Logo
YenetaTube
ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተናገሩት የጨረቃ ግርዶሽ ይከሰታል ! / የአሜሪካው ምርምር ተቋም ናሳ/
‎
‎
‎ከ6 ዓመታት በፊት በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እና በዶክተር ጌትነት ፈለቀ በተዘጋጀው አንድሮሜዳ መጽሐፍ ገጽ 193 ላይ ጳጉሜን 2/ 2017 እንደሚታይ ቀድመዉ የነገሩን የፀሀይ ግርዶሽ (የጨረቃ ደም መስሎ መታየት) እንደማይቀርና የሙሉ ጨረቃ ግርዶሽ መታየቱ እና የጨረቃ ደም መምሰል የሚከሰት እዉነታ መሆኑን ናሳ አረጋግጧል ።
‎
‎ኢትዮጵያዊ ዕውቀትን የሚዘክሩ በስነ-ፈለክ ፣ዐውደ-ጠፈር እና መሰል ሳይንሳዊ መስኮች ምርምሮች
‎የሚያሳዩ በርካታ መጽሃፍትን በመፃፍ እንዲሁም
‎ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ከቀሰመው በማያልቀውተዝቆ በማይደርቀው እንደ ውቅያኖስ በጠለቀ እውቀቱ ሰፊ ትንታኔ በመስጠት የምናውቀው ሳይንቲስት መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳሰ ታደሰ ከስድስት አመታት በፊት ከስድስት አመታት በፊት በአንድሮ ሜዳ መፅሐፍ ገጽ 193 ላይ ቀድሞ የነገረን እዉነት እንደሆነ ያረጋገጠዉ ናሳ እንዳለው የጨረቃ ግርዶሽ በአውስትራሊያ፣ እስያ፣ አፍሪካ እና አውሮፓ ከምድር ግማሽ ላይ በሆነው ክፍል ይታያል። ብሏል ።
‎
‎መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳሰ ታደሰ ጳጉሜን 2
‎ከምሽቱ 12፡21 (6:21 PM) - ደማቋ ሙሉዋ ጨረቃ በምሥራቅ አድማስ መውጣት እንደምትጀምር
‎እና ከምሽቱ 12፡28 (6፡28 PM) መሬት ጨረቃን መከለል ስትዠምር ድብዝዙ ግርዶሽ መታየት እንደሚጀመር እንዲሁም ከምሽቱ 2፡30 ላይ (8፡30 PM) ተጠባቂው ሙሉው የጨረቃ ግርዶሽ ዠምሮ ጨረቃ ደም የምትመስልበት ሰዓት መሆኑንና ከምሽቱ 3፡52 (9:52 PM) ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ (ደም መምሰሏ) ማብቂያ እንደሚሆን በቪዲዮ ማብራሪያ ከሰጠበት በኋላ የናሳ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በጥናት በደረሱት መሰረት "በተለያዩ ሰአት አቆጣጠሮች በሴፕቴምበር 7 እና 8 አጠቃላይ "የጨረቃ ግርዶሽ በአለም አቀፍ ደረጃ ይከሰታል ክስተቱንም ከ 7 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የማየት እድል ይኖራቸዋል ሲል Space.com ዘግቧል ።
‎
‎CBN News በበኩሉ ክስተቱን ሀይማኖታዊ መልክ በማየት በሰራው ዘገባ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርቧል ።
‎
‎በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የደም ጨረቃዎች በተለያዩ ቦታዎች ተጠቅሰዋል፤ እነዚህም በኢዩኤል መጽሐፍ፣ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እና በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ ሲል በጀመረው ጥልቅ ዳሰሳ።
‎
‎የደም ጨረቃዎች በመጀመሪያ በኢዩኤል 2፡31፡- “ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ” ተብሎ ተነግሯል። ሐዋርያው ​​ጴጥሮስ ያንን ትንቢት በሐዋርያት ሥራ 2፡20 ደጋግሞታል።
‎
‎ከዚያም የፍጻሜው ዘመን መጽሐፍ የራእይ 6:12 እንዲህ ይላል:- “ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ እነሆም፥ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ ጨረቃም እንደ ደም ሆነ።
‎
‎እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች ጨረቃ ወደ ደም ቀይ መለወጧን የፍጻሜው ዘመን እየደረሰ መሆኑን የሚያሳይ ሰማያዊ ምልክት እንደሆነ ይናገራሉ ።
‎ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የታልሙድ የአይሁድ አስተምህሮዎች የጨረቃ እና የፀሐይ ግርዶሾች ለረጅም ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ምልክት ይታዩ እንደነበር ያመለክታሉ።
‎
‎ከታሪክ አኳያ፣ የደም ጨረቃ መከሰት ከእስራኤል ጋር በቀጥታ በተያያዙ አንዳንድ በእውነት ዓለምን በሚለዋወጡ ክስተቶች መሆናቸውን የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት የሚያጠኑ የክርስቲያን መሪዎች፣ እንደ ፓስተር ጆን ሄጊ እና ፓስተር ማርክ ቢልትዝ ያሉት የሀይማኖት መሪዎች ገልፀዋል ባለፈው ሺህ ዓመት ውስጥ ሶስት ግርዶሾች ጎልተው የወጡ ሲሆን ይህም ከአይሁድ ህዝብ ዋና ዋና ክስተቶች ጋር ይገጣጠማል። ከ1493-1494፣ 1949-1950 እና 1967-1968 ተከስተዋል ብለዋል ።
‎
‎በመሲሐዊ ትንቢት የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮጄክት መሠረት ታልሙድ እንዲህ ይላል፡- “የእኛ ረቢዎች አስተምረዋል፣ ፀሐይ በግርዶሽ ጊዜ ጣዖት አምላኪዎች ዘንድ መጥፎ ምልክት ነው፣ ጨረቃም ግርዶሽ በሆነ ጊዜ፣ እስራኤል በጨረቃ፣ ጣዖትን አምላኪዎች በፀሐይ ስለሚቆጥሩ... በፀሐይ ግርዶሽ ከሆነ፣ በምሥራቅ መጥፎ ሰዎች ይኖራሉ፣ እርሱ ለእስራኤል መጥፎ ምልክት ነው፤ በምዕራብ ለሚኖሩት መጥፎ ምልክት በሰማይ ውስጥ ቢሆኑ ለዓለሙ ሁሉ መጥፎ ምልክት ነው። ብለዋል ።
‎
‎እንደ ናሳ ዘገባ፣ የምድር ጥላ ጨረቃን ሙሉ በሙሉ በሚሸፍንበት ጊዜ አጠቃላይ ደረጃው ለአንድ ሰዓት ከ22 ደቂቃ ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል። በአጠቃላይ ምድር በጨረቃ ፊት ለፊት ለማለፍ ሶስት ሰአት ከ29 ደቂቃ ይወስዳል። ሲል ገልጿል ።
‎
‎አለም በሰበር ዜና መልክ ትላንትና ዛሬ እየዘገቡት የሚገኘው የምድር ጥላ በጨረቃ ላይ ወድቆ ወደ ቀይ ቀይ ቀለም መለወጥና የጨረቃ ግርዶሽ በተለይም ሦስቱ ኢትዮጵያዊያን ነገሥታቶች ካሲዮፕያ (Cassiopeia)፣ሰፌውስ (cepheus) እና አንድሮሜዳ (Andromeda) በጠለቀ እውቀቱ ለብዙዎቻችን ያሳወቀን ፣ በዓለማዊ እውቀቱ ቢሆንም እስከ ዶክትሬት ዲግሪ [ PhD in astronomy (degree of philosophy in astronomical science )] ድረስ የዘለቀው የቅድስት ቤተክርስቲያንን የዘመን አቆጣጠር በፀሐይና በጨረቃ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማመሳጠር አስልቶ ነገረን መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ቀድሞ ደርሶበት አሳዉቆናልና ክብር ይገባል ።
‎
‎
‎
‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ
‎
‎
‎
‎

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.