መሬት አዲስ ጨረቃ አገኘች
👉"ጊዜያዊዋ የጨረቃችን" አዲስ ጎረቤት ተገኘች : 'አስቴሮይድ 2025 ፒኤን7' ምድርን ስታጅብ የቆየችው ለ60 ዓመታት ነው ተብሏል
#ethiopia | የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች አስገራሚ ግኝት ይፋ አደረጉ! በናሳ ድጋፍ በ'ፓን-ስታርስ' ጥናት አማካኝነት አስቴሮይድ 2025 ፒኤን7 የተሰኘች ትንሽ ጠፈር ድንጋይ ተለይታለች። ይህች የጠፈር አካል ለ60 ዓመታት ያህል በጸጥታ ከምድር ጋር ተጓዥ ሆና ቆይታለች።
ይህች አዲስ 'ኳሲ-ሳተላይት'፣ ወይም "ጊዜያዊ ጨረቃ"፣ በጠፈር ላይ የምድር ጎረቤት ብትሆንም በቀጥታ ምድርን የምትዞር ሳይሆን፣ በፀሐይ ዙሪያ የምድርን ምሕዋር ተከትላ የምትጓዝ ናት። ግኝቱ የተካሄደው በኦገስት 2, 2025 ዓ.ም. በሃዋይ ሃሌአካላ በሚገኘው የፓን-ስታርስ ቴሌስኮፕ ነው።
ስፋቷ ወደ 19 ሜትር (60 ጫማ) ገደማ የሆነች፣ እጅግ ትንሽ በመሆኗ በብርሃን እጥረት ምክንያት እስከ አሁን ድረስ ለመለየት አስቸጋሪ ሆና ቆይታለች ነው የተባለው።
አስቴሮይዷ ፀሐይን ለመዞር በግምት አንድ ዓመት የሚፈጅባት ሲሆን፣ ከምድር ጋር 1፡1 የሆነ የምሕዋር ተመሳሳይነት ትጠብቃለች። ከምድር እይታ አንጻር ስትታይ፣ ፕላኔታችንን የምትዞር ትመስላለች ነው የተባለው።
ትንተናዎች እንደሚያሳዩት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ይህን የምሕዋር ዝምድና ስትጠብቅ የቆየች ሲሆን፣ በዚህ ሁኔታ እስከ 2083 ዓ.ም. ድረስ ከምድር ጋር እንደምትጓዝ ይተነበያል።
ከምድር የምትኖረው ርቀት ከአነስተኛ ሚሊዮን ኪሎሜትሮች አንስቶ እስከ 17 ሚሊዮን ኪሎሜትር ድረስ የሚለያይ በመሆኑ፣ እንደ እውነተኛ የጨረቃ ቅርብ ሳተላይት አትቆጠርም ተብሏል።
የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ 2025 ፒኤን7 ምንም ዓይነት የመጋጨት አደጋ አትፈጥርም። ምሕዋሯ የተረጋጋ በመሆኑ እና መጠኗ በጣም ትንሽ በመሆኑ ምክንያት፣ በምድር ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይኖራትም ተብሏል።
እንደ 2025 ፒኤን7 ያሉ "ጊዜያዊ ጨረቃዎች" መገኘት ከፍተኛ ሳይንሳዊ ጠቀሜታ አለው የተባለ ሲሆን እንደዚህ ያሉ ትናንሽ አካላት በፕላኔቶች ስበት እንዴት ለጊዜያዊነት ጎረቤት እንደሚሆኑ ለማጥናት ተመራማሪዎችን ይረዳል ነው የተባለው።
ምድርን የምትከተልበት መንገድ ለወደፊቱ የጠፈር መንኮራኩር ተልዕኮዎች ወይም የአስቴሮይድ ቁሶችን የማምጣት ቴክኖሎጂዎችን ለመሞከር እንደ ምቹ የጠፈር ላቦራቶሪ እንድትታይ ያደርጋታል ነው የተባለው።
በዚህ ግኝት ምድር ቋሚ አዲስ ጨረቃ ባታገኝም፣ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ከእኛ ጋር በዝምታ ስትጓዝ የቆየች ጠባብ ጠፈር ድንጋይ መኖሯ ተረጋግጧል። ይህች ጊዜያዊ ጎረቤት፣ የፕላኔታችን ምሕዋር በብዙ የጠፈር ተጓዦች የተሞላ መሆኑን የሚያሳይ የቅርብ ማሳሰቢያ ሆናለች ያለው መናኸሪያ ሬዲዮ ነው።

10 months ago