አፍጋኒስታን የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ዛሬ እያከበረች ነው
በአፍጋኒስታን የሸዋል ወር ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ የዘንድሮው የዒድ ዛሬ ሐሙስ (መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም.) እየተከበረ መሆኑን የታሊባን አስተዳደር አስታወቀ።
የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጨረቃ በደቡባዊ ሄልማንድ እና በምዕራብ ፋራህ ግዛቶች መታየቷን አረጋግጧል።
ይህ ውሳኔ አፍጋኒስታንን ከሌሎች የእስልምና እምነት ተከታይ አገራት የተለየ የዒድ ቀን እንዲኖራት አድርጓታል።
ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኳታር እና ኩዌት ጨረቃ ባለመታየቷ በዓሉን ነገ ዓርብ እንደሚያከብሩ አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ ቱርክ እና አውስትራሊያ በሥነ-ፈለክ ስሌት መሠረት ዓርብን የዒድ ዕለት አድርገው ሰይመዋል።
ቀደም ሲል አፍጋኒስታን ከሳውዲ አረቢያ ጋር በዓላትን ብታከብርም፣ በቅርብ ዓመታት ግን የራሷን የጨረቃ ምልከታ ዘዴ በመጠቀም መወሰን ጀምራለች።
ምንጭ፦ አናዶሉ ኤጀንሲ

5 months ago