16 days ago
አዲስ አበባ እና ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራረሙ
#ethiopia | አዲስ አበባ እና ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ጋር የተፈረመው ስምምነት፤ በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ በቱሪዝም (ስፖርት ቱሪዝምን) ጨምሮ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የባህልና የታሪክ ልውውጥን የሚያጠናክር መሆኑን አመልክተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ እና የአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የባህልና የታሪክ ልውውጥ የሚያጠናክር ነው፡፡
በተጨማሪም በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ የስፖርት ቱሪዝምን ጨምሮ በቱሪዝም ልማት የሁለቱን ከተሞች ትብብር ያጠናክራል ነው ያሉት፡፡

************
አዲስ አበባ እና የአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ የእህትማማች ከተሞች (Sister Cities) ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ (ስፖርት ቱሪዝምን ጨምሮ) በቱሪዝም እና በሁለቱ ህዝቦች መካከል የባህልና የታሪክ ልውውጥን የሚያጠናክር መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
#ethiopia #azerbaijan #addisababa #baku #sistercities #ebc

17 days ago
አዲስአበባውያን በአዘርባጃን ባኩ ከተማ
📌በአዘርባጃን ባኩ ከተማ ያደረግነው ጉብኝት ለከተሞቻችን ልማት ትልቅ ልምድ የቀሰምንበት ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም አቀፉ የከተሞች ፎረም ጎን ለጎን በአዘርባጃን ባኩ ከተማ ያደረግነው ጉብኝት ለከተሞቻችን ልማት ትልቅ ልምድ የቀሰምንበት ነው አሉ፡፡
በፎረሙ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ በባኩ ከተማ የተለያዩ የመስህብ ስፍራዎችን እና የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ የባኩ ከተማ የከተማ እድሳት ሂደት የአዲስ አበባን እና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችን ተሞክሮ የሚያንፀባርቅ ነው።
ጉብኝቱ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የጀመርናቸውን የከተማ ልማት፣ የቅርስ እድሳትና ጥበቃ ስራዎችን ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ተጨማሪ ትልቅ ልምድ የተቀሰመበት ነው ብለዋል።
አሮጌና ጎስቋላ የነበረውን ስፍራ ሙሉ በሙሉ በማፍረስና እንደ አዲስ በመገንባት እንዲሁም ጥንታዊቷ ከተማ በመባል የሚታወቀውን የከተማዋ ክፍል በጥንቃቄ በማደስ ለጉብኝት ክፍት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
ይህ የከተማ እድሳት ሂደት የኢትዮጵያን ተሞክሮ የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልጸው፥ ታሪክና ቅርሶችን ጠብቆ በማደስ ጎስቋላ አካባቢዎችን በአዲስ መልክ እየገነባን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ለአብነትም በፒያሳ እና አራት ኪሎ ያሉ ጥንታዊ ሕንፃዎችን፣ የመጀመሪያውን ሲኒማ ቤት፣ የመጀመሪያውን ማዘጋጃ ቤት፣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን እንዲሁም የተለያዩ ሐውልቶችን እድሳት ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር እንደ ሐረር ጀጎል ግንብ፣ የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግሥት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እና የጎንደር ፋሲል ቤተ መንግሥት የመሳሰሉትን ታላላቅ ቅርሶች በማደስ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
እጅግ ጎስቋላና ለመኖር ምቹ ያልነበሩ መንደሮችን በማፍረስ ዘመናዊና ምቹ በሆነ መልኩ መገንባታቸውን ጠቅሰው፥ በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች በተሳካ ሁኔታ የተተገበረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የዚሁ ራዕይ ዋነኛ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።
ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ይበልጥ ምቹ፣ ማራኪ፣ አረንጓዴና ዘመናዊ በማድረግ ረገድ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን በማስፋት፣ ለእግረኛና ለብስክሌት ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን በመፍጠር እንዲሁም የከተማዋን ገጽታ በመቀየር እጅግ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ነው ያሉት።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

18 days ago
በዓለም አቀፉ የከተሞች ፎረም የሀገራችንን እና የመዲናችንን እያስተዋወቅን እንገኛለን፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
************
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአዘርባጃን መዲና ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው ዓለም አቀፍ የከተሞች ፎረም (13th World Urban Forum) ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
ፎረሙ “ቤት ለሁሉም፤ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ጠንካራ ከተሞች እና ማህበረሰቦች” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባኤውም ዓለም አቀፋዊ የመኖሪያ ቤት ችግርን መፍታት፣ ዘላቂ የከተማ ልማት፣ ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ ከተሞችን መገንባት፣ የአየር ንብረት እና የመኖሪያ ቤት ግንኙነቶች፣ መልሶ ግንባታ እንዲሁም ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት በዋናነት እየተመከረባቸው መሆኑን በፎረሙ ላይ የተሳተፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
በፎረሙ ላይ ጠቃሚ የልምድ ልውውጥና የመስክ ጉብኝቶች እየተደረጉ እንደሚገኝ የጠቆሙት ከንቲባዋ ፤ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከውይይቶቹ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን እና የመዲናዋን አዲስ አበባን ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ሰፊ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም መሠረት በዛሬው ዕለት በተከፈተው ኤክስፖ ላይ መንግሥት ከግል ዘርፍ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ገጽታ የሚገልጽ ልዩ ፓቪልዮን (ቡዝ) በማዘጋጀት፤ የተከናወኑ ዘላቂ የከተማ ልማት ሥራዎችን በጽሑፍ፣ በቪዲዮ እና በቪርቹዋል ሪአሊቲ ቴክኖሎጂዎች ለታዳሚዎች የማስተዋወቅ ሥራ በስፋት እየተሠራ ይገኛል።
#worldurbanforum #mayoradanechabiebie #ethiopia #addisababa #bakuazerbaijan #ethiopianbroadcastingcorporation

2 months ago
አደገኛው የጥፋት መረብ ተበጠሰ‼️ አደገኛው የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊትና ግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ::
አዲስ አበባ — መጋቢት 28፣ 2018 በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት ለገደል የዳረገውና በዓለም አቀፍ ደረጃ በብርቱ ሲፈለግ የነበረው አደገኛው የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) በመጨረሻም በፌደራል ፖሊስ ብርቱ ክንድ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህ ግለሰብ በሰዎች መነገድን እንደ ትርፋማ ንግድ ተመልክቶ፣ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ለሞትና ለስቃይ የዳረገ ጨካኝ ወንጀለኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ይፋ እንዳደረገው፣ በዋና አዘዋዋሪው ይትባረክ ዳዊት ላይ የተመዘገቡት ወንጀሎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
1. ከ3,000 በላይ ዜጎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር፣
2. ከ100 በላይ ሰዎችን ለሞት መዳረግ፣
3. ከ50 በላይ ሴቶች ላይ አስከፊ የጥቃት (የደፍሮት) ወንጀል እንዲፈጸም ማድረግ።
ፖሊስ ይህን ድንበር ተሻጋሪ ወንጀለኛ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከROCK (The Regional Operational Centre) ጋር የቅርብ የመረጃ ልውውጥ ሲያደርግ ቆይቶ፣ በመጨረሻም በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ላይ በድንገተኛ አሰሳ በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።
በምስሉ ላይ የሚታዩትና በወንጀል ተባባሪነት የተያዙት ግለሰቦች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
* ይትባረክ ዳዊት አለሙ (ዋናው አደራጅ/አዘዋዋሪ)
* ሰለሞን ቀለም ደበበ
* ቤተልሔም ካሳ አላሮ
* መብራቶም ኢታይ ሀሽ
* ሀፍቶም ሀይላይ ሀይሉ
* መርሃዊ ታቦት ገብረሕይወት
* ራሄል አለሙ ገ/ጊዮርጊስ
* አብዱሰላም ቲጃኒ አባኩምሳ
* በእምነት ስራቃ ሃጎስ
* ሺሻይ ኪዳኔ ጉዕሽ
የፖሊስ መልዕክት፡ "የሰው ልጅ የንግድ ዕቃ አይደለም!" ፌደራል ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለዓቃቢ ህግ የላከ ሲሆን፣ ፍትህ ለተጎጂዎች ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል።
Via የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
seledadotio

Sponsored by
Surafel
3 months ago
ኢትዮጵያና አዘርባጃን በመከላከያና በኢኮኖሚ መስኮች ለመተባበር ተስማሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በባኩ ካደረጉት የመጀመሪያ ይፋዊ ጉብኝት ከአዘርባጃን ከፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊየቭ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሁለቱ አገራት በተለይ በመከላከያ ትብብር ላይ ያተኮሩ የመግባቢያ ሰነዶችን ተፈራርመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአቪዬሽን፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በነፃ ንግድ ቀጠናዎች ላይ የተጀመሩ ሥራዎች እያደጉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከአዘርባጃን አቻው ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማምቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዘርባጃን ገቡ
#ethiopia | በኢትዮጵያና በአዘርባጃን መካከል በየጊዜው እያደገ የመጣውን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በመሆን ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ የሚገኘው ሄዳር አሊዬቭ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የጉብኝቱ ትኩረትና ፋይዳ
ይህ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያና በአዘርባጃን መካከል ያለው ቅርርብ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በዲፕሎማሲያዊ መድረኮች ጎልቶ የታየ ሲሆን፣ የዛሬው ጉብኝትም የዚሁ ስኬታማ ትብብር ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
በቆይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዘርባጃን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል አዳዲስ የኢኮኖሚና የቴክኒክ ትብብር መስኮችን ለመክፈት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርም ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች ይጠቁማሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #አዘርባጃን #ዲፕሎማሲ #ዐቢይ_አሕመድ #ባኩ #የሥራ_ጉብኝት #ethiopia #azerbaijan #diplomacy

5 months ago
የፈረንኦቹ እንባ እና የዳካር አንበሶቹ የምሽት ደስታ...
በሞሮኮ ሰሜናዊ ጫፍ፣ የታንጂየር የባህር ነፋስ ከበረሃው ሙቀት ጋር በሚታገልበት በዚያ ታሪካዊ ምሽት፣ የግራንድ ስታድ ኢብን ባቱታ ስታዲየም ሰማይ ላይ የተንጠለጠለችው ጨረቃ የሞሐመድ ሳላህን የድካም ፊት በሀዘን የምታበራው ይመስል ነበር። በስታዲየሙ ውስጥ የሚሰማው የ52,000 ተመልካቾች ጩኸት ለሴኔጋላውያን የድል መዝሙር ቢሆንም፣ ለግብፆች ግን የረጅም ዘመን ሕልም ሲሰበር የሚሰማ የመጨረሻው የጥፋት ድምፅ ነበር። ዛሬ እግር ኳስ ብቻ ሳይሆን፣ የአንድ ትውልድ ተስፋ እና የአንድ ታላቅ መሪ የመጨረሻ ተጋድሎ በታሪክ መዝገብ ላይ በሐዘን ቀለም እየተጻፈ ነበር።
የዝምታው ግንብ እና የደም ዋጋ
ጨዋታው ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ በውጥረት የተሞላ ነበር። የአሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን ታክቲክ ግልጽ ነበር—እንደ ፒራሚድ ጸንቶ መቆም፣ አለመሸነፍ፣ እና እድል ሲገኝ እንደ በረሃ ንስር መጥለፍ። ግብፆች ሜዳው ላይ ነፍሳቸውን ሰጥተው ተከላክለዋል። በተለይም ግብ ጠባቂው መሐመድ አል-ሸናዊ የሴኔጋልን ጥቃት ሲመክት፣ ጣቶቹ እስከሚደሙ ድረስ የግብ መስመሩን ጠብቋል። በእያንዳንዱ ድላዊ ቅፅበት ውስጥ ግን የድካም ጥላ ይታይ ነበር።
በ23ኛው ደቂቃ ላይ የታየው ትዕይንት ግን የሁሉንም ልብ ሰባሪ ነበር። የሴኔጋሉ አምበል ካሊዱ ኩሊባሊ፣ በደረሰበት ጉዳት ሜዳው ላይ ሲወድቅ አይኖቹ በእንባ ተሞልተው ነበር። ጀግናው መሪ መቆም አለመቻሉን ሲያውቅ ያሳየው የተስፋ መቁረጥ ስሜት፣ ስታዲየሙን ለጥቂት ሰከንዶች በዝምታ ዋጠው። እግር ኳስ ጀግኖችን ሲቀጥፍ ማየት ሁሌም ያማል። ኩሊባሊ ሜዳውን ሲለቅ፣ ሴኔጋላውያን መሪያቸውን በማጣታቸው ቢደነግጡም፣ ግብፆች ግን ይህንን ክፍተት ለመጠቀም የሚያስችል ጉልበት አልነበራቸውም።
የሳዲዮ ማኔ ሰይፍ እና የሳላህ ስብራት
ሁለተኛው አጋማሽ ሲቀጥል ግብፆች መዛል ጀመሩ። ሆሳም ሀሰን ከሜዳው ዳር ቆሞ "ታገሱ! ለሀገራችሁ ስትሉ ቆሙ!" እያለ ቢጮህም፣ ድካም ግን የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው። በ78ኛው ደቂቃ ላይ ዓለም ለግብፆች ተደፋች።
ሳዲዮ ማኔ—ያ የሊቨርፑል የቀድሞ ንጉስ፣ የሳላህ የቅርብ ወዳጅና የዛሬው ባላንጣ—ኳሷን ከግብ ክልል ውጪ አገኘ። ማኔ ኳሷን ሲመታ የነበረው ፍጥነትና ኃይል ግብ ጠባቂውን አል-ሸናዊን አቅም አሳጣው። ኳሷ መረቡን ስትቆርሰው፣ መላው ግብፅ በድንገተኛ ዝምታ ተዋጠች። ማኔ ወደ ደጋፊዎቹ እየሮጠ ሲጨፍር፣ ሳላህ ግን እጆቹን በወገቡ ላይ አድርጎ ወደ መሬት ተመለከተ። ያቺ ቅጽበት ለሳላህ የዘላለም ያህል ረጅም ነበረች። የናይል ወንዝ በታንጂየር አሸዋ ላይ የደረቀ ያህል ተሰማው።
የወንድማማቾች እቅፍ በስታዲየሙ መሃል
ጨዋታው ሲጠናቀቅና የሴኔጋል ድል ሲረጋገጥ፣ የታየው ትዕይንት ግን ዓለምን ያስለቀሰ ነበር። ሳላህ በሽንፈትና በሐዘን ተንበርክኮ ሳለ፣ ማኔ ከቡድን አጋሮቹ ጋር ከመጨፈር ይልቅ ቀጥታ ወደ ሳላህ አመራ። ለዓመታት በሊቨርፑል መለያ በደስታና በችግር አብረው የቆሙት እነዚህ ሁለት ታላላቅ ሰዎች ፊት ለፊት ተገናኙ።
ማኔ የሳላህን ትከሻ ይዞ ቀና አደረገው። ሳላህ አይኖቹ በእንባ ቀልተው፣ በድካም ዝሎ ማኔን ሲያቅፈው፣ ይህ ትዕይንት ከእግር ኳስ በላይ የሆነ የሰው ልጅ ትስስርን የሚያሳይ ነበር። ማኔ ለሳላህ በጆሮው እንዲህ አለው፦ "ወንድሜ፣ ዛሬ ያሸነፍኩት አንተን ሳይሆን ግብፅን ነው። አንተ ግን ለዘላለም የኔ ጀግና ነህ።" ሳላህ ግን መልስ አልነበረውም፤ እንባው ብቻ በጉንጩ ላይ ይፈስ ነበር። ይህ እንባ የሽንፈት ብቻ ሳይሆን፣ የአንድ ትልቅ ምዕራፍ ማብቂያ ምልክት ነበር።
የካይሮ ጎዳናዎች እና የጠፋው ተስፋ
በዚህ ሰዓት በሩቅ በምትገኘው ካይሮ፣ የከተማዋ ትርታ በአንዴ የቆመ መሰለ። በናይል ወንዝ ዳርቻ ተሰብስበው ጨዋታውን ሲመለከቱ የነበሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ፊታቸውን በእጃቸው ሸፈኑ። አንዲት አረጋዊት እናት የሳላህን ምስል ይዘው "ልጄን አታስለቅሱብኝ" በሚል ስሜት ሲያለቅሱ ይታያሉ።
ለግብፃውያን ሳላህ ተራ ተጫዋች አይደለም፤ እርሱ የሀገሪቱ ኩራት፣ የድሆች ተስፋ እና የዓለም መመኪያ ነው። ዛሬ ያለቀሱት ስለ ተሸነፉ ብቻ አልነበረም፤ ሳላህ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና በየጨዋታው የሚከፍለውን መስዋዕትነት ስለሚያውቁ ጭምር ነው። "ለሳላህ አንድ ዋንጫ እንኳን እንዴት ይነፈገዋል?" የሚለው ጥያቄ በካይሮ ጎዳናዎች ውስጥ በሐዘን ሲንሸራሸር አደረ። በታምባኩንዳ ደስታ ሲበራ፣ በካይሮ ግን ቤቶች በሀዘን ተዘጉ።
የሆሳም ሀሰን ቁስለኛ ኩራት
በጨዋታው ማጠቃለያ ላይ አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን ወደ ተጫዋቾቹ ሄደ። እያለቀሱ የነበሩትን ወጣቶች ቀና አደረጋቸው። "አታልቅሱ!" አላቸው። "እናንተ ጀግኖች ናችሁ።" ለካሜራዎች ሰባት ጣቶቹን በማሳየት "እኛ የሰባት ጊዜ ሻምፒዮን ነን፣ ክብራችንን ማንም አይወስደውም" ቢልም፣ በውስጡ ግን ከባድ ሀዘን እንደነበረ አይኖቹ ያሳብቃሉ። ዳኛው ፊሽካውን ሲነፋ የግብፅ እግር ኳስ አንድ ትልቅ ተስፋ አብሮ ተነፋ።
ታንጂየር ዛሬ የአሸናፊዎችን ሳቅና የተሸናፊዎችን እሮሮ አስተናግዳ በዝምታ ተዋጠች። እግር ኳስ እንዲህ ነው—በአንድ በኩል ህይወት ሲዘራ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ልብን ይሰብራል። የፒራሚዱ ልጆች ዛሬ አንገታቸውን ደፍተው ቢወጡም፣ የሳላህ እንባ ግን በታንጂየር አሸዋ ላይ ለዘላለም ተቀርጾ ይቀራል።
የሳላህ የመጨረሻው የአፍሪካ ዋንጫ ህልም በታንጂየር ጨረቃ ስር አበቃ። ንጉሱ ያለ ዘውድ ሊሰናበት መሆኑን ሲያውቅ፣ መላው አፍሪካ ለታላቁ ተጫዋች ክብር ዝቅ አለ። የናይል ወንዝ ዛሬ በሀዘን ሞልቷል፤ በታንጂየር ሰማይ ላይ የነበረችው ጨረቃም የፈርኦኑን የመጨረሻ እንባ ምስክር ሆና ቀረች።
በሰኔጋል...
የከተማዋ ደም ስሮች በሙሉ በአንድ ጊዜ የፈሰሱ መሰሉ። ከየሰፈር መተላለፊያዎቹ የሚወጣው ህዝብ የብሄራዊ ቡድኑን ማሊያ ለብሶ፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማትን ተጎናጽፎ እንደ ማዕበል ይተማመናል። የሁሉንም እግር የሚመራው አንድ ኮምፓስ ብቻ ነበር፦ የአይኒና ፎል ጎዳና አደባባይ። ያ ስፍራ የደስታው ማዕከል፣ የከተማዋ ትርታ ሆኗል።
ወጣቶች ከህጻናት ጋር፣ አሮጊቶች ከጎረምሶች ጋር ተቀላቅለው በደስታ ሰክረዋል። አየሩ በጩኸትና በዝማሬ ተሞልቷል። "ፊናል ሬክ!" (ፍጻሜው ብቻ!) የሚለው ጩኸት ከአደባባዩ ጥግ እስከ ጥግ ይስተጋባል። "መርሲ ሳዲዮ ማኔ!" እያሉ በጀግናቸው ስም ይምላሉ። መሃል መሃል ላይ ደግሞ የሁሉንም የጋራ ናፍቆት የሚገልጽ ድምጽ ይሰማል፦ "ሁለተኛዋን ኮከብ እንፈልጋለን!"
የባሩድ ሽታና የጢስ ቦምቦች ጭጋግ አካባቢውን ወርሶታል። የቩቩዜላ ድምጽ ከርችት ፍንዳታ ጋር ተደምሮ ደንቆሮ የሚያደርግ ጫጫታ ቢፈጥርም፣ ለሰፈነው እብደት ግን እንደ ሙዚቃ ዜማ ነበር። ደጋፊዎቹ በዚያው ጩኸት ውስጥ አስገራሚ የዳንስ እርምጃዎችን ይረግጣሉ።
ለአንድ ሰዓት ያህል በዚያ ቁልፍ ስፍራ ላይ ትራፊክ ቆሞ ቀረ። መኪኖች በሰው ባህር ተከበው መንቀሳቀስ አቃታቸው። ፖሊሶች ህዝቡን ለመቆጣጠርና መንገዱን ለማስከፈት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። በዚህ መሃል የ"ጃካርታ" ሞተር ብስክሌት ነጂዎች በሰዎች መሃል እየተሽሎከሎኩ የሚያሳዩት አደገኛ ትዕይንት ልብ ያቆማል። አልፎ አልፎ ትናንሽ ግጭቶች ቢፈጠሩም፣ የድሉ ስሜት ስለበለጠ ማንም ፊቱን አላጠቆረም፤ ሁሉም ይሳሳቃል።

6 months ago
🎅🥊 በባኩ የገና አባት ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ተደባደቡ
በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ውስጥ፣ የሳንታ ክላውስ ልብስ የለበሱ ሁለት አኒሜተሮች በሱፐርማርኬት ውስጥ ግብግብ ጀመሩ።
ከእውነተኛ ክስተት ይልቅ የአዲስ ዓመት ኮሜዲን የሚመስል ያልተለመደ ክስተት ተከስቷል።
Zakon.kz እንደዘገበው፣ የሳንታ ክላውስ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች የፖም መሸጫ አጠገብ ሆነው መጣላት ጀመሩ።
ቅድመ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የበዓል ድባብ ለመፍጠር የተቀጠሩት እነዚህ መዝናኛ ፈጣሪዎች አለመግባባት ታይቶባቸዋል።
ግጭቱ በፍጥነት ወደ አካላዊ ግብግብ ያደገ ሲሆን፣ "አዛውንቶቹ" በተገረሙ ሸማቾች ፊት ለፊት ሲገፋፉ እና ሲደበድቡ ታይተዋል።
ሁኔታው በሱቁ የጥበቃ ሰራተኛ ቁጥጥር ስር ውሏል። ዘበኛው ወደ ጠብ ቦታው በመሮጥ የተጣሉትን ሰዎች ለመለያየት ችሏል።
በ በሞቀ ግብግብ ወቅት ከተጋጨው ሰው ወይም ከታዛቢዎች መካከል ከባድ ጉዳት የደረሰበት የለም።
አንዳንዶቹም ድብድቡን በቪዲዮ መቅረጽ ችለዋል፣ ይህም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት ተሰራጭቷል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ “ሸኔ ታጣቂዎች” ፈፀሙት በተባለ ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ቅዳሜ ህዳር 13/2018 ዓ.ም የ “ሸኔ ታጣቂዎች” ፈፀሙት በተባለ ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስሜ ባይጠቀስ ያሉ አንድ የበኩጂ ነዋሪ ጥቃቱ ቅዳሜ ከማለዳ 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ 2 ሰዓት ድረስ መፈፀሙን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል።
“ጥቃት አድራሾቹ በየቤቱ እየገቡ ነበረ ግድያውን ሲፈፅሙ የነበረው” ያሉት እኚሁ ነዋሪ፤ “በዚህም ከአንድ ቤተሰብ እስከ አምስት ሰዎች የተገደሉም ነበሩ” ሲሉ ስለ ሁኔታው አስረድተዋል።
ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ባደረገው በዚህ ጥቃት የሟቾች ቁጥር እስከ 44 ይደርሳል የሚሉት ነዋሪው ለጥቃቱ የ “ሸኔ ታጣቂዎችን” ተጠያቂ አድርገዋል።
የቡለን ወረዳ ምክትል አስተዳደሪ አቶ ሺበሺ ባሬዳ፣ “ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድን” ሲሉ የጠሩት አካል ህዳር 13/2018 ዓ/ም ከንጋት 11:30 ወደ ወረዳው ባኩጅ ቀበሌ በመግባት “በንጹሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጥቃት” አድርሷል ብለዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው፣ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት የወረዳው መንግሥት “እጅግ ማዘኑን” ጠቅሰው እንዲዚህ አይነት “አስጸያፊ ድርጊትን” ማህበረሰብ ማዉገዝ እንዳለበት አሳስበዋል። በጥቃቱ ለተሰዉ ዜጎች ቤተሰብ መጽናናትን ተመኝተዋል ሲል የወረዳው ኮሚኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
Addis Standard

7 months ago
ቁልፍ የአልሻባብ መሪ ተገደለ
በሶማሊያ በተደረገ ወታደራዊ ዘመቻ ሶስት ከፍተኛ የአልሻባብ አሸባሪ ቡድን መሪዎች መግደሉን የሞቃዲሾ መንግስት አስታወቀ።
ከተገደሉት መካከል በባኩል ግዛት በሚፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች ቀንደኛ አቀነባባሪው ሞሀመድ አብዲ ሞሀመድ ኑር ይገኝበታል ተብሏል።
የሶማሊያ መንግስት እንደገለፀው፣ በባኩል እና ቤይ ግዛቶች በርካታ ንፁሃንን የገደለው ሞሀመድ በቅፅል ስሙ ጎፎው የተባለው ግለሰብ በአባል መንደር በተደረገ ልዩ ዘመቻ መገደሉን ነው።
ያህየ ወይም አቡ ካህሊድ እና ሻሪፍ አሚር የተባሉ ተጨማሪ ቁልፍ የሽብር ቡድኑ አባላት በዘመቻው መገደላቸውንም የሞቃዲሾ ወታደራዊ ሀላፊዎች አክለው ተናግረዋል ።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር አልሻባብን የመመንጠር ዘመቻው ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ፣ ቡድኑ ጨርሶ እስካልጠፋ ድረስ ሰላም እንደማይኖር በመግለጫው አመላክቷል። አናዶሉ እንደዘገበው ።

8 months ago
ኢኳኢተስ
ዓባይ እና አዲሱ የፍትሕ ዓውድ
ፕ/ር ምዋንጊ ሳምሶን ኪመኒ እና ፕ/ር ጆን ሙከም ምባኩ
ትርጉም:- ሰለሞን በጋሻው
#ethiopia | በዘመኑ የነበሩት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሀገራቸው ለምትመኘው ብሔራዊ ልማትና ብልጽግና የሙህ ሀብቷን መጠቀም እንደሚያስፈልጋት ጠንቅቀው ይገነዘቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ዶ/ር ዳንኤል ክንዴ አንዳቀረበው የመከራከሪያ ሀላብ በብሪታኒያና በኢትዮጵያ መካከል በ1902 ተፈጽሟል የተባለውን የሁለትዮሽ ስምምነት እርባና ቢስ የሚያደርጉ እና ተጨባጭ የሆኑ ኹነት ገላጭ መረጃዎች አሉ።
ተፈጸመ የተባለው የሁለትዮሽ ስምምነት በብሪታኒያ ፓርላማም ሆነ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና የንጉሠ ነገሥቱ አማካሪ ባለሟሎች ምክር ቤት ዘንድ ቀርቦ፤ በመጽደቅ ወደ ሕግነት የተለወጠበት አጋጣሚ አለመከሰቱ ስምምነቱን ወረቀት ላይ ብቻ የቀረ ባዶ ደንብ እንዲሆን አድርጎታል። ሁለቱም ሀገራት ይህንን በማድረግ ስምምነቱን ወደ ሕግነት አጽድቀው አላሳለፉትም። ኢትዮጵያ በስምምነቱ ታሳሪ አለመሆኗን ለማስረዳት የሚገልጽ ከዚህ የበለጠ ጭብጥ የለም፡፡ ክንዴ 1999,p.146) "
በመሆኑም ኢትዮጵያ ከብሪታኒያ ጋር ፈጸመች በተባለው ስምምነት መሠረት ታሳሪ አለመሆኗን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ከርክር ማድረግ ወይም ጭብጥ ማቅረብ አያስፈልጋትም።
****
"በደቡብ የአሜሪካ ግዛት ይመረት ከነበረው የጥጥ ምርት አብዝሐኛው የሚላከው ወደ ታላቋ ብሪታንያ ላንክሻየር የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ነበር (ቤከርት 2004) ። በ1861 አሜሪካ ውስጥ ተከስቶ የነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ሲነሳ በደቡብ ግዛት በሰፊው ይመረት የነበረው የጥጥ ምርት ተስተጓጎለ ። ……"
" እንግሊዞች ሰፊ የሆነው የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪያቸው የገጠመውን የግብዓት እጥረት ለመታደግ ግብፅ ውስጥ ጥጥ ላይ ብቻ ያተኮረ የመስኖ ልማት እንዲከወን ማድረግ ነበረባቸው ።"
ከአሜሪካኖች የእርስ በርስ ጦርነት ውጤት እስከ የኤርትራ መገንጠል የዓባይ ጉዳይ ኢትዮጲያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ ውስጥ የከተታት የመልክዓ ፖለቲካ ጉዳይ እጅጉን ብዙ ነው ።
#ኢኳኢተስ እነዚህን ውስብስብ የብሔራዊ ጥቅማችን የሚመለከቱ ጉዳዮች ከሌሎች በርካታ ጉዳዮች ጋር ከከዲቭ እስማዔል እስከ አብዱል ፈታህ አልሲሲ ዘመን ድረስ በሰፊው ታስቃኘናለች ።
በሁሉም የጃዓፈር መጽሐፍት መደብር ያገኙታል ።