Logo
Getu Temesgen
ስፔስ ኤክስ በጠፈር ላይ ከሚገኙት አጠቃላይ ሳተላይቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛው ባለቤት ሆነ
#ethiopia | የኢሎን መስክ ኩባንያ ስፔስ ኤክስ 10 ሺኛ የስታርሊንክ ሳተላይቱን ወደ ሕዋ በማምጠቅ፣ በጠፈር ላይ ከሚገኙት አጠቃላይ ሳተላይቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛው ባለቤት ሆኗል።

በመሬት ምህዋር ላይ ስራቸውን እያከናወኑ ከሚገኙ 12 ሺ 955 ሳተላይቶች ውስጥ 8 ሺ 562 የሚሆኑት የስፔስ ኤክስ ንብረቶች መሆናቸው ተመላክቷል።

ከስፔስ ኤክስ ቀጥሎ ያለው የቅርብ ተፎካካሪ የሆነው ዋን ዌብ 651 ሳተላይቶች ብቻ አሉት ሲል የዘገበው ኢንዲፔንደንት ነው።

የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ የሳተላይት ፍርስራሾች ከባቢ አየርን በመጉዳት ለዓለም ሙቀት መጨመር አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል ብለው ያስጠነቅቃሉ።

በሴራን ታደሰ
#ebc #space

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.