ቁልፍ የአልሻባብ መሪ ተገደለ
በሶማሊያ በተደረገ ወታደራዊ ዘመቻ ሶስት ከፍተኛ የአልሻባብ አሸባሪ ቡድን መሪዎች መግደሉን የሞቃዲሾ መንግስት አስታወቀ።
ከተገደሉት መካከል በባኩል ግዛት በሚፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች ቀንደኛ አቀነባባሪው ሞሀመድ አብዲ ሞሀመድ ኑር ይገኝበታል ተብሏል።
የሶማሊያ መንግስት እንደገለፀው፣ በባኩል እና ቤይ ግዛቶች በርካታ ንፁሃንን የገደለው ሞሀመድ በቅፅል ስሙ ጎፎው የተባለው ግለሰብ በአባል መንደር በተደረገ ልዩ ዘመቻ መገደሉን ነው።
ያህየ ወይም አቡ ካህሊድ እና ሻሪፍ አሚር የተባሉ ተጨማሪ ቁልፍ የሽብር ቡድኑ አባላት በዘመቻው መገደላቸውንም የሞቃዲሾ ወታደራዊ ሀላፊዎች አክለው ተናግረዋል ።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር አልሻባብን የመመንጠር ዘመቻው ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ፣ ቡድኑ ጨርሶ እስካልጠፋ ድረስ ሰላም እንደማይኖር በመግለጫው አመላክቷል። አናዶሉ እንደዘገበው ።
seledadotio

7 months ago