2 months ago
በቲቤት ሰማይ ላይ የታየው አስደናቂውና አስፈሪው የደመቀ ቀይ ብርሃን
ከሰማይ ወደ መሬት ሳይሆን ከመሬት ወደ ጠፈር የሚተኮሰው ያልተለመደው መብረቅ።
ቲቤት በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኝ፣ ከኔፓል፣ ህንድ እና ቡታን ጋር የምትካለልና እጅግ ሰፊ በሆነው የኪንግሃይ-ቲቤት እምብርት ላይ ያለች ከፍተኛ ተራራማ ቀጠና ናት።
በአማካይ ከባህር ጠለል በላይ ከ4,000 እስከ 5,000 ሜትር ከፍታ ላይ በመገኘቷ "የዓለም ጣሪያ" (Roof of the World) በሚል ስያሜ ትታወቃለች።
በዚሁ ልዩ ስፍራ በቅርቡ በቲቤት ሻናን ክልል በሚገኘውና ከባህር ጠለል በላይ ከ5,000 ሜትር በላይ ከፍታ ባለው ፑማ ዩምኮ ሐይቅ (Lake Puma Yumco) አቅራቢያ በተከሰተ ኃይለኛ የነጎድጓድ ማዕበል ላይ እጅግ አስደናቂ እና አስፈሪ የሆነ የበራ ቀይ የብርሃን ምሰሶ ብልጭታ በቪዲዮ ተቀርጾ ወጥቷል።
የሳይንስ ልብ-ወለድ ፊልም የሚመስለውና "ሬድ ስፕራይትስ" (Red Sprites) በመባል የሚታወቀው ይህ ክስተት፣ ልክ እንደ ግዙፍ የባህር እንስሳ ቅርፅ ያላቸው የብርሃን ዘንጎች ወደ ጠፈር ሲዘረጉ ታይቷል።
ክስተቱን በከፍተኛ ጥራት የቀረጸው ዶንግ ሹቻንግ የተባለ የቻይና የሥነ-ፈለክ ተመራማሪና ፎቶግራፍ አንሺ ሲሆን፤ ክስተቱ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህ ክስተት በተለምዶ እኛ ከምናየው መብረቅ እጅግ በጣም የተለየ ሲሆን የሚከሰተውም ከምድር ገጽ ከ50 እስከ 90 ኪሎ ሜትር ከፍታ ባለው የከባቢ አየር ክፍል ላይ ነው።
ከታች ባለው ደመና ውስጥ በጣም ኃይለኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ብልጭታ ሲከሰትና ከደመናው በላይ ባለው የላይኛው ከባቢ አየር ላይ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስክ ሲፈጥር የሚመጣ ነው ተብሏል።
Seledadotio

4 months ago
ፍቼ ጫምበላላ በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ
የሰላም፣ የመከባበርና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነው የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፍቼ ጫምበላላ ዛሬ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ለሰባተኛ ጊዜ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በምርቃት ተጀምሯል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፍቼ ጫምበላላ የፍቅርና የአዲስ ተስፋ መገለጫ ከመሆኑም ባለፈ የጨረቃንና የከዋክብትን ዑደት የቀመረ ጥልቅ ሀገር በቀል እውቀት የሚታይበት የአለም ህዝብ ቅርስ ነው ብለዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዓሉ የሲዳማ አባቶች ያላቸውን ጥልቅ የሥነ-ፈለክ ዕውቀት ለዓለም ያስተዋወቀ የታሪክና የባህል ማንነት መገለጫ መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ በዓሉ በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበና የከተማዋን ብዝኀነት ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ይህ በዓል እሴቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍና የቱሪዝም ዘርፉን እንዲያነቃቃ ከክልሉ መንግሥት ጋር በትኩረት እንደሚሠራ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

5 months ago
አፍጋኒስታን የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ዛሬ እያከበረች ነው
በአፍጋኒስታን የሸዋል ወር ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ የዘንድሮው የዒድ ዛሬ ሐሙስ (መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም.) እየተከበረ መሆኑን የታሊባን አስተዳደር አስታወቀ።
የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጨረቃ በደቡባዊ ሄልማንድ እና በምዕራብ ፋራህ ግዛቶች መታየቷን አረጋግጧል።
ይህ ውሳኔ አፍጋኒስታንን ከሌሎች የእስልምና እምነት ተከታይ አገራት የተለየ የዒድ ቀን እንዲኖራት አድርጓታል።
ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኳታር እና ኩዌት ጨረቃ ባለመታየቷ በዓሉን ነገ ዓርብ እንደሚያከብሩ አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ ቱርክ እና አውስትራሊያ በሥነ-ፈለክ ስሌት መሠረት ዓርብን የዒድ ዕለት አድርገው ሰይመዋል።
ቀደም ሲል አፍጋኒስታን ከሳውዲ አረቢያ ጋር በዓላትን ብታከብርም፣ በቅርብ ዓመታት ግን የራሷን የጨረቃ ምልከታ ዘዴ በመጠቀም መወሰን ጀምራለች።
ምንጭ፦ አናዶሉ ኤጀንሲ

የሲዳማ የጊዜ አቆጣጠር ጥበብ...ይነበብ!!
የሲዳማ ዘመን አቆጣጠር መነሻው የፀሐይ፣ የጨረቃና ከዋክብት ሕግ በማጤን ላይ የተመሠረተ ነው። የሲዳማ ሀገረሰባዊ ዕውቀት ከዘመናዊ የሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ሕግጋት ጋር የሚገናኝ ነው። ያ አያንቶ (ባህላዊ አስትሮኖመር) የሰማይን ሚስጥር ያለ ቴሌስኮፕ በማጥናት ይሄንን ድንቅ ጥበብ እንዴት ለዚህ ትውልድ ማኖር ቻለ? የሚገርም ጥበብ ነው።
የሲዳማ የጊዜ አቆጣጠር ፀሐይንና ጨረቃን (Solar & Lunar Calander) መነሻ ያደረገ መሆኑን የወሥፉ አጥኚ መሠለ ካዳ "የሲዳማ ጊዜ አቆጣጠር" ለጊዜው ታትሞ ለገበያ ባልቀረበ መጽሐፉ ያትታል።
ሲዳማ የጨረቃ ካላንደር የሚጠቀመው የወቅቶችን መፈራረቅ ለመለየትና ለእርሻ ሥራ ነው። Badheessa, Hawado, Birra, Arro (በልግ፣ ክረምት፣ ፀደይ እና በጋ) የፀሐይ ካሌንደር ወቅቶች ናቸው።
በሲዳማ ማህበራዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው የጨረቃ ካሌንደር ነው። Lunar Calendar. ሲዳማ የጨረቃ ካሌንደር በሁለት ዓይነት አቆጣጠር እንደሚገለፅ ተመራማሪው መሠለ በግልጽ ያስቀምጠዋል። Siderial Lunar Cycle & Synodic Lunar Cycle.
Siderial Lunar Cycle (የአያንቶ ካሌንደር) ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ጨረቃ በምድር ዙሪያ የምታደርገውን ዑደት ከከዋክብቶችና ከሌሎች ፕላኔቶች አንፃር የሚቆጠር አቆጣጠር ነው። በሥነ ፈለክ ዘርፍ ጨረቃ መሬትን ዞራ ለመጨረስ 27/28 ቀናት እንደሚፈጅባት የሚታወቅ ሲሆን በሲዳማ አያንቶዎች ዘንድም 27/28 ቀኖች እንዳሉ ይታወቃል። እነኝ ቀናቶች ከመጀመሪያው ቀን Argaajjima ጀምሮ Bolla Bassa, Adula ama, Adula beetto....Bita... 28 (Lao) እየተባሉ የሚታወቁ ናቸው።
ሌላው የጨረቃ ካሌንደር Synodic Lunar Cycle (የፍቼ ጫምባላላ ካሌንደር) ተብሎ ይታወቃል። በዚህ ካሌንደር አቆጣጠር ሲዳማ የጨረቃ ቅርፅ (አዲስ ጨረቃ፣ ግማሽ ጨረቃ፣ ሙሉ ጨረቃ) ብቻ መሠረት በማድረግ ቀን የሚቆጥር ቀመር ሲሆን የፍቼ ጫምባላላ ቀን የሚውልበትን ዕለት የሚለይበት አቆጣጠር ነው።
በSynodic Lunar Cycle (Calandar) መሠረት 12 የጨረቃ ወራቶች የሚኖሩ ሲሆን ፍቼ ጫምባላላ የሚውለው በ12 የጨረቃ ወር በመጨረሻው ሳምንት፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ቃዋዶ ዕለት ሲሆን አሥራ ሶስተኛ ው አዲስ የጨረቃ ወር ከመጀመሩ በፊት ነው።
በአጠቃላይ የሲዳማ ህዝብ የጊዜ አቆጣጠር እጅግ የሚደንቅ የቀደምት አባቶች ጥበብ የሚገልፅ ሆኖ ብዙዎች ይሄንን ድንቅ ባህል ለማጥላላት ከጥንቆላ ወይም ከኮከብ ቆጠራ ጋር እንደሚያገናኙ ሳይሆን በሳይሳዊ ዕውቀት ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን ነው ተመራማሪው መሠለ ካዳ የሲዳማ አባቶች ዕውቀት ከሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ሳይንስ ጋር እያስተያዩ የሚገልፁት።
ይህ የሲዳማ ጊዜ አቆጣጠር መጽሐፍ ታትሞ በገበያ ላይ ሲውል ለአዲሱ ትውልድ ባህሉን እንዲያውቅ፣ እንዲጠብቅና እንዲያበለፅግ ትልቅ አቅም እንደሚሆነው እተማመናለሁ።
ሳሙኤል በላይነህ ቃ'ሜ
መጋቢት 4/2018 ዓ.ም
ሐዋሳ፣ ሲዳማ | ኢትዮጵያ 🇪🇹

6 months ago
ቅዳሜ ስድስቱን ፕላኔቶች በአይናችን እናያቸዋለን
📌ከሌሉቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ
#ethiopia | በመጪው ቅዳሜ ምሽት ስድስት ፕላኔቶች በአንድ ላይ በሰማይ ላይ የሚታዩበትና "Planetary Parade" ተብሎ የሚጠራው ድንቅ የተፈጥሮ ክስተት እንደሚታይ ተገለጸ።
በዚህ ብርቅዬ አጋጣሚ ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን፣ ኡራነስ እና ኔፕቲዩን በአንድ አካባቢ ተሰልፈው የሚታዩ ሲሆን፣ ለሥነ-ፈለክ አፍቃሪዎች ልዩ ትዕይንትን ይፈጥራሉ።
ትዕይንቱን ለመታዘብ የሚረዱ ነጥቦች፦
* የመመልከቻ ሰዓት፦ ፕላኔቶቹ ፀሐይ እንደጠለቀች ወዲያውኑ የሚታዩ ሲሆን፣ የእይታ ጊዜያቸውም ለ30 እስከ 45 ደቂቃዎች ብቻ የሚቆይ በመሆኑ ፈጠን ብሎ መመልከት ያስፈልጋል።
*ክስተቱ ለምን ይፈጠራል?፦ ይህ ሁኔታ የሚከሰተው ፕላኔቶቹ ፀሐይን በሚዞሩበት ምህዋር (Plane) ላይ በተመሳሳይ አቅጣጫ ሲሰለፉና ከምድር ሆነን ስንመለከታቸው በአንድ መስመር ላይ ያሉ ሲመስሉ ነው።
* የማየት ዕድል፦ አራቱን ፕላኔቶች (ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ ጁፒተር እና ሳተርን) በአይናችን በቀላሉ ማየት የምንችል ቢሆንም፣ ኡራነስ እና ኔፕቲዩን ግን በርቀታቸውና በዕለቱ በሚኖረው የሙሉ ጨረቃ ብርሃን ምክንያት ያለ አጋዥ መሣሪያ (Binoculars ወይም Telescope) ለማየት አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ።
ተፈጥሮ የምታሳየንን ይህንን ድንቅ ትዕይንት ቅዳሜ ምሽት ወደ ሰማይ በመመልከት እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የፕላኔቶች_ሰልፍ #ሥነ_ፈለክ #ሳይንስ #ቅዳሜ_ምሽት #planetaryparade #spaceethiopia

8 months ago
ይህ መረጃ በኢትዮጵያ የስነ-ከዋክብት ተመራማሪ በሆኑት በዶ/ር ሮዳስ ታደሰ የተሰጠ ሳይንሳዊ ትንበያ ሲሆን፣ ከሥነ-ፈለክ (Astronomy) አንጻር ሲታይ ፍጹም ትክክልና የሚከሰት ክስተት ነው።
የዕለቱ ዋና ዜና፡ የታህሳስ 11/12 ልዩ የሥነ-ፈለክ ክስተት
በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ታህሳስ 12 (በፈረንጆቹ December 21 ወይም 22) "Winter Solstice" ወይም የክረምት መለወጫ ተብሎ የሚጠራው ዕለት ነው። ዶ/ር ሮዳስ ያስተላለፉት መልዕክት የሚከተሉትን ነጥቦች ያጠቃልላል፦
* የቀኑ ርዝመት፡ ይህ ዕለት በሰሜናዊው የዓለም ክፍል (ኢትዮጵያን ጨምሮ) የዓመቱ አጭሩ ቀን ነው።
* የሌሊቱ ርዝመት፡ በአንጻሩ የዓመቱ ረጅሙ ሌሊት የሚመዘገብበት ወቅት ነው።
* ምክንያቱ፡ መሬት በዝንባሌዋ (Axial tilt) ምክንያት ከፀሐይ ርቃ የምትገኝበት የመጨረሻው ነጥብ ላይ በመድረሷ ነው።
ለምን እውነት ይሆናል? (ሳይንሳዊ ማብራሪያ)
ይሁን እንጂ ዶ/ር ሮዳስ ማህበረሰቡ ስለ ተፈጥሮ ክስተቶች ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ የሚጠቀሙበት ሳይንሳዊ ሃቅ ነው።
* የፀሐይ ጉዞ፦ ፀሐይ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ (Tropic of Capricorn) ላይ ቀጥታ ስለምታርፍ፣ ለእኛ ለሰሜናዊያኑ ብርሃኗ አጭር ሰዓት ብቻ ይቆያል።
* ቀጥታ ተፅዕኖ፦ ነገ እሁድ ፀሐይ ዘግይታ ትወጣለች፤ ቀድማም ትጠልቃለች። ይህም "ቶሎ ይመሻል" የተባለበትን ምክንያት ያረጋግጣል።
ማሳሰቢያ፦ ነገ እሁድ ታህሳስ 12 ቀን፣ ቀኑ አጭር በመሆኑ ለስራና ለጉዞ የምታቅዱ ሰዎች ጊዜያችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙ ይመከራል። ፀሐይ ቀድማ ስለምትጠልቅ የምሽቱ ጨለማ ረጅም ይሆናል።
በዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
seledadotio

Sponsored by
Surafel
10 months ago
መሬት አዲስ ጨረቃ አገኘች
👉"ጊዜያዊዋ የጨረቃችን" አዲስ ጎረቤት ተገኘች : 'አስቴሮይድ 2025 ፒኤን7' ምድርን ስታጅብ የቆየችው ለ60 ዓመታት ነው ተብሏል
#ethiopia | የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች አስገራሚ ግኝት ይፋ አደረጉ! በናሳ ድጋፍ በ'ፓን-ስታርስ' ጥናት አማካኝነት አስቴሮይድ 2025 ፒኤን7 የተሰኘች ትንሽ ጠፈር ድንጋይ ተለይታለች። ይህች የጠፈር አካል ለ60 ዓመታት ያህል በጸጥታ ከምድር ጋር ተጓዥ ሆና ቆይታለች።
ይህች አዲስ 'ኳሲ-ሳተላይት'፣ ወይም "ጊዜያዊ ጨረቃ"፣ በጠፈር ላይ የምድር ጎረቤት ብትሆንም በቀጥታ ምድርን የምትዞር ሳይሆን፣ በፀሐይ ዙሪያ የምድርን ምሕዋር ተከትላ የምትጓዝ ናት። ግኝቱ የተካሄደው በኦገስት 2, 2025 ዓ.ም. በሃዋይ ሃሌአካላ በሚገኘው የፓን-ስታርስ ቴሌስኮፕ ነው።
ስፋቷ ወደ 19 ሜትር (60 ጫማ) ገደማ የሆነች፣ እጅግ ትንሽ በመሆኗ በብርሃን እጥረት ምክንያት እስከ አሁን ድረስ ለመለየት አስቸጋሪ ሆና ቆይታለች ነው የተባለው።
አስቴሮይዷ ፀሐይን ለመዞር በግምት አንድ ዓመት የሚፈጅባት ሲሆን፣ ከምድር ጋር 1፡1 የሆነ የምሕዋር ተመሳሳይነት ትጠብቃለች። ከምድር እይታ አንጻር ስትታይ፣ ፕላኔታችንን የምትዞር ትመስላለች ነው የተባለው።
ትንተናዎች እንደሚያሳዩት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ይህን የምሕዋር ዝምድና ስትጠብቅ የቆየች ሲሆን፣ በዚህ ሁኔታ እስከ 2083 ዓ.ም. ድረስ ከምድር ጋር እንደምትጓዝ ይተነበያል።
ከምድር የምትኖረው ርቀት ከአነስተኛ ሚሊዮን ኪሎሜትሮች አንስቶ እስከ 17 ሚሊዮን ኪሎሜትር ድረስ የሚለያይ በመሆኑ፣ እንደ እውነተኛ የጨረቃ ቅርብ ሳተላይት አትቆጠርም ተብሏል።
የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ 2025 ፒኤን7 ምንም ዓይነት የመጋጨት አደጋ አትፈጥርም። ምሕዋሯ የተረጋጋ በመሆኑ እና መጠኗ በጣም ትንሽ በመሆኑ ምክንያት፣ በምድር ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይኖራትም ተብሏል።
እንደ 2025 ፒኤን7 ያሉ "ጊዜያዊ ጨረቃዎች" መገኘት ከፍተኛ ሳይንሳዊ ጠቀሜታ አለው የተባለ ሲሆን እንደዚህ ያሉ ትናንሽ አካላት በፕላኔቶች ስበት እንዴት ለጊዜያዊነት ጎረቤት እንደሚሆኑ ለማጥናት ተመራማሪዎችን ይረዳል ነው የተባለው።
ምድርን የምትከተልበት መንገድ ለወደፊቱ የጠፈር መንኮራኩር ተልዕኮዎች ወይም የአስቴሮይድ ቁሶችን የማምጣት ቴክኖሎጂዎችን ለመሞከር እንደ ምቹ የጠፈር ላቦራቶሪ እንድትታይ ያደርጋታል ነው የተባለው።
በዚህ ግኝት ምድር ቋሚ አዲስ ጨረቃ ባታገኝም፣ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ከእኛ ጋር በዝምታ ስትጓዝ የቆየች ጠባብ ጠፈር ድንጋይ መኖሯ ተረጋግጧል። ይህች ጊዜያዊ ጎረቤት፣ የፕላኔታችን ምሕዋር በብዙ የጠፈር ተጓዦች የተሞላ መሆኑን የሚያሳይ የቅርብ ማሳሰቢያ ሆናለች ያለው መናኸሪያ ሬዲዮ ነው።

ስፔስ ኤክስ በጠፈር ላይ ከሚገኙት አጠቃላይ ሳተላይቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛው ባለቤት ሆነ
#ethiopia | የኢሎን መስክ ኩባንያ ስፔስ ኤክስ 10 ሺኛ የስታርሊንክ ሳተላይቱን ወደ ሕዋ በማምጠቅ፣ በጠፈር ላይ ከሚገኙት አጠቃላይ ሳተላይቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛው ባለቤት ሆኗል።
በመሬት ምህዋር ላይ ስራቸውን እያከናወኑ ከሚገኙ 12 ሺ 955 ሳተላይቶች ውስጥ 8 ሺ 562 የሚሆኑት የስፔስ ኤክስ ንብረቶች መሆናቸው ተመላክቷል።
ከስፔስ ኤክስ ቀጥሎ ያለው የቅርብ ተፎካካሪ የሆነው ዋን ዌብ 651 ሳተላይቶች ብቻ አሉት ሲል የዘገበው ኢንዲፔንደንት ነው።
የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ የሳተላይት ፍርስራሾች ከባቢ አየርን በመጉዳት ለዓለም ሙቀት መጨመር አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል ብለው ያስጠነቅቃሉ።
በሴራን ታደሰ
#ebc #space

የዓመቱን የመጀመሪያ ሙሉ ጨረቃ አመሻሽ ይመልከቱ
#ethiopia | ዛሬ መስከረም 27 ቀን የ2018 ዓ.ም ዐዲስ ዓመት የመስከረም ወር የመጀመሪያዋ ሙሉ ጨረቃ በኢትዮጵያ እንደምትታይ የሥነ ፈለክ ተመራመሪው ዶክተር ሮዳስ ታደሰ አስታውቀዋል።
ሙሉ ጨረቃዋ በኢትዮጵያሠአት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሠአት ከ26 ደቂቃ ጀምራ በመውጣት እንደምታነጋውም ገልጸዋል።
ያለፈው ዓመት የመጨረሻዋ ሙሉ ጨረቃ በሙሉ የደም ጨረቃ ግርዶሽ ጳጉሜን2 ቀን መታየቷ ይታወሳል።
የዐዲሱን ዓመት ደማቅ እና ውብ ጨረቃ ደግሞ ዛሬ ምሽት ትታያለች ነው ያሉት ። #arada

ያልተነገረው እዉነታ !
አማርኛ የሚጠቀምበት ፊደል 78.8% የግዕዝ ነዉ !
በዓለም ከ7000 በላይ ቋንቋዎች በመግባቢያነት እንደሚያገለግሉ ይነገራል። በዓለም ላይ ከሚገኙ ቋንቋዎች 6 በመቶው የሚሆኑትን 94 በመቶ የዓለም ህዝብ በመግባቢያነት ይጠቀምባቸዋል።
እንደ ሳይንሳዊ ጥናት አድራጊ ምሁራን አባባል፤ የሰው ልጅ ፊደልን በሚሊዮኖች ዓመታት የዕድገት ደረጃዎች ለውጡ ቋንቋውን ከሥልጣኔ ዕድገቱ ጋር አብሮ እያራመደ ሲመጣ ያገኘው ውጤቱ መሆኑን ይገልፃሉ
በእነዚህ ሥዕላዊ ምልክቶች (Pictographic Symbols) ከመጠቀም አልፎም ወደ ጽሑፍ ቋንቋ (Writing Language) በቅቷል የሚል ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
የሳይንሳዊ ጥናት ተመራማሪዎች ከላይ እንደተገለጸው፤ የሰው ልጅ ለንግግሩ ጽሑፋዊ መግለጫ የሆነውን ፊደል መፍጠር እንደቻለ አረጋግጠዋል፡፡
የግብፅን ሂሮግሊፍክ (ሥዕላዊ ጽሑፍ) መሠረት በማድረግ፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት 1800-1500 በሴማውያን ከተፈለሰፈው ጥንት ሲናዊ (Proto - sinaific) ፊደል፣ በርካታ ሌሎች ፊደላት መገኘት ችለዋል፡፡ ከተፈለሰፉት መካከል ግን እንደ ዐረብኛ፣ ዕብራይስጥኛና ኢትዮጵያዊኛ ያሉት እናት ፊደላቸውን መምሰል እየተውና እየራቁ በመሔድ የተገኙ ናቸው፡፡
እዚህ ላይ ግን አንድ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ይኖራል፡፡ ሃይማኖታዊም ሆነ ሳይንሳዊ አመለካከት ያላቸው ሁለት ክፍሎች፤ በፊደል ታሪካዊ አመጣጥ ላይ የተለያየ አቀራረብ ቢኖራቸውም በአጠባበቅና በአጠቃቀም በኩል ግን በአብዛኛው አንድነት ያላቸው መኾኑን ልንረዳ ይገባል፡፡
ከላይ እንደተመለከትነው፤ የሰው ልጅ ፊደልን ከማግኘቱ በፊት ለፊደል መፈልሰፍ መሰረት የሆኑት ሥዕላዊ ምልክቶችን ይጠቀም እንደነበረ ተገንዝበናል፡፡ እነዚህ ሥዕላዊ ምልክቶች የግብፅ ሂሮግሊፊክ እና የመሶጶታሚያው ኩኒፎርም በመባል የሚታወቁ ናቸው፡፡ በዓለም ውስጥ ያሉት ፊደሎችም በሙሉ ከእነዚህ ሥዕላዊ ምልክቶች የተገኙ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
የግዕዝ ፊደል የሚባሉት 26ቱ ድምፆችና አራቱ ዲቃሎች ባለቤት የሆነችው
ሀ፣ ለ፣ ሐ፣ መ፣ ሠ፣ ረ፣ ሰ፣ ቀ፣ በ፣ ተ፣ ኀ፣ ነ፣ አ፣ ከ፣ ወ፣ ዐ፣ ዘ፣ የ፣ ደ፣ ገ፣ ጠ፣ ጰ፣ ጸ፣ ፀ፣ ፈ፣ ፐ እንዲሁም ኰ፣ ጐ፣ ቈ፣ ኈ ፡፡
ኢትዮጵያ በጥንታዊው የሥነ ጽሑፍ ታሪክ በዓለም የመጀመሪያውን ረድፍ የምትይዝ አገር ያደርጋታል ፡፡
በእንግሊዝ፤ በፈረንሳይ፣ በጀርመን ዛሬ የሚፃፉት ሁሉ ከኢትዮጵያ ሥነ-ፅሁፍ በኋላ የመጡ ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ጋር የሚወዳደሩት ትልልቆቹ የግሪክ፣ የአራማይክ፣ የላቲን፣ የመሳሰሉቱ ናቸው፡፡ …” በማለት ኢትዮጵያን ታላቅ ከሚያደርጓት ሀብቶቿ አንዱ ይኸው የግዕዝ ሥነ ፅሑፍ መሆኑን በግዕዝ ቋንቋና ፊደል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንና ቅዱሳት መጻሕፍትዋ ላይ የጻፏቸውን ጨምሮ የአያሌ መጣጥፎችና መጻሕፍት ደራሲ የሆኑት ምሁር ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ በሐመር መጽሔት ሐምሌ/ነሐሴ ፲፱፻፺፮ ዓ.ም እትም፤ “…ላይ በስፋትና
በዝርዝር አስቀምጠዋል ።
የሰው ልጅ አለኝታውና ማዕረጉ፣ ሞገሱና ኩራቱ ታሪኩ ነው፡፡ ታሪክ ደግሞ ታሪክነቱን ሊያገኝ የሚችለው የሰው ልጅ ራሱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ጠብቆ በሚያስተላልፋቸው ወጐቹ፣ ቋንቋዎቹ፣ አፍአዊ ኪነቃሎቹ፣ ፊደልና ሥነ ጽሑፎቹ አማካኝነተ መኾኑ አያከራክርም፡፡ ታሪኩን በራሱ ፊደል መዝግቦ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍ አገር ደግሞ በእጅጉ የታደለ ነው፡፡ የሚሉት የ “ብቸኛው አፍሪካዊ ፊደል (The Sole African Alphabet) መጽሐፍ አቅራቢ በኢትዮጵያ ፊደል ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳላቸውና ከፍተኛ ጥናት እንዳካሄሔዱም መጽሐፋቸው የሚመሰክርላቸዉ ዶክተር በዚሁ ከላይ በተገለጸው መጽሐፋቸው እስከ ገጽ 10 ድረስ የኢትዮጵያ ፊደል ከ3000 ዓመታት የማያንስ ዕድሜ ያለውና በዓለም ላይ በቀደምትነት ከተፈለሰፉት ፊደላት መሐከል መሆኑን በመጥቀስ ያሞካሹታል፡፡ ታድያ! ይህን ያህል ያደነቁትንና ከኢትዮጵያም አልፈው አፍሪካዊ ፊደል ብለው ክብር የሰጡትን ፊደል እንዴት እንዳልነበረ ለማድረግ ተፈለገ ? ያሰኛል፡፡
በሰለጠነው ዓለም በቋንቋህ አስተርጓሚ ቆሞልህ ታወራለህ ለአስተርጓሚው መንግስት ከፍሎልህ አንተ በነጻ ታወራለህ ቋንቋ መግባቢያ ስለሆነ አትነፈግም ወይም ቋንቋ ስለማትችል አናክምህም አይሉም በትርጉም ያክሙሃል እኛ የተውነውንና የቀበርነውን የኛን ፊደል ጀርመኖች አጥንተው የኛን መጻህፍት ከትራሳችን ስር ወስደው ተርጉመውና ተራቀው ለዓለም በሚያቀርቡት መድኃኒት አንቱ ተብለውበታል በዩንቨርሲቲዎቻቸው በስፋት በማስተማር ተዝቆ የማያልቅ እውቀትን ያፍሱበታል ።
በኛ ሀገር ግን በዚህ ክልል ይህ ቋንቋ እንዳይነገር ይህ ፊደል ልጆች እንዳያውቁት እያሉ ከፍተኛ ጥላቻን በመስበክ እነሱ አቀላጥፈው የሚናገሩትን ቋንቋ ሚድያ ከፍተው የሚነግዱበትን ቋንቋ ልጁን እንዳትማር እንዳታውቅ ብሎ ትውልድን ማደንቆር ምን ይሉት ስልጣኔ ይሆን?
እንዲህ ትውልድን ለመግደል ወንድም ከወንድሙ ጋር እንዳይግባባ ማድረግ ህሊናን ከማጣት ውጪ ሌላ ምን ይባላል ? የሚለውን ብንተወዉ እንኳን ቋንቋን አለማወቅ ግን ብዙ ጉዳት አለው ያሉና ቋንቋን ማወቅ ማንን ሲጎዳስ አየን? የሚሉ በርካታ ሀገራት ግዕዝን እያስተማሩ ይገኛል ።
የጀርመን የቋንቋ ጥናት ተቋም፣ግዕዝን እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ሲያስተምር በዓለም ላይ መነቃቃትን ፈጠረና ግዕዝ ዓለማአቀፋዊ ትኩረት ሳበ፡፡ በ 2008 ዓም የካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ግዕዝን ከዕብራይስጥ፣ከግሪክ ፣ ከፅርዕ፣ከአራማይክ፣ከላቲን ፣ ከአረብኛና ሌሎች ጥንታዊ የዓለም ቋንቋዎች ጋር እያስተማረ ነው፡፡
የምስራቅ አፍሪካን ታሪክና ባህል ለማጥናት ግዕዝ ተመራጭ ሆኗል፡፡በሚያዚያ 2009 ዓ ም የአሜሪካው ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲም ግዕዝን ማስተማር መጀመሩን ይፋ ባደረገ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ግዕዝን ለመማር ተማሪዎች ሰልፍ ይዘው ታይተዋል፡፡
በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ መምህር የሆኑት ፕሮፊሰር ሀምዛ ዛፊር”ግዕዝ የአፍሪካ ጉዳዮችን ብቻ ሳይሆን የዓለም ሃይማኖቶችን አመጣጥ ለማጥናት ተመራጭ ቋንቋ ነው”ይላሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ግዕዝ፣ለባህላዊ መድሐኒት ቅመማ፣ለዘመን ቆጠራ ፣ለሂሳባዊ ስሌት፣ ለሥነ ፈለክ ምርምር፣ስለ ከበሩ ማዕድናት ጥናትና ምርምር፣ስለ ማይታወቁ ዓለማትና በውስጣቸው ስላሉ ልዩ ልዩ ፍጥረታት ምርምር ወዘተ አጋዥ ቋንቋ ነው፡፡
“ፊደል፡- ንግግርን በጽሑፍ ለማስፈር የሚያስችልና ድምጽን ወክሎ የሚቆም ምልክት (ለምሳሌ ሀ፣ ለ …) በማለት የምንጠራቸው ሆሄያት ከሀ-ሆ ወይም ከሀ-ፐ) ያለው የፊደላት ስምና መልክ ወይም ቅርፅ” ከግእዝ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታተመው የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር አማርኛ መዝገበ ቃላት ፊደል የሚለውን ማንበብ በቂ ነዉ ።
አንድ ቋንቋ ወይም አገር የራሱ ፊደል አለው ብሎ መናገር የሚቻለው የቋንቋውን ድምፆች የሚወክሉ ሆሄያትን የያዘ ፊደል መፈልሰፍ ሲችል ነው፡፡ ስለሆነም አማርኛ የሚጠቀምበት ፊደል 78.8% የግዕዝ በመሆኑ ፊደሉ የአማርኛ ነው ማለት ይከብዳል፡፡ እናም ግዕዝን አንፈልግም ስንል የአማርኛንም ቋንቋ መጥላታችን ነዉ
አማርኛ ቋንቋ ብልጥ ነው። ፊደል ባይኖረውም ፊደልን የተዋሠው ከግዕዝ ነው። ብዙ ሠዎች አማርኛ የራሡ ፊደል ያለው ይመስላቸዋል። ነገር ግን አብዛኛዎቹን ፊደሎች የተዋሰው ከሀገሩ ልጅ ከግዕዝ ቋንቋ ነው። የተወሠኑ ፊደሎችን ብቻ ለራሡ ድምፅ ጨመረ። የተቀሩት የግዕዝ ቋንቋ ፊደሎች ናቸው። በተውሶ የዳበረ ቋንቋ ነው።
ለነገሩ ትግርኛም፣ አደርኛም፣ ጉራግኛም ፊደሎቻቸውን የተዋሡት ከግዕዝ ነው። ሌላ ሀገር ሆና ዛሬ የተገነጠለችው ኤርትራ ሣትቀር የቋንቋዋ ፊደል የግዕዝ ነው። እነዚህ ቋንቋዎች የተዋሡት ከጐረቤታቸው፣ ከቅርባቸው ነው። ሩቅ አልሄዱም። በፊደል ሕግ ሩቅ መሔድ ብዙ አያዋጣም። አንዳንድ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የላቲን ፊደልን በመጠቀማቸው የተነሣ ዛሬ ተጐጅዎች ሆነዋል።
ተጐጂ የሆኑበት ምክንያት የላቲን ፊደሎች በውስጣችው አናባቢ (Vowel) የላቸውም። በላቲን ተነባቢው (Consonant) ሲፃፍ አናባቢው አብሮ ነው የሚፃፈው። ስለዚህ የላቲን ፊደል የተጠቀሙ የሃገራችን ቋንቋዎች አንድ ነገር ለመፃፍ ሲፈልጉ በጣም ረጅም ይሆንባቸዋል። ለምሣሌ
በአማርኛ በላቲን
አበበ Aababa
አንዱ ቃል በእጥፍ ይጨምራል። ስለዚህ ፍቅር እሰከመቃብርን ወደ ላቲን ወደሚጠቀሙ የሃገራችን ቋንቋዎቸ ብንተረጉመው ብዙ ቅጽ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። የግዕዝ ፊደሎች በውስጣቸው አናባቢውን (Vowel) ሰለሚይዙ አፃፃፋቸው ስብሰብ ይላል። ቅለትም አለው።
ለማንኛዉም ግዕዛውያን ስለምን የራሳችን ፊደል እያለን በማይገባ ጥላቻ የኛነታችንን ሀብት ጥለን በሰው ሀገር ፊደል እንጎለዳደፋልን?ሰከን ብሎ የሚጠቅመውን በቅን ልቦና ማየትና ይዞ መጓዝ ለሀገርም ለትውልድም ይጠቅማልና እመለስበታለሁ ።
የኔታ ቲዩብ በታዴ የማመይ ልጅ

11 months ago
ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተናገሩት የጨረቃ ግርዶሽ ይከሰታል ! / የአሜሪካው ምርምር ተቋም ናሳ/
ከ6 ዓመታት በፊት በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እና በዶክተር ጌትነት ፈለቀ በተዘጋጀው አንድሮሜዳ መጽሐፍ ገጽ 193 ላይ ጳጉሜን 2/ 2017 እንደሚታይ ቀድመዉ የነገሩን የፀሀይ ግርዶሽ (የጨረቃ ደም መስሎ መታየት) እንደማይቀርና የሙሉ ጨረቃ ግርዶሽ መታየቱ እና የጨረቃ ደም መምሰል የሚከሰት እዉነታ መሆኑን ናሳ አረጋግጧል ።
ኢትዮጵያዊ ዕውቀትን የሚዘክሩ በስነ-ፈለክ ፣ዐውደ-ጠፈር እና መሰል ሳይንሳዊ መስኮች ምርምሮች
የሚያሳዩ በርካታ መጽሃፍትን በመፃፍ እንዲሁም
ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ከቀሰመው በማያልቀውተዝቆ በማይደርቀው እንደ ውቅያኖስ በጠለቀ እውቀቱ ሰፊ ትንታኔ በመስጠት የምናውቀው ሳይንቲስት መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳሰ ታደሰ ከስድስት አመታት በፊት ከስድስት አመታት በፊት በአንድሮ ሜዳ መፅሐፍ ገጽ 193 ላይ ቀድሞ የነገረን እዉነት እንደሆነ ያረጋገጠዉ ናሳ እንዳለው የጨረቃ ግርዶሽ በአውስትራሊያ፣ እስያ፣ አፍሪካ እና አውሮፓ ከምድር ግማሽ ላይ በሆነው ክፍል ይታያል። ብሏል ።
መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳሰ ታደሰ ጳጉሜን 2
ከምሽቱ 12፡21 (6:21 PM) - ደማቋ ሙሉዋ ጨረቃ በምሥራቅ አድማስ መውጣት እንደምትጀምር
እና ከምሽቱ 12፡28 (6፡28 PM) መሬት ጨረቃን መከለል ስትዠምር ድብዝዙ ግርዶሽ መታየት እንደሚጀመር እንዲሁም ከምሽቱ 2፡30 ላይ (8፡30 PM) ተጠባቂው ሙሉው የጨረቃ ግርዶሽ ዠምሮ ጨረቃ ደም የምትመስልበት ሰዓት መሆኑንና ከምሽቱ 3፡52 (9:52 PM) ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ (ደም መምሰሏ) ማብቂያ እንደሚሆን በቪዲዮ ማብራሪያ ከሰጠበት በኋላ የናሳ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በጥናት በደረሱት መሰረት "በተለያዩ ሰአት አቆጣጠሮች በሴፕቴምበር 7 እና 8 አጠቃላይ "የጨረቃ ግርዶሽ በአለም አቀፍ ደረጃ ይከሰታል ክስተቱንም ከ 7 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የማየት እድል ይኖራቸዋል ሲል Space.com ዘግቧል ።
CBN News በበኩሉ ክስተቱን ሀይማኖታዊ መልክ በማየት በሰራው ዘገባ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርቧል ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የደም ጨረቃዎች በተለያዩ ቦታዎች ተጠቅሰዋል፤ እነዚህም በኢዩኤል መጽሐፍ፣ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እና በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ ሲል በጀመረው ጥልቅ ዳሰሳ።
የደም ጨረቃዎች በመጀመሪያ በኢዩኤል 2፡31፡- “ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ” ተብሎ ተነግሯል። ሐዋርያው ጴጥሮስ ያንን ትንቢት በሐዋርያት ሥራ 2፡20 ደጋግሞታል።
ከዚያም የፍጻሜው ዘመን መጽሐፍ የራእይ 6:12 እንዲህ ይላል:- “ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ እነሆም፥ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ ጨረቃም እንደ ደም ሆነ።
እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች ጨረቃ ወደ ደም ቀይ መለወጧን የፍጻሜው ዘመን እየደረሰ መሆኑን የሚያሳይ ሰማያዊ ምልክት እንደሆነ ይናገራሉ ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የታልሙድ የአይሁድ አስተምህሮዎች የጨረቃ እና የፀሐይ ግርዶሾች ለረጅም ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ምልክት ይታዩ እንደነበር ያመለክታሉ።
ከታሪክ አኳያ፣ የደም ጨረቃ መከሰት ከእስራኤል ጋር በቀጥታ በተያያዙ አንዳንድ በእውነት ዓለምን በሚለዋወጡ ክስተቶች መሆናቸውን የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት የሚያጠኑ የክርስቲያን መሪዎች፣ እንደ ፓስተር ጆን ሄጊ እና ፓስተር ማርክ ቢልትዝ ያሉት የሀይማኖት መሪዎች ገልፀዋል ባለፈው ሺህ ዓመት ውስጥ ሶስት ግርዶሾች ጎልተው የወጡ ሲሆን ይህም ከአይሁድ ህዝብ ዋና ዋና ክስተቶች ጋር ይገጣጠማል። ከ1493-1494፣ 1949-1950 እና 1967-1968 ተከስተዋል ብለዋል ።
በመሲሐዊ ትንቢት የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮጄክት መሠረት ታልሙድ እንዲህ ይላል፡- “የእኛ ረቢዎች አስተምረዋል፣ ፀሐይ በግርዶሽ ጊዜ ጣዖት አምላኪዎች ዘንድ መጥፎ ምልክት ነው፣ ጨረቃም ግርዶሽ በሆነ ጊዜ፣ እስራኤል በጨረቃ፣ ጣዖትን አምላኪዎች በፀሐይ ስለሚቆጥሩ... በፀሐይ ግርዶሽ ከሆነ፣ በምሥራቅ መጥፎ ሰዎች ይኖራሉ፣ እርሱ ለእስራኤል መጥፎ ምልክት ነው፤ በምዕራብ ለሚኖሩት መጥፎ ምልክት በሰማይ ውስጥ ቢሆኑ ለዓለሙ ሁሉ መጥፎ ምልክት ነው። ብለዋል ።
እንደ ናሳ ዘገባ፣ የምድር ጥላ ጨረቃን ሙሉ በሙሉ በሚሸፍንበት ጊዜ አጠቃላይ ደረጃው ለአንድ ሰዓት ከ22 ደቂቃ ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል። በአጠቃላይ ምድር በጨረቃ ፊት ለፊት ለማለፍ ሶስት ሰአት ከ29 ደቂቃ ይወስዳል። ሲል ገልጿል ።
አለም በሰበር ዜና መልክ ትላንትና ዛሬ እየዘገቡት የሚገኘው የምድር ጥላ በጨረቃ ላይ ወድቆ ወደ ቀይ ቀይ ቀለም መለወጥና የጨረቃ ግርዶሽ በተለይም ሦስቱ ኢትዮጵያዊያን ነገሥታቶች ካሲዮፕያ (Cassiopeia)፣ሰፌውስ (cepheus) እና አንድሮሜዳ (Andromeda) በጠለቀ እውቀቱ ለብዙዎቻችን ያሳወቀን ፣ በዓለማዊ እውቀቱ ቢሆንም እስከ ዶክትሬት ዲግሪ [ PhD in astronomy (degree of philosophy in astronomical science )] ድረስ የዘለቀው የቅድስት ቤተክርስቲያንን የዘመን አቆጣጠር በፀሐይና በጨረቃ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማመሳጠር አስልቶ ነገረን መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ቀድሞ ደርሶበት አሳዉቆናልና ክብር ይገባል ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

Comments