Logo
FIDEL POST NEWS
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ “ሸኔ ታጣቂዎች” ፈፀሙት በተባለ ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ቅዳሜ ህዳር 13/2018 ዓ.ም የ “ሸኔ ታጣቂዎች” ፈፀሙት በተባለ ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስሜ ባይጠቀስ ያሉ አንድ የበኩጂ ነዋሪ ጥቃቱ ቅዳሜ ከማለዳ 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ 2 ሰዓት ድረስ መፈፀሙን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል።

“ጥቃት አድራሾቹ በየቤቱ እየገቡ ነበረ ግድያውን ሲፈፅሙ የነበረው” ያሉት እኚሁ ነዋሪ፤ “በዚህም ከአንድ ቤተሰብ እስከ አምስት ሰዎች የተገደሉም ነበሩ” ሲሉ ስለ ሁኔታው አስረድተዋል።

ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ባደረገው በዚህ ጥቃት የሟቾች ቁጥር እስከ 44 ይደርሳል የሚሉት ነዋሪው ለጥቃቱ የ “ሸኔ ታጣቂዎችን” ተጠያቂ አድርገዋል።

የቡለን ወረዳ ምክትል አስተዳደሪ አቶ ሺበሺ ባሬዳ፣ “ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድን” ሲሉ የጠሩት አካል ህዳር 13/2018 ዓ/ም ከንጋት 11:30 ወደ ወረዳው ባኩጅ ቀበሌ በመግባት “በንጹሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጥቃት” አድርሷል ብለዋል።

ምክትል አስተዳዳሪው፣ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት የወረዳው መንግሥት “እጅግ ማዘኑን” ጠቅሰው እንዲዚህ አይነት “አስጸያፊ ድርጊትን” ማህበረሰብ ማዉገዝ እንዳለበት አሳስበዋል። በጥቃቱ ለተሰዉ ዜጎች ቤተሰብ መጽናናትን ተመኝተዋል ሲል የወረዳው ኮሚኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

Addis Standard
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.