2 days ago
ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት፡ ስልክ ላይ የማቀርቀርን አዚም የሰበረው ባለታክሲ
********************
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚንቀሳቀሱ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች አብዛኛውን ጊዜ በሙዚቃ ጩኸት፣ በትራፊክ ጫጫታና በጉዞ ድካም አዙሪት ውስጥ በመቆየት ይታወቃሉ።
ተሳፋሪውም ታክሲ ውስጥ እንደገባ አንገቱን ደፍቶ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ መንሸራሸር የዘመናችን የተለመደ እውነታ ሆኗል። ወጣት ሰሎሞን አማረ ግን፣ የራሱን ሜትር ታክሲ ከዚህ አሰልቺ እና የተለመደ ምህዋር በማውጣት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወደ የሚሽከረከር "ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት" ቀይሮታል።
በንግድና በጥድፊያ በሚታወቀው የመርካቶ ሰባተኛ ሰፈር ተወልዶ ያደገው ሰሎሞን፣ ከቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ከዲጂታል ሚዲያው መስፋፋት ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ፣ በተለይም ወጣቱ፣ ከመጽሐፍት እየራቀ መምጣቱ በእጅጉ አሳስቦታል። በዚህም የተነሳ፣ ላለፉት ጥቂት ወራት ታክሲውን የዕውቀት ማዕከል በማድረግ ልዩ ልዩ የአማርኛና የእንግሊዝኛ መጻሕፍትን ለተሳፋሪዎቹ እንደ አዲስ አማራጭ ማቅረብ ጀምሯል።
ሁሉም ሰው ስልኩ ላይ ባቀረቀረበት በዚህ ዘመን፣ ሰሎሞን የታክሲው ውስጥ መደርደሪያዎች ላይ መጽሐፍትን በማስቀመጥ የሰዎችን ትኩረት ወደ ንባብ ለመመለስ የራሱን የትግል ስልት ነድፏል።
ሰለሞን ወደ ታክሲው ለሚገቡ መንገደኞች የሚያቀርበው ሞቅ ያለ ፈገግታና ሰላምታን ብቻ አይደለም፤ በስርዓት የተደረደሩ የዕውቀት ማህደሮችንም ጭምር እንጂ። የትራፊክ መጨናነቅን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ተሳፋሪዎች በጉዞ ወቅት መጽሐፍትን እንዲያነቡ ይጋብዛል።
የጀመሩት መጽሐፍ ልባቸውን ከሰረቀው ደግሞ፣ እዚያው ታክሲ ውስጥ ገዝተውት መንገዳቸውን ያለመሰልቸት በዕውቀት ታጅበው ያጠናቅቃሉ። ይህ አሰራር ከማህበራዊ ሚዲያ ጩኸት ለተወሰኑ ደቂቃዎችም ቢሆን አእምሮን የሚያሳርፉበት ልዩ የጉዞ ተሞክሮ ሆኗል።
የሰሎሞን አካሄድ የንባብ ባህልን ከማበረታታት ባለፈ፣ የገበያ ጥናትን (Marketing Management) ከተግባር ጋር ያዋሃደ አዲስ የስራ ፈጠራ ነው።
ጊዜን ወደ እሴት መቀየር፡ የታክሲ ተሳፋሪን የትራፊክ ውስጥ የባከነ ጊዜ ወደ ምርታማ የገበያ ሰዓት ቀይሮታል።
ድርብ ገቢ፡ ከትራንስፖርት አገልግሎቱ ባሻገር፣ መጽሐፍትን በመሸጥ የራሱን የገቢ ምንጭ አሳድጓል።
ማህበራዊ ካፒታል፡ "ተሳፋሪዎች የሚሰጡት አዎንታዊ ምላሽና አስደናቂ ስሜት ለስራዬ ትልቅ መነቃቃት ይፈጥርልኛል" የሚለው ሰሎሞን፣ በየቀኑ ከሚያገኛቸው አዳዲስ ሰዎች ጋር የሚያደርገው ገንቢ ውይይት ከገንዘብ በላይ የሆነ ትልቅ የህይወት ስንቅ እንደሆነለት ይናገራል።
የሰሎሞን አስገራሚው ጎን የዲጂታል ዓለሙን ሙሉ በሙሉ መሸሹ ሳይሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለራሱ ዓላማ ማዋሉ ነው። "Sol Books" በሚል ስያሜ በቲክቶክና በሌሎች ማኅበራዊ ገጾች መጻሕፍትን በማስተዋወቅ፣ ዲጂታል ትውልዱን በዲጂታል መድረክ እየቀሰቀሰ ይገኛል።
የዚህ አብዮተኛ ወጣት መልዕክት አጭር እና ግልጽ ነው፦ የተለመደውን አሰራር በመስበር ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም ይህን መሰል በጎ ተግባር ቢያራምዱ፣ ታክሲዎቻችንን ከትራፊክ ጫና ማምለጫነት አልፈው የዕውቀት፣ የሰላምና የፈጠራ ማዕከል ማድረግ ይቻላል።
በሊያ ተስፋዬ
Ethiopian Broadcasting Corporation FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/ #መጽሀፍ #ንባብ

3 days ago
“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

9 days ago
በሆነ በዘመን የቀረውን እኔን የመለሰ አልበም!
የአህመድ ተሸመ (ዲንቢ) “ጊዜ አይሄድም”!
ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕሮፌሰር)
#ethiopia | መቸም የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ድንቅ የዜማ ደራሲነት ሰብዕና ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ ለራሱ የሠራቸውን ዘግየት እናድርግና ለሌሎች የሙያ አጋሮቹ ሠርቶላቸው በብዙኋን አድማጮች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነትን ያገኙትን የዜማ ድርሰቶቹን እንዘርዝር ብንል ጊዜም ሥፍራም አይበቃንም፡፡
እንደው ከግምታችን በላይ ስለሆነው ስለዲንቢ የላቀ የዜማ ደራሲነት ሰብዕና መሠረታዊ ግንዛቤ ሊያስጨብጠን ቢችል ግን ጥቂቱን ብቻ ከዚህ እንደሚከተለው እዘረዝርላችኋለሁ፡—
ለአሊ ቢራና ሄለን በርሄ - “ሲያዴ”፤ ለፀሀዬ ዮሐንስ - “ማን ልበልሽ”፤ ለማዲንጎ አፈወርቅ - “ላላተርፍ”፤ ለብዙአየሁ ደምሴ - “የህልሜ ንግስት”፤ ለዘቢባ ግርማ - “ገራገር”፤ ለኢሳያስ ታምራት - “እያዳነ ያማል”፤ ለታረቀኝ ሙሉ - “ስሚያቸው”፤ ለሚኪያስ ቸርነት - “ግርማ ሞገሴ”፤ ለሃይማኖት ግርማ - “ከዚራ ቁ-2”፤ ለግርማ ተፈራ - “ልዩ”፤ ለሀመልማል አባተ - “ሀሴት”፤ እና የመሳሰሉቱን የአህመድ ዲንቢን የዜማ ፈጠራዎች ከብዙ በጥቂቱ ማስታወስ ይቻላል፡፡
አንዳንድ ሙዚቃዎች ለጆሮ ብቻ አይሰሩም፤ ለስሜት ይደርሳሉ፤ ዛሬ ተሰርተው ግን ትዝታችንን ይመልሱልናል፡፡
አንዳንድ ዜማዎች፣ በውስጣችን የተከረቸሙ የጊዜ በሮችን ያንኳኳሉ፤ ይከፍታሉምም፡፡ በሮቹ ሲከፈቱ ደግሞ የተዘነጉ ፊቶች፣ የተለየናቸው ጓደኞች፣ የተራመድንባቸውን ጎዳናዎች… ብቻ ምኑ ቅጡ ትላንታችንን እንደ መጽሀፍ ይገልጡልናል፡፡ በሆነ ዘመን የቀረውን ማንነታችንን እንደገና ይመልሱልናል።
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ከ14 ዓመታት በኋላ በአዲስ አልበሙ ሲመለስ፣ እኔ የሰማሁት የአዳዲስ ዜማዎች ስብስብን አይደለም። አንድ በሆነ ዘመን የነበረ የዜማ ሰዋሰውና በዚሁ ዜማ ምክንያት የተሰፋ፣ የምናፍቀውን ዘመን የመለሰልኝ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡
ያ የኔ ዘመን የምለው “ዘጠናዎቹ”ን ነው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆኜ የገባሁት በ1997 ዓ.ም. ነው። አይ፣ ተማሪነት! እንዴት ያለ ጣፋጭ፣ እንዴት ያለ የማይደገም ዘመን ነበር! ያ ዘመን ለእኔ የወጣትነት ወርቃማ ጠዋት ነበር። ዓለምን እንደ አዲስ ማየት የጀመርኩበት፤ ከተማዋን፣ ሕይወትን፣ ፍቅርን፣ ሐሳብንና ነፃነትን ለመጀመሪያ ጊዜ በሙሉ ልብ ያጣጣምኩበት ዘመን ነበር።
ያ ዘመን ከጓደኞቸ ጋር እንደፈለግን የኖርንበት ዘመን ነበር። በአደባባይ የተከራከርንበት፣ አለምን የጠየቅንበት፣ መንግሥትን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃወምንበት፣ ነፃነትን ያየንበት፣ ዜማን ያጣጣምንበት ወቅት ነበር። ያ ዘመን “ዘጠናዎቹ” ነበር፡፡
ያንን ዘመን ሁሌም እናፍቀዋለሁ፤ ምናልባትም የምናፍቀው ዘመኑን ራሱን አይደለም፤ በዚያ ዘመን ውስጥ የነበርነውን እሱን፣ እሷን፣እኔን፣እኛን ነው። እንደገና እንዲመጣም እመኛለሁ።
ማርሴል ፕሩስት የተባለ ፈረንሳያዊ የልብ ወለድ ጸሀፊና ሀያሲ ጥልቅ የሆነን ትዝታ አስበን ለማስታወስ በምናደርገው ጥረት አይመለስም፤ ነገር ግን የስሜት ሕዋሳችን በሚነካ አንድ ድንገተኛ ልምድ ሊቀሰቀስ ይችላል ይላል፡፡ ሙዚቃም ከእነዚህ የትዝታ ቀስቃሾች መካከል እጅግ ኃይለኛው ሳይሆን አይቀርም።
በዚህ ረገድ እንደ አህመድ ተሾመ ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራ ዜማ የተረሳ ግን ተደበቀ ስሜትን ይቀሰቅሳል፤ የጠፋ የሚመስለውን የዜማ ስልተ ምት ይመልሳል፤ በዘመን ጥላ ሥር ተደብቆ የኖረ ማንነት እንደገና ያነቃቃል።
በ1990ዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የራሱ የሆነ የዜማ ሰዋሰው፣ ቀለምና የአወራረድ ለዛ ነበረው። ያ ዘመን ለእኔ ሙዚቃን ከመስማት ወደ ማዳመጥ የተሸጋገርኩበት ጊዜ ነው። ስለዚህ የዚያ ዘመን ዜማዎች በጆሮዬ ብቻ ተደምጠው አልቀሩም፤ በማንነቴ ውስጥ ህያው ናቸው።
እኔ የሙዚቃ ባለሙያ አይደለሁም፤ ሙዚቃን ግን በልቤ አዳምጠዋለሁ። በእኔ የዜማ አረዳድ፣ የዚያ ዘመን የዜማ አሠራሮች በቀላሉ የሚደገሙ አይደሉም። ምክንያቱም ዜማው የተፈጠረው በድምፅ ብቻ ሳይሆን፣ በዘመኑ መንፈስም ጭምር ነው። ከዚያ በኋላ የመጡት ዘመናት የራሳቸውን የሙዚቃ ቋንቋ ፈጥረዋል።
ያው ዘመን ሲለወጥ የዜማ ሰዋሰውም የሚለወጥ ይመስለኛል፡፡ ይህም የሥነ ጥበብ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው፤ ዋናው ጉዳይ ግን በ1990ዎቹና ከዚያ በኋላ በመጡት ዜማዎች መካከል የተቋረጠ ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ መቆራረጡ ለሙዚቃ ባለሙያዎች ትልቅ የጥናት ርዕስ የሚሆንም ነው፡፡
ታዲያ የአህመድ ተሾመ አዲስ አልበም፣ የ1990ዎቹን የዜማ መንፈስ አገኘሁበት፤ የቀድሞውን በቀጥታ ሳይደግም፣ ያንን ለዛ በአዲስ ስልተ ምት የቀነበበ ዜማ ሆኖ አዳመጥኩት። ጉዳዩን ሳይንቲፊካሊ መግለጽ ባልችልም ልቤ ግን አልበሙ በዚያን ጊዜና በዛሬው የሙዚቃ ዘመን መካከል የተዘረጋ የዜማ ድልድይ እንደሆነ ይነግረኛል።
በአጠቃላይ ለእኔ፣ የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ጊዜ አይሄድም አዲስ አልበም የአዳዲስ ዜማዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ካለፈ ጊዜና ትዝታ ጋር የተደረገ ውይይት ነው፤ ትናንትን ከዛሬ ጋር ያስታረቀ የዜማ ድልድይ ነው፤ በዘጠናዎቹ የቀረውን እኔን የመለሰ አልበም ነው። ይመችሽ ዲንቢ!!
ካላመናችሁኝ ደግሞ ከአዲስ አልበሙ መካከል "ጊዜ አይሄድም"፣"አይሽና"፣ "ይረፍዳል" እና "ህልም ነው" አድመጣችሁ ፍረዱኝ፤ ካጠፋሁ እኔ ሳልሆን ዲንቢ ይቀጣል፡፡

1 month ago
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለታዋቂው የሰው ዘር ጥናት ምሁር ፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሃንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባኤ በሰው ልጅ አመጣጥ ሳይንስ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ፣ በምርምርና በትምህርት ዘርፍ ለአለም ያበረከቱትን የዕድሜ ልክ አገልግሎት እንዲሁም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ ምድር መሆኗን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስታወቅ ላደረጉት ታላቅ ሚና ዕውቅና በመስጠት ለፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሃንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት (Doctor of Science, Honoris Causa) ዲግሪ ሰጥቷል።
ፕሮፌሰር ጆሃንሰን በ1974 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ “ሉሲ” ወይም “ድንቅነሽ” በመባል የምትታወቀውን የ3.2 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላት የሰው ዘር ቅሪተ አካል በማግኘታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ሆነዋል። ይህ ግኝት የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥን የሚመለከቱ ሳይንሳዊ እውቀቶችን በእጅጉ የቀየረ ሲሆን፣ የቀደሙ የሰው ዝርያዎች አእምሯቸው ከማደጉ በፊት በሁለት እግራቸው ቀጥ ብለው ይራመዱ እንደነበር ለማረጋገጥ ወሳኝ ማስረጃ ሆኗል።
ፕሮፌሰር ጆሃንሰን ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ በአንትሮፖሎጂ የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል። በኋላም በሰው ልጅ መገኛ ጥናት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያለውን የሉሲን ግኝት በማሳካት ለሳይንሱ ዘርፍ የማይረሳ አሻራ አስቀምጠዋል። ፕሮፌሰር ጆሃንሰን በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሰው ዝግመተ ለውጥና ማኅበራዊ ለውጥ ትምህርት ቤት (School of Human Evolution and Social Change) የክብር ፕሮፌሰር (Professor Emeritus) ሲሆኑ፣ እንዲሁም የ የሰው ልጅ አመጣጥ ጥናት ተቋም (Institute of Human Origins) መስራች ዳይሬክተር ናቸው።
“Lucy: The Beginnings of Humankind” የተሰኘውን መጽሀፍ ጨምሮ በርካታ ሳይንሳዊ ሥራዎችን በማበርከት፣ በማስተማርና ለሕዝብ ተደራሽ የሆኑ የሳይንስ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሳይንስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን ቅርሶች ለመጠበቅና ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ጆሃንሰን ለሰው ልጅ መገኛ ሳይንስ ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋፅኦ፣ በሰው ዘር መነሻ ጥናት ውስጥ የኢትዮጵያን ሚና በማጉላት ያሳዩትን ክብር እና ለዓለም አቀፍ ትምህርትና ምርምር ያበረከቱትን ልዩ አገልግሎት በማድነቅ ይህንን ከፍተኛ ክብር አበርክቶላቸዋል።

Sponsored by
Surafel
1 month ago
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለታዋቂው የሰው ዘር ጥናት ምሁር ፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሃንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ።
#ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባኤ በሰው ልጅ አመጣጥ ሳይንስ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ፣ በምርምርና በትምህርት ዘርፍ ለአለም ያበረከቱትን የዕድሜ ልክ አገልግሎት ይህንን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ ምድር መሆኗን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስታወቅ ላደረጉት ታላቅ ሚና ዕውቅና በመስጠት ለፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሃንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት (Doctor of Science, Honoris Causa) ዲግሪ ሰጥቷል።
ፕሮፌሰር ጆሃንሰን በ1974 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ “ሉሲ” ወይም “ድንቅነሽ” በመባል የምትታወቀውን የ3.2 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላት የሰው ዘር ቅሪተ አካል በማግኘታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ሆነዋል።
ይህ ግኝት የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥን የሚመለከቱ ሳይንሳዊ እውቀቶችን በእጅጉ የቀየረ ሲሆን፣ የቀደሙ የሰው ዝርያዎች አእምሯቸው ከማደጉ በፊት በሁለት እግራቸው ቀጥ ብለው ይራመዱ እንደነበር ለማረጋገጥ ወሳኝ ማስረጃ ሆኗል።
ፕሮፌሰር ጆሃንሰን ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ በአንትሮፖሎጂ የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል።
በኋላም በሰው ልጅ መገኛ ጥናት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያለውን የሉሲን ግኝት በማሳካት ለሳይንሱ ዘርፍ የማይረሳ አሻራ አስቀምጠዋል።
ፕሮፌሰር ጆሃንሰን በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሰው ዝግመተ ለውጥና ማኅበራዊ ለውጥ ትምህርት ቤት (School of Human Evolution and Social Change) የክብር ፕሮፌሰር (Professor Emeritus) ሲሆኑ፣ እንዲሁም የ የሰው ልጅ አመጣጥ ጥናት ተቋም (Institute of Human Origins) መስራች ዳይሬክተር ናቸው።
“Lucy: The Beginnings of Humankind” የተሰኘውን መጽሀፍ ጨምሮ በርካታ ሳይንሳዊ ሥራዎችን በማበርከት፣ በማስተማርና ለሕዝብ ተደራሽ የሆኑ የሳይንስ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሳይንስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ቅርሶች ለመጠበቅና ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ጆሃንሰን ለሰው ልጅ መገኛ ሳይንስ ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋፅኦ፣ በሰው ዘር መነሻ ጥናት ውስጥ የኢትዮጵያን ሚና በማጉላት ያሳዩትን ክብር እና ለዓለም አቀፍ ትምህርትና ምርምር ያበረከቱትን ልዩ አገልግሎት በማድነቅ ይህንን ከፍተኛ ክብር አበርክቶላቸዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ጎንደርዩኒቨርስቲ #ፕሮፌሰርጆሃንሰን #ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

3 months ago
THE REMAKING OF ADDIS ABABA!!
#ethiopia | ዛሬ የመፅናትና የማሸነፍ፣ የድላችንን አሻራ፣ የከተማችንን ለውጥ የታዘቡ የውጭ ሀገራት ፀሀፊዎችና ባህርማዶ የሚኖሩ ምሁራን በራሳቸው ተነሳሽነትና ገንዘብ ያሳተሙትን “THE REMAKING OF ADDIS ABABA/አዲስ አበባን እንደ አዲስ ” የተሰኘ መጽሐፍ ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት አስመርቀናል።
ይህ መጽሀፍ ለህዝባችን ቃል ገብተን፣ ቃላችንን በተግበር የቀየርንበትን ታሪክ የሚተርክ ነው። ሕዝባችን በገንዘቡ፣ በጉልበቱ፣ በሀሳቡ የተሳተፈበት የሁላችንም ውጤት ነው።
ከባህር ማዶ እንግሊዛዊው ጸሐፊዉ ኘሮፌሰር ስሞን ሊ፣ ዶ/ር ክሌመንት ካቱሉሺ፣ ትዉልደ ኢትዮዽያዊው ዶ/ ር ሂርዾ ቁምቢ እና ቡድናቸው በጋራ የጻፋት መጽሐፍ፣ ጠንካራ እሳቤ ወደ ተጨባጭ ስኬት መቀየሩን እና የአዲስ አበባን ትራንስፎርሜሽን ያሳየ እንዲሁም ለትውልድ የሚሻገር ታሪክን የሰነደ በመሆኑ ለጸሀፊዎቹ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
የባህር ማዶ ሰዎችን ቀልብ በሳበው የከተማችን ልማት፤ የሺዎች ድካምና ብርታት፣ የትወልድ አሻራ ለማሳረፍ የደከሙትን ሁሉ እውቅና እንሰጣለን፤ እናመሰግናለን!!!
የለውጥ ጉዞው የሁላችንም ኩራት ሲሆን፣ በቀጣይም ከተማችንን ይበልጥ ለማበልጸግ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም በአቡ ዳቢ ተመረቀ
#ethiopia | በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም የምረቃ ሰነ-ስርዓት በአቡዳቢ ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሻክቦት ናሃያን አል ናሃያን እና ሌሎች የአገሪቷ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ንጉሣዊ ቤተሰቦች፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የቢዝነስ ማህበረሰቡ፣ እና የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ታዳሚ ሆነዋል።
በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት ''የመደመር እሳቤ'' ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሃገራትና ለዓለም ህዝቦች ያላትን የትብብር መርህ የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዉ ወደ አረብኛ መተርጎሙ በመደመር እሳቤ የምትመራዋን ኢትዮጵያን በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ሁሉም ዓረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራትና ሕዝቦች ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
አክለዉም የኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሁለትዮሽ ግንኙነት በጠንካራ የወንድማማችነት መርህ ላይ የተመሰረተ መሆኑንም አንስተዋል።
የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሻክቦት ናሃያን አል ናሃያን በበኩላቸው ''የመደመር መንግስት'' መጽሀፍ በዐረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በመቅረቡ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ መፅሀፋ በህዝቦች መካከል ያለውን የባህልና የእሴት ትስስር እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በሃገራቸው እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ጠንካራ ግንኙነት በአስቸጋሪ ጊዚያት ማይናወጥ መሆኑን በማንሳት ግንኙነቱን የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሃገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል።
በፕሮግራሙ ላይ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስል ጄኔራል አቶ ዘሪሁን መገርሳን ጨምሮ የዕለቱ የክብር እንግዶች መፀሀፉን በይፋ የመረቁ ሲሆን የኢትዮጵያን የባህላዊ ምግቦችና ዉዝዋዜዎች ለዕይታ መቅረባቸዉን በአቡዳቢ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #amn

የሀገር ፍቅርን ከእናታቸው የተማሩት ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይናን ለ13 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት የመሩት ሺ ጂንፒንግ አሁን ለደረሱበት ተፅዕኖ ፈጣሪነት እና የመሪነት ደረጃ እናታቸው ቺ ዢን መሰረት እንደሆኑላቸው ይነገራል፡፡
በዓለም ላይ ያሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና መሪዎች አሁን ላይ ለደረሱበት ደረጃ የተለያዩ የህይዎት ተሞክሮዎች እና ምሳሌ የሆኗቸው ሰዎችን በምክንያትነት ያነሳሉ፡፡
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግም አሁን ለደረሱበት ደረጃ እና የፖለቲካ ተፅዕኖ ፈጣሪነት እናታቸው ቺ ዢን ምሳሌ ሆነዋቸዋል፡፡
ቺ ዢን በ1939 ኮሙኒስት ፓርቲን በመቀላቀል በፓርቲው ውስጥ በበርካታ የኃላፊነት ቦታ ላይ አገልግለዋል፡፡
በ1953 የተወለዱት ፕሬዚዳንት ሺ የእናታቸውን ሀገር ወዳድነት ስሜት እየተመለከቱ ስለ ሀገር ፍቅር ምንነት ተምረዋል።
ከእለታት አንድ ቀንም እናት ቺ ዢን በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሰራው ጀብዱ እና ታማኝነት በቻይናውያን ዘንድ የሚዘከረውን ዩ ፌይ ታሪክ የሚያወሳ መጽሀፍ ገዝተው ለልጃቸው ሺ ሰጡ፡፡
ከዚህ የዩ ፌይ ታሪክ ለሀገር እስከ መስዋዕት የደረሰ ዋጋ መክፈልን የተማሩት ፕሬዚዳንት ሺ የህይዎታቸውን መርህ ከመጽሀፉ ቀድተዋል።
በተጨማሪም ቀለል ያለ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ሺ ጂንፒንግ ከእናታቸው ተምረዋል፡፡
ለአብነትም በ1980ዎቹ ፕሬዚዳንት ሺ በቻይና ሁቤይ ግዛት እየሰሩ በነበረበት ወቅት እናታቸው ከአስር ዓመታት በፊት ከአሮጌ ጨርቃጨርቅ የሰሩላቸውን ብርድ ልብስ ሲለብሱ ታይተዋል፡፡
ፕሬዚዳቱ አዲስ ብርድ ልብስ ቢገዛላቸውም “የእናቴ ብርድ ልብሶች ተመችተውኛል” ሲሉ መናገራቸው ለብዙዎች አግራሞትን ፈጥሮም ነበር፡፡
በፈረንጆቹ 2012 ላይ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሺ፤ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ የቻይና ፕሬዚዳንት በመሆን እስካሁን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
እንደ ታይም መጽሔት ዘገባ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ዶናልድ ትራምፕን፣ ቤኒያሚን ናታኒያሁን፣ ናሬንድራ ሞዲን እና ክላውዲያ ሼንቦም በመብለጥ ዓለማችን ካሉ ተጸዕኖ ፈጣሪ መሪዎች ቀዳሚ ናቸው፡፡
በሚኪያስ አየለ

4 months ago
መ/ቁ 00030
ፍትህ በጲላጦስ
ከሳሽ ፦አይሁድ ጠበቃ💥 ዲያብሎስ ጋር ቀርበዋል
ተከሳሽ ፦ኢየሱስ ክርስቶስ💠 ጠበቃ መንፈስ ቅዱስ ጋር ቀርበዋል
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዪ ፍርድ ተሰጥቷል
🔥 ፍርድ
#ethiopia | ለዚህ ክስ ምክንያት የሆነው ከሳሽ በጠበቃቸው አማካይነት በ30 አ.ም ተከሳሽ ለግርፋት ስቃይ እና መስቀል ሞት የሚያበቃ ወንጀል ፈጽሟል በመባሉ ምክንያት ሲሆን የወንጀሉ ዝርዝር 1/የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱ በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 22፥71 እንደተጻፈው
2/የአይሁድ ንጉስ ነኝ ማለቱ
3/ለቄሳር ግብር ህዝቡ እንዳይሰጥ ማድረጉ
4/ህዝብን በማሳመጽ በሉቃስ ወንጌል 23፥1-3 እንደተገለጸው የሙሴን ህግጋት በመተላለፉ ነው።
💥ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ የፍርድ ችሎት ከቀረበ በኋላ ከከሳሽ የቀረበለትን ክስ ተመልክቶ በመጀመሪያ ደረጃ ጉዳዩን ተቀብሎ ለማየት የግዛት ስልጣን አለኝ ወይንስ የለኝም የሚለውን መርምሯል🔥
ይህን በተመለከተ ሲያጣራ የተከበሩ ዳኛ ጲላጦስ ኢየሱስ ክርስቶስ ገሊላዊ መሆኑን በመረዳት ገሊላም በሄሮድስ ግዛት መሆኑን በመረዳት ይህን ጉዳይ ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት ጉዳዩ በሄሮድስ ግዛት እንዲታይ ብይን ሰጥቶበታል ።
ወደ ሄሮድስ ግዛት እንዲታይ ታጅቦ የተላከው ክርሰቶስ ከሄሮድስ ፊት ቀረበ።ሄሮድስም የኢየሱስን ዜና ስለሚሰማ በፊቱ ስለቀረበ ደስ አለው።ሄሮድስም ኢየሱስን ሲጠይቀው ኢየሱስ ዝም ብሏል። ዝም ማለቱ እንዳላመነ አስቆጥሮለታል።ሄሮድስ የማየት ስልጣኑን በተመለከተ ምክንያቱን ባያስረዳም ጉዳዩን ወደ ጲላጦስ መልሶታል ።
💥ጲላጦስም ጉዳዩን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው መሆኑን ተረድቶ ለኢየሱስ የእምነት ክህደት ቃል አቅርቦለት ኢየሱስ ከተከሰሰበት ሁለቱን ክሶች ያመነ ሲሆን እነዚህም የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ና የአይሁድ ንጉስ ነኝ ማለቱን ነው
በእነዚህ ሁለቱ ክሶች ላይ ብያለሁ ይበል እንጂ ጥፋተኛ ነኝ አላለም ከዚህ ጋር ተያይዞ የተከሰሰበት ህግ ምን ይላል የሚለውን ማየቱ ተገቢ ነው።ባልታመኑት ሁለቱ ክሶች ላይም ጲላጦስ መርምሯል።
💠ኢየሱስ ክርስቶስ ግብርን በተመለከተ በሉቃስ ወንጌል 20፥25 የቄሳርን ግብር ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር በማለት አይሁዳውያን ስለግብር ለጠየቁት ጥያቄ መልስ ሰጥቷል ይህ ለእርሱ ማስረጃ ሲሆን አይሁዳውያን ግን በዚህ ላይ ማስረጃ አላቀረቡም
💠ኢየሱስ ህዝብን አሳምጿል?ሁከት አስነስቷል?"የሚለውን ስንመለከት ኢየሱስን አምስት ገበያ ህዝብ በፍላጐት ተከትለውታል አብልቶ አጠጥቶዋቸዋል ፈውሷል የሞተ አስነስቷል አይነስውር አብርቷል ሽባ ተርትሯል ጎባጣ አንቅቷል በውሀ ላይ ተራምዷል እነርሱ ራሳቸው በመጻህፋቸው የሚጠባበቁትን መንግስተሰማያት ሰብኳል ለብዙ ዘመናት በበሽታ በደዌ የተያዙትን ከህመማቸው ነጻ አድርጓል ይህን ተግባር ራሳቸው የሚያውቁት ሲሆን በአራቱም የወንጌል መጽሀፍ ተቀምጧል።የወንጀል ባህሪም የለውም ።እነርሱ ግን ለዚህ ተጨባጭ ማስረጃ አላቀረቡም ።
💠ከሁከት ጋር ተያይዞ ለተነሳው አይሁዳውያን በሰለሞን ቤተመቅደስ ንግድ ሲገበያዩ ነጋዴዎችን ማባረሩ እንስሳቶችን ከየጎሪያቸው መልቀቁ የንግድ እቃዎችን መበተኑ በተመለከተ ሲመረመር ሁከት የሚያስብል አይደለም ።ምክንያቱም 1/ቤተመቅደሱን ያሰራው ጠቢቡ ሰለሞን ሲሆን አገልግሎቱም ህዝቡ ከአምላኩ እግዚአብሔር ጋር በጸሎት እንዲገናኝ እንዲያመሰግን ነው።ለንግድ አልተፈቀደላቸውም ።እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ወይም ለጸሎት የሚመጣ በንጉስ ሰሎሞን መብት አለው ።ገባይተኞች ህገወጥ በሆነ መንገድ የያዙት ነው።ኢየሱስ ለመጸለይ ለማመስገን በሰለሞን መብት ተሰጥቶታል ።
መብቱን ለመጠቀም ደግሞ ገባይተኛው መውጣት አለበት።ኢየሱስ ቤቴ የጸሎት ቤት ነው እያለ ነው ሲያስወጣቸው የነበረው ።ኢየሱስ የሰለሞን ዘር ስለመሆኑ የሚካድ አይደለም በሌላ አነጋገር የቅድመ አያቶቹ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ቀጥታ የመፋለም መብት ስላለው በህገወጥ መንገድ የያዙትን የማስወጣት መብት(inheritance and lawful ) አለው ። ከዚህ አንጻር ሁከት አልተፈጠረም።
💠ሌላው የህግ አከራካሪ ጉዳይ ያለበት የአይሁድ ንጉሥ ነኝ ፣የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱ ነው።ይህ ሲመረመር በክቡር ዳኛው ጲላጦስ ክርስቶስ🔥 አምላክ መሆኑን ተጨባጭ (tangible ) ማስረጃ አልተገኘም ።ግን ሙታን እያስነሳ ሌሎች ተአምራቶችን ማድረጉ ይታወቃል (judicial notice )።አምስት ገበያ ህዝብም በታምራቱ አስከትሏል ።ይህን ካደረገ ንጉስ የማይሆንበት ምክንያት ሊኖር አይችልም ተአምራቱም ምድራዊ አይመስልም ።ንጉስ ነኝ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱ የትኛውንም የሙሴ ህግ የተላለፈ ስለመሆኑ አላሳዩም ፣አልተላለፈም
💠የጲላጦስ ችሎት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከህግ አግባብ ከመረመረ በኀላ በኢየሱስ ላይ 💦በደል አላገኘሁትም 😴 ሲል ውሳኔውን አሳውቋል ።
በዚህ ጊዜ ካህናቱ እና አይሁዳውያን እድምተኞች እጅግ በጣም ተቆጡ ጮኹ 💥ንጉሱም ፈራ🔥ስቀለው ስቀለው እያሉ እጅግ በጣም ጮኹ?ንጉሡ እጅግ በጣም ፈራ።ከዚህም የተነሳ በስቅላት እንዲሞት ፈቀደላቸው።
የቅጣት ውሳኔ እና አፈጻጸም
ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸመው ጥፋት ስለመኖሩ ማስረጃ ባይገኝበትም የህዝቡ ጬሀት እና ማስፈራራት ለጲላጦስ አገዛዝ ከፍተኛ ስጋት ከመሆኑ የተነሳ ክርስቶስ በከፍተኛ መከራ ስቃይ ውርደት ስቅላት ሞት እንዲቀጣ ሆኖ አፈጻጸሙም ከጎሎጎታ እስከ ቀራንዮ እንዲሆን ተወስኗል ➕
ትእዛዝ
1. በሲኦል ያሉ ነፍሳት ማረፊያቸው ገነት እንዲሆን ታዟል
2. ይግባኝ የለውም
3.በክርስቶስ ያመነ የሲኦሉ መዝገቡ ተዘግቷል ።
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 2012 ዓ.ም

የፍተሀብሔር የፍርድ ቤት ስልጣን መርሆች
የኢትዮጵያ ፍተሀብሔር ስነስረአት ህግ
በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
0929101037,0983337690
መግቢያ #ethiopia | ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ የፍርድ ቤት ስልጣን በኢትዮጵያ አስመልክቶ በድንጋጌዎቹ የሚያስቀምጠው የኢትዮጵያ ፍትሀብሔር ስነስረአት ህግ በአንደኛ መጽሀፍ በፍርድ ቤቶች ስልጣን በጠቅላላ ድንጋጌው የሚያስቀምጣቸውን አጠር አድርጎ በሚገባ መጠን ማቅረቡ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ማቅረብ ተገቢ መሆኑን አምኛለው። የፍትሀብሔር ስነስረአት ህጋችን በ1958 የወጣው የፍትሀብሄር ጉዳዮችን በፍርድ ቤት እና ህግ በሚፈቅዳቸው እንዴት መምራት እንደምንችል የሚያስቀምጥ ሲሆን በዘጠኝ መጽሀፍ የተከፈለ ነው። ከዚህ ውስጥ የመጀመሪያው መጽሀፍ ስለ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ሲሆን የመጀመሪያው መጽሀፍ በምእራፎች የተከፋፈለ ሆኖ የመጀመሪያው ጠቅላላ ድንጋጌዎች በሚል ስያሜ ሰጥቶ ይጀምረዋል። ድንጋጌዎቹም ከቁጥር 4 እስከ 11 የተቀመጡ ናቸው። እነዚህ ድንጋጌዎች እንዴት የፍርድ ቤት ስልጣን መርሆች እንደተባሉ ወደ እናንተ አጠር አጠር ባለ መንገድ እናቀርባለን።
1. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ አንድ
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 4
ክስን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው የፍርድ ቤት ብቻ መሆኑ
በሌላ ህግ ካልታገደ በቀር የፍትሀብሔር ጉዳዮችን ተቀብሎ ለማየት ለሌላ አካል ማለትም ከፍርድ ቤት ውጪ የሆነ ተቋም ወይም አካል ተቀብሎ ለማየት ስልጣን በህግ ካልተሰጠው በቀር ለማየት የፍትሀብሄር ክሶችን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ ነው።
2. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ሁለት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5
የመጨረሻ ውሳኔ በፍርድ ቤት ያገኙ ጉዳዮች
የመጨረሻ ውሳኔ በፍርድ ቤት ያገኙ ጉዳዮች ድጋሜ ክስ ሊቀርብባቸውና ሊታዩ አይገባም።
3. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ሶስት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 6
ድጋሚ ዳኝነት ቀድሞ በተወሰነበት ጉዳይ የሚታይበት አግባብ
ፍርዱ የተሰጠው በቀረበ ማስረጃ በሀሰት፣በመደለያ፣በተሳሳተ ማስረጃ ከሆነ ይህንን ማስረጃ በማቅረብና እና በማስረዳት የተሰጠውን ፍርድ በመተው ድጋሚ ዳኝነት እኔዲታይ መጠየቅ ይቻላል።
4. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ አራት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 7
የቀደምትነት መብት
አንድን ጉዳይ አንድ ፍርድ ቤት ብቻ የማየት ስልጣን ያለው ሲሆን
የተለያዩ ፍርድ ቤቶች በአንድ ጉዳይ የማየት ስልጣን ሲኖራቸው ቅድምያ ለማየት የጀመረው ስልጣን ያለው በመሆኑ ሌሎቹ ፍርድ ቤት በአንዱ ቅድሚያ ከተጀመረ በኋላ የማየት ስልጣን የላቸውም።
የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ አምስት
5. የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 8
በሌላ ፍርድ ቤት በቀጠሮ ላይ ያለ ጉዳይ
በሌላ ፍርድ ቤት በቀጠሮ ላይ ክስ፣ክርክር እየለ በዚሁ በተመሳሳይ ጉዳይ ሌላ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ አይቻልም።
6. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ስድስት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 9
የስረነገር ስልጣን
ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ከሌላቸው ማየት አይችሉም።
የስረነገር ስልጣን ማለት የቀረበለትን ጉዳይ ከንብረቱ የገንዘብ ግምት ወይም ከጉዳዩ አይነት በህግ ከተደነገገው አንጻር ለማየት የሚያስችል ስልጣን ሲሆን ይህ ስልጣን ከሌለው ማየት አይችልም።
7. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ሰባት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 10
የግዛት ስልጣን
ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የነገሩ መነሻ የሆነው ነገር ክስን ተቀብሎ ለማየት የአከባቢ ስልጣን ያለው ስለመሆኑ አረጋግጦ ፍርድ ቤቱ መቀበል ያለበት ሲሆን የግዛት ስልጣን ከሌለው ፍርድ ቤት ክሱን መመለስ አለበት። ይህንንም የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 19-30 መሠረት በማረጋገገጥ የግዛት ስልጠን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ሌላ ተመሳሳይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመቀበል የግዛት ስልጣን አለው በሚል ብቻ አልቀበልም ማለት አይችልም።
8.የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ስምንት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 11
ክሶችን ስለማጣመር
የተለያዩ ክሶች ወይም ይግባኝ በአንድ ፍርድ ቤት በመሰማት ላይ ሲገኙ የህግ ክርክር ወይም የነገሩ ጭብጥ ተመሳሳይ እንደሆነ እንዲሁም ተከራካሪዎች በአንድ ዘንግ የሚመደቡ ከሆነ እንዲጣመሩ አንዱ ተከራካሪ ወገን ሲያመለክት ወይም ፍርድ ቤቱ ካመነበት የሚጣመር ሲሆን በተመሳሳይ በተለያዩ ፍርድ ቤቶችም ክሱ በመሰማት ላይ ሲሆን አንዱ እንዲጣመር ማመልከት ይችላል።
9. ማጠቃለያ
በዚህ አጭር ጽሁፍ ያቀረብነው የፍርድ ቤቶችን አስመልክቶ መታወቅ የሚገባቸው ወሰኝ ነጥቦች እንደ መርህ ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን በፍትሃብሔር ጉዳይ ክስ ፍርድ ከመቅረባቸው በፊት በጥንቃቄ ተለይተው መታወቅ የሚገባቸው ናቸው።
ማጠቀሻ
1. የፍትሀብሄር ስነስርዓት ህግ 1958
2. አለን ስድለር የፍ/ስ/ስ/ህግ ማብራሪያ
https://www.facebook.com/s...
https://t.me/Fantahunlawye...

5 months ago
አዲሱ የንግድ ህግ ለኢትዮጵያ ንግድ እድገት ያለው ፋይዳ
የንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/13
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
0929101037,0983337690
1. መግቢያ
#ethiopia | በ1952 ዓ.ም የወጣው ነባሩ የንግድ ህግ አዲሱ የንግድ ህግ 2013 ዓ.ም እስኪወጣ ድረስ የኢትዮጲያ የንግድ ስረአትን መስመር በማሥያዝ ረገድ ቀላል የማይባል ሚና የነበረው ሲሆን በዚህም ነጋዴ ማለት ምን ፤ ምን የሚሰራ ስለመሆኑ በነባሩ ንግድ ህግ አንቀጽ 5 ላይ የተቀመጠ ከመሆነኑም ባሻግር በግል እና በማህበር ወይም በመደራጀት እንዴት ሊሰራ እንደሚችል አወቃቀሩን (structures), አመሰራረቱን (formations), መብት ግዴታዎች አጠቃላይ መደንገጋቸውን ማስታወስ ይቻላል፡፡1 ሲሆን በተነጻጻሪም በዚህ በአዲሱ የንግድ ህግም በዚህ ይዘት የተደገገ ሲሆን ተሻሽሎ የተቀመጡ ድንጋጌዎችም ስፍረውበታል፡፡
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነውም አዲሱ የንግድ ህግ የወጣበትን ምክንያት ማሰስ እና እነዚህስ ልዩነቶች ምንድን ናቸው፤ ተሻሽሎ በመምጣቱ ይዞ የመጣው ፋይዳ ምንድ ነው የሚሉትን ነጥቦች በአጭሩ ለመዳሰስ ነው፡፡
2. አዲሱ የንግድ ህግ የወጣበት ምክንያት
ከላይ በመግቢያው ለመግለጽ እንደሞከርኩት በንጉሱ አሰተዳደር የኢኮኖሚእድገትን እና የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋጥ ለንግድ ስራ ጽኑ የህግ መሰረት መጣል የግድ አስፈላጊ በመሆኑ በ1952 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጲያ የንግድ ህግ ለዚህ ዓላማ ከግብ መድረስ አስፈላጊውን መደላደል ለማድረግ
አንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ይሁን እንጂ ህጉ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ስልሳ አመታት ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል፡፡ የንግድ እና የመዋእለን ንዋይ ፍሰት እጅግ ከመጨመራቸውም በላይ እያደር አለምአቀፋዊ ባህሪ እየተላበሱ መጥተዋል፡፡
እነዚህ ክስተቶች በተለይ ኢትዮጲያ ገበያ መር ስረአት መከተል ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ህጉ እንዲከለስ ምክነንያትን የፈጠረ ሲሆን ከዚህም የተነሳ በህጉ ውስጥ አንዳንድ ክፍተቶች ታይተዋል፡፡ ከእነዚህ አለምአቀፍዊ የንግድ እንቅስቃሴ መስተጋብር
እነዲሁም ኢትዮፒያ አሁን ካለችበት ገበያመር የንግድ እንቅስቃሴ አንጻር ለአፈጻጸም የማይመቹ እና ለተለያዩ ትርጉሞች የተጋለጡ ድንጋጌዎቸች እንዳሉ ተስተውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ኢትዮጲያ ለደረሰችበት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ደረጃ ህጉ የተሟላ አለመሆኑን ድምዳሜ ላይ ተደርስዋል፡፡
ስለዚህ የኢትዮጲያ አለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማስፋፈት፤የነጋዴዎችን፤የባለሃብቶችን እና በህጉ ጥቅማቸው በቀጥታ የሚነካ ባለድርሻ አካላት መብቶችን በሚዛናዊ ሁኔታ ለማስተናገድ ብሎም የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ አዲሱን የንግድ ህግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝትዋል፡፡
3. በአዲሱ ንግድ ህግ የተካተቱ ነጥቦች
በዚህ ክፍል በአዲሱ ንግድ ማለትም በአዋጅ ቁጥር 1243/13 የተካተቱትን ጉዳዮች ከምክንያታቸው ጭምር አጠር አጠር ባለ መንገድ አስቀምጠናል።
3.1. ኀላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር
ኀላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር በአዲሱ የንግድ ህግ ከተካተቱት አዳዲሰ የንግድ ማህበራት አንዱ
ነው፡፡ ሥያሜው ዕንደሚያመለክተው ይህ የሽርክና ማህበር ውስጥ ያ አባላት በሙሉ ለማህበሩ ዕዳ ያለባቸው ኃላፊነት የተወሰነ ሲሆን ይህም በንግድ ህጉ አንቀጽ 221 ላይ የተቀመጠ ነው፡፡ ይሀውም ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰወች የሙያና ለሙያው ደጋፊ ደጋፊ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት
የሚያቐቐሙት ሲሆን የማህበርተኞች ኀላፊነት በመዋጮቹ የተወሰነ የንግድ ማህበር ነው፡፡ ለዚህ ማህበር አላማ፣ የሙያ አገልግሎት ማለት በህግ አግባብ ባለው አካል በተሰጠ የሙያ ፍቃድ መሰረት የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡
3.2. ባለአንድ አባል ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ
ይህ ኩባንያ ወይም ማህበር ከ534 እስከ 545 ድረስ ባሉት አዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የገባ ሲሆን በአንቀጽ 534 ላይ አእንደተቀመጠው ማህበር ሲል ያሰቀመጠ ቢሆንም በአንድ ሰው የሚቐቐም ነው፡፡ ይህ ማህበር የተካተተበት አላማም በማህበሩ አባል አንድ ብቻ ሊሆን በሚገደድበት ጊዜ ከንግድ ማህበሩ ባህርይ አንጻር በዚህ አግባብ ተዘጋጅቶ የንግድ እንቅስቀሴውን ለማሰቀጠል ሲባል የተመሰረተ መሆኑን የሚሰማሙበት ነው፡፡
3.3. አመሰራረት
በነባሩ የንግድ ህግ የንግድ ማህበራትን ለመመስረት የመመስረጫ እና የመተዳደርያ ጽሁፍ የሚያስፈልግ ሲሆን ነገር ግን በአዲሱ የንግድ ህግ ማህበር የመመስረቻ ጽሁፍ ብጫ አስፈላጊ መሆኑን የተደነገገ ነው፡፡ በህብረት ሽርክና ማህበር አንቀጽ 185፣የአክስዮን ማህበር አንቀጽ 255 ፣
ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር በተመለከተ አንቀጽ 500 ላይ የተደነገገ ነው፡፡ በአጠቃላይ ለንግድ ማህበራት አመሰራረት የመተዳደርያ ደንብን በማስቀረት የመመስረቻ ጽሁፍ በቂ ሲሆን በዚህ ላይ
የንግድ ማህበሩን አላማ ፤ ጥቅም፤መብት፤ግዴታ የመሳሰሉት ሰፋ ያለ ዝርዝር ጉዳዮች የሚሰፍሩበት ነው፡፡
3.4. የአነስተኛ ባለአክስኖች መብት እና ጥበቃ
ቀደም ሲል የነበረው የኢትዮጲያ ንግድ ህግ ለአነስተኛ ባለአክስዮኖች የሚያደርገው ጥበቃ የተለያየ
ጥናት እነንደሚያሳየው ከሌሎች ሀገሮች አንጻር በአማካይ አነስተኛ ሲሆን በአዲሱ ህግ ግን ብዙ ማሻሻዮች የተደረገ ነው፡፡5 ይሀውም አነስተኛ ባለአክስዮን ከቦርድ፣ከከፍተኛ ድርሻ ካላቸው
ባለአክስዮን የሚደርስባቸውን ጭቆና ለመጠበቅ ሲባል መፍቴዎች ተቀምጠዋል፡፡ ይሀውም በአዲሱ ንግድ ህግ አንቀጽ 276/1/፣363፣383፣ 343፣355-361፣400፣402(2)፣ 403፣451(1) እና በመሳሰሉት የተቀመጠ ነው፡፡
3.5. የአክስዮን መመዝገብ
በአዲሱ የንግደ ህግ አንቀጽ 267/1/ አክስዮን በባለአክስዮኑ ስም መመዝገብ እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ የቀድሞው የንግድ ህግ ግን በአንቀጽ 325 በአመጭው ጭምር ሊመዘገብ እንደሚችል በአማራጭ ያስቀምጣል፡፡ የአሁን ንግድ ህግ አክሥዮን ቀድሞ ይህ ህግ ከመውጣቱ በፊት ለአምጪው በሚል የወጡ አክስዮኖች ባለቤት የሆነ ቢኖርም ይህ ህግ በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሶስት አመት ውስጥ አክስዮኖቹ ስም በሚል መመዝገብ አለበት፡፡
ይህ ሀገራችን
የአክስዮኖችን ሽያጭ በካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/13 እና በሌሎች የተሻሸሉ የባንክ፤የፋይናነስ አዋጆች፤ደንቦች፤መመርያዎች ከፍተኛ የህግ እና የተቐማት አወቃቀር (legal and institutional framework) እየተበጀ ሲሆን አዲሱ የንግድ ህጉም ከዚህ ጋር ተያይዞ የመዋእለሰነዶች ገበያ ሽያጭ (security exchange market) ፣ የአክስዮን ሽያጭ ማሰተላለፍ፣ ጋገር ጠያይዞ ባለአክስዮኖች በገበያ ላይ ጥበቃ እንዲኖራቸው ፍትሀዊ፣ብቁ እና የገበያ ግልጸኝነት እንዲፈጠር አዲሱ የንግድ ሕግ ፣ ከካፒታል አዋጁ በተጨማሪ ከፍተኛ መደላደልን ለአክስዮን ገበያ አመቻችትዋል፡፡
3.6. ሆለዲነግ ካምፓኒ በነግድ ስራ እንዲሰራ ስለመፈቀዱ
በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 5 ስር በተመለከቱት ስራዎች ላይ በመሰማራት በቀጥታ ራሱ ምርትን የንግድ ማህበራት ውሥጥ መዋእለ ንዋይ በማፈሰስ ድርሻ የሚይዝ ኩባንያ ወይም ሆለዲነግ
ካምፓኒ እንደ ነጋዴ እንደሚቆጠር አዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 9 ከማመልከቱም በተጨማሪ በቀጠታ ምርትና አገልግሎተ ማቅረብ ይችላል፡፡
3.7. ተራ የሽርክና ማህበር በአዲሱ ህግ ያልተካተተ መሆኑ
በነባሩ የንግድ ህግ ሁለተኛ መጽሀፉ ላይ በሰፊው የተቀመጠ ቢሆንም በንግድ ስራ ውስጥ የማይሳተፍ መሆኑን በግልጽ በነባር ህጉ የተቀመጠ ነው፡፡ ይህ ከሆነ አዲሱ ህግ ከዚህ አመክን
በመነሳት ይመስል ከእነአካቴው ያወጣው ሲሆን ይህ በነባሩ ህግ በመቀመጡ ምክንያት ለሚፈጠሩ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ነው፡፡
3.8. በንግድ ድረጅቶች መካከል የሚፈጠር ዝምድና
በአዲሱ የንግድ ህግ የነግድ ማህበራት እርስ በእርሳቸው የተገዛዙ ከሆነ አንዱ አንድኛውን ከገዛ ፣ እናት(holding)፣ ተቀጽላ (subsidiary )፤group የተዛመዱ(Affiliated) ማህበራት ስያሜ የሚሰጣቸው ሲሆን በአንቀጽ 550-577 የኩባንያዎችን ይዘት፣አቋም፣ስልጣን መብት፣ግዴታ፤ከድምጽ ጋር ተያይዞ ያለው አሰራር እና ውጤት፣ የስራ አመራር ፣ተጠያቂነት
አሰራር ፣ ስለመወሀድ እና ውጤቱ የመሳሰሉት በተመለከተም በዝርዝር የተቀመጠ ነው፡፡
3.9. ማህበራትን መልሶ የማደራጀት ስራ በአዲሱ ህግ የተካተተ መሆኑ
በአዲሱ የንግድ ህግ ሶስተኛ መጽሀፍ ፤ ርእስ አንድ፣ምእራፍ አንድ አንቀጽ 588 ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው የአንድን ማህበር እዳ መልሶ ማዋቀር ጽንሰ ሃሳብ ላይ በሰፊው የተቃኘ ስነስረአቱም
እንዴት ሊሆን እንደሚችልም የተብራራ ሲሆን በተከታዮች ድንጋጌ ላይም የተብራራ ነው፡፡ የእነዚህ ድንጋጌዎች አላማቸው ቀልጣፋና ውጠየታማ በሆነ ጊዜውን ጠብቆ በሚከናወን ስነስረአት
አማካኝነት የኢኮኖሚ መረጋገትን ማሰፋፋት፣የንብረቱን ዋጋ ከፍ ማድረግ እና የህግ ተገማችነትንና ግልጸኝነትን ማረጋገጥ ነው፡፡ ገንዘብ ጠያቂዎችም በተወሰነ አብላጫ ድምጽ የሚፈቅዱ ከሆነ መልሶ በማደራጀት እቅድ አማካይነት ገንዘብ ጠያቂዎችን ተተቃሚ በሚያደርግ መልኩ የባለእዳዎችን እዳዎች እንዲሁም የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎችን በጠበቀ መልኩ መልሶ በማደራጀት የንግድ ስራ
መሸጥ ነው፡፡
3.10. ለማህበር ቦርድ አባላትነት የአክስዮን ድርሻ የሌላቸውን የሚፈቅድ መሆኑን
በቀድሞው የንግድ ህግ የቦርድ አባላት ከባለአክስዮን ድርሻ ብቻ ሲሆን በአዲሱ ግን ባለ ድርሻ ባይሆኑም እስከ አንድ ሶስተኛው ድረስ የቦርድ አባላቱን ድርሻ መያዝ ይችላሉ፡፡ ይህ ቦርድ ከፍተኛ
ሙያ ባላቸው ፤ልምድ ፣እውቀት ባላቸው የቦረድ ዳይርክተር አባላት የተቀናጀ እና የህጉን አላማ ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡አንቀጽ 296/2/ ላይ የተደነገገ ነው፡፡
3.11. በአዲሱ የንግድ ህግ ነጋዴ የሚያስብል የንግድ ስራዎች መጨመር
በቀድሞወ ህግ አንቀጽ 5 ላይ 21 የንግድ ስራዎች ላ የሚሰማራ ነጋዴ የሚያስብል ሲሆን በአዲሱ ግን በተጨማሪነት በማካተት 37 የደረሰ ሲሆን የቀብር ስራ እና ተያያዥነት ስራዎች የሚሰሩ እነደ
አንድ የንግድ ስራ የተካተተ ነው፡፡
4. ማጠቃለያ
ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት በቂ የሆነ የንግድ ህግ ማእቀፍ እና የሚመጥኑ ወይም በቂ የሆነ የንግድ ተቋመት መኖር እጅጉን በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ በቂ የህግ ማዕቀፍ ኖሮ ህግን ወደ
ተግባር ሊቀይር የሚችል በህጎች የተሰናዳ ተቋም፣ አስተዳደር ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጲያ ሃገራችን በገበያ መር ስረአት መመራት ከጀመረች ሁለት አስር አመታትን አልፋለች፡፡ ይሁን እንጂ ተስፋ ሰጪ እና በጊዜው ዘመናዊ የሆኑ የ1952 ዓ.ም የንግድ ህግ ትልቁ የሀገራችን የጀርባ አጥንት የሆነ የንግድ ህግ ማእቀፍ ቢሆንም ሀገራችን አሁን ካላት የንግድ እንቅስቃሴ እድገት ፍላጎት፤የአኮኖሚ እድገት ፣ አለም አቀፍ የገበያ ትስስር ፣ የዜጎችን መሰረታዊ የአኮኖሚ ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም ከአለምአቀፍ የንግድ ፣ የገንዘብ ተቋማት ህጎች እና የፋይናንስ ስረአት ጋር በማጣጣም የዳበረ ኢኮኖሚ ለሀገር እድገት ለማስመዝገብ ነባሩ የንግድ ህግ ክፍትት ያለበት መሆኑን በመረዳት ይህ አዲሱ ህግ እንደዲሻሻል አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት አዲሱ የንግድ ህግ 1243/2013 ወጥቶ በስራ ለይ ውሏል፡፡ይህ ብቻ በቂ ባለመሆኑ የአኮኖሚ እድገቱን ለማሳለጥ፤ የንግድ ስረአቱን
ለማዘመን ሌሎች የባንክ፤የፋይናንስ፣የካፒታልገበያ ዐዋጅ እነዚህን የሚያስፈጽሙ ደንቦች፣መመሪያዎች ወጥተው ወደ የሚጠበቅባቸው ስራ ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ፡፡
በቅርቡ እንደሚታወቀው በሀገራችን ትልቅ የኢኮኖሚ ሃብት ይዞ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው የካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/2013 አዲሱ የንግድ ህግ በወጣበት አመት የወጣ ሲሆን
በ2017 ዓ.ም የንግድ ስራውን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር አብሳሪነት የተቋቋማለትን አላማ በማብሰር ኢትዮጲያ ይህን ትልቅ የገበያ ሲሳይ ተግባራዊ ለማድረግ የምትችል
መሆኑን ገልጸው በዚህ በካፒታል አዋጅ ስር እንደ ዋና ፈርጅ ስራ የሚቆጠረውን የኢትዮጲያ የሰነዶች መዋለ ነዋይ ገበያ ጥር/2017 ዓ.ም በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን አዲሱ የንግድ አዋጅ መውጣት ለዚህ በር እና መሰረታዊ ነው፡፡
ዋቢ መጽሀፍት
1. የኢትዮጲያ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/2013፣የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣27ኛ ዓመት ቁጥር 23፣አዲሰአበባ፣ሚያዚያ 4 ቀን 2013
2. የኢትዮጲያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የንግድ ሕግ (ነጋሪት ጋዜጣ፣በተለየ የወጣ፣19ኛኣመት፣ቁጥር 3/1952
ዓ.ም)
3. ፈቃዱ ጴጥሮስ፣የኢትዮጲያ ኩባንያ ህግ፣2014 (3ኛ እትም)
4. የካፒታለ ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 (የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣27ኛ ዓመት ቁጥር 33፤2013፤2013
ዓ.ም.)
5. የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1360/2017
6. የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008(የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣22ኛ ዓመት ቁጥር 101፣ሀምሌ
29 ቀን 2002 ዓ.ም)

6 months ago
የመጽሐፍ የፊርማ ስነ-ስርዓት
ሀብታሙ አለባቸው
ቅዳሜ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም
ከቀኑ 9፡00 እስከ 11፡00 ባለው ጊዜ
አዲሱ የጃዕፈር መጽሀፍ መደብር
ተቃርኖ
የሱፍ አበባ
ጉልጥምት ኢትዮጵያ
የቁሓር እዒብ
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
አድራሻችን፡
ለገሃር ተወልደ ህንጻ
ስልክ፡ 0911 125324
ሀብታሙ አለባቸው
ቅዳሜ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም
ከቀኑ 9፡00 እስከ 11፡00 ባለው ጊዜ
አዲሱ የጃዕፈር መጽሀፍ መደብር
ተቃርኖ
የሱፍ አበባ
ጉልጥምት ኢትዮጵያ
የቁሓር እዒብ
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
አድራሻችን፡
ለገሃር ተወልደ ህንጻ
ስልክ፡ 0911 125324
7 months ago
"ያ ትውልድ" ቅጽ 1 ቅጽ 2 እና ቅጽ 3፣ “የሻምላው ትውልድ”፣ "ትውልድ ያናወጠ ጦርነት" እና ሌሎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ላይ አተኩረው የተጻፉ መጽሀፍቶችን ጥናታዊ ጽሁፎችን እና መጣጥፎችን በEthio Meda/ ethiomeda የዩቲዩብ ቻናል በድምጽ ይከታተሉ!!
https://www.youtube.com/pl...
https://www.youtube.com/pl...
https://www.youtube.com/pl...
በደርግ የአስተዳደር ዘመን ከፍተኛ አመራር የነበሩት፤ በአስተዳደሩ የፕላን ኮሚሽን ሐላፊ፣ የማሕበራዊ እና ኢኮኖሚ ክፍሉም መሪ የነበሩትና እና ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጓድ ፋሲካ ሲደልል በቀጣይ የደርግ ዘመን ፓለቲካ፣ የብሔር ጉዳዮችን እና ጦርነቶችን የቃኙበትን የሻምላው ትውልድ ቅጽ 2 መጽሀፍን በማዘጋጀት ላይ መናቸውንም ገልጸውልናል፡፡

የመላኩ ብርሃኑ ልደት 🎈
#ethiopia | "ዛሬ ልደቴ ነው፡፡ በቀረኝ ዘመን እግዚአብሄር የማይከፋብኝ ልጁ እሆን ዘንድ እሱ ይርዳኝ፡፡ መወለድም መኖርም በርሱ ፍቃድ ብቻ ነውና እዚህች ቀን ላይ እቆም ዘንድ ለፈቀደልኝ አምላክ ምስጋና ይግባው፡፡"
መላኩ ብርሃኑ ተስፋዬ
*** #ተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ)
ትውልድ ፤ልጅነት
ጋዜጠኛ መላኩ ብርሀኑ አዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ‹‹ኦሎምፒያ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተወለደ። በትንሳዔ ብርሃን እና በቦሌ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትሏል። ከተማሪነት ዘመኑ ጀምሮ ላደላበት የስነ-ጽሁፍ ፍቅር የተሸነፈው በጊዜ ነው። ሲመኘው የኖረውን ጋዜጠኛ የመሆን ህልም ለማሳካት መንደርደሪያዎቹ የተማረባቸው ትምህርት ቤቶች ሚኒ ሚዲያዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ የመጀመሪያ ልብ-ወለድ ስራውን አይተው ወደሚኒ ሚዲያ እንዲመጣ ብርታት የሰጡትን የ9ኛ ክፍል የአማርኛ መምህሩን አቶ አለማየሁ የስጋትን ያመሰግናል።
የንባብ ፍቅር-የመጻፍ ክህሎት
መላኩ፤ ጋዜጠኝነትን ከመስራቱ አስቀድሞ ረጅም አመታትን በንባብ አሳልፏል። የአባቱን የንባብ ፍቅር እያየ ያደገ በመሆኑም ከእድሜው የቀደሙ መጽሃፍትን በልጅነቱ ለማንበብ እድል አግኝቷል። ‹‹ጣምራ ጦር›› የሚለውን የገበየሁ አየለ መጽሃፍ የ3ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ ማንበቡን ይናገራል። ከዚያ በኋላም ‹‹ስደተኛው››፣ ‹‹ደራሲው››፣ ‹‹የቀይ ኮከብ ጥሪ››፣ ‹‹ብቀላ›› እና የመሳሰሉ ዳጎስ ያሉ መጽሃፍትን በልጅነቱ አንብቧቸዋል። ይህ የማንበብ ፍቅሩ እጁን ማፍታታት እስከጀመረበት እስከ 9ኛ ክፍል ድረስ ከዚያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እስኪጨርስ ድረስ አብሮት ኖሯል። “በዘመኑ የታተሙ ፣ እኔ ያላነበብኳቸው መጽሃፍት የሉም” ይላል በሙሉ ልብ። መጽሃፍቱ የዛሬ ማንነቱንና አስተሳሰቡን የቀረጹለት በመሆናቸውም አሁን ድረስ በልጅነቱ ማንበብ መጀመሩን እንደአንድ የህይወቱ አዲስ የተከፈተ መጋረጃ ይቆጥረዋል።
“ለእኩዮችህ አርአያ ሆነህ ማደግ አለብህ” የሚሉትንና የሚወዳቸውን እናቱን ቃል እየሰማ ማደጉን የሚናገረው መላኩ ያንን ቃል ለማክበርና ቤተሰቦቹ በሚፈልጉት ቦታ ለመገኘት ህይወቱን በስርዓት አስገዝቶ በልጅነት እና ወጣትነት ሳይታለል ያሰበበት ለመድረስ ጉዞ የጀመረውም በልጅነቱ መሆኑን ይናገራል።
አባቱ ለስራ ጉዳይ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍላተ ሃገራት ይዞሩ ስለነበር የመጻፍ ችሎታውን ያሟሸው ለርሳቸው የሰላምታ ደብዳቤ በመጻፍ መሆኑንና የስነጽሁፍ ችሎታውን ያዩ ጎረቤቶቹና የአካባቢው ሰዎችም ለቀበሌ ማመልከቻ የሚያጽፉት እርሱን እንደነበር በፈገግታ ያስታውሳል።
መላኩ ለልጅነቱ ፣ ለትውልድ ሰፈሩ እና እና ላደገበት ማህበረሰብ ልዩ ፍቅርና ህይወቱን ሙሉ የማይዘነጋውን ናፍቆትና ትውስታ ሲገልጽ “ዘነበ ወላ “ልጅነት” የሚለውን መጽሃፍ ቀድሞኝ ባይጽፍ ኖሮ የልጅነት ታሪኩን የሚጽፍ አንደኛ ደራሴ እኔ መሆኔ አይቀርም ነበር” በማለት ነው። የአለማየሁ ገላጋይን “የብርሃን ፈለጎች እና የዘነበ ወላን ልጅነት የራሴ የልጅነት ዘመን ማስታወሻ አድርጌ ስለምቆጥራቸው ከሁሉም መጽሃፍት የበለጠ ዋጋ እሰጣቸዋለሁ” ነው የሚለው መላኩ።
መላኩ መደበኛ ትምህርቱን ከማጠናቀቁ አስቀድሞ በተለያዩ የስነጽሁፍ ውድድሮች እየተሳተፈ ችሎታውን ያዳብር ነበር። የስነጽሁፍ እና ግጥም አስተዋጽዖ በሚፈለግበት ቦታ ሁሉ ስራዎቹን እያቀረበ ምስጋናም ይቸረው እንደነበር ይገልጻል።
የጋዜጠኝነት አለም
12ኛ ክፍልን አጠናቅቆ ከመደበኛ ትምህርት ቤት ከወጣ በኋላ የመጀመሪያውን የጋዜጠኝነት ስልጠና ከፎቶግራፍ ሙያ ጋር አጣምሮ የወሰደው በቀድሞው የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ በዛሬው የፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ነው። በስልጠና ላይ እያለ “ኮርስ ሜቶቼ” የሚላቸው የርሱ ባቾች /እኩያ ባልደረቦች/የሚያውቁትና ሁሌም የሚያስታውሱት በስነጽሁፍ ስራዎቹ ነው።
መላኩ ወደመደበኛ የጋዜጠኝነት ስራ የገባው ከፖሊስ ኮሌጅ ምረቃ በኋላ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የጋዜጠኝነት ሙያ አገልግሎቱን በወንጀል ዘገባ ዘርፍ አሃዱ ብሎ ጀመረ። በጊዜው ለፖሊስና ርምጃው ጋዜጣ እንዲሁም ለፖሊስና ህብረተሰብ የራዲዮና ቴሌቪዠን ፕሮግራሞች 1989 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሪፖርተር ሆኖ መስራት ጀመረ።
በፖሊስ ሚዲያ ውስጥ ትክክለኛውን የጋዜጠኝነት ዘርፍ እንዳውቀውና እንድተገብረው መሰረት የሆነኝ ሰው የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ አዘጋጅና ታዋቂ የስነጽሁፍ ሰው የነበረው የመጀመሪያ አለቃዬ መቶ አለቃ ሃይሉ አበበ ነው ይላል። ከፖሊስና ህብረተሰብ ሚዲያ ሪፖርተርነቱ በተጨማሪ ዘወትር ማክሰኞና ሃሙስ ምሽት ላይ በአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን (የቀድሞው ኢቲቪ 2) ላይ የሚተላለፈውን “አዲስ ፖሊስ” የሚባል የቴሌቪዠን ፕሮግራም ከቡድን አባሎቹ ጋር በማስጀመር በዋና አዘጋጅነት ሰርቷል።አዲስ ፖሊስ የተባለ መጽሄትም መስራችና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።
መማር-መማር
የቀድሞው ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የአሁኑ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በሃገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት በመክፈት በዲፕሎማ መርሃግብር ጋዜጠኞችን ማሰልጠን ሲጀምር መላኩ ‘የነፍሴ ጥሪ ነው’ የሚለውን የጋዜጠኝነት ሙያ ሳይንሱ በሚፈቅደው ትምህርት ለማገዝ ወደዚያው አቀና። የሶስት ዓመት የጋዜጠኝነት ስልጠናውንም በ1997 ዓ.ም በማዕረግ ተመራቂነት አጠናቀቀ።
የዩኒቲን የትምህርት ዘመን “የህይወት ዘመኔ የሙያ መሰረት” ብሎ ይጠራዋል። ከዛሬዎቹ የቪኦኤ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ ጀምሮ የዛሬው ሪፖርተር ጋዜጣ ዋና አዘጋጁ ታምሩ ጽጌ፣ የቀድሞው ጦቢያና ልሳነ ህዝብ መጽሄት አዘጋጁ ታዬ በላቸው እንዲሁም ሌሎች በርካታ የዘመኑ ታዋቂ የግል ፕሬስ ጋዜጠኞች የዩኒቲ ኮሌጅ ባቾቹ/ በአንድ ዘመን አብረው/ የተማሩ ናቸው።
መላኩ ዩኒቲን ከተሰናበተ በኋላ በዚያው ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ከፍቶ ጋዜጠኝነትን በዲግሪ ፕሮግራም መስጠት በመጀመሩ ወደዚያው በማቅናት በብሮድካስት ጆርናሊዝም ዘርፍ በቴሌቪዠን ጋዜጠኝነት የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ሮዝ መስቲካ፣ መሰለ ገብረህይወት ፣ ታምሩ ጽጌ፣ የትነበርክ ታደለ፣ ጸዳለ ለማ፣ በፍቃዱ በሻህ፣ አንዱአለም ሲሳይ እና ሌሎችም የእርሱ ባቾች ዛሬ ድረስ ጋዜጠኝነትን አክብረው ያስከበሩ መሆናቸውን ይመሰክራል።
ከዚህ ዩኒቨርሲቲ ተመርቆ ከወጣ በኋላ መላኩ ሙያውን በሳይንሳዊ ዕውቀት ለማበልጸግ የነበረው ፍላጎት ከአንድ አመት በላይ ከትምርት ርቆ እንዳይቆይና ትምህርቱን እዚህ ላይ እንዳያቆም አድርጎታል። ቀጣዩ የትምህርት ጉዞው ህንድ ሃገር በሚገኘው ሲኪም ማኒፓል ዪኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክኖሎጂካል ሳይንስስ ወደተባለ ዩኒቨርሲቲ ነበር። በዚያም በጆርናሊዝም እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ልዩ ሙያ (specialization) የማስተርስ ኦፍ አርትስ ኢንተርናሽናል ዲግሪውን ተቀብሏል። መላኩ ከኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርቶቹ ባሻገር ከ21 በላይ አጫጭርና ረጃጅም የጋዜጠኝነት ስልጠናዎችን በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት ተከታትሎ ሰርተፍኬቶችን አገኝቷል።
ሙሉ የስራ ዘመኑን በጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ስራዎች ላይ ያሳለፈው መላኩ ከእድሜው እኩሌታ የላቀ ዘመኑን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ላይ አገልግሏል። ለ9 ዓመታት በፖሊስ መገናኛ ብዙሃን ውስጥ ከሪፖርተርነት እስከዋና አዘጋጅነት በደረሱ መደቦች ላይ በፖሊስ ራዲዮ፣ጋዜጣና ቴሌቪዠን እንዲሁም በአዲስ ፖሊስ ቴሌቪዠን ፕሮግራም እና መጽሄት ላይ ነው የሰራው።
በተጨማሪም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ እና ቀድሞ ኢቲቪ 2 ይባል በነበረው የአ/አ መገናኛ ብዙሃን ቴሌቪዠን ፕሮግራም ላይ በአምድ ጽሁፍ አዘጋጅነትና እና በወንጀል ዘገባዎች አቅራቢነት ሰርቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ከተቀላቀለ በኋላም ለ7 ዓመታት ያህል በዜና አገልግሎቱ ከዜና ኤዲተርነት እስከ ፕሮግራም ፕሮዳክሽን ሃላፊነት በደረሱ የጋዜጠኝነት ሙያ መደቦች ላይ እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ አገልግሏል። “ጋዜጠኝነትን ሳስብ ለዜና አገልግሎት ቆይታዬ ልዩ ከበሬታ እና ፍቅር አለኝ” ይላል።
መላኩ እና መምህርነት
መላኩ ከጋዜጠኝነት ስራው ባሻገር መምህር በመሆንም እውቀቱን አካፍሏል። ለአዲስ አበባ ፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ሰልጣኞችም የህዝብ ግንኙነት ትምህርት መምህር ሆኖ አገልግሏል። ከጋዜጠኝነት ስራው ጎን ለጎን እንደኢስት አፍሪካ ጆርናሊዝም አሊያንስ፣ ግሎባል ሄልዝ፣ ሲአርዲኤ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትና የመሳሰሉ ዓለምአቀፍና አህጉራዊ ተቋማት እንዲሁም የሃገር ውስጥ ድርጅቶች ለባለሙያዎች ባዘጋጁት የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን፣ የጤና ጋዜጠኝነት እና የምርመራ ጋዜጠኝነት ስልጠናዎች ላይ በዋና አሰልጣኝነት አገልግሏል።የምስራች የጋዜጠኝነት ስልጠና ማዕከል ለሚሰጣቸው ስልጠናዎችም የኮሙኒኬሽን፣ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ዘገባዎች መምህር ሆኖ ሰርቷል።
መላኩ ከመደበኛ ስራው በተጨማሪ ጦማር ፣ ሮዝ ፣ ዘ ፕሬስ እና ዕለታዊ አዲስ ለተሰኙ የያኔው ጋዜጦችና መጽሄቶች ፍሪላንስ ዘጋቢ ሆኖም ሰርቷል። በተለይም በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ፣ በወንጀል እና በምርመራ ዘገባዎቹ በርካታ አንባቢዎችን ሊያፈራ ችሏል። በቀድሞ ጊዜ የሸዋጌጥ ተካልኝ፣ መላከ ብርሃን ተስፋይ በመጨረሻም እስከቅርብ ጊዜ “ኮከብ አሳየ” የመላኩ የብዕር ስሞች ሆነው ዘልቀዋል።
አዲስ ጉዳይ-ትልቁ የነጻነት ቤት
መላኩ ዋናውንና በህይወቴ ትልቅ ቦታ የምሰጠውን ጋዜጠኝነት ጀመርኩ የሚለው ‹‹አዲስ ጉዳይ መጽሄትን በማኔጂንግ ኤዲተርነት ከተቀላቀለ በኋላ በሰራቸው ስራዎች ነው። ‹‹አዲስ ጉዳይ መጽሄት ከ2004 ጀምሮ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሙሉ ቀለም እና በየሳምንቱ በመዘጋጀት ቀዳሚ የሆነ በብዙሃን ዘንድ እጅግ የሚከበርና እና የሚሰደድ ፣ መንግስት ተጽዕኖ ፈጣሪ ብሎ ከፈራቸውና በመጨረሻም ሆን ብሎ ካፈረሳቸው መጽሄቶች ግንባር ቀደሙ ነበር።
የግል ፕሬሱ ዋና ሰው እንዳልካቸው ተስፋዬ
መላኩ “የማይታየው የወቅቱ የግል ፕሬስ ዋና ሰው” ይለዋል እንዳልካቸውን፡፡ እንዳልካቸው በኢትዮጵያ የህትመት ስራ ውስጥ በጋዜጣ እና በመጽሄት የማከፋል ስራ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያበረከተ ነው፡፡ እንዳልካቸው አዲስ ጉዳይ መጽሄትን ማሳተም ሲጀምር መላኩ በምስረታው ላይ ትልቁን ድርሻ አበርክቷል፡፡ ።አዲስ ጉዳይ ከሮዝ መጽሄት በኋላ ተሻሽሎና በጥናት ተቀርጾ ለለውጥ እና ለማህብረሰብ እውቀት የተፈጠረ ፣ እንደዘመን አቻው ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ በብዙ ባለሙያዎች የተደራጀ ባለራዕይ መጽሄት ሆኖ እንዲቀጥል ከፍ ያለ ሙያዊ አስተዋጽኦውን በፍቅር አበርክቷል::
ስለአዲስ ጉዳይ ባልደረቦች ሳነሳ ክሪኤቲቭ ዲዛይነሮቹ ዘሪሁን አሰፋ እና መስፍን አድነው መጠቀስ አለባቸው፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች መጽሄቷ በሌይ አውት ምርጥ እንድትሆን ትልቅ ስራ የሰሩ ናቸው፡፡
እነበእውቀቱ ስዩም፣ ዳንኤል ክብረት፣ ረ/ፕ አበባው አያሌው፣ ሰለሞን ተሰማ ጂ. ፣ ቀሲስ ኤፍሬም፣ ዶክተር ብርሃኔ ረዳኢ፣ ሰርጸ ፍሬ ስብሃት፣ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ፣ሃብታሙ ስዩም ወዘተ የሚጽፉበት የወቅቱ የምሁራንና የአዋቂዎች ድምጽ የሚሰማበት መጽሄት አዲስ ጉዳይ እንደነበር ያስታውሳል።
መላኩ እንዳልካቸው ተስፋዬን “የምንጊዜም የኔ ምርጥ ሰው ነው” የሚለው ይህንን ሁሉ ምሁርና አዋቂ ሰው በየዘርፉ አሰባስቦ ለሃገሪቱ በታሪክ የማይዘነጋ ምርጥ የህትመት ውጤት መፍጠር የቻለ ሰው በመሆኑ ነው ይላል። ለ4 አመታት ከ100 በላይ እትሞችን በማቅረብየዘለቀችው አዲስ ጉዳይ ደረጃዋን ጠብቃ መጓዟን ባለሙያዎች ይመሰክራሉ፡፡ ነፍስ ሄር ኢብራሂም ሻፊ ፣ ዮሃንስ ካሳሁን፣ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፣ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ፣ እንዳለ ተሺ የሙያ ባልደረቦቹ ሲሆኑ ከቴዎድሮስ ተክለአረጋይ ውጪ አዳዲሶቹን የስታፍ አባላት እነአዚዛ መሃመድ እና መድሃኒት ረዳን ጨምሮ ሁሉም በመንግስት ማስፈራሪያ እና ክስ ሳቢያ ዛሬ በውጭ ሃገራት በተለያየ ስራና ህይወት ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች ናቸው። መላኩ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ ዛሬን በህይወት ቆሞ አለማየቱ ይቆጨኛል ይላል። ኢብራሂም ሻፊ በሁሉ ልብ ውስጥ የእግር እሳት የሆነ፣ ስደት ላይ ሳለ ህይወቱ ያለፈ ምርጥ ማንም የማይስተካከለው አዋቂ የስፖርት ጋዜጠኛ ነው ይላል መላኩ።
“እንዳልካቸው ተስፋዬ ለዚህች ሃገር የፕሬስ ነጻነት ማበብ እና አንባቢ የሚገባውን ክብር እንዲያገኝ ሙሉ ነገሩን አጥቶም ቢሆን ከአደጋ ጋር ተጋፍጦ የታተረ ሊሸለም የሚገባው ታላቅ ሰው ሰው ነው” ይላል መላኩ የአዲስ ጉዳይ ባልደረቦቹንና ጓደኞቹን ሲያስታውስ።
መላኩና አዲስ ጉዳይ መጽሄት
መላኩ ይህንን መጽሄትነት መንግስት እስኪዘጋው ድረስ በማኔጂንግ ኤዲተርነት መርቷል። የታፈኑ እውነቶች፣ ፍቅርና ወንጀል፣ ቢዝነስቴይመንት፣ ትዳር እና ፍቅር፣ ማንን እንማ የመሳሰሉትን በጊዜው ከፍ ያለ አንባቢ የነበራቸውን አምዶችን በባለቤትነት ይዞ ሰርቷል። በተለይ “ዐቢይ ጉዳይ” በተሰኘ አምድ ላይ ይቀርቡ ከነበሩ በርካታ የፖለቲካ ትንታኔዎች ውስጥ የርሱ ስራዎችም ብዙ ናቸው። በታፈኑ ዕውነቶች አምድ ስር የሚቀርቡ በማህበራዊ ችግሮች ላይ ያተኮሩና በተግባር ለውጥ ያመጡ ዘገባዎችን እንዲሁም የወንጀል አምድ ስር የሚቀርቡ እውነተኛ ታሪኮችን እያዘጋጀ መጽሄቱ በመንግስት እስከተዘጋበት 2007 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ አዲስ ጉዳይ ላይ አገልግሏል።
መላኩ በዚህ መጽሄት በጊዜው የነበረውን የፖለቲካ ስርዓት ችግሮች ገንቢ በሆነ መንገድ በማሳየት የህዝብ መብት እንዲከበር እና መንግስትም ተገቢ የአስተዳደር ተግባሩን በብቃት እንዲወጣ የመልካም አስተዳደር እና የፖለቲካ ባህል ለውጥ እንዲመጣ የበኩሉን ሙያዊ ድርሻ ተወጥቷል።ለዚህም ነው “በጋዜጠኝነት ህይወቴ ለአላማ የሰራሁበትና የሙያ መስዋዕትነት የከፈልኩበት ዘመን ያ ጊዜ ነው” ብሎ የሚኮራው።
መላኩ-ወደ አርትስ ቲቪ
በዘመኑ በፕሬስ ላይ በነበረው ጫና እና ምቹ ያልሆነ ከባቢ ለሶስት አመታት ያህል ጋዜጠኝነትን በመደበኛነት ከመስራት ርቆ በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ስራ ላይ የቆየው መላኩ ከለውጡ ጋር ተያይዞ አዲስ ጮራ በፈነጠቀው የሃገሪቱ ፕሬስ ላይ ዳግም ለመስራት ከመስከረም 2019 ጀምሮ አሁን ድረስ በአፍሪካ ሬይነሰንስ ቴሌቪዠን ሰርቪስ (አርትስ ቴሌቪዠንን) በዜና ክፍል ሃላፊነት በመቀላቀል እስከ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰርነት በደረሰ የሃላፊነት ቦታ አገልግሏል። በብዙሃን ዘንድ እውቅና ያገኘበትን “ዐቢይ ጉዳይ” በመባል በሚታወቀውን የውይይት ፕሮግራም በመቅረጽና በአዘጋጅነትና አቅራቢነት በመስራት የሃገራችንን የፖለቲካ እና ማህበራዊ ዲስኮርስ ባህሎች ወደውይይት እና መግባባት ባህል ለማምጣት የበኩሉን ሙያዊ ሃላፊነት እየተወጣም ይገኛል።
“ፍቅርና ወንጀል” የመላኩ መጽሀፍ
መላኩ በጋዜጠኝነት የስራ ዘመኑ ከመደበኛነት ከሰራባቸው ከላይ የተጠቀሱ ሚዲያዎች ባሻገር ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ በወንጀል እና በማህበራዊ ጉዳዮች አምደኝነት እንደ ጦማር፣ ዕለታዊ አዲስ እና ዘ-ፕሬስ እንዲሁም ጽጌረዳ እና ሮዝ የመሳሰሉ በዘመኑ ተነባቢ ጋዜጦችና መጽሄቶች ላይ ሰርቷል። በተለይም ኮከብ አሳየ በሚል የብዕር ስም “ፍቅርና ወንጀል” እንዲሁም “የታፈኑ ዕውነቶች” በተሰኙ አምዶች ላይ ያቀርባቸው በነበሩ በወንጀል እና ማህበራዊ ችግሮች ላይ ያተኮሩ የምርመራ ዘገባዎች ብዙ አንባቢያን ያውቁታል። እነዚህን ታሪኮች በማሰባሰብ በ2009 ዓ.ም “ፍቅርና ወንጀል” የተሰኘ አንድ መጽሃፍም ለንባብ አብቅቷል። የበርካታ መጽሃፍትም አርታኢ ነው። በቅርቡም ግዮን በተባለ መጽሄት ላይ በፍሪላንስ ለብዙ ዕትሞች የዘለቀ የከቨር ስቶሪዎች ጸሃፊ ሆኖም ሰርቷል።
ስልጠና
መላኩ ብርሃኑ በስራ ዘመኑ ከጋዜጠኝነት ሙያው ጋር ለተያያዙ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች፣ ስልጠናዎችና ጥናታዊ ጉብኝቶች 11 ወደሚጠጉ የአፍሪካ፣የአውሮፓ፣የእስያ እንዲሁም የመካከለኛውና የሩቅ ምስራቅ ሃገራት ተጉዟል። ይህ ጋዜጠኛ በአብዛኛው በጤና ዘገባ ፣ በተጨማሪም በህገ-ወጥ ስደት እና በሌሎች ርዕሶች ላይ በተዘጋጁ የሚዲያ ዘገባ ውድድሮች ተሳታፊ በመሆን ለንባብ ባበቃቸው ስራዎቹ ከ International Centre For Journalists የአለምአቀፍ ሽልማት ተሸላሚ ነው። በተጨማሪም የ Africa Media Initiative የአንድ አህጉራዊ ሽልማት 2nd place AMI award አሸናፊ ሲሆን በሃገር ውስጥ ውድድሮችም የ IOM, PANOS, EAJA , ICFP ENHIA እና MoH ሃገር አቀፍ የጋዜጠኝነትናሚዲያ ዘገባዎች ሽልማቶች እና ግራንቶች አሸናፊ ባለሙያ ነው።
የሙያ ማህበራት
በሙያ ማህበራት ተሳትፎ በኩልም መላኩ ቀዳሚው የኢትዮጵያ ፕሬስ ካውንስል ሲመሰረት በአካባቢ ጋዜጠኞች ማህበር ተወካይነት ፈራሚ ሲሆን የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጋዜጠኞች ህብረት ፣የኢትዮጵያ አካባቢ ጋዜጠኞች ማህበርም የቦርድ ሰክረታሪ ሆኖ አገልግሏል። በቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ጋዜጠኞች ኢኒሺየቲቭ እና የአፍሪካ የጤና ጋዜጠኞች ማህበርም በአባልነትና በተጨማሪም በኢትዮጵያ የቤተሰብ ጤና ጋዜጠኞች ማህበር ውስጥ በልዩ አባልነትም አገልግሏል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጰያ አርታኢያን ማህበር የስራ አስፈጻሚ አባል እንዲሁም በኢትዮጲያ ሚዲያ ሴክተር አሊያንስ ውስጥ አባል ነው።
ሌሎች…..
በኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ኖቬ ኮንሰልቲንግ በተባለ የጣሊያን ኩባንያ ውስጥ ቺፍ ኮሙኒኬሽን ስፔሻሊስትነት፣ በጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን እና ፕሮሞሽን ስራ አስኪያጅነት ሰርቷል። በአሁኑ ወቅትም በቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የኮሙኒኬሽን እና ፕሮሞሽን ስራ አስኪያጅ ነው።
መላኩ ከ24 አመት በዘለቀ የጋዜጠኝነት ህይወቱ ለአንዲትም ቀን ቢሆን አቅሙን ሳይቆጥብ ሰርቷል፡፡ አብረውት ይሰሩ የነበሩ በግልጽ እንደተናገሩት መላኩ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ሁለ-ገብ እውቀትን የተላበሰ ባለሙያ ነው፡፡ ይህን ክህሎቱንም ጽሁፎቹን በጥልቀት ከማንበብ መረዳት ይቻላል፡፡ መላኩ በቅድመ-ዝግጅት ያምናል፡፡ ስለ አንድ ጉዳይ ከመስራቱ በፊት በበቂ ሁኔታ ይዘጋጃል፡፡ ይህን በማድረጉም ስራዎቹ ብስለትን የተላበሱ ሊሆኑ ችለዋል፡፡
ቤተሰባዊ ህይወት
መላኩ ከወይዘሮ ሊዲያ ተስፋዬ ጋር ትዳር በመመስረት ሰንፔር መላኩ፣ ሚካኤል መላኩ እና አሜን መላኩ የተባሉ 3 ልጆችን አፍርቷል። “ቀሪው ዘመን በኮሙኒኬሽን ለውጥ የማመጣበት፣ በጋዜጠኝነቴም ሃገሬን የምጠቅምበት፣ በመምህርነት ትውልድ የምቀርጽበት ዘመን ነው” ይላል መላኩ።
መላኩ ብርሃኑን በየዕለቱ ጽሁፎቹንና ምልከታዎቹን በሚያጋራበትና በርካታ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ አድራሻው https://www.facebook.com/m... ማግኘት ይቻላል

ራስን በራስ ማስተዳደር እስከ መገንጠል
የሕገመንግስት አንቀጽ 39 እና ዓለም አቀፍ ህጎች
በህግ ባለሙያ ፋንታሁን ደለለው
መግቢያ #ethiopia | በአለምአቀፍ ደረጃ ራስን በራስ ማስተዳደር /self determination/ ጽነስ ሀሳቡ እስከ የት ድረስ እንደሆነ የተለያየ ትርጉም ሲሰጥበት ይስተዋላል። አንዳንዶች የመገንጠልን ጽንሰ ሀሳብን የሚያካትቱ ሲሆን አንዳንዳቹ ደግሞ የመገንጠልን ጽንሰሀሳብ በፍጹም በህገመንግስታቸው ውስጥ ሳያካትቱ እንደውም መገንጠል ላይ በዝምታም ሆነ በግልጽ የሚከለክሉ ሀገራት አሉ።
ራስን በራስ እስከ ማስተዳደር መገንጠል ስረአት በህገመንግስታቸው የሚያካትቱ ሀገራት ደግሞ በግልጽ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በግልጽ አስቀምጠዋል። ከዚህ ውጭ ባለፈም በህጋዊ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ተገንጥለው ሀገር ነን የሚሉ እያስተዋልናቸው ያለ ሲሆን እነዚህ ሀገራት "እጣፋንታቸው ምንድነው?" የሚለውን በዚህ አጭር ጽሁፍ የምንመለከተው ይሆናል
1. ራስን በራስ ማስተዳደር ምንድነው?
(self determination)
ራስን በራስ ማስተዳደር አንድ ሀገር ወይም የአንድ ሀገር ክልል የሀገሩን የህገመንግስት እና የህግ የበላይነት በማክበር ያለማንም ጣልቃ ገብነት ራሳቸውን በራሳቸው እድል የሚያስተዳድረበት ነው። በዚህ ረገድ የተለያየ አይነት ዙርያ ጥምጥም አይነት ትርጉም ቢመላለስም ራስን በራስ ማስተዳደር ማለት ከማንም ከጣልቃገብነት ነጻ በመሆን በህግ የበላይነትና በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አስተዳደር ነው።
2. ራስን በራስ ማስተዳደር እስከመገንጠል እንዴት ይፈጸማል? self determination to succesion
ራስን በራስ ማስዳደር እስከ መገንጠልን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልግ ሀገር ከነበረበት ሀገር ጋር ለመቀጠል የሚያስችለው ዲሞክሪያሳዊ ፣ ህገመንግስታዊ መብትን ፣ አለምአቀፍ የዲሞክሪያሳዊ እና የሰብአዊ መብቶችን ለመጎናጻፍ ከእናት ሀገሩ ያጣ እንደሆና በህዝቡ ላይ ተደጋጋሚ የመብት ጭቆና እና የመብት ጥሰት እየደረሰበት ከሆነ ነው።
በዚህ ጊዜ ራስን በራስ የማስተዳደር እስከ መገንጠል መብት ጥያቄው ለሀገረ መንግስቱ ለሀገረ መንግስቱ መብት የተሰጠው ሲሆን ይህን በማቅረብ ህጉን ተከትሎ የሚወሰን ይሆናል።
ከዚያም በሀገሩ ህዝብና ህገመንግስት መሠረት በማድረግ አጠቃላይ ውሳኔ መገንጠል የሚፈልገው ህዝብ ጭምር ተጠይቆ የመጨረሻ መልሱ ያለ ልዩነት የመገንጠል መብትን የሚፈቅድ ከሆነ መገንጠል ተግባራዊ ይሆናል።
ይህ የሚሆነውም የመገንጠል መብት በህጉ በግልጽ የተቀመጠ እንደሆነ ነው። አለበለዚያ ግን መገንጠል አይታሰብም ተገነጠልኩ ቢልም የቅዥት ተግባር ይሆናል እንጂ ህጉን የጠበቀ ተግባር አይሆንም።
3. ራስን በራስ ማስተዳደር እስከ መገንጠል ተግባር እንዴት ይፈጸማል?
በመጀመሪያ ደረጃ የመጀመሪያዋ ሀገር የመገንጠል ጥያቄ የሚቀርብባት ህጋዊ ሀገር ልትሆን ያስፈልጋል። ይህም ማለት በአለም አቀፍ ልምድ ህጎች ውሳኔዎች መሠረት ሀገር ለማለት የምትበቃ ልትሆን ያስፈልጋል።
ሀገር ስትሆን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈጻሚ ፣ህገመንግስት፣ህዝብ፣ግዛት፣የውጭ ግንኙነት አቅም ፣ ሉአላዊነት ሊኖራት ያስፈልጋል።
ይህቺ ሀገር በዚህ ልክ ህጋዊ ከሆነች በኋላ ነው የመገንጠል ጥያቄን የተወሰነው ሀገረ ግዛት ወይም ክልል ራስን በራስ ማስተዳደር ወይም እስከ መገንጠል የሚለውን በመጠየቅ በጠያቂው ህዝብ፣ ግዛትና እና በተጠያቂው ሀገር ህዝብ ሙሉ ፍቃድ ተፈጻሚ የሚሆነው።
ለምሳሌ ከኢትዮጵያ መገንጠል የሚፈልግ ክልል የሁሉም ክልሎች ፣ የፌደራል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤ፥ የፌድሬሽን ምክር ቤት እንዲሁም የጠያቂው ክልል ምክር ቤት በሙሉ ያለ ምንም ልዩነት የመገንጠል ይሁንታን ሊገኝ ያስፈልጋል።
አንዱ እንኳን የልዩነት ሀሳብ ካመጣ የመገንጠል ሀሳብ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ይህ በኢፊድሪ ከመንግሥት አንቀጽ 39 ላይ የተቀመጠ ነው።
ለምሳሌ በኢትዮጵያ ይህ ህገመንግስት ሳይወጣ መንግስት ሳይመረጥ የመገንጠል ስረአት የሚከናወንበት ህግና ህገመንግስት ሳይኖር ሀገርንና ህዝብን ወክሎ የውጭ ግንኙነቶች ጋር የድርድርና የማስፈጸም አቅም ያለው የፖለቲካ ፓርቲ ወደ መንግስት የተቀየረ ሳይኖር ሀገርን በበላይነት የሚገዛ ህመንግስት ሳይመሰረት በተረባበሸ የሀገር ስሜት ውስጥ በመሆን ተገንጥያለው ብሎ በተወሰኑ ቡድኖች ብቻ በተደረገ የማይጸና ውል የመገንጠል ጥያቄ አቅራቢውም ሆነ ተቀባይውም ህጋዊ ቅቡልነት የሌላቸው ናቸው።
3. ቅቡልነት ያለው ህግን ሳይከተሉ መገንጠልን በራሳቸው ህጋዊ ያደረጉ ሀገራት እጣ ፈንታቸው ምን ይሆናል?
እነዚህ ሀገራት by defacfo(ያለ ህግ ቅቡልነት) ያላቸው ቢሆንም ከሌሎች ሀገሮች ጋር በሚያደርጉት ግንኙነቶች የሌላን ሀገርን ብሔራዊ ጥቅም መብት የሚነካ ከሆነ ጥቅሙ የሚነካበት ሀገር በተለይም ሀገር የሆነበት አካሄድ ህጋዊ ጥያቄን የሚያስነሳ ከሆነ ይህንን በመቃወሚያነት በማንሳት ብሔራዊ ጥቅሙ የተነካበት ሀገር መብቱን ማስከበር ይችላል።
4. መደምደሚያ
ይህ እንደ ጸሀፊው የህግ ምርምርና አስተያየት የቀረበ ቢሆንም ዋናው ነገር እንደ ጸሀፊው አስተያየት ሀገራት እንደ ህጋዊ ሀገር ሆነው ህዝባቸውን በማስተዳደር የዜጎችን እና የሀገርን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በመጀመረያ ደረጃ በህግ ቅቡልነት ሊኖራቸው ያስፈልጋል።
References/ዋቢ መጽሀፍት/
1. Crawford, J. (2006). The Creation of States in International Law (2nd ed.). Oxford University Press.
2. International Court of Justice (ICJ). (2010). Accordance with International Law of the Unilateral Declaration of Independence in Respect of Kosovo, Advisory Opinion.
3. International Court of Justice (ICJ). (1986). Frontier Dispute (Burkina Faso/Republic of Mali), Judgment.
4. Montevideo Convention on the Rights and Duties of States. (1933).
5. United Nations Human Rights Council (UNHRC). (2022). Report of the Special Rapporteur on the situation of human rights in Eritrea. A/HRC/50/20.
6. United Nations Security Council (UNSC). (1999). Resolution 1244. S/RES/1244.
7. United Nations Security Council (UNSC). (1961). Resolution 169. S/RES/169.
8. Vaughan, S. (2011). The Ethio-Eritrean Conflict and the Algiers Agreement: A Legal Analysis. In A. Jacquin-Berdal & M. Plaut (Eds.), Unfinished Business: Ethiopia and Eritrea at War. Red Sea Press.
9. Woods, T. (2019). The Law of Territorial Integrity and the Eritrea-Ethiopia Boundary Commission. Cambridge Journal of International and Comparative Law.

8 months ago
ሳሎን አልባዋ ደራሲ /እቴቴ/
#ethiopia | የታደሉ ሳሎኖች ትውልድ ይታነፅባቸዋል ፡ ሀገር ይገነባባቸዋል ፡አንድነት ይሰበክባቸዋል ፣ ስርዓት ይፀናባቸዋል ፡ ባህል ይከበርባቸዋል ።
ወልውለን አፅድተን ህፃናት እንዳይገቡ በምንከለክልበት ሳሎን ፈንታ ለትውልድ ያልሆነ ፣ በቁስ ቢያሸበርቅ ፡ ሀገር ከሌለ ፡ ህብረት ከሌለ እንኳን ሳሎን ሙሉ ቤትስ ትርጉም አልባ አይደል ተብሎ ለወገን የተዋለ ውለታ እነሆ --
ዛሬ ልጆቻችን ኢትዮጵያን አያዉቁም፡ መስመር ሳቱብን ስንል ፡ ሀገራቸውን እንዲወዱና በማንነታቸው እንዲኮሩ በለጋነታቸው ምን ዘርተንባቸው ይሆን ?
ያልሰጠናቸውን ኢትዮጵያዊነት አምጡ ማለታችንስ ልክ ነን ወይ ? ብለን ከተፀፀትን መፍትሄው እንደ ደራሲ የዝና ወርቁ በራስ ምቾት ላይ ጨክኖ መልካም ዘርን መዝራት ፣ ማረም ማነፅ ነዋ ወጉ !
በጡረታ ዕድሜና ደሞዝ በፀጥታና በዝግታ በር ከርችማ ከመኖር ይልቅ “ችግኝ የአንድ መንደር ልጆች የንባብ እና የውይይት ክበብ “ በማቋቋም
“ማንበብ ብርሃናችን ውይይት ሰላማችን “ በሚል መርህ ያካባቢውን ህፃናት የማንበብ ባህልን እንዲያዳብሩ ፣ እንዲወያዩ ፣ እንዲከራከሩ ፣ በሰው ፊት በድፍረት እንዲናገሩ ፡ስለማንነታቸው እንዲያውቁ ያስተማረቻቸው ፣ ያሰለጠነቻቸው ቤቷን የሞሉ ህፃናትና ታዳጊዎች የማህበራቸው አስረኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝቼ የተለፋባቸውን ጉልበት ፡ የፈሰሰባቸውን ፍቅር ፡በትዕግስት ያነበበችላቸው መጻህፍት ፡ ለነርሱ ስትል የገበረቻቸውን ውድ እሁዶች ከንቱ ያላስቀሩባት ይልቁምን ቱቱ ካይን ያውጣችሁ ተብለው የተመረቁ ከሁለት መቶ በላይ ማንበብ የሚወዱ ስዕል የሚስሉ ፡ የሚነገራቸው የሚያደምጡ ፡በስርዓት የተገሩ የነግ ኢትዮጵያ መልኮች አይቼ ተስፋዬ ለመለመ።
በአንድ መንደር የዚህን ያህል ህፃናት ማቅናት ከተቻለ የየአካባቢያችንን ችግኝን ብናፈላ ፡ ያንዱ ሰፈር ህፃናት ከሌላው ጋር ብናስተዋውቅ ፡ ዓመታዊ በዓል ላይ የከተማው ችግኞችን ባንድ ላይ በሰፊ ስታዲየም ሰብስበን በሺህ የሚቆጠሩ የዛሬ ችግኞች የነገ ዋርካ ጥላ የሚሆኑንን ድንቅ አንባቢ ህፃናትን ማየት ተመኘሁ ።
የህፃናቱ ወላጆች —
የዝና በልጆቹ አጠራራር / እቴቴ/ እሁድን በልጆቻችን ስልክ ፣አይፓድና ፣ ሪሞት መነጣጠጠቅ ተሸቅበን ለምንውል ወላጆች ፡ ሸክማችንን ያቀለለችበት ትጋት ስንመለከት ፡ በምድረበዳ እንደፈለቀ ብርቅ ምንጭ ልጆቻችንን ለመታደግ የተፈጠረች ታማኝ መልዕክተኛ ናት ብለው ያመሰግኗታል ።
ልብ በሉ “በችግኝ የንባብ ክበብ “ አባል የሆኑ ህፃናት በየቤቶቻቸው ጥፋት ካጠፋ" ዋ እሁድ እቴቴ ጋር አትሄዷትም " መባል ቀናቸውን የሚያበላሽ በደል ነው።
መዝናኛቸውን ፣ ከኩዮቻቸው ጋር በህብረት የሚውሉበትን ፣ የእቴቴን ሽሮ ተሻምተው የሚበሉበትን ፣ ተረቶች የሚያደምጡበትን ፣ ከተዘጉ ቤቶቻቸው የሚያስመልጣቸውን አንድ መተንፈሻቸውን መከልከል አይፈልጉም አይሞክሯትምም።
የዝናን እና በየአካባቢው እንዲህ ባለ መሰጠት ህዝብን የሚያገለግሉ ጥቂቶችን እንዲበዙ ማስቻል ፡ በሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ መደገፍ የሁላችን ኃላፊነትና ግዴታ እንደሆነ በማመን በጋራ ካልቆምን ከርግብግቢታች ከፈጠነ ጥፋት ልጆቻችንን አናተርፋቸውም ። እንደ የዝና ጎረቤቶች ፣ ዕድሮች ፣ ለራዕይዋ ምርኩዝ እንደሆኗት በአካባቢያችን ያሉትን እንቃኝ እንደግፍ ።
ደራሲ የዝና ወርቁ በእኔ እና በእኩዮቼ በኛም ልጆች የተሻገረውን ውለታና ፍቅርሽን ቆጥሮ እግዚአብሄር እድሜና ጤና ይጨመርልሽ ዘንድ ፀሎቴ ነው።
ፅሁፌን ያረዘምኩት የእቴቴን ልጆች የማንበብ ትዕግስት ተማምኜ ነበር ለካ መጽሀፍ እንጂ ስልክ አይሰጣቸውም አበቃሁ።
አድራሻ
“ ችግኝ የንባብና የውይይት ክበብ “ ኃይሌ ጋርመንት ።

9 months ago
ዮም
ንሴብሖ ፍቅሬ
አሰናኝ፡፦ ጥላሁን ክፍሌ እርገጤ
#ethiopia | በተለያዩ ጊዜያት፣ በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት፣ ከተለያዩ ቤተሰቦች የኦቲዝም ተጠቂ የሆኑ ህጻናት ይወለዳሉ፡፡ በስልጣኔና በአመለካከት የበለጸጉት ሀገራትም ኦቲዝምን እንደአንድ የተፈጥሮ ጸጋ በመቀበል በኦቲዝም ጥላ ሥር ለመኖር ዓለማችንን የተቀላቀሉትን ህጻናት እንደየፍላጎታቸው ተንከባክበው በማሳደግ፣ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ሁሉ ለሚኖሩባት ዓለም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ይሠራሉ፡፡
በእርግጥ ከዓለማችን ሀገሮች ብዛት አንጻር በዚህ መልኩ የሚተጉት ጥቂት ናቸው፡፡ ቀላል ቁጥር የማይዘው የዓለማችን በተለይም የሀገራችን ማህበረሰብ ኦቲዝምን ድጋፍና እንክብካቤ የሚሻ እክል አድርጎ ከመቁጠር ይልቅ፣ “ርግማን” እንደሆነ አምኖ ይህንኑ የሚያስተጋባ ነው፡፡
የበኩር ልጃችን ዮም ንሴብሖ፣ የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ካወቅንበት ዕለት ጀምሮ እኔና ቤተሰቤ እያደረግናቸው ያሉትን ወሰን አልባ ጥረቶች በመጽሐፍ ሰንዶ ለአንባቢያን ለማድረስ መነሳቱን ከተፈጠሩት ምክንያቶች አንዱም ኦቲዝምን በሚመለከት ያለን መረዳት ለማረቅ መሻት ነው፡፡
በሀገራችን በኦቲዝም ዙሪያ ያለውን የተዛባ አረዳድ በማስተካከል ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖር የሚረዳ ተጠቃሽ መጽሐፍ' ካበረከተው ከዶክተር ዮናስ ባህረጥበብ ጋር በዮም ምክንያት በተደጋጋሚ የመገናኘት አጋጣሚ ነበረኝ።
ከእነዚህ ቀናት በአንዱ ዶክተር ዮናስ፣ “የሕይወት ተሞክሮህ በመጽሐፍ ተዘጋጅቶ ለአንባቢ ቢቀርብ ብዙ ነገር ሊያስተምርይችላል" በሚል የሰነዘረው አስተያየት ልቤን ሰቅዞ ይዞት፣ ለረጅም ጊዜ ሳስብበት ቆየሁ:: የዶክተር ዮናስ ሃሳብ በልቤ ውስጥ ብቻ አልቀረም:: ከወዳጄ እና አብሮ አድጌ ጥላሁን ክፍሌ ጋር በመሆን ይህንን በእጃችሁ ላይ የሚገኘው መጽሐፍ እንዲወለድ ሆነ፡፡ በእርግጥም ምጡ ቀላል አልነበረም!
ከጥላሁን ጋር መጽሐፉን ለማዘጋጀት በምንተጋበት ጊዜ፣ እጅግ የሚወዳቸውና የሚሳሳላቸው እናቱ ወ/ሮ ጥሩወርቅ በጠና ታመው ሆስፒታል ገቡ፡፡ በዚህ ሁኔታ የመጽሐፉን ዝግጅት ማስቀጠል፣ ሙሉ ጊዜውን ተጠቅሞ እናቱን ለሚያስታምመው ጥላሁን ከባድ ነበርና፣ ሂደቱ ለጊዜውም ቢሆን እንዲቋረጥ ሆነ:: ሆኖም የፈጣሪ ፈቃድ ሆነና፣ ለአምስት ወራት ያህል በሕክምና ሲረዱ የቆዩት እናቱ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ፡፡ ጥላሁን ክፍሌን የሚያውቅ ማንም ሰው እናቱን ያውቃል፧ ሁለቱን የሚያውቅ ደግሞ በመካከላቸው ያለውን የተለየ ፍቅር ያውቃል:: ያን ጊዜ፣ ጥላሁን የቀድሞው ጥንካሬ እና ሞራል ኖሮት ይህን ሥራ እንጨርሰዋለን
ምክንያት አለው ብዬ ራሴን አሳመንኩ። እንዴት ይበረታ ይሆን? እያልኩ ብጨነቅም ምስጋና ለፈጣሪ ይሁንና አጽናኝ መላእኩን ልኮ እኒያን ጥቋቁር የሐዘን ቀናት በጸጋው አሳለፋቸው:: ብርቱው ባለተሰጥኦ ጥላሁንም በሚያስደንቅ ትጋትና ብርታት መጽሐፉን አጠናቆ እነሆኝ አለኝ፡
ባሳለፍኩት የሕይወት መንገድ ያጋጠሙኝን የደስታም ሆነ የሐዘን፣ የከፍታም ሆነ የዝቅታ፣ የስኬትም ሆነ የመፈተን ውጣ ውረዶችን በዚህ መጽሐፍ ለማጋራት ሞክሬአለሁ፡፡ በተለይም ልጃችን ዮም ንሴብሖ የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ካወቅንበት ዕለት ጀምሮ እኔና ቤተሰቤ መፍትሔና ፈውስ ፍለጋ፣ የወጣን የወረድንባቸው ጎዳናዎች፣ ያንኳኳናቸው ደጆች፣ የገፋናቸው የመከፋትና የመፈተን ወራት እና ለዐይን ጥቅሻ ዕድሜ እንኳን ከጎናችን ባልተለየንና ይልቁንም ከፊታችን ይቀድም በነበረው እግዚአብሔር የቻልናቸውን ስኬቶች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ታነባላችሁ፡፡
ከሕይወት ልምዴ ከተወሰደ ቀጥተኛ ተሞክሮ በተጨማሪ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከንባብ እና በኦቲዝም የተጠቁ ልጆች ካላቸው ወላጆችም ጋርበነበረኝ ማኅበራዊ ግንኙነቶች የተረዳኋቸውን ግንዛቤዎች በመጽሐፉ ለማካተት ሞክሪያለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ኦቲዝምን በተመለከተ ህብረተሰባችን ያለው ግንዛቤ በአብዛኛው የተዛባ ነው፡፡ ይህም ወላጆች/አሳዳጊዎች ሊሻሻል በሚችለው በዚህ የአእምሮ ዕድገት እክል የተጠቁ ልጆቻቸውን ለማገዝ የሚችሉትን እንዳያደርጉ፣ በዚህም የእነሱና የልጆቻቸው ስቃይ ቀጣይና ማብቂያ የሌለው እንዲሆን አድርጓል፡፡
ይህ መጽሐፍ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆች ላላቸው ወላጆች እና በኦቲዝም ሳቢያ የሚፈጠሩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ለሚሰሩ አካላት እንዲሁም ለመላው ማኅበረሰባችን የተሻለ ግንዛቤን በማስጨበጥ አዎንታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ፡፡
መጽሀፉ በአራት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን የመጀመሪያ ምዕራፍ ዮም ከመወለዱ በፊት የነበረኝን ህይወት በመጠኑም ቢሆን የሚያስቃኝ ነው:: ሁለተኛው ምዕራፍ የመጽሃፉ ዋና አስኳል ሲሆን ይህም ዮም ከተወለደ ጀምሮ ይህ መጽሀፍ እስኪዘጋጅ ድረስ የተኖረውን ዋና ዋና የህይወት ክፍል ይዳስሳል:: ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ ልጆቻቸው በኦቲዝም የተጠቁ እና በእኔ ማህበራዊ ህይወት ዙሪያ የነበሩ ወላጆች ቅንጫቢ ታሪኮች ስብስብ ነው:: በመጨረሻው ምዕራፍ ከእኔ የህይወት ልምድ እና ትዝብት በተጨማሪ በኦቲዝም ዙሪያ ከተለያዩ ምንጮች የቃረምኳቸው ጠቃሚ እውነታዎች ተገልፀዋል:: በእኔ እና በልጄ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ለበጎ አላማና ተግባር የተዘጋጀውን ይህን መፅሃፍ በአክብሮት ታነቡልኝ ዘንድ የምጋብዛችሁ በፍፁም ትህትና ዝቅ ብዬ ነው፡፡
መልካም ንባብ!
ንሴብሖ ፍቅሬ ወንድማገኝ
***
አቶ ንሴብሖ ፍቅሪ ከባለቤቱ ጋር በመሆን የኦቲዝም ተግዳሮት ያለበትን ልጃቸውን በመንከባከብ ያለፉበትንና እያደረጉ ያለውን ልምድ ለህብረተሰቡ ለማካፈል ይህን መጽሐፍ በማዘጋጀቱ እጅግ እመሰግነዋለሁ።
ጥንዶቹ ባጋጠማቸው ተግዳሮት ተስፋ ላይቆርጡ ስለሁኔታውና መወለድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች በራሳቸው ጥረት ተረድተው አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ በፍጹም ፍቅር እያደረጉ መገኘታቸው የሚደነቅ ነው።
ይህ ልምዳቸውም በመጽሐፍ መታተሙ፣ ተመሳሳይ ተግዳሮት በቤተሰባቸው ውስጥ ኖሮ ፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ለተጋቡና፣ ምናልባትም የማይገቡ እርምጃዎችን ለሚተገብሩ ቤተሰቦች ተገቢውን መንገድ በማመላከት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ ነው።
በህብረተሰቡ ውስጥ ከሚወለዱ እንድ መቶ ህፃናት አንዱ ወይም ሁለቱ የኦቲዝም ተግዳሮት የሆነ የነርቭ እና የእድገት ልዩነት ሊያጋጥማቸው ይችላል ፤ ነገሩ እጣ ነው። እጣው በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛችንም ቤት ሊከሰት ይችላል። ስለዚህ ሁላችንም በተጨባጭ ልምድ ከካበተው ንሴብሖና ቤተሰቡ በመማር ስለጉዳዩ እውቀት እንዲኖረን እመክራለሁ። ለዚህም የዚህ መጽሐፍ አስተዋጽኦ የጎላ ነው።
ዶ/ር ምኒልክ ደስታ
የአዋቂዎችና ህፃናት አእምሮ ሐኪም
***
ልጆቻቸው የኦቲዝም ችግር ያለባቸው በርካታ ወላጆች ፣ የሰዎችን አላዋቂ አንደበትና መገለል በመፍራት የልጆቻቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ችግርና ስቃይ በሚደብቁበት ወቅት፣ ንሴብሖ የኦቲዝም ተጠቂ የሆነውን ልጁን ችግርና የቤተሰቡን ውጣ ውረድ በመጽሐፍ መተረኩ የሚያስመሰግነው ነው።
እርግጥ ነው ንሴብሖ በልጁ ዮም ምክንያት በብዙ መረበሸ፤ እንቅልፍ ማጣት፤ ማህበራዊ መገለል ተከብቦ ያሳለፈውን ህይወት እና የከፈለው ዋጋ ቀላል አልነበረም፤ ይህም ሆኖ "የዮም መፃኢ እድል ፈንታ ምን ይሆን?'' የሚለው ከባድ የሃሳብ ሸክም አሁንም ከትከሻው አልወረደም።
ይህ ግለ ታሪክ በዚህ ችግር ውሰጥ የምናልፍ ቤተሰቦችን ችግሮች ገልጦና አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን ፣ መጽሐፉን ልዩ የሚያደረገው ዋናው ነገር እንደተለመደው ስለ ችግሩ እውቀት ባላቸው ባለሞያዎች ሳይሆን የችግሩ ገፈት ቀማሽ በሆነ አባት መቅረቡ ነው።
መልዕክቱ የኦቲዝምን ችግር እየተጋፈጡ ላሉ ቤተሰቦች አስተማሪና ጉልበትን የሚሰጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ተጋብተው መውለድ ለሚያቅዱ ጥንዶች፣ ለእምነትና ለትምህርት ተቋማት፣ በኦቲዝም ላይ ለሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ለመላው ማህበረሰብ ጥልቅ ግንዛቤን በማስጨበጥ ረገድ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው።
ይህንን መጽሐፍ ሳነብ ፣ በፈተና ውስጥም ሆነን በጎ ማሰብና ፣ ከችግራችን በላይ በሆነ ጠንካራ ማንነት መታነጽ እንደሚቻል አይቻለሁና ሁሉም እንዲያነበው እመኛለሁ።
ዶ/ር ፍርድአወቀ ማሞ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
***
ለብዙዎቻችን ፈተና (መከራ) ሁልጊዜ የኃጢአት ውጤት ይመስለናል። አንድ ሰው ጤናን፣ ሀብትን፣ ልጅንና የመሳሰሉትን ሲያጣ እግዚአብሔር በኃጢአቱ እየቀጣው ነው ብለን እንደመድማለን፡፡
አቶ ንሴብሖ ፍቅሬና ባለቤቱ ወይዘሮ ሳምራዊት ድንቁ ፈተናን በመጋፈጥ የጽናት ተምሳሌት ሆነውናል… አቶ ንሴብሖ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆችን ለሚያሳድጉ ወላጆች/ አሳዳጊዎች ጉልበትን የሚሰጥ፣ ጥበብን የሚያመላክት ሥራን መሥራቱ ደስ ያሰኛል።
ይኸውም ያላዋቂዎችን ትችት በመፍራት በእንዲህ ዓይነት ሕይወት ያሉ ወገኖችን ከማግለል ይልቅ ማቀፍና መንከባከብ፣ ሰብአዊና ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን በመጽሐፍ ሰንዶ በማቅረቡ ሊመሰገን ይገባል።
በብዙ ፈተና ውስጥ ቢያልፍም ንሴብሖ አሁንም አምላኩን አመስጋኝ መሆኑ ሌላው በጣም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። ይህንን መጽሐፍም ማንበብ ለሁሉም፣ በሁሉ መንገድ አቅም ይሰጣል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
***
ንሴብሖ ፍቅሬ
ስልክ
+251911212012
ኢ-ሜይል
yomnesebehogmail.com

የዜናነህ መኮንን ማስታወሻ ተዘጋጀ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያና ኮምዩኒኬሽን የአንጋፋው ደራሲ፣ የዜና አቅራቢ የዜናነህ መኮንን የአንደኛ ዓመት የህልፈት ማስታወሻ አስመልክቶ አንድ መሠናዶ ህዳር 7 2018 አዘጋጅቷል።
ሲኤምሲ ሚካኤል አጠገብ በሚገኘው የአሀዱ ሬድዮ ስቱድዮ በተደረገ ዝግጅት የዜናነህ የሙያ አጋሮችና አድናቂዎች ተገኝተዋል።
ዜናነህ መኮንን በእስራኤል አገር መኖሪያውን ያደረገ የሚድያ ሰው ሲሆን ለ15 ዓመታትም በኢቲቪ በዜና አንባቢነት ያገለገለ ነው።
በዕለቱ ለዜናነህ ክብር ሁለት አጫጭር የቪድዮ ቅንብሮች ለዕይታ የበቁ ሲሆን ዜናነህን በቅርበት የሚያውቁም ምስክርነት ሰጥተዋል። ታላላቆችን እናክብር! ከቀደሙት ምን እንማር" በሚል ርዕስ በተዘጋጀው በዚህ መርሐ -ግብር የቀድሞ የዜናነህ ባልደረቦች ምስክርነት ሰጥተዋል።
አቶ ኃይሉ ወልደፃድቅ የኢትዮጵያ ሬድዮ የቀድሞ ባልደረባ እና የፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ በዕለቱ ታድመው ለዜናነህ ያላቸውን አክብሮት ገልፀው የዛን ጊዜዎቹን ስመ ገናና የዜና አቅራቢዎችን እያነሱ በዛን ወቅት የነበረውን አሠራር በዳሰሳ መልክ አቅርበዋል።
ከቀደምት የቪድዮ ኤዲተሮች አንዷ የሆኑት ወይዘሮ አስናቀች ፀጋዬም ቴክኖሎጂ እንደአሁኑ ባላደገበት ጊዜ ያኔ ፕሮግራሞች ኤዲት የሚደረጉበት መንገድ አድካሚ እንደነበር ገልፀዋል።
የሚድያ ሰው አስፋው ኢዶሳ፣ ደራሲ ገነት አየለ፣ ጋዜጠኛ ታዬ በላቸው ፣ የቴክኒክ ሰው ለዊ ገሠሠ፣ ጋዜጠኛ አንተነህ ደግፌ እና ሌሎችም ለዜናነህ እንዲህ አይነት መታወሻ መደረጉ ትልቅ ነገር ነው ሲሉ ሀሣብ ሰጥተዋል።
ተወዳጅ ሚድያ ውለታ የዋሉ የሚድያ ሰዎችን" መዝገበ አእምሮ" በተሰኘው መፅሀፍ ላይ ማካተቱ የሚታወቅ ሲሆን ዜናነህም የሕይወት ታሪካቸው ከተሰነደላቸው አንዱ ነበር።
ዜናነህ ህይወቱ ካለፈ አንድ ዓመት የሞላው ሲሆን ይህን ባለውለታ ለማሰብ ከዜናነህ መኮንን ቤተሰቦችና ላስቬጋስ ከሚገኝ የሙያ አጋሩ ጋር አንድ ላይ በመሆን የማስታወሻ መርሀ ግብር ሊዘጋጅ ችሏል።
በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ የነበረውን የጋዜጠኝነት አሠራር የሚያሳይ አጭር ዘጋቢ ቅንብር በዕለቱ ለዕይታ የቀረበ ሲሆን ታዳሚዎች በሰጡት አስተያየትም ወደ ኃላ መለስ ብለን የሚድያውን ታሪክ እንድንቃኝ አስችሎናል ብለዋል።
ዋናው የፕሮግራሙ ግብ ከእነ ዜናነህ መኮንን አዲሱ ትውልድ ምን ልምድ ይቀስማል? የሚለው በመሆኑመሰ በፕሮግራሙ ላይ እንዲታደሙ የተጋበዙት የመስከረም ሚድያ የጋዜጠኝነት ተማሪዎችም ከእንዲህ አይነት መሰናዶ ትልቅ ትምህርት መቅሰም እንደቻሉ ተናግረዋል።
የማስታወሻ መርሀ ግብሩ ላይ የታደሙት ቀደምት ጋዜጠኛ ፀሐይ ተፈረደኝም በሰጡት ሀሣብ ተወዳጅ ሚድያ የቀድሞ ጋዜጠኞችን በዚህ መልኩ ማገናኘት እንዲጀምር ከጎኑ ሆነን ልናግዘው ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።የዕለቱን መርሀ ግብር በቪድዮ እና ፎቶግራፊ በመቅረፅ ጉልህ ተግባር ያከናወነው መጋቢት ቪዲዮ ፕሮዳክሽን ሲሆን የአሀዱ ሬድዮ ከማኔጅመንቱ እስከ ቴክኒክ ሰዎች ድጋፋቸውን ያለ አንዳች ስስት አሳይተዋል።
ከመርሀ ግብሩ አዘጋጆች አንዱ ዕዝራ እጅጉ በጋዜጠኝነት ላለፉት 26 አመታት የቆየ፣ በአሁኑ ሰአት የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን መስራች እና ሥራ አስፈጻሚ ነው፡፡ እዝራ 45 ታሪኮችን በሲዲ፣ 21 ታሪኮችን ደግሞ በመጽሀፍ ያቀረበ ነው፡፡
‹‹መዝገበ-አእምሮ›› በሚል ርእስም በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን በጠንካራ ሽፋን የወጣ ኢንሳይክሎፒዲያን በሁለት ቅፅ ያሳተመ ነው፡፡ ታላላቆችን የማክበር እና ልምድና ታሪካቸውን የሚያካፍሉበትንም ስልት በመንደፍ ላይ የሚገኘው ተወዳጅ ሚድያ ይህን ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ታውቋል።

ጉራጌ ዞን : የዶ/ር ዐቢይ አህመድ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
#ethiopia | በጉራጌ ዞን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስም የተሰየመው ት/ቤት በዛሬው እለት ተመርቋል።
በምስጋና የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የዶክተር አብይ አህመድ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ ሀዋሪያት ከተማ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።
በዚህም የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ የሚታወቅ ሲሆን የተገነባው ትምህርት ቤት የዞኑ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ከማሻሻል ባለፈ በሀገር ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት አበርክቶው ከፍተኛ ነው ተብሏል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታም 8 የመማሪያ ክፍሎች፣ ዘመናዊ ቤተመጽሀፍት፣ የአስተዳደር ቢሮ፣ የመምህራን ስታፍና ሌሎችም ያካተተ ነው ተብሏል።
በምረቃ ፕሮግራሙም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶክተር እዮብ ተካልኝ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል፣ የምስጋናው የበጎ አድራጎት መስራችና የበላይ ጠባቂ አምባሳደር ምስጋናው አርጋው እና የእምድብር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ ተገኝተዋል።
#ጉራጌ ዞን

የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች ላይ አዲስ ክስ ማቅረብ
Res judicata, Latin for "a matter judged,"
( የፍትሀብሔር ስነስርአት ሕግ አንቀጽ 5)
(Fantahun Delelew LLB,LL.M) 0929101037/0983337690
መነሻ #ethiopia | ይህቺን አጭር ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በፍርድ ያለቁ ጉዳዮች በድጋሚ ዳኝነት ሊጠይቅባቸው የማይገባ ስለመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5 ላይ የተቀመጠ ሲሆን ይህም በዚህ ህግ 1ኛ መጽሀፍ በፍርድ ቤቶች ስልጣን ምእራፍ አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ክፍል የሚገኝ ነው። በዚህ ድንጋጌ የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ምንድነው? በዚህ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ላይ በተመሳሳይ ጉዳይ ዳኝነት ለመጠየቅ የማያስችለው ተመሳሳይ የሚባለው ጉዳይ ምን ሲሆን ነው? ተመሳሳይ ጉዳይ የሚባለው ነገር እስከ ምን ድረስ ነው? በዚህ ተመሳሳይ በተባለበት ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ላይ ማን እንዴት ምን መጠየቅ ይችላል? በዚህ ተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ዳኝነት መጠየቅ አይቻልም ወይ? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ለማህረሰቡ የህግ ግንዛቤ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ በህግ ባለሙያውም ዘንድ ተገቢ አረዳድ እና ትኩረት እንዲኖረው ይህ ጹሁፍ ቀርቧል።
ከታች ተዝርዝሮ ለቀረቡት አጭር ማብራርያ ይረዳ ዘንድ የፍ/ስ/ስ/ህጉ አንቀጽ 5ን ማስፈሩ አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን እንደሚከተለው ተቀምጧል።
1. በፍርድ ያለቁ ጉዳዮች ማለት ምን ማለት ነው?
ከፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5 አንጻር በፍርድ ያለቁ ጉዳየች ማለት በህግ ስልጣን የተሰጠው ፍርድ ቤት በአንድ ጉዳይ ላይ ፍርድ የተሠጠው እንደሆነ ጉዳዩ በፍርድ እንዳለቀ እንደሚቆጠር በህጉ የተቀመጠ ነው። ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመቀበል በህግ ስልጣን የተሠጠው መሆኑን የሚያመለክት ነው። "በህግ ስልጣን የተሠጠው ፍርድ ቤት ማን ነው?" የሚለውን ስንመለክት ፍርድ ቤቶች በፌድራልም ሆነ በክልል የሚገኙ በአዋጅ በምን የስረ ነገር ጉዳይ ላይ ማየት እንደሚችሉ በግልጽ ስልጣን የተሠጣቸው መሆኑ ነው። የፌደራል ፍርድ ቤቶች በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 5 ላይ የስረ ነገር ስልጣናቸው በዝርዝር ተቀምጧል።በህገመንግስቱ ፣ በዚህ እና በክልሎች በራሳቸው የፍርድ ቤቶች አዋጅ መሠረት ፍርድ ቤቶች በህግ ስልጣን ተሰጥቶአቸዋል። እንግዲህ የስነስረአት ህጋችን ይህን የህግ ስልጣን ምንጭ መሠረት በማድረግ ነው በህግ ስልጣን የተሰጠው ፍርድ ቤት ፍርድ የሰጠበት ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ያረፈበት ጉዳይ ነው በማለት ደንግጎ ያስቀመጠው።
2. ቀድሞ በተሰጠ ፍርድ ላይ ማለት ድጋሚ ክስ ወይም ክርክ ማቅረብ አይቻለም ሲባል ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?
በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5 ላይ እንደተቀመጠው በአንድ ተመሳሳይ ጉዳይ አስቀድሞ ፍርድ በተሰጠው ጉዳይ በድጋሚ ክስ ወይም ክርክር ማቅረብ እንደማይቻል ተመላክቷል።የሚቀርበው ጉዳይም በስር ነገር፣በጭብጥ እና በክርክር ተመሳሳይ በሆነው ጉዳይ አስቀድሞ ፍርድ የተሰጠበት እንደሆነ በዚህ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ላይ በድጋሚ ክስ ወይም ክርክር ማቅረብ እንደማይቻል በአንቀጽ 5/1/ ላይ የተደነገገ ሲሆን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎች በመ/ቁ 111067 አስገዳጅ የሆነ የህግ ትርጉም የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5 እና 544/2/ለ/ መሠረት በማድረግ ሠጥቷል። የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5 ላይ እንደሠፈረው አስቀድሞ ፍርድ በተሰጠበት በክርክር በስረነገርም ሆነ በጭብጥ ተመሳሳይ በሆነበት ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ደጋሚ በክስ በክርክር መጠየቅ አይገባም በማለት ያስቀመጠ ሲሆን የበለጠ ለመረዳት ስረነገር፣ጭብጥ፣ክርክር ሲል ምን ማለት እንደሆነ መረዳቱ ተገቢነት ያለው ነው።
2.1. ስረ ነገሩ ተመሳሳይ መሆን አለበት ሲባል ምን ማለት ነው?
ስረነገር ማለት አንድ ፍርድ ቤት ተቀብሎ ሊያይ የሚችለው ጉዳይ ማለት ነው። ይህንን በተመለከተም ፍተሀብሄር ስነስረአት ህግ ቁጥር አንቀጽ 9 እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ 1234/13 አንቀጽ 5 ላይ በዝርዝር የስረ ነገር ጉዳዮች በገንዘብም ሆነ በአይነትም ተቀምጠዋል። በሌላ አነጋገር የሚቀርበው የክስ ጉዳይ ማለት ነው።በዚህ ጉዳይ በህግም፣በጭብጥም፣በክርክርም ህነ በህግ ተመሳሳይ በሆነ ጉዳይ ላይ አስቀድሞ ፍርድ የተሠጠበት በድጋሚ ክስ ማቅረብ የማይቻል ነው።
2.3 ጭብጡስ ተመሳሳይ መሆን አለበት ሲባል ምን ማለት ነው?
ጭብጥ ማለት በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 247 ላይ የተቀመጠ ሲሆን ከምን ከምን እንደሚመሰረትም ተደንግጓል። ይህም ከከሳሽ ክስ፣ከተከሳሽ መልስ፣ ከግራ ቀኙ ማስረጃ ከግራ ቀኙ ተከራካሪ ምርመራ ፍርድ ቤቱ በራሱ ከሚያጣራው ምርመራ የሚመሰረት ሲሆን ይህም በከሳሽ ተከሳሽ ወይም በግራ ቀኙ ያልተማመኑት ጉዳዮችን መሠረት በማድረግ የሚመሰረት ነው። በዚህ ጭብጥ ላይ አስቀድሞ ውሳኔ የተሰጠበት እንደሆነ በድጋሚ ክስ ማቅረብ የማይቻል እንደሆነ የፍ/ስ/ስ ህጋችን አንቀጽ 5/1/ ደንግጓል። ይህም ሲሆን ክርክሩም ሆነ የህግ ጉዳዩ ተመሳሳይ መሆን አለበት።
3. ክርክሩ ተመሳሳይ መሆን አለበት ሲባል ምን ለማለት ነው?
ክርክር ማለት ከፍተሀብሔር ስነስረአታችን እንደምንረዳው ከከሰሽ ክስ ማስረጃ፣ከተከሳሽ መልስ መከላከያ ማስረጃ ከተካካዱበት የዳኝነት ጥያቄ መሠረት ተደርጎ አጠቃላይ በግራቀኙ መካከል የተደረጉ የክስ ሂደትና ሙግት ነው። ይህ ክርክር ተመሳሳይ በሆነበት ሁኔታ ከተመሳሳይ ስረነገሩ እና ጭብጥ ጋር አንድ በሆነ አስቀድሞ ባለቀ ወይም ፍርድ በተሰጠ ጉዳይ ድጋሚ ክስ መጠየቅ አይቻልም።
4. አስቀድሞ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ድጋሚ ክስ ለመጠየቅ የተከለከለው ወገን ማን ነው?
አስቀድሞ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ላይ በክርክሩ ተሳታፊ የሆኑም ሆነ ያልሆኑ ጥቅሜን ይነካል የሚል ማናቸውም ወገን ድጋሚ ክስ ማቅረብ እንደማይችሉ የፍ/ስ/ስ/ህጋችን አንቀጽ 5/1/ ላይ ተቀምጧል።
ክርክሩ፣ጭብጡ፣የህግ ነገሩ ተመሳሳይ በሆነበት አስቀደሞ በተወሰነበት በክርክሩ ያልተሳተፈ ተከራካሪ ቢሆንም አዲስ ክስ ማቅረብ አይችልም።
5. ክርክሩን ያላወቁ ወገኖች ሊሳተፋ የሚገቡ አዲስ ክስ ማቅረብ ካልቻሉ እጣ ፈንታቸው ምንድ ነው? መብታቸውንስ እንዴት ማስጠበቅ ይችላሉ?
አንቀጽ 5/4/ቀድሞ በተሰጠው ፍርድ እንደተሳተፉ ተደርጎ የሚቆጠር ሲሆን ነገር ግን አዲስ ክስ የማቅረብ መብት ባይኖራቸውም በክርክሩ ያልተሳተፋ መሳተፍ የሚገባቸው የነበሩ ማናቸውም ወገኖች ፍርድ እስኪሰጥ ድረስ ጉዳዩን ያልሰሙ ፍርዱ ክርክሩ መብታቸውን የሚገዳ እንደሆነ ይህን በማስረዳት በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 358 መሠረት አቤቱታውን ፍርዱን ለሰጠው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል።
6.ተከራካሪ ወገኖች በተሰጠው ፍርድ ላይ ድጋሚ እንዲታይላቸው የሚፈቅድ የህግ አግባብ አለ?
ፍርዱ የተሰጠው በሐሰት ማስረጃ መደለያ በመሳሰሉት አማካኝነት ስለመሆኑ ማስረጃ ያለው ተከራካሪ እንደገና ጉዳዩ እንዲታይለት ፍርዱን ለሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታውን ማቅረብ ይችላል። ፍርድ ቤቱም በድጋሚ መታየት አለበት ወይንስ የለበትም በሚለው ላይ ውሳኔ ይሰጣል
ተቀባይነትን ከገኘ ጉዳዩ በድጋሚ ይታያል። ተቀባይነት ከሌለው ፍርዱ እንደጸና የሚቀጥል ሲሆን ጉዳዩ በድጋሚ ሊታይ አይገባም በማለት በተሰጠው ብይን ላይ ግን ይግባኝ መጠየቅ አይቻልም። አንቀጽ 6
7. ሊቀርቡ የሚገባቸው ማስረጃዎች ሳይቀርቡ ፍርድ የተሰጠ እንደሆነስ?
አስቀድሞ በተሰጠው ፍርድ ላይ በነበረው ክርክር ሊቀርቡ የሚገቡ ማስረጃዎች ባይቀርቡ እንኳን እንደቀረቡ ተደርጎ ይቀጠራል አንቀጽ 5/3/።ለዚህም ምክንያቱ ማስረጃዎች ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው በሙሉ አስቀድመው ተጠቃለው መቀረብ ያለባቸው በመሆኑ ሲሆን አስቀድሞ በክርክሩ ሂደት እንደቀረቡ ተደርገው ይቆጠራሉ።
8. በቀድሞ ክርክር ላይ ለማስረጃ ለመከላከል ለመቃወሚያ ምክንያት ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ፍሬ ነገሮች በተመለከተ
እነዚህ ነገሮችም ምንም እንኳን ለክርክሩ ጠቃሚ ቢሆኑም አስቀድሞ ፍርድ በተሰጠው ክርክር ውስጥ ሳይቀርቡ ውሳኔ የተሰጠ ከሆነ እንደታዩ ተደርጎ የሚቆጠር መሆኑን በአንቀጽ 5/2/ ላይ ተደንግጓል።
9. አስቀድሞ በተሰጠው ፍርድ ላይ ግልጽ ዳኝነት ተጠይቆ የታለፈ ከሆነስ
በክሱ ውስጥ ዳኝነት ከተጠየቁባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የዳኝነት ጥያቄዎች በፍርዱ ላይ ዳኝነት ወይም ውሳኔ ያልተሰጠበት ከሆነ ተቀባይነት እንደሌለው እንደሚቆጠር አንቀጽ 5/3/ ላይ ተደንግጓል
በአጠቃላይ በፍ/ስ/ስ/ህጋችን አንደኛ መጽሀፍ በፍርድ ቤቶች ስልጣን ጠቅላላ ድንጋጌዎች ላይ በአንቀጽ 5 ላይ እንደተመለከተው በክርክር በጭብጥና በስረነገር ተመሳሳይ በሆነበት አስቀድሞ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ላይ ድጋሚ ክስ መጠየቅ እንደማይቻል በመርህ ደረጃ ተደንግጓል።
(ለ) ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ጉዳይ (Res Judicata) የማይሠራባቸው ልዩ ሁኔታዎች....
#1 . በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 153 መሠረት ዕግድ እንዲነሳ በቀረበ አቤቱታ ላይ የሚሰጥ ውሳኔ በሥረ-ነገሩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ አይሰጥም። የሰ/መ/ቁ 182044/220980
• 2. የአፈፃፀም ጥያቄ
የሰበር መ/ቁጥር 182361
• በፍርድ የተረጋገጠን መብት ለማስፈጸም የሚቀርብ የአፈጻጸም ጥያቄ፣ በድጋሚ የቀረበ ነው (Res Judicata) በሚል ምክንያት ውድቅ ሊደረግ አይችልም።
• የአፈጻጸም ክስ የዋናው ውሳኔ አካል እንጂ አዲስ ክስ አይደለም።
#3_የክርክር ዓላማ ልዩነት
የሰበር መ/ቁጥር 197368
• የውል መሠረት ልዩነት: በአንድ አይነት ጉዳይ ላይ በሌላ ፍርድ ቤት ክርክር እየተካሄደ ነው (ፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 244(2)(ሐ)) የሚለው መቃወሚያ፣ ሁለቱ ክሶች የተለዩ ውሎችን (ለምሳሌ የሽርክና ውል እና የኪራይ ውል) መነሻ ካደረጉ ተቀባይነት የለውም።
• ክሶች የጋራ ጭብጥ ቢኖራቸውም የመነሻ ውላቸው የተለያየ ከሆነ፣ Res Judicata አይሆንም።
የሰበር መ/ቁጥር 221446
• ቀደም ሲል የነበረ የውርስ ማጣራት ክስ ውሳኔ፣ በኋላ የቀረበውን የንብረት የመፋለም ክስ (ይለቀቅልኝ) አይከለክልም፤ ምክንያቱም የሁለቱ ክርክሮች ሥረ ነገርና ጭብጥ ፍፁም የተለያየ ነው።
#4_ክስ የማቅረብ መብት በፍርድ ቤት ሲጠበቅ
የሰበር መ/ቁጥር 207553
• በፍርድ ቤት ውሳኔ ወቅት አንድ ወገን በውሳኔው ውስጥ መብቱ ተጠብቆለት፣ ለሁለተኛ ጊዜ ያንን መብት ተጠቅሞ ክስ ሲያቀርብ፣ ክሱ Res Judicata በሚል ውድቅ ሊደረግ አይገባም።
• ምክንያት: የፍርድ ቤቱ ቀዳሚ ውሳኔ የክስ የማቅረብ መብቱን (right to sue) ስላስጠበቀለት፣ ክልከላ አይሠራም።
#6_ሁከት ክስ (Possessory Action) እና የመፋለም ክስ (Petitory Action)
የሰበር መ/ቁጥር 198022
• የሁከትና የባለሀብትነት ክስ: የቀድሞ ፍርድ የሁከት ይወገድልኝ ክስን የሚመለከት ከሆነ፣ አሁን የቀረበው የባለሀብትነት (መፋለም) ክስ በመሆኑ ቀድሞ በፍርድ የጨረሰ ጉዳይ ነው ሊባል አይችልም (ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5).
• የሁለት ዓይነት ክሶች ሥረ ነገር የተለያየ በመሆኑ የፍርድ የመጨረሻነት መርህ አይሠራባቸውም።
የሰበር መ/ቁጥር 182044
(ሐ) ማጠቃለያ
ከላይ በ(ሀ) ስር እንደተዘረዘሩት ድጋሚ ክስ ቀድሞ በፍርድ ባለቁ ጉዳዮች አዲስ ክስ ማቅረብ እንደማይቻል በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5 ላይ የተቀመጠ ነው። ስለሆነም ይህን ጠንቅቆ መረዳቱ እጅግ አስፈላጊ የህግ ግንዛቤ ነው። በ(ለ) ስር በተዘረዘሩት የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5 መሠረት ምንም እንኳን ጉዳዩ አስቀድሞ ፍርድ ያገኘ ቢሆንም ይህ መሠረታዊ ሕግ የማይሰራባቸው ልዩ ሁኔታዎች ናቸው።
https://t.me/Fantahunlawye...
https://www.youtube.com/@w...

61 ሻማዎች / በዕዝራ እጅጉ -(ተወዳጅ ሚድያ)
ኢቲቪ ነገ ጥቅምት 23፣61 ዓመት ይሞላዋል
(ክፍል አንድ)
#ethiopia | ውድ ክቡራት እና ክቡራን የዚህ ገጽ ተከታታዮች ‹‹61ሻማዎች›› በሚል ርእስ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን 61ኛ አመት በኦን ላይን ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለማክበር የተነሳሳነው አንድም ጣቢያው የሁላችንም ስለሆነ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ኢቲቪን ስንመለከት አድገናል፡፡ከሚተላለፉት ምክር አዘልና የመዝናኛ ፕሮግራሞች ተጠቅመናል፡፡ አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችንም ቃርመናል፡፡ ጣቢያው በ4 መንግስታት እንደማለፉ ስለ ሁሉም መንግስታት የሚናገረው አለው፡፡
ኢቲቪ የኢትዮጵያን ታሪክ በቪድዮ የያዘ ፣ የወቅቱ ሁኔታዎችን የሚገልጽ መረጃ ያከማቸ እና ብዙዎች የደከሙለት የባለሙያዎች ቤት ነው፡፡ እንደ ብረት የጀገኑ ታታሪ ባለሙያዎች ለፍሬ ያበቃም አንጋፋ ቤት ነው፡፡ ባለፉት 61ዓመታት ኢቲቪን 22 የሥራ መሪዎች መርተውታል፡፡
የዚህን አንጋፋ ጣቢያ ልደት ልናከብር ሀሳብ ስናፈልቅ የእስከዛሬዎቹ የተቋሙ ባለሙያዎች እስከ ህይወት መስዋእትነት የከፈሉበትን ልክ ለማሳየትና የባለሙያዎቹንም እውቅና እና ትጋት በደማቅ ብእር ልንከትበው ፈልገን ነው፡፡
አንድ ተቋም ያለ ብቁ ባለሙያ ተቋም ሊባል አይችልምና እነሆ ይህ ጣቢያ በሺህ የሚቆጠሩ ባለሙያዎች ደክመውለት፤ ሮጠውለት ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ይህን ከግማሽ ክፍለ-ዘመን በላይ የቆየ ጣቢያን እንኳን ለበአለ-ልደቱ አደረሰው እንላለን፡፡
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የሚድያ ባለሙያዎችን እና የሚድያ ተቋማትን ታሪክ በምርምር መልክ እየሰነደ እና ለትውልድ እያስቀመጠ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ኢቲቪም ካሉት ሚድያዎች ከአንጋፋዎቹ ተርታ የሚመደብ እንደመሆኑ የያዛቸው የቪድዮ ሰነዶች ስለ ቀደመችው ኢትዮጵያ በሚያሳምን መልኩ የሚናገሩ ናቸው፡፡ እነዚህ የቆዩ ሰነዶች አዲሱን ትውልድ የማስተማር አቅም ስላላቸው ከወዲሁ ለህዝብ እይታ የሚቀርቡበት ስልት ቢነደፍ ጠቃሚ ነው እንላለን፡፡
የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን አባላት በራሳችን ተነሳሽነት ባለፉት 7 አመታት የሀገራችን አንጋፋ ሚድያዎች አመሰራረት ፤ እድገትና አሁናዊ ሁኔታ ላይ መለስተኛ ዳሰሳዊ ጥናት ስናሰናዳ ቆይተናል፡፡
እንዲሁም በሙያቸው ላይ ጉልህ አሻራ ያኖሩ ባለሙያዎች ወደየት አሉ? ምን የተለየ ነገር አበረከቱ? ስንል የህይወት ታሪካቸውን በብዙ ጥረት ስናሰባስብ ቆይተናል፡፡ 285 ያህሉን የሚድያ ሰዎች ደረጃውን በጠበቀ ጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ ‹‹መዝገበ-አእምሮ ››በሚል ርእስ አሳትመን አስመርቀናል፡፡ የባለሙያዎቹ ታሪክ በአንድ በኩል በከፊል የመስሪያ ቤታቸውን ታሪክ የሚነግር ነው፡፡
እስከዛሬ የህይወት ታሪካቸውን ከጻፍንላቸው ባለሙያዎች ውስጥ 81 ወይም 27 ከመቶ ያህሉ ኢቲቪ በአንድ ወቅት ያገለገሉና እያገለገሉ ያሉ ይገኙበታል፡ይህ ማለት የኢቲቪ ታሪክ በእነዚህ ሰዎች ታሪክ ውስጥ ይገኛል ማለት ነው።ብዙዎች በታሪካቸው ላይ እንዳቀረቡትና ለእኛም በተደጋጋሚ እንዳጫወቱን ኢቲቪን እንደ ቤታቸው ከመቁጠራቸው የተነሳ ለእድገቱ ይቆረቆራሉ፡፡ ምንም ቢሆን ምን የተማርንበት ፤ አይረሴ ትዝታ ያሳለፍንበት ቤት ነው በማለት የኢቲቪን መልካም ቦታ መድረስ እንደሚመኙ ነግረውናል፡፡
ኢቲቪ በ61 አመት ውስጥ ማደግ የሚገባውን ያህል አድጓል ወይ? በዘመናት ውስጥ ያሉት ውጣውረዶች ምንድናቸው ?የሚለውን ወደፊት በጥናት መልክ የምናየው ሆኖ አሁን ግን ግባችን የልደት ሻማ መለኮስ፣ታሪክን ወደ ኃላ መቃኘትና ባለሙያዎችን ማውሳት ይሆናል ፡፡
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽንም ኢቲቪን የሚያስታውሱ የቀድሞ ቪድዮዎችን ለእይታ በማቅረብ ፤ የባለሙያዎችንም ትዝታ ከኢቲቪ አመሰራረት ጋር አንድ ላይ በማድረግ 61ዱን ሻማ ለመለኮስ አስበናል፡፡ በተጨማሪም ለጣቢያው እዚህ መድረስ ጉልህ ሚና የነበራቸውን ሰዎች በደምሳሳው እናነሳለን፡፡
ይህ ማለት ግን እዚህ ባለሙያዎች በተጨማሪም ሌሎች የሉም ለማለት ሳይሆን ለእኛ ለመዝገበ-አእምሮ ፕሮጀክት ፈቃደኛ ሆነው ታሪካቸውን የሰጡንን ብቻ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ለማካተት ወስነናል፡፡ ከዛሬም ጥቅምት 3 2018- ጥቅምት 30 2018 ተከታታይ ጽሁፎችን እያወጣን የኢቲቪን 61ኛ አመት የልደት በአል እናስባለን፡፡
በመዝገበ-አእምሮ ፕሮጀክት ታሪካቸው የተካተተ የኢቲቪ ባለሙያዎች( የነበሩና እያገለገሉ ያሉ)
1.አቶ ሳሙኤል ፈረንጅ
2.ኢንጂነር ገሰሰ አባይ
3. አባባ ተስፋዬ ሣህሉ
4.አቶ ሰሎሞን ተሰማ
5. ተክሉ ታቦር
6. አሳምነው ገብረወልድ
7.እሌኒ መኩርያ
8.ጌታቸው ኃይለማርያም
9.ህሊና ተፈራ
10. ብርቄ ወልደገብርኤል
11. ተሾመ ብርሀኑ ከማል
12. ታዬ በላቸው
13. አማረ አረጋዊ
14. ኢሳያስ ሆርዶፋ
15. ዜናነህ መኮንን
16. ፀጋዬ ኃይሉ ተፈራ
17 .ስለሺ ሽብሩ
18. ሮማን ተገኝ
19 .አስካለ ተስፋዬ
20. አዲስ አለም ሀድጉ
21. እሸቴ አሰፋ
22 ዘሩ በላይ
23.ገነት አየለ
24. መሳይ ወንድሜነህ
25. መቲ ሸዋዬ ይልማ
26. ተገኝ ጃለታ
27. አሸብር ጌትነት
28. አንድነት አማረ
29. እመቤት ደመቀ
30. ዮሀንስ አያሌው
31. ደረጀ ገብረማርያም
32. ጌጡ ተመስገን
33.ፍፁም ጌታቸው
34. መስከረም ጌታቸው
35.መዓዛ መላኩ
36.መኳንንት በርሄ
37. አንተነህ ደግፌ
38. ጀማል አህመድ
39. ከብካብ አስፋው
40. ሺበሺ ዓለማየሁ
41. ዘላለም ቱሉ
42. አስናቀች ፀጋዬ
43. አይናለም ባልቻ
44. ሻምበል አክሊሉ ዘለቀ
45. ሰብለወንጌል አሰፋ
46. ብዙወንድም አገኘሁ
47. ሀብቴ ገመዳ
48 ሰላማዊት ካሳ (ቱሪዝም ሚኒስትር)
49 . ሳሙኤል ፍቅሬ
50.ሀቢባ ፋሪስ
51.መልካሙ ደምሴ
52.መሰለ ገብረህይወት
53.መኮንን ተሾመ ቶሌራ
54.ሚሊዮን ተረፈ
55.ሰሎሜ ታደሠ
56.ሰሎሞን አባተ
57.ሰሎሞን አሞባቸው
58 .ስመኝ ቴሶ
59.በቀለ መንገሻ
60.ትሩፋት ገብረየስ
61.አስፋው ኢዶሳ
62.ኤልያስ ብሩ
63.እናትዓለም መለስ(ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚ/ር)
64.እዮብ እሸቱ
65.ካሣሁን ገርማሞ
66.አይናለም ባልቻ
67 ዓለሙ ቶሎሳ
68.ዓለም ብርሀኔ
69.ዘከሪያ መሀመድ
70.ፍቅሩ ካሳ
71ጌትነት ታደሰ
72 ዶክተር ፍሰሐ ይታገሱ(የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋ/ሥራ አስፈጻሚ
73 የሺጥላ አንተነህ
74 ዮናስ ከበደ
75.ግዛው ዳኜ
76.ፀጋዬ ተስፋሚካኤል
77.ፀሓይ አክሊሉ
78.አይናለም ሀድራ
79.ካሣ አያሌው ካሣ
80.ዘካሪያስ ብርሀኑ
81.ሌዊ ገሠሠ ተሰማ
በዚህ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ቲቪ ሰርተው ጉልህ አሻራ አኑረዋል የምትሏቸውን በቴክኒክ ፤ በጋዜጠኝነት እና በሚድያ አመራርነት ላይ ያሉ ሰዎችን በtewedajemediagmail.com ብትጠቁሙን ስራችንን የተሟላ ለማድረግ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡ ለኢቲቪ ያላችሁንም የእንኳን አደረሰህ መልእክት ማድረስ ትችላላችሁ፡፡

በፍ/ስ/ስ/ሕግ 154 መሠረት የሚሰጡ እግዶች
(Fantahun Delelew. LLB,LLM በፌደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ) 0929101037/0983337690
መግቢያ #ethiopia | እግድ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 154 መሠረት ተጠይቆ ሊታገድ የሚችለው ተከሳሽ የሆነው ወገን ንብረቱን ወይንም ገንዘቡን ሊያሸሽ ይችላል ተብሎ በቃላመሀላ የተደገፈ አቤቱታ በከሳሽ ሲጠየቅ ነው። ፍርድ ቤቱም ይህን ከህግ አግባብ መርምሮ እግዱን የሚሰጥበት አግባብ የሚኖር ሲሆን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን መሥሎ ከታየው እግዱን ላይሰጥ ይችላል። ከዚህ ጋር ተያይዞ እግድ እንዴት ይሰጣል? ከሚታገዱት ንብረቶች ባህርይ እና ከፍ/ስ/ስ/ህጋችን አንጻር እንዴት ይተገበራል? በሚልና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የህግ ግንዛቤ መስጠቱ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ጽሁፍ ቀርቧል። እግድ በፍ/ስ/ህጋችን በ3ኛው መጽሀፍ በምእራፍ አምስት ክፍል ሶስት ላይ የተቀመጠ ሲሆን አጠቃላይ ምእራፍ አምስት ስር የተቀመጡት ድንጋጌዎች በባህርያቸው ከንብረት እግድ ጋር የተያያዙ ናቸው። እነዚህም ከንብረት ማስከበር ፥ ለክርክር ውሳኔ አፈጻጸም ዋስትና ተከሳሽ እንዲያስዝ ፣ ንብረት ማሸግ የመሳሰሉ እንደ ባህሪያቸው በክፍል በክፍል ተቀምጠዋል። እነዚህን አጠቃላይ አያይዞ ለማህበረሰቡ የህግ ግንዛቤ እንዲያድግ አስፈላጊና ወደፊት የሚታሰብበት ሆኖ ነገር ግን ለዚህ ጽሁፍ ስለ እግድ በተመለከተ በዚህ አጭር ጽሁፍ መሠረታዊ ናቸው በማለት ጸሀፊው ያሰባቸውን የህግ ግንዛቤ ለማከል ቀርበ እንጂ ከዚህ በተሻለ በሰፊው ሊቀርብ የሚችል የህግ ክፍል ነው። ያንብቡ ያተርፉበታል።
1. ለእግድ መነሻ ምክንያት
በመግቢያው እንደገለጽነው አንደ ሰው በጉዳዩ ላይ እግድ የሚያሰጠው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ንብረት ወይም ገንዘብ ላይ መብት ወይም ጥቅም ያለው መሆኑን ለፍርድ ቤት በክሱ ላይ ለዚህም ተገቢነት ያላቸውን ማስረጃዎችን በማቅረብ ሲሆን በዚህም የከሳሽ መብትና ጥቅም ያለበት ተከሳሽ ንብረቱን ለማሸሽ ያቀደ የዛተ ያሰበ መሆኑን በቃለመሀላ ወይም በሌላ ማስረጃ ያረጋገጠ እንደሆነ መሆኑን በፍ/ስ/ስ/ ህግ ቁጥር 154 ላይ ተደንግጎ ከተቀመጠው መንፈስ መረዳት የሚቻል ነው።
2. ክስ ስለቀረበበት ማናቸውም ወገን ንብረቱ ወይም ገንዘቡ ሊታገድበት የማይችል ስለመሆኑ
በመጀመሪያ አንድ ክስ ወደ ፍርድ ቤት ሲቀርብ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 222፥223፥229 እና 230 መሠረት ወደ ፍርድ ቤት ዳኛ ዘንድ ከመቅረቡ በፊት ሬጀስትራር ዘንድ በመቀረብ ክሱ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 222 መሠረት የተሟላ ስለመሆኑ ያረጋግጣል።በዚህም መሠረት የክሱን ምክንያት ፣ስልጣኑን፣ተከሳሽ በጉዳዩ የሚያገባው ስለመሆኑ ዝርዝር ነገሮች እንዲሁም ይህን ሊያረጋግጡ የሚችሉ አባሪ ማስረጆች ስለመያያዛቸው እና ስለመረጋገጣቸው በአግባቡ ሌሎች የተዘረዘሩትን ጭምር የተሟሉ ስለመሆኑ በማረጋገጥ ከተሟሉ አስፈላጊውን የምዝገባ ስነስረአት አከናውኖ ወይም ተከናውኖ ወደ ዳኛው እንዲደርስ ይደረጋል። ካልተሟላ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመግለጽ ክሱን ወይም አቤቱታውን መዝግቦ ይመልሳል። በሬጅስትራር የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነትን ያጣ እንደሆነ ሳይታገድ አቤቱታው ይመለሳል። ይሁን እንጂ የክሱ አቤቱታ በሬጅስትራር ተቀባይነትን ያጣ እንደሆነ አቤቱታውን በቅሬታ መልክ ዳኛው ዘንድ በማቅረብ ጉዳዩ እንዲታይለት ማድረግ ይችላል። 232/1/ሀ/ ዳኛው ካመነበት አቤቱታውን እንዲቀበል በማድረግ ክሱ አስፈላጊውን የክስ አቤቱታ አሟልቷል አላሟላም አቤቱታው ያስከስሳል ወይንስ አያስከስስም እንዲሁም ጉዳዩን ተቀብሎ ለማየት ፍርድ ቤቱ ስልጣን አለው ወይንስ የለውም የሚለወን በተመለከተ መርምሮ አጣርቶ ተቀባይነት ያለው እንደሆነ እንደ አግባብነቱ እግድ የሚሰጥ ይሆናል።
3. ዳኛው ክሱ ሲቀርብለት የሚመረምራቸው ጉዳዮች
ጉዳዩን የሚመለከተው ዳኛ ዘንድ ክሱ ሲደርስ ዳኛው በወናነት ሁለት መሠረታዊ ነገሮችን ይመረምራል። አንደኛው ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን አለው ወይንስ የለውም የሚለውን ነጥብ በተመለከተ ነው። ፍርድ ቤት የስረ ነገር ወይም የግዛት ስልጣን ጉዳዩን ለመመልከት ከሌለው መዝገቡን በመዝጋት እግድ ሳይሰጥበት ያሰናብታል ማለት ነው። ሁለተኛው በተመለከተ ክሱ ያስከስሳል ወይንስ የማያስከስስ ነው ወይ የሚለውን በተመለከተ ነው። እንደሚታወቀው የፌደራልም ሆነ የክልሎች የስረ ነገር ስልጣን በአይነት(subject mater) ሆነ በገንዘብ(pecuniary matter) ምን ምን ጉዳዮችን ፍርድ ሊመለከት እንደሚችል የተደነገገ ነው። እነዚህ ሊያስከስሱ የሚችሉ ነገሮች(justiceble matters) የህግ ማእቀፍ ያላቸው ጉዳዩ በህግ ጥበቃ ያደረገላቸው ናቸው። በዚህ መሠረት ሊያስከስስ ይችላል ወይንስ አይችልም የሚለውን በተመለከተ በደንብ ሊመረምር ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር ፍርድ ቤቱ ስልጣን የሌለው ወይም ጉዳዩ የማይስከስስ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ እግድ ሳይሰጥ መዝገቡን በመዝጋት ወደ መዝገብት እንዲመለስ ትእዛዝ ይሰጣል። ከዚህ ባለፈ ፍርድ ቤቱ ስልጣን ያለው እና ነገሩም የሚያስከስስ ከሆነ ንብረቱም ለክርክር መነሻ መሆኑን ካረጋገጠ እግድ በመስጠት ተከሳሽ መልሱን ይዞ እንዲቀርብበት ትእዛዝ ይሰጣል።
4. እግድ ከመስጠቱ በፊት ፍርድ ቤት የክሱን ምክንያት ይመለከታል።
ፍርድ ቤቱ ከሳሽ ያቀረበው ለክስ መነሻ ምክንያት የሆነው ጉዳይ
በህግ የሚሰጠው ህጋዊ መፍትሄ አለው ወይ? ከተከሳሽ ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ አለው ወይ? ተከሳሽ በኀላፊነት ሊጠየቅበት የሚችለበት ምክንያት አለ ወይ? ለዚህ አስረጂ የሆኑ አግባብነት(relevant) እና አሳማኝ(admissible) የሆኑ ማስረጃዎች ተረጋግጠው ቀርበዋል ወይ በማለት ይመረምራል። ፍርድ ቤቱም የክስ ምክንያት ያለው መሆኑን ሲረዳ በቀረበለት የእግድ አቤቱታ ላይ አስፈላጊውን ምርመራ ያደርጋል።
5. ንብረት ማሳገድ(154) ከንብረት ማስከበር(151) የሚለይበት መሠረታዊ ምክንያት
በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 154 መሠረት ንብረት ማሳገድ ማለት ለክርክር መነሻ የሆነውን ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ክርክሩ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ባለበት እንዲቆይ ሲሆን ንብረት ማስከበር ማለት በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 151 መሠረት ክርክር የተነሳበትን ንብረት ተከሳሹ ባላቀረበ ጊዜ እንዲያቀርብ ወይም ለፍርድ አፈጻጸም ይሆን ዘንድ ተከሳሹ ተመጣጣኝ የሆነ ንብረቱን እንዲያሲዝ የሚጠየቅበት ነው። ይሁን እንጂ በንብረት ማስከበር ደረጃ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 404 በተዘረዘሩት መሠረት የፍርድ ባለእዳው ኑሮውን ፥ቤተሰቡን ሊያስተዳደር የሚችልባቸው መሠረታዊ የሆኑ ነገሮች ሊከበሩ የማይችሉ ሲሆን ደመወዝ በተመለከተም ከ1/3ኛ በላይ ሊከበር አይችልም።
6.እግድ ሳይሰጥ ቢዘገይ ጉዳት የማያስከትል ከሆነ የተከሳሽነ/ ተጠረ/ ን አስተያየት መስማት አስፈላጊ መሆኑ
ከሳሽ/አመልካች/ እግድ እንዲሰጠው ስላመለከተ ብቻ ወዲያው እግድ ላይሰጥ ይችላል።እግድ ሳይሰጥ መዘግየቱ ጉዳት የማያስከትል መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳው እንደሆነ ትእዛዝ ከመሥጠቱ በፊት ለተከሳሽ እንዲያውቀው በማድረግ አስተያየቱን እንዲሰጥበት ይደረጋል። ከዚያም ፍርድ ቤቱ በእግዱ ጥያቄ ላይ አስፈላጊውን ትእዛዝ ይሰጣል። ይሀውም እግድ ሊሰጥበት ወይም ላይሰጥበት የሚችል ይሆናል።
7. በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 155 መሠረት ከሂሳባ ነክ ጋር የተያያዙ እግድ ጥያቄዎች ሲሆኑ
ከሂሳብ ነክ ጋ በተመለከተ በተያያዘ የእግድ ትእዛዞች በከሳሽ ሲጠየቁ ፍርድ ቤቱ አስፈላጊ የሆነ ዋስትና ሊጠይቅ የሚችል ሲሆን አስፈላጊ የሚላቸውን ትእዛዞች ጭምር ሊሰጥ ይችላል።
8. የተሰጠው እግድ ንብረት ቢቆይ ሊበላሽ የሚችል ቢሆንስ
በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 160 መሠረት ድንጋጌ ላይ እንደተቀመጠው የታገደው ንብረት ሊበላሽ የሚችል ከሆነ ከፍርድ በፊት መሸጡ የግድ ወየም የተሻለ ሲሆን በዚህ መልክ ተሽጦ በገንዘብ ሊቀየር እንደሚችል ተደንግጓል። ይህ የታገዱ ሊበላሹ የሚችሉ ንብረቶችን እንዳይበላሹ የሚጠብቅ የህግ ድንጋጌ ነው።
9. እግድ ሲሰጥ ምን ጉዳዮችን መመልከት አለበት?
ፍርድ ቤቱ እግድ የሚሰጥበት ንብረት ወይም ገንዘብ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዳይ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አለበት። ባይታገድ ኖሮ ንብረቱ የሚሸሽ ፣ የሚጠፋ፣ የሚበላሽ ስለመሆኑ መታወቅ አለበት። ይህንን በቃለመሀላ ወይም በማስረጃ ሊረጋገጥ የሚችል ሲሆን ፍርድ ቤቱ በራሱ ሊያረጋግጥ የሚችልባቸው የምርመራ ሂደቶች ማጣራት ህግ የሚከለክለው አይደለም። ይህም የሚሆነው አላግባብ የዜጎች የሶስተኛ ወገኖች የንብረት ባለቤትነት መብት፣የንግድ ስራ እንቅስቃሴ እና ተያያዥ መብቶች አላግባብ እንዳይታገድ ነው። የማይመለስ ወይም የማይተካ ጉዳት የሚደርስ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አለበት። ሌላው ክርክር የተነሳበትን ንብረት ተከሳሽ ሊያሸሸው የሚችለው ስለመሆኑና እያሸሸው ስለመሆኑ መረጋገጥ አለበት። ከሳሽ የሚያረጋግጠው ቃለመሀላ ለከሳሽ ማስረጃ እንጂ እግድ እንዲሰጠው መደምደሚያነት የሚያሰጥ አይደለም። ስለዚህ ከሳሽ ለክርክር መነሻ የሆነው ንብረት መታገዱ ለካሳሽ የዳኝነት መፍትሄ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሲሆን እና ከላይ የተገለጹት ጉዳዮች ሲረጋገጡ ፍርድ ቤት እግድ ይሰጥበታል።
10. እግድ ከፍ ያለ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መሆኑ
እግድ ሲሰጥ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያስፈልገው የሚገባው ነው። እኛ ሀገር በፍ/ስ/ስ/ህጎቻችን የሚተገበሩበት ደንብ ወይም መመሪያ( rule) አለመኖሩ በክርከሩ አይነትና ባህርይ እንዴት ተደርጎ መታገድ እንዳለበት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይገጥሙናል። ለዚህም በጉዳዮች አይነት እንዴት ሊፈጸም እንደሚችል መመሪያ አለመኖሩ ወጥነት ያለው አተገባበር እንዳይኖር እና የፍትህ ስረአቱ ተገማችነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሲፈጥር ይታያል። ለምሳሌ የህንድ ሀገር የፍ/ስ/ስ/ህግን ስንመለከት ድንጋጌዎቹ የሚተገበሩበት መመሪያ እና አሰራር ያስቀመጡ ሲሆን እግድ ሊሰጡባቸው የሚገባቸው የጉዳዮች አይነቶች ለይቶ በመመደብ እነዚህም እንዴት እንደሚፈጸሙ መመሪያ(rules) ወጥቶላቸዋል::እነዚህም የጉዳይ አይነቶች ለግንዛቤ ያህል ይረዳ ዘንድ ወደ አስር አይነቶች የተቀመጡ ሲሆን እነዚህም 1. Temporary injuction 2. Interlocutery injuction 3. preleminery injuction 4. permanent injection 5. Mandatory injection 6. Prohibatory injuction 7. Quia Timet injection 8. Mareva injuction 9. Anton piller injection 10. Dynamic injection በመባል የሚታወቁ ናቸው። እነዚህ የጉዳዮች አይነት ከባህሪያቸው አይነት የተነሳ ተመድበው የተከፋፈሉ ሲሆን እነዚህ አይነቶች እግዶች እያንዳንዳቸው የፍ/ስ/ስ/ህጋቸውን መሠረት ተደርጎ የሚተገበሩበት መመሪያዎች ወይም አሰራሮች (rules) አሉአቸው። ስለዚህ በእኛም ሀገር የህግ አውጪ አካላት ስልጣን የተሠጠው ክፍል ወይም ስልጣን ሊሰጣው የሚገባው ነገር ግን ያልተሰጠው ለምሳሌ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ውሳኔ በተጨማሪ በፍ/ስ/ስ/ህጎች ላይ ለአተገባበር መመሪያ የማውጣት ስልጣን ተሰጥቶት ይህን በማውጣት ጉዳዮች እንደ ባህሪያቸው እና አይነታቸው ልክ መመሪያ በማውጣት እንዲተገበር ማደረጉ ለፍትህ ጠያቂዎችም ሆነ ለፍትህ ስረአቱ ትልቅ ጉልህ ድርሻ ያለው ነው። በእኛ ሀገር የጉዳዩ አይነት በተመለከተ በፍ/ስ/ስ/ህጉ ህጉ 154 እና 155 ላይ መገንዘብ እንደሚቻለው የጉዳዮችን ባህሪ፣ ንብረት፣ሊበላሹ የሚችሉ፣ሊጠፉ የሚችሉ፣ከውል ጋ በተያያዘ እንዳይፈርሱ ሌሎችንም ቢሆን ያልጠቀስኳቸው እግድ የሚሰጠጥባቸው ጉዳዮች በማለት ለመግለጽ ሞከረ እንጂ በክርክር ሂደት ብዙ አይነት ጉዳዮች እንደ ባህሪያቸው የሚኖሩ ሲሆን በዚህ ልክ ለአሰራር መመሪያ የወጣላቸው አለመሆኑ ለእግድ አተገባበር ላይ በስራ አፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ይኖራሉ። ለዚህ መፍትሄው በመመሪያ እግድ ሊተላለፍብቻው የሚችሉ የጉዳይ አይነቶችን በመለየት እነዚህም እንዴት እንደሚታገዱ ግልጽ መመሪያ ወይም አሰራር በማውጣት ፍትህ ተፈጻሚ ሊሆን ያስፈልጋል። ለምሳሌ አንድ ማሳ ላይ የሚገኝ ሰብል ምርቱ የደረሰም ሆነ ያልደረሰ ሰብል በተመለከተ ክርክር ተነስቶበት እግድ ቢጠየቅበት እንዴት እግዱ እንደሚሰጥ ፣ እንደሚተገበር ተገቢ የሆነ መመሪያ ወይም አሰራር መኖሩ ለዳኛውም ስራውን በቀላሉ እንዲሰራ የሚረዳው ሲሆን አተገባበሩም ወጥ ተገማች ፍትሀዊ ይሆናል። በመሆነም ከዚህ አንጻር የፍ/ስ/ስ/ህጎች አተገባበር ላይ ተቢውን መመሪያ እና አሰራር በማጎልበት ከሌሎችም ሀገር ተገቢውን ልምድ በመውሰድ ለፍትህ ስረአት ማደግ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ግድ ይላል።
ከዚህ አንጻር ለሚቀርቡ የእግድ ጥያቄዎች ትእዛዝ ሲሰጥ አስፈላጊውን የሙያ ጥንቃቄ የተከራካሪዎችን የህግ የበላይነትን መብት ከመጠበቅም አንጻር አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢነት ያለው ነው።
11. ሊበላሹ በሚችሉ ንብረቶች(ምግቦች ፣ አትክልት የመሳሰሉት) ላይ የእሸጋ እግድ ሊሰጥ የማይገባ መሆኑ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 173 መሠረት ለማሸግ ትእዛዝ የማይወጣባቸው ተዘርዝረው የተቀመጡ ሲሆን እነዚህም ቢታሸጉ ሊበላሹ ሊበሰብሱ የሚችሉ ነገሮች እና ፍርድ ቤት እንዳይታሸግ ትእዛዝ የሰጠባቸው ነገሮች ናቸው። ይሁን እንጂ ከዚህ በቀር በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 170 171 172 መሠረት የንብረቶች ዝርዝር ተቆጥረው ሊታሸግባቸው እንደሚችል በፍርድ ቤት ትእዛዝ ሊሰጥ እንደሚችል ተደንግጓል።
12. የተሰጠ እግድ ሊከበር የሚገባ መሆኑ(156) እና በተከሳሽ የሚቀርብ የእግድ ይነሳልኝ ቅሬታ በተመለከተ
ተከሳሽ የተሰጠን እግድ ያላከበረ፣የጣሰ እንደሆነ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 156 መሠረት እና በወንጀል ህጉ መሠረት የወንጀል ተጠያቂ ኃላፊነትን የሚያስከትል በመሆኑ ማክበር ግዴታ ነው ይሁን እንጂ በእግዱ ላይ ቅሬታ ካለበት እግድ እንዲነሳለት ከበቂ ምክንያት ጋር አቤቱታ የማቅረብ መብት ያለው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ቅሬታውን በመመልከት የከሳሽን አስተያየት በማድመጥ እግዱን ሊያነሳው፣ሊያሻሽለው ወይም ውድቅ ሊያደርገው ይችላል።
13. እግድ ክስ ሳይቀርብ ይቻላል?
አንዳንድ ጊዜ እግድ ለማሳገድ ጊዜ የማይጠይቁ ጉዳዮች ያሉ ሲሆን ክስ እስከሚዘጋጅ ድረስ ጊዜ የሚጠይቅ ሲሆን ክስ ማዘጋጀቱ ግድ ሆኖ ቢጠበቅ ለክርክር መነሻ የሆነው ንብረት ሊሸሽ የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል። ለምሳሌ የባንክ ገንዘብ ቢሆን በቶሎ ወደ ሌላ ግለሰብ አካል በማስተላለፍ ገንዘቡ ሊሸሽ ይችላል። ስለዚህ ይህን ለመከላከል ያስችል ዘንድ መብት ሊፈጥር ማስረጃ በመያዝ ክስ እስኪዘጋጅ ድረስ ይህንን ንብረት ባለበት ያለ ክስ ማሳገድ እንደሚቻል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 191402 ቅጽ 25 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
14. ሲጠቃለል
ስለሆነም እግድን በተመለከተ ይህንን በአጭሩ ለማስገንዘብ ያህል አነሳን እንጂ የፍ/ስ/ስ/ ህጋችን ሶስተኛ መጽሀፍ ምእራፍ አምስት በመሉ የሚያነሳው ቃላቱ እና ሀሳቡ በተወሰነ መልክ ቢለያይም ከእግድ ጋር የሚያይዝ ባህርያት አሉት። ይህም ከ147_176 ባለው ውስጥ ተደንግገው የተቀመጡ ናቸው። እኛም ይጠቅም ዘንድ ብለን ይህን አቀረብን እንጂ በሰፊው ተተንትነው ሊጻፉ የሚገባቸው ናቸው። በዚህ ጹሁፍ ግን ዋና ጉዳያችን ከእግድ ጋር በተያያዘ ሲሆን ወደፊት ከዚህ በበለጠ በመጻፍ ለማህበረሰቡ ይደርስ ዘንድ ያብቃን እንላለን። ለመደምደሚያ ለማውሳት ያህል ከእግድ ጋር የተያያዘ ሰፊ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 154 እና ተከታይ ህጎች መሠረት ሲሰጥ ከሳሽ ተከሳሽን በኃላፊነት ለመጠየቅ የሚያስችል መብት ወይም ጥቅም ያለው ስለመሆኑ በማስረጃ የተደገፈ በመቅረብ ፍርድ ቤቱም ተገቢውን ምርመራ ካደረገ በኋላ እግድ የሚሰጥበት ሲሆን በዚህ ህግና እና ሌሎች ተገቢነት ባላቸው ህጎች መሠረት አስፈላጊውን ያላሟላ እንደሆነ እግድ የሚሰጥበት አይደለም።ዋናው ነጥብ ለክርክር መነሻ የሆነውን ንብረት ተከሳሽ ሊያሸሸው፣ሊያጠፋው፣ የሚችል መሆኑ የሚረጋገጥበት መንገድ በፍ/ስ/ስ/ህጉ 154 መሠረት እንደተመለከተው ከተገኘ እግድ የሚሰጥ ሲሆን ተከሳሽም እግዱ እንዲነሳለት የመጠየቅ መብት አለው። ንብረት የማሸሽ ባህሪይ ፈጣን ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ከሳሽ ተጨባጭ ማስረጃ ካለው ክስ እስኪ መሠረት ድረስ ጊዜ የማይሰጥ ከሆነ ክስ እስከሚዘጋጅ ድረስ ባለው አሳማኝ ማስረጃ ከሳሽ ክርክር የተነሳበትን ንብረት ማሳገድ እንደሚቻል በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።እግድ በባህሪው የሰወችን ንብረት እንደፈለጉ ለማንቀሳቀስ ፣ለመሸጥ፣ ለመለወጥ፣ለማስተላለፍ መብትን የሚያግድ ሲሆን ከጉዳዮች አይነትና ባህሪም አንጻር ልዩ የሆነ የአተገባበር መመሪያ ወይም አሰራር ያልወጣ ያልተዘረጋ በመሆኑ እግድ ሲሰጥ ሲነሱ አተገባበሩ ላይ ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ማድረጉ አስፈላጊ ሲሆን ይህንን ህጋችን ወጥነትእና ፍትሀዊ ዳኝነት ትእዛዝ ለመስጠት አጋዥ መመሪያዎች እና አሰራሮች ቢዘረጉ ቢወጡ ለፍትህ ስረአታችን መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ የሚኖራቸው ስለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም።
ለበለጠ የህግ ጉዳይ
https://t.me/Fantahunlawye...
https://www.youtube.com/@w...
https://www.facebook.com

10 months ago
የሙፍቲን የደግነትና የሰብአዊነት ሁለንተናዊ ሌጋሲ ለማስቀጠል አራት ፕሮጀክቶች በሂደት ላይ ናቸው፦
1- የሀይማኖት ትምህሮት ማዕከል
ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ ያለውን 8000 ካሬ ሜትር ያህል ቦታቸውን ሙፍቲ ለመስጊድና ለዲን ትምለህርት ማዕከልነት "ወቅፍ" ስላደረጉ የ500 ሚሊየን ብር ግኖባታ ለማሳረፍ ዲዛየኑ ተሠርቶ አልቋል። በአላህ ፈቃድ ወደፈንዶ ሬይዚንግና ግንባታ እንቅሶቃሴ በቅርቡ ይገባል።
2- የቁርአን ተፍሲር
ሙሉውን ቁርአን የፈሰሩበት ሥራ ኤዲቲንግና ሌሎች ሥራዎቹ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ለህዝብ ይለቀቃል።
በተጨማሪም ይኸንኑ ሥራቸውን በመጽሀፍ መልክ የማዘጋጀቱ ተግባር በሂደት ላይ ነው።
3- የህይወት ታሪክ ዝግጅት
የህይወት ታሪካቸውን በአማርኛና በዐረብኛ ለማዘጋጀት የታቀደ ሲሆን የአማርኛው ቅጅ ሥራ በመገባደድ ላይ በመሆኑ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ወደ ህትመት ይገባል። ኢንሻአላሀ።
የአረብኛው ቅጅም እርሱን ተከትሎ ይታተማል።
4- ሀገር አቀፍ የምስጋና ቀን
የሙፍቲን ክብርና የዘመናት አገልግሎት የሚመጥን ሀገር አቀፍ የምስጋና ቀን ከረመዳን በፊት ተዘጋጅቶ ሙፍቲን ለማመስገን ታቅዶ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን የርሳቸው ማረፍ በዝግጅት ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ቢኖረውም ከዳር ለማድረስ በአዘጋጆቹ በኩል ቁርጥ ውሳኔ ያለ በመሆኑ ዕወን ይሆን ዘንድ ጥረቶች የሚቀጥሉ ይሆናል።
ሙፍቲ ለነዚህ ፕሮጀክቶች ይሁንታ (ኢጃዛ) የሰጡ ሲሆን የቁርአን ተፍሲራቸው ጋር የተያያዙ ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ከማረፋቸው አሥር ቀናት ቀደም ብሎ አይተው ተደስተዋል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ ዕውን ይሆኑ ዘንድ የሁሉም ወገን ትብብር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ፕሮጀክቶችን በመምራት ላይ ያለው ኮሚቴ በጽኑ ያምናል።
ዑስታዝ ሀሰን ታጁ

''የሌላ ሀገር ዜግነት መቀበል ወራዳነት ነው'' ኮሎኔል አብዲሳ አጋ
ህይወታቸው ካለፈ ነገ ጥቅምት 3 ድፍን 41 ዓመት የሚሞላቸውን ኮሎኔል አብዲሳ አጋን መዘከር ቀጥለናል፡ በወለጋ የተወለደው አብዲሳ የኢትዮጲያን ጦር የተቀላቀለው በ14 አመቱ ሲሆን ጣልያን ኢትዮጲያን ስትወር አገሩን ለመከላከል በሚደረግ ውጊያ ላይ መሳተፍ ጀመረ። እጅግ ዘመናዊ መሳሪያዎች ከታጠቀው የጣልያን ጦር ጋር በሚደረገው ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሱማሊያ በኩል ወደ ሲሲሊ ተወስዶ በጣልያን አገር የጦር እስረኛ ተደረገ። በእስር ቤት ጠባዎች ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት አብዲሳ እዛው ታስሮ የሚገኝ ሁሊዮ የተባለ የዩጎዝላቪያ ምርኮኛ በጋራ እቅድ በማውጣት ከእስር ቤት ማምለጥ ቻለ። ከእስር ካመለጡ በኋላ ከፋሺስት ጣልያን ወታደሮች በመደበቅ እና በመሸሽ ፋንታ በአብዲሳ መሪነት እና እቅድ አውጪነት በሌሊት ታስረው ወደነበረበት እስር ቤት ተመልሰው ጠባቂዎቹ ላይ ጥቃት በመፈጸም የታሰሩትን እስረኞች በሙሉ ነጻ በማውጣት የኢትዮጲያውያንን ጀግንነት በአድዋ ብቻ ሳይሆን በጣልያን ምድርም ያስመሰከረ ድንቅ ተዋጊ ነበር።
የአብዲሳ ጀግንነት በዚህ አላበቃም ከእስር ቤት ያስመለጧቸውን ሰዎች በማሰባሰብ የራሱን ጦር ካደራጀ በኋላ ጣልያኖችን በገዛ አገራቸው ያንቆራጥጣቸው ገባ። ከአድዋ ጀምሮ የኢትዮጲያውያንን ወኔ የተረዱት ጣልያኖች የአብዲሳን ጦር በፍርሃት ያዩ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች ከጣልያን ጦር ጋር በመዋጋት ብዙ ድሎችን እያስመዘገበ ነበር። ቆራጥነቱን የተረዱት ጣልያኖች የሚያረጉት ግራ ቢገባቸው ከበርካታ ስጦታዎች ጋር ጦሩን ይዞ የጣልያንን ሰራዊት እንዲቀላቀል መማጸን ጀምረው ነበር። የሌላ ሀገር ዜግነት መቀበል ወራዳነት ነው በማለት ለፋሺስት ጦር መዋጋት አገር መክዳት እንደሆነ አስረግጦ የተናገረው አብዲሳ ትግሉን አፋፍሞ በቀጠለበት ወቅት የሁለተኛው የአለም ጦርነት ተቀሰቀሰ።
የተባበሩት የአሜሪካ እና እንግሊዝ መንግስታት ከጀርመን ጋር ያበረችውን ጣልያንን እየተዋጉ በነበረ ሰዓት ስለ አብዲሳ ዝና ከሰሙ በኋላ ለጦሩ የሚገባውን ድጋፍ በማድረግ የፋሺስት ስርዓቱን ለማዳከም ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ሆኗቸው ነበር። በድጋፉ በመጠናከር ፋሺስቱን ሰራዊት ማርበድበድ የቀጠለው አብዲሳ የጣልያን ጦር ተሸንፎ ዋና ከተማዋ ሮም በአሜሪካን እና እንግሊዝ የሚመራ ጦር እጅ ስር ከወደቀች በኋላ የሚመራቸውን ከተለያዩ አገር የወጡ ወታደሮች በሙሉ ክንዳቸው ላይ የኢትዮጲያን ባንዲራ እንዲያስሩ በማድረግ የሃገሩን ባንዲራ እያውለበለበ ሮም ከተማ ሲገባ በአለም አቀፉ ህብረት ጦር ትልቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር። ከዛም በኋላ ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ በመሆን ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታ የጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር።
ምንጭ:- “አብዲሳ አጋ በኢጣሊያ በረሃዎች የተሰኝ መጽሀፍ
Via Muktarovich usmanova

ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እናቶች የሚወክል የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ
#ethiopia | እናት ባንክ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እናቶች የሚወክል "እማዬ" የተሰኘ ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ በፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት አካባቢ የሴቶችን ጉዳይ ርእሰ ጉዳይ እንዲሆን ባደረገው በቀድሞው የኢትዮጵያ ሬዲዮ በነበረበት ህንጻ ላይ በደማቅ ሥነ ስርዓት በዛሬው እለት ተመርቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ቅርንጫፉ ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ሰዎች ስለእናታቸው የሚሰማችውን የሚጽፉበት መዝገብ የተዘጋጀለት ፣እናቶች በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸው ባህላዊ ቁሳቁሶች፣ ስለእናቶች የተጻፉ መጽሀፍት የሚገኝበት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ መሠራቱ በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።
እናት ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ በተለየ መልኩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበትና ለሁሉም ህብረተሰብ የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ታሳቢ በማድረግ ከዛሬ 13 አመት በፊት የተቋቋመ ሲሆን የሴቶችን የፋይናንስ አካታችነትና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎት መሰረት በማድረግ በመላ አገሪቱ 218 ቅርንጫፎችን በመክፈት እንዲሁም በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት በብቁና በተደራጀ የሰው ኃይል ቀልጣፋና ፈጣን የሆነ አገልግሎት በመሰጠት በባንክ ኢንዱስትሪው አበረታች ውጤት በማስመዝገብ ተወዳዳሪነቱን ከፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

እናት ባንክ “እማዬ” የተሰኘዉን ቅርንጫፉን በዛሬዉ እለት አስመረቀ።
#fastmereja I እናት ባንክ በዛሬዉ እለት ጥቅምት 1/2/2018 በአዲስ አበባ በፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሀዉልት አካባቢ የቀድሞዉ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ህንፃ በልዩ ሁኔታ አስመርቋል።
ቅርንጫፉ ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ሰዎች ስለ እናቶቻቸው የሚሰማችውን የሚጽፉበት መዝገብ የተዘጋጀለት እናቶች በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸው ባህላዊ ቁሳቁሶች ስለእናቶች የተጻፉ መጽህፍቶች የሚገኝበት እንደሆነ ተገልጿል።
እናት ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በአስኮ እካባቢ የሚገኘውን የህዝብ ቤተመጽሀፍት ከ3ዐ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቅ መልኩ አድሶ ለማስረከብ ዝግጁ ማድረጉን ተገልፀዋል።
ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን ድረሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በተጨማሪም የዜጎችን የፈጠራ ሥራ በመደገፍ ረገድ ሚናውን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ፣የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ወጣቶችን ሥራ ንድፈ ሀሳብ ወደ ተግባር በመቀየር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡
#ቢዝነስ

11 months ago
ቤድሮስ ስቫጅያን በኢትዮጵያውያን አጠራር ጴጥሮስ ስቫጅያን
የግርማዊ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት የወርቅና የጌጥ ዕቃ አቅራቢ
(አበበ ሙሉ)
#ethiopia | አርመናውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው በሰፊው የታወቀ ነው፡፡ አርመናውያን በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በንጉሱ ዘመን በብዙ ዘርፍ ውስጥ ድርሻ ነበራቸው፡፡
ከእነዚያ ውስጥ ቤድሮስ ስቫጅያን ወይም ጴጥሮስ ስቫጅያን ለተለያዩ አገራት መሪዎች የሚሰጡ ስጦታዎች ላይ ድርሻ ነበረው፤ ቤድሮስ ስቫጅያን ለቤተ መንግስት የወርቅና የጌጥ ዕቃ አቅራቢ በመሆን ለመንግስታት የሚሰጡ ስጦታዎችን፣ እውቅናዎችን ኒሻኖችን እና ሜዳሊያዎችን በማቅረብ ተጠቃሽ ነው፡፡
ስጦታ በተለይም ከሌላ አገርና ባህል ለመጣ ሰው ሲበረከት አገርን ማስተዋወቂያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ስጦታ ዓላማውም ሆነ ግቡ ግንኙነትን ማጠናከር ነው፡፡ በዚህ ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ ስጦታ ዘመናትን ተሻግሮ አይረሴነትን ይፈጥራል፡፡
ስጦታ ወዳጅነትን መግለጫና የግንኙነት ማጠናከሪያ መሳሪያዎች ከሆኑት መንገዶች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን በራስ ተነሳሽነት ወይም ከሌላ ወገን ለተበረከቱ ስጦታዎች በምላሽነት የሚሰጡ ሲሆን የሚበረከቱት ስጦታዎች ዓይነትና መጠን አብዛኛውን ጊዜ የስጦታውን አበርካች ባህል፣ ልማድና የአኗኗር ዘይቤን በሚያንጸባርቅ መልኩ የሚከናወኑ ናቸው፡፡ የስጦታዎች ዓይነት በሚመረጥበት ወቅት የራስን ባህል፣ ሃይማኖትና ማህበራዊ እሴቶች ብቻ እንዲያንጸባርቅ ከማድረግ አልፎ የተቀባዩን አገር ባህልና ሃይማኖት ከግምት ውስጥ ያስገባ ጭምር መሆን ይኖርበታል፡፡
ከቤድሮስ ስራዎች አንዱ የሆነውና በ1957 ንግሥት ኤልሳቤጥ አገራችንን ሊጎበኙ በመጡበት ወቅት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለመታሰቢያ የተሰጣቸው ከወርቅ የተሰራ ትሪ ዛሬ ላይ በባኪንግሃም ቤተ መንግስት ውስጥ ለጎብኝዎች ይታያል፡፡
ከኢትዮጵያ ምድር በተገኘና እጅግ ጥራት ባለው 22 ካራት ወርቅ የተሰራው ይህ ትልቅ ትሪ አስራ አራት (14) ኪሎ ክብደት ያለው ነው፤ቤድሮስ ከወርቅ፣ ከብርና ከነሐስ የተሰሩ የተለያዩ ስጦታዎችን በመስራትና ለስጦታ የሚሆኑ የእደ ጥበብ ውጤቶችን በማቅረብ ተጠቃሽ ነበር፡፡ ጴጥሮስ ሳቫጅያን አጼ ኃይለ ስላሴ ለሙያው እውቅና የሰጡት ወርቅና ብር አንጥረኛ ነበር፡፡ ኮንትራት እየወሰደ የመከላከያና ፖሊስ ሠራዊት የማዕረግ ምልክቶች፣ ሜዳልያዎች፣ የቀበቶ መቆለፊያና የተለያዩ ጌጣጌጦችን ይሠራ ነበር፡፡ በጥንት ዘመን የቤተ መንግስት አንጥረኛ፣ የቤተ መንግስት ካባ ሰፊና ሙካሽ ጠላፊ ባለሙያዎች በስፋት ይታወቁ ነበር፡፡
ጴጥሮስ ሳቫጂያን የተወለዱት በኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ የሳቫጅያን ቤተሰብ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በአጼ ምኒልክ ዘመን ንጉሱ የተለያዩ ባለሙያ አርመኖች እንዲመጡ በፈቀዱ ጊዜ ነበር፡፡
የጴጥሮስ ሳቫጅያን አጎት በዚያን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የቤተ መንግስት አትክልተኛ ሆነው ያገለግሉ ነበር፡፡ የጴጥሮስ ሳቫጅያን አባት አቨዲ ሳቫጅያን ይባላሉ፡፡
የሳቫጅያን ቤተሰቦች በኃላ ላይ በተለያዩ ስራዎች በመሰማራት ታዋቂና ባለጸጋ ሆነው ነበር፡፡ የጴጥሮስ ሳቫጅያን አባት የአስኮ ጫማ ፋብሪካን የመሰረቱና ባለቤትም ነበሩ፡፡ ከአቨዲ ሳቫጅያን ከሚወለዱት ልጆች አንዱ የሆኑት ጴጥሮስ ሳቫጅያን በወርቅና ብር ስራ ከሰለጠኑ በኃላ ዋነኛ ስራ አድርገው የተሰማሩትም በዚህ መስክ ነበር፡፡ እንደ እርሳቸው ሁሉ በዚህ ሙያ የተሰማሩ ብዙ አርመናውያን ነበሩ፡፡ በ1950ዎቹ ሁሉም የፒያሳ ወርቅና ብር ሰሪ መደብር ባለቤቶች አርመናውያን የሆኑበት ምክንያት ይህ ነበር፡፡ አርመናውያን በአገራችን የአንጥረኝነት ሙያ እንዲያድግና እንዲስፋፋ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
ጴጥሮስ ሳቫጅያን በዋነኛነት የሚታወቁበት ስራ በህትመት ቅርጽ እያወጡ ሜዳሊያዎችን፣ ኒሻኖችን፣ ለወታደራዊ ዩኒፎርም የሚያገለግሉ የልብስ ቁልፎችን ማምረት ነበር፡፡ ማህተም መቅረጽን ጨምሮ ለቤተ መንግስት በጣም ብዙ ነገሮችን እየሰሩ ያቀርቡ ነበር፡፡ በዘመኑ ለስራው ጨረታ የሚወዳደር ብዙ ባለሙያ አልነበረም፡፡ የጴጥሮስ ሳቫጅያን ኢንዱስትሪ በ1950ዎቹ በጣም ታዋቂና ብዙ ስራዎችን የሰራ ተቋም ነበር፡፡
የትራፊክ ፖሊሶች ፊሽካ፣ ለወታደር የክብር አልባሳት የሚሆኑ የተለያዩ የማዕረግ ምልክቶችና ቁልፎች፣ ለቤተ መንግስት መገልገያ የሚሆኑ ሰሃን፣ ትሪና መሰል ቁሳቁስ በሳቫጅያን ድርጅት ይሰራ ነበር፡፡ የንጉስ ኃይለሥላሴ 80ኛ የልደት በዓል ሲከበር ግለሰቦችና ተቋማት ለንጉሰ ነገስቱ ስጦታ ለማበርከት ከወርቅና ከብር ያሰሯቸው በርካታ የስጦታ ዕቃዎች በሳቫጂያን ተሰርተዋል፡፡
በዘመኑ እንዲህ ዓይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመስራት የሚታወቁት ጴጥሮስ ሳቫጅያንና የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጥይት ፋብሪካ ብቻ ነበሩ፡፡ በሳቫጅያ ድርጅት ለሚመረቱ ዕቃዎች ዲዛይን የሚሰሩ አንድ ጣሊያናዊ ነበሩ፡፡
በንጉሥ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ለነበረው የፖሊስ ሠራዊት የክብር አልባሳት የብረታ ብረት ጌጣጌጦችን በመስራት የሚታወቀው ይህ ድርጅት በብረት የልብስ ቁልፍ ምርቶቹ በውስጠኛው ክፍልም “ሳቫጅያን አዲስ አበባ” የሚል መለያ ጽሁፍ ያትም ስለነበር ምርቶቹ እጁ የገባ ሁሉ ለይቶ ያውቃቸዋል፡፡
የጴጥሮስ ሳቫጅያን መኖሪያ ቤት አሁን በቦሌ አካባቢ የብራዚል ኤምባሲ ሆኖ እያገለገለ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ቤት ነበር፡፡
በሰሯቸው የስጦታ እቃዎችና ጌጣጌጦች በአገራት መካከል አይረሴትን የፈጠሩት፣ ግንኙነቱ እንዲዳብርና እንዲጠናከር ትልቅ ድርሻ ነበራቸው፡፡ እርሳቸውም በሰሩት ዘመን ተሻጋሪ ስራ ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡
በአገሪቱ የሥርዓት ለውጥ ከተካሄደ በኃላ ጴጥሮስ ሳቫጅያንም እንደ ሌሎች ባለሃብቶች ጉዳት አግኝቷቸዋል፡፡ በወቅቱ ልጆቻቸው በውጭ አገራት ነበሩ፡፡ አንዷ ልጃቸው ባለችበት ሀገር ትዳር ስትመሰርት አባቷ እንዲገኙ ብትጋብዛቸውም ከኢትዮጵያ እንዲወጡ አልተፈቀደላቸውም፡፡ ወደ ውጭ እንዳይሄዱ ከተከለከሉ በኃላ በድሬዳዋ በኩል ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ ጉዞ ጀምረው ከዛ በኃላ የት እንደደረሱ ሳይታወቅ እንደወጡ እንደቀሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡
ድርጅታቸውም በኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራዎች ድርጅት ስር እንዲሆን ተደረገ፡፡
ከዓመታት በኃላ የጴጥሮስ ሳቫጅያን ልጆች በአዋጅ ያልተወረሰው የአባታቸውን ቤት ሲያስመልሱ የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅትም ቤቱን ለቆ ወጣ፡፡ እንዲህ ዓይነት ታሪኮችን ያሳለፈው ተቋም በመጨረሻ ለወርቅ አምራቾች ማህበር መሸጡ ታውቋል፡፡
(ለዚህ ዝግጅት በምንጭነት በቤጥሮስ ሳቫጂያን ስም የተከፈተውን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም በብርሃኑ ሰሙ የተጻፈውን የአዝራር ዲዛይንና ፋሽን በኢትዮጵያ የሚለውን መጽሀፍ ተጠቅመናል፡፡)

ጥንታዊው የቶንጎላ መስጂድ …
#ethiopia | በካፋ ሚንጅዎ ስርወ መንግስት እንደተቆረቆረ የሚነግርለት የቶንጎላ መስጂድ ከ600 ዓመታት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል።
ይህ ዕድሜ ጠገብ መስጂድ የሚገኘው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ውስጥ ነው፡፡
እስልምና በካፋ የተዋወቀውና መስፋፋት የጀመረው በካፋ ጠንካራ ራስ ገዝ አስተዳደር በተገነባበት በመካከለኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይነገራል።
የታሪክ ባለሙያ አቶ አሰፋ ገ/ማሪያም ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የካፋ ሚንጅዎ ስርወ መንግስት ከ13ኛው እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ቆይቷል።
ይህ ስርወ መንግስት ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የተመሰረተውን ጠንካራ የንግድ ግንኙነት ተከትሎ የእስልምና አስተምህሮ ወደ ካፋ ገብቷል ይላሉ።
በወቅቱ የነበረው የካፋ መንግስት ከውጭው ዓለም ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲና የንግድ ግንኙት መመስረቱን አስታውሰው÷ በተለይ ከአረብ ሀገራት ጋር የተዘረጋው የንግድ መስመር ለእስልምና ወደ ካፋ መምጣት ዋናው ምክንያት እንደሆነ ያስረዳሉ።
በርካታ የታሪክ ጸሀፊዎችም በዚህ ጉዳይ ላይ እንደሚስማሙ አቶ አሰፋ ይገልጻሉ።
እስልምናን ወደ ካፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ይዘው የመጡት የየመን ዜግነት ያላቸው አብዱልሰላም ቢን ሀጂ ሱሌማን መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሌላኛው የታሪክ ባለሙያ አቶ ወንድሙ ማሞ በበኩላቸው÷ አብዱልሰላም ቢን ሀጂ ሱሌማን በካፋው ንጉስ ተቀባይነት እንዳገኙ ያብራራሉ።
የካፋው ንጉስ ዓላማህ እምነትህን ማስተማር ብቻ ከሆነና ሌላ አላማ ከሌለህ እዚህ መቆዬት ትችላለህ ሲሉ ለአብዱልሰላም ቢን ሀጂ ሱሌማን ይሁንታቸውን እንደገለጹላቸው ያስረዳሉ።
በዚህም ከቦንጋ ከተማ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ማረፊያ ቦታ እንደሰጧቸው ይናገራሉ።
በዚህ ስፍራም አብዱልሰላም ከ600 ዓመታት በላይ ዕድሜ እንዳስቆጠረ የሚነገርለትን ጥንታዊን የቶንጎላ መስጂድን ለመመስረት በቅተዋል።
ጥንታዊው የቶንጎላ መስጂድ ጥንታዊ መንፈሳዊ መጽሀፍትን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች የያዘ ነው፡፡
በጥንታዊው የቶንጎላ አብዱልሰላም መስጂድ በየዓመቱ የመውሊድን በዓልን ለማክበር በርካቶች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ይሰባሰባሉ።
FMC

ተማሪ ህሊና ፍቅሩ በ6 አመቷ The red fox country የሚል ርእስ ያለው በእንግሊዘኛ የተጻፈ የልጆች መጽሀፍ ለንባብ ያበቃች በሀገራችን የመጀመሪያዋ ህፃን ጸሀፊ ያደርጋታል:(ከተሳሳትኩ እርማት እቀበላለሁ):።
አሁን ደግሞ በ14 አመትዋ Anna's story hood በሚል ሁለተኛ የልጆች መጽሀፏን በደማቅ ሁኔታ አስመርቃ ለንባብ አብቅታለች።
ማንኛውም ወላጅ ለልጁ ይህን ምርጥ መጽሀፍ ገዝቶ ሙሉ ሠው የሚያደርገውን ስጦታ ለልጆቹ ያበርክት:
መጽሀፎቹን እራሷ በከፈተችው Halin books and Amazon ላይ ያገኙታል:ሊንኮቹን ከታች አስቀምጫለሁ:ተማሪና ጸሀፊ የወደፊት የሀገር ተስፋ የሆነችው ህሊና ፍቅሩን በማበረታታ አብረን ልጆቻችን ላይ እንስራ እላላሁ:ልጆች ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት ስለሆነ።
አመሰግናለሁ🙏🥰
👇 https://youtube.com/halin...
👉https://halinbooks.fws.sto...
👇 https://www.pinterest.com/...
👉https://t.me/halinbooks

12 months ago
ዝክረ ~ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ
የአንጋፋው የአደባባይ ምሁር የመታሰቢያ ፕሮግራም በድምቀት ተካሄደ
ይትባረክ ዋለልኝ
#ethiopia | የአንጋፋው ምሁር ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በህይወት የተለየበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የዶ/ር ደረጄጀ ዘለቀ የቅርብ ጓደኞች ያዘጋጁት "ዝክረ "ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ " የመታሰቢያ ፕሮግራም ትላንት ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በአማራጭ የማረፊያ ስፍራ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተካሂዷል።
አዳራሹ በታዳሚያን ሞልቶ የነበረው "ዝክረ "ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ " የመታሰቢያ ፕሮግራም የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን የተለያዩ የህይወት ገፅታዎች የሚያሳዬ ፕሮግራሞች በስነፁሑፍና በኳይር የሙዚቃዎች በታጀበዉ ቀርበዋል::
ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በአደባባይ ምሁርነቱ በማሕበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በማንሳትና የትችት ዓይኑ በስሜት ያልተዳከመ ፣ በብሶትና በእውነት ላይ የተመሠረተ ማንነቱን ለራሱን ሳይሆን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅምና ክብር ያበረከተውን አስተዋጸኦ በተመለከተ የፊልም ባለሙያዉ ዳዊት ተስፋዬ ፣ ሠዓሊና ገጣሚ ቸርነት ወ/ገብርኤል ፣ ሰለሞን ሹምዬ ዲስኩር አቅርበዋል::
እንዲሁም ሠዓሊና ገጣሚ ቸርነት ወ/ገብርኤል አሪፍ ግጥም
ያቀረበ ሲሆን ሳውንድ የኳይር ቡድን ደግሞ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በህይወት በነበረበት ጊዜ የሚወዳቸውን የዘማሪ ሐና ተክሌን መዝሙሮች እና የድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃዎች አቅርበዋል::
በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ተማሪው ና ተመካሪው የነበረውና አሁን በቴላቪቭ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት ተማሪ የሆነው አቶ ደጀን አማን ብዙዎቻችን የማናውቀውን የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የአካዲያሚያዊ ስብእናው በዝርዝር ያሳየ ግሩም የጥናት ፁሑፍ አቅርቦአል::
አቶ ደጀን አማን በዚህ ፅሑፋቸው ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በሕግ ሙያው መስክ በመምህርነቱ በጥናትና ምርምሩ ዘርፍ ስላበረከትው አስተዋፅኦ በሐገር ውስጥና በዓለማቀፍ ጆርናሎች ላይ ስላሳተማቸው የጥናት ፁሑፎች እንዲሁም ታላላቅ የውጭ ሐገር የህግ ምሁራን ስለ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የሰጡትን ምስክርነት አካቶ ምርጥ የጥናት ፁሑፍ አቅርቦአል::
በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን የህይወት ታሪክ እና በማሕበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በጥናትና ምርምሩ ዘርፍ የሰራቸውን ተግባራት በዝርዝር የሚያሳይ እንዲሁም በርካታ ታላላቅ ሰዎች ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የሰጡትን ምስክርነት እና አስተያየት የያዘ መፅሔት ታትሞ ለታዳሚው ተሰጥቷል::
በተጨማሪም የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን ብዙ መልኮች የሚያሳይ ቤተሰቦቹ: አብሮ አደግ ጓደኞቹ የቅርብ ጓደኞቹእና የስራ ባልደረቦቹ የተሳተፉበት ዶክመንተሪ ፊልም በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ለዕይታ በቅቷል::
እንዲሁም ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በህይወት በነበረበት ወቅት እናትዋን በህይወት ላጣችው ልጅ በድምፁ ቀርፆ የላከላትን እጅግ አስገራሚ የማፅናኛ መልእክት ሰለሞን ሹምዬ ከምስል ጋር አዋህዶ በትላንቱ ፕሮግራም ላይ አቅርቦልናል::
በተጨማሪም የፕሮግራሙ ድምቀት የነበረው የደረጀ አድናቂ በሆነው በሰዓሊ ግርማዊ ዓለማየሁ የተሰራው የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ፓርትሬት የጥበብ ስራ ነው:: ይህፓርትሬት በኮላዥ የሥዕል ስራ የተሰራ ሲሆን የደረጅ መለያዎች ከሆኑ ሃሳቦች ጋር ተዋህዶ የተሰራ ምርጥ የጥበብ ስራ ነው::
ትላንት የተካሄደው "ዝክረ "ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ " የመታሰቢያ ፕሮግራም የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን ብዙ የህይወት መልኮች ያሳየ ብቻ ሳይሆን ዶ/ር ደረጀ ዘለቀን በስነጽሑፍ: በፊልም: በሥዕል እና በሙዚቃ የተገለፀበት ፕሮግራም ነበር::
በመጨረሻም በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ በቤተ ጉራጌ ተገንብቶ በዶ/ር ደረጄ ዘለቀ ዘለቀ ስም ለተሰየመው የመታሰቢያ ቤተመጽሀፍት የመጽሐፍ ልገሳ ተከናውኗል::
በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ የዶ/ር ደረጄ ቤተሰቦቹ የአ.አ.ዩ መምህራንና የስራ ባልደረቦቹ የፈረንሳይ ለጋሲዬን አብሮ እደግ የሰፈር ጓደኞቹ በርካታ አድናቂዋቹ ተገኝተዋል::

Comments