Logo
SeledaPost
አደገኛው የጥፋት መረብ ተበጠሰ‼️ አደገኛው የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊትና ግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ::

አዲስ አበባ — መጋቢት 28፣ 2018 በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት ለገደል የዳረገውና በዓለም አቀፍ ደረጃ በብርቱ ሲፈለግ የነበረው አደገኛው የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) በመጨረሻም በፌደራል ፖሊስ ብርቱ ክንድ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ይህ ግለሰብ በሰዎች መነገድን እንደ ትርፋማ ንግድ ተመልክቶ፣ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ለሞትና ለስቃይ የዳረገ ጨካኝ ወንጀለኛ መሆኑ ተረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ይፋ እንዳደረገው፣ በዋና አዘዋዋሪው ይትባረክ ዳዊት ላይ የተመዘገቡት ወንጀሎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

1. ከ3,000 በላይ ዜጎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር፣

2. ከ100 በላይ ሰዎችን ለሞት መዳረግ፣

3. ከ50 በላይ ሴቶች ላይ አስከፊ የጥቃት (የደፍሮት) ወንጀል እንዲፈጸም ማድረግ።

ፖሊስ ይህን ድንበር ተሻጋሪ ወንጀለኛ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከROCK (The Regional Operational Centre) ጋር የቅርብ የመረጃ ልውውጥ ሲያደርግ ቆይቶ፣ በመጨረሻም በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ላይ በድንገተኛ አሰሳ በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።

በምስሉ ላይ የሚታዩትና በወንጀል ተባባሪነት የተያዙት ግለሰቦች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

* ይትባረክ ዳዊት አለሙ (ዋናው አደራጅ/አዘዋዋሪ)
* ሰለሞን ቀለም ደበበ
* ቤተልሔም ካሳ አላሮ
* መብራቶም ኢታይ ሀሽ
* ሀፍቶም ሀይላይ ሀይሉ
* መርሃዊ ታቦት ገብረሕይወት
* ራሄል አለሙ ገ/ጊዮርጊስ
* አብዱሰላም ቲጃኒ አባኩምሳ
* በእምነት ስራቃ ሃጎስ
* ሺሻይ ኪዳኔ ጉዕሽ

የፖሊስ መልዕክት፡ "የሰው ልጅ የንግድ ዕቃ አይደለም!" ፌደራል ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለዓቃቢ ህግ የላከ ሲሆን፣ ፍትህ ለተጎጂዎች ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል።
Via የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

seledadotio
seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.