሄንሪ አማካኝነት ባስቆጠረችው ግብ ጨዋታውን 1 ለ 0 አሸንፋ የወቅቱን የዓለም ሻምፒዮን ከውድድሩ አሰናበተቻት። ያኔ ብዙ አለማመኖች ነበሩ፣ የሆነው ከብዙዎቹ ጥበቃ በተቃራኒ ነው።
የ1998 ዓለም ዋንጫ አሸናፊ፣ የነ ዚነዲን ዚዳን ሀገር የወቅቱን የዓለም ሻምፒዮን ከዓለም ዋንጫ አስወጣቻት የሚለው በመጨረሻ የዳኛውን ፊሽካ ተከትሎ የተሰማው ዜና ነበር።
ያ ታሪክ በፍራንክፈርቱ ባልድ ስታዲየም የመጫወቻ ሜዳ ብቻ ተፈፅሞ ያበቃ አልሆነም። ወደ ካናሪንሀ መልበሻ ክፍልም ተከትሎ አምርቷል። በዕለቱ ልዩ የነበረው፣ ለቴሪ ሄንሪም ለግብ የምትሆነውን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለው ዚነዲን ዚዳን ወደዚያች መልበሻ ክፍል አመራ።
አንድም ሊያፅናና አንድም በትልልቅ የእግር ኳስ መድረኮች እንደተለመደው መለያ ሊቀያየር።
‛ኤል ፌኖሜኖ’ ይህን የዚዳን ተግባር በበጎ አልተመከተውም። ሮናልዶ ከ20 ዓመታት በኋላ ሁነቱን አስመልክቶ ሲናገር “ሁላችንም ዛሬ ድረስ አብረን የቀጠልን ጓደኛሞች ነን፣ እርሱ ወደ መልበሻ ክፍል ሲገባ ግን የነበረው ድባብ አስፈሪ ነበር።
ብዙ ተጫዋቾች እያነቡ ነበር፤ እናም መለያ ለመቀያየር ወደ መልበሻ ክፍሉ የመጣበት ሰዓት ትክክለኛ እንዳልሆነና እንዲመለስ አስረግጬ ነገርኩት” ይላል።
እንደ ሮናልዶ እምነት ያች ዕለት የዓለም ዋንጫን ታሪክ ራሱን ቀይራለች። በእርግጥም በብራዚል በኩል ሆኖ ለተመለከተው ብዙ እውነት የሚመስሉ ነገሮችን የያዘ ሃሳብ ነው።
ለዓለም እግር ኳስ የስኬታማነት ናሙና የሆኑ ክዋክብትን ያበረከተችው ብራዚል ከትልቁ መድረክ አሸናፊነት እንደተናጠበች ሩብ ምዕተ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው። እነዛን ኮከቦች ግን እግር ኳስ ሊዘነጋቸው አይቻለውም።
በእርግጥ ፈረንሳይ አስከ ፍፃሜ ብትጓዝም፣ በዚነዲን ዚዳን እና ማርኮ ማታራዚ ድራማ በታጀበው ጨዋታ፣ በነ ማርሴሎ ሊፒ እና አንድሪያ ፒርሎ ጣሊያን ተረታ ለሌላ ዓለም ዋንጫ አሸናፊነት 12 ዓመታት ለመጠበቅ ተገዳለች።
ዚዳንን የ2006ቱ ዓለም ዋንጫ ‛አንተ በእግር ኳስ ስንብትህ ደጃፍ ላይ ቆመህ በእኔ ያበራህ ኮከብ ነህ’ ብሎታል።
ዓለም ዋንጫ ትዝታ ነው። ድልና ሽንፈት፣ ደስታ እና ሀዘን፣ ሳቅ እና ለቅሶ የሚመላለስበት የስፖርት አውድማ፤ የትውስታ መቼት ነው። መንገዱ ይቀጥላል!
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #brazil #sports #japan #ebc Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

ባለውለታዋን እናት
ከ12 ዓመታት በኋላ የተገለጠ የደግነት ታሪክ
ብሩክታይት ሽመልስ ባለውለታዋን እናት አገኘች፤ የእንባና የምስጋና አፍታ
#ethiopia | አንዳንድ የሰው መልካምነት ከጊዜ ጋር አይረሳም፤ ዓመታት ቢያልፉም በሰው ልብ ውስጥ እንደ ብርሃን ይኖራል። በ"ሰይፉ በኢቢኤስ" ፕሮግራም ላይ የታየው የብሩክታይት ሽመልስ (ብርክቲ) እና የወይዘሮ አዜብ ገብረ መስቀል መገናኘት የዚህ እውነት ሕያው ማሳያ ነው።
ያልተረሳ ውለታ
ከ12 ዓመታት በፊት፣ የ15 ዓመት ታዳጊ የነበረችው ብሩክታይት ከሐዋሳ ወጥታ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳለች ጭንቀትና ፍርሃት ውስጥ ገብታ ነበር። በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ሕይወቷን የቀየረች አንዲት ሴት አገኘቻት፤ ዛሬ የምትጠራት "ባለውለታዬ" ብላ ነው።
"ማን እንደላካት አላውቅም፤ እኔ ግን እግዚአብሔር የላከልኝ ሰው ነበረች ብዬ አምናለሁ" ስትል ብሩክታይት የዚያን ቀን ትዝታ በእንባ አስታወሰች።
አንዲት እናት... አንድ የሰብአዊነት ውሳኔ
ወይዘሮ አዜብ ገብረ መስቀል በዚያ ዕለት ብሩክታይትን በአውቶቡስ ላይ አገኘቻት። የታዳጊዋ ጭንቀትና ፍርሃት በፊቷ ይነበብ ነበር።
ምሳ እንድትበላ ብትጋብዛትም እንባዋን ማቆም አልቻለችም። ወይዘሮ አዜብም ጉዳዩን በእርጋታ ለማወቅ ሞከረች፤ ከዚያም ወደ ቤቷ ወስዳ አሳረፈቻት፣ አረጋጋቻት፣ ከቤተሰቦቿም ጋር እንድትገናኝ አደረገች።
"እናትሽና አባትሽ በጣም ይጨነቃሉ፤ የምትፈልጊው ቦታ በሰላም ትደርሻለሽ" ብላ በፍቅር ያረጋጋቻትን ቀን ዛሬም በግልጽ ታስታውሳለች።
"ይህ የኢትዮጵያዊነት ባህል ነው"
ወይዘሮ አዜብ ያደረገችውን እንደ ልዩ ጀግንነት አትቆጥረውም። ይልቁንም እውነተኛ ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ትገልጻለች።
"እኔ ልጅ ያለችኝ እናት ነኝ። ያንን ልጅ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቢያገኛት እንደዚያው ያደርግላት ነበር። ይህ የባህላችንና የማንነታችን መገለጫ ነው" ብላለች።
የደግነት ዋጋ
በፕሮግራሙ ላይ የተፈጠረው መገናኘት የተመልካቾችን ልብ ነክቷል። ብሩክታይት ባለውለታዋን እናት አቅፋ ስታለቅስ፣ ወይዘሮ አዜብም በደስታ እንባ ታጠበች።
ይህ ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፤ የሰው መልካምነት አይጠፋም፣ አይረሳም። በአንድ አስቸጋሪ ወቅት የተዘራ የደግነት ዘር፣ ከዓመታት በኋላም በምስጋና፣ በክብርና በፍቅር ፍሬውን ያፈራል።
ወይዘሮ አዜብ የተናገረችው አንድ ሐረግ ደግሞ የዚህን ታሪክ ሙሉ ትርጉም ይገልጻል፦
"ለሰው ብትኖር ምንም አትጎዳም፤ በምድርም በሰማይም ዋጋውን ታገኛለህ።"

Comments