በዓለም አቀፉ የከተሞች ፎረም የሀገራችንን እና የመዲናችንን እያስተዋወቅን እንገኛለን፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
************
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአዘርባጃን መዲና ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው ዓለም አቀፍ የከተሞች ፎረም (13th World Urban Forum) ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
ፎረሙ “ቤት ለሁሉም፤ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ጠንካራ ከተሞች እና ማህበረሰቦች” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባኤውም ዓለም አቀፋዊ የመኖሪያ ቤት ችግርን መፍታት፣ ዘላቂ የከተማ ልማት፣ ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ ከተሞችን መገንባት፣ የአየር ንብረት እና የመኖሪያ ቤት ግንኙነቶች፣ መልሶ ግንባታ እንዲሁም ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት በዋናነት እየተመከረባቸው መሆኑን በፎረሙ ላይ የተሳተፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
በፎረሙ ላይ ጠቃሚ የልምድ ልውውጥና የመስክ ጉብኝቶች እየተደረጉ እንደሚገኝ የጠቆሙት ከንቲባዋ ፤ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከውይይቶቹ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን እና የመዲናዋን አዲስ አበባን ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ሰፊ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም መሠረት በዛሬው ዕለት በተከፈተው ኤክስፖ ላይ መንግሥት ከግል ዘርፍ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ገጽታ የሚገልጽ ልዩ ፓቪልዮን (ቡዝ) በማዘጋጀት፤ የተከናወኑ ዘላቂ የከተማ ልማት ሥራዎችን በጽሑፍ፣ በቪዲዮ እና በቪርቹዋል ሪአሊቲ ቴክኖሎጂዎች ለታዳሚዎች የማስተዋወቅ ሥራ በስፋት እየተሠራ ይገኛል።
#worldurbanforum #mayoradanechabiebie #ethiopia #addisababa #bakuazerbaijan #ethiopianbroadcastingcorporation

18 days ago