Logo
Getu Temesgen
61 ሻማዎች / በዕዝራ እጅጉ -(ተወዳጅ ሚድያ)

ኢቲቪ ነገ ጥቅምት 23፣61 ዓመት ይሞላዋል

(ክፍል አንድ)
#ethiopia | ውድ ክቡራት እና ክቡራን የዚህ ገጽ ተከታታዮች ‹‹61ሻማዎች›› በሚል ርእስ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን 61ኛ አመት በኦን ላይን ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለማክበር የተነሳሳነው አንድም ጣቢያው የሁላችንም ስለሆነ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ኢቲቪን ስንመለከት አድገናል፡፡ከሚተላለፉት ምክር አዘልና የመዝናኛ ፕሮግራሞች ተጠቅመናል፡፡ አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችንም ቃርመናል፡፡ ጣቢያው በ4 መንግስታት እንደማለፉ ስለ ሁሉም መንግስታት የሚናገረው አለው፡፡

ኢቲቪ የኢትዮጵያን ታሪክ በቪድዮ የያዘ ፣ የወቅቱ ሁኔታዎችን የሚገልጽ መረጃ ያከማቸ እና ብዙዎች የደከሙለት የባለሙያዎች ቤት ነው፡፡ እንደ ብረት የጀገኑ ታታሪ ባለሙያዎች ለፍሬ ያበቃም አንጋፋ ቤት ነው፡፡ ባለፉት 61ዓመታት ኢቲቪን 22 የሥራ መሪዎች መርተውታል፡፡

የዚህን አንጋፋ ጣቢያ ልደት ልናከብር ሀሳብ ስናፈልቅ የእስከዛሬዎቹ የተቋሙ ባለሙያዎች እስከ ህይወት መስዋእትነት የከፈሉበትን ልክ ለማሳየትና የባለሙያዎቹንም እውቅና እና ትጋት በደማቅ ብእር ልንከትበው ፈልገን ነው፡፡

አንድ ተቋም ያለ ብቁ ባለሙያ ተቋም ሊባል አይችልምና እነሆ ይህ ጣቢያ በሺህ የሚቆጠሩ ባለሙያዎች ደክመውለት፤ ሮጠውለት ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ይህን ከግማሽ ክፍለ-ዘመን በላይ የቆየ ጣቢያን እንኳን ለበአለ-ልደቱ አደረሰው እንላለን፡፡

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የሚድያ ባለሙያዎችን እና የሚድያ ተቋማትን ታሪክ በምርምር መልክ እየሰነደ እና ለትውልድ እያስቀመጠ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ኢቲቪም ካሉት ሚድያዎች ከአንጋፋዎቹ ተርታ የሚመደብ እንደመሆኑ የያዛቸው የቪድዮ ሰነዶች ስለ ቀደመችው ኢትዮጵያ በሚያሳምን መልኩ የሚናገሩ ናቸው፡፡ እነዚህ የቆዩ ሰነዶች አዲሱን ትውልድ የማስተማር አቅም ስላላቸው ከወዲሁ ለህዝብ እይታ የሚቀርቡበት ስልት ቢነደፍ ጠቃሚ ነው እንላለን፡፡

የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን አባላት በራሳችን ተነሳሽነት ባለፉት 7 አመታት የሀገራችን አንጋፋ ሚድያዎች አመሰራረት ፤ እድገትና አሁናዊ ሁኔታ ላይ መለስተኛ ዳሰሳዊ ጥናት ስናሰናዳ ቆይተናል፡፡

እንዲሁም በሙያቸው ላይ ጉልህ አሻራ ያኖሩ ባለሙያዎች ወደየት አሉ? ምን የተለየ ነገር አበረከቱ? ስንል የህይወት ታሪካቸውን በብዙ ጥረት ስናሰባስብ ቆይተናል፡፡ 285 ያህሉን የሚድያ ሰዎች ደረጃውን በጠበቀ ጠንካራ ሽፋን መጽሀፍ ‹‹መዝገበ-አእምሮ ››በሚል ርእስ አሳትመን አስመርቀናል፡፡ የባለሙያዎቹ ታሪክ በአንድ በኩል በከፊል የመስሪያ ቤታቸውን ታሪክ የሚነግር ነው፡፡

እስከዛሬ የህይወት ታሪካቸውን ከጻፍንላቸው ባለሙያዎች ውስጥ 81 ወይም 27 ከመቶ ያህሉ ኢቲቪ በአንድ ወቅት ያገለገሉና እያገለገሉ ያሉ ይገኙበታል፡ይህ ማለት የኢቲቪ ታሪክ በእነዚህ ሰዎች ታሪክ ውስጥ ይገኛል ማለት ነው።ብዙዎች በታሪካቸው ላይ እንዳቀረቡትና ለእኛም በተደጋጋሚ እንዳጫወቱን ኢቲቪን እንደ ቤታቸው ከመቁጠራቸው የተነሳ ለእድገቱ ይቆረቆራሉ፡፡ ምንም ቢሆን ምን የተማርንበት ፤ አይረሴ ትዝታ ያሳለፍንበት ቤት ነው በማለት የኢቲቪን መልካም ቦታ መድረስ እንደሚመኙ ነግረውናል፡፡

ኢቲቪ በ61 አመት ውስጥ ማደግ የሚገባውን ያህል አድጓል ወይ? በዘመናት ውስጥ ያሉት ውጣውረዶች ምንድናቸው ?የሚለውን ወደፊት በጥናት መልክ የምናየው ሆኖ አሁን ግን ግባችን የልደት ሻማ መለኮስ፣ታሪክን ወደ ኃላ መቃኘትና ባለሙያዎችን ማውሳት ይሆናል ፡፡

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽንም ኢቲቪን የሚያስታውሱ የቀድሞ ቪድዮዎችን ለእይታ በማቅረብ ፤ የባለሙያዎችንም ትዝታ ከኢቲቪ አመሰራረት ጋር አንድ ላይ በማድረግ 61ዱን ሻማ ለመለኮስ አስበናል፡፡ በተጨማሪም ለጣቢያው እዚህ መድረስ ጉልህ ሚና የነበራቸውን ሰዎች በደምሳሳው እናነሳለን፡፡

ይህ ማለት ግን እዚህ ባለሙያዎች በተጨማሪም ሌሎች የሉም ለማለት ሳይሆን ለእኛ ለመዝገበ-አእምሮ ፕሮጀክት ፈቃደኛ ሆነው ታሪካቸውን የሰጡንን ብቻ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ለማካተት ወስነናል፡፡ ከዛሬም ጥቅምት 3 2018- ጥቅምት 30 2018 ተከታታይ ጽሁፎችን እያወጣን የኢቲቪን 61ኛ አመት የልደት በአል እናስባለን፡፡

በመዝገበ-አእምሮ ፕሮጀክት ታሪካቸው የተካተተ የኢቲቪ ባለሙያዎች( የነበሩና እያገለገሉ ያሉ)

1.አቶ ሳሙኤል ፈረንጅ
2.ኢንጂነር ገሰሰ አባይ
3. አባባ ተስፋዬ ሣህሉ
4.አቶ ሰሎሞን ተሰማ
5. ተክሉ ታቦር
6. አሳምነው ገብረወልድ
7.እሌኒ መኩርያ
8.ጌታቸው ኃይለማርያም
9.ህሊና ተፈራ
10. ብርቄ ወልደገብርኤል
11. ተሾመ ብርሀኑ ከማል
12. ታዬ በላቸው
13. አማረ አረጋዊ
14. ኢሳያስ ሆርዶፋ
15. ዜናነህ መኮንን
16. ፀጋዬ ኃይሉ ተፈራ
17 .ስለሺ ሽብሩ
18. ሮማን ተገኝ
19 .አስካለ ተስፋዬ
20. አዲስ አለም ሀድጉ
21. እሸቴ አሰፋ
22 ዘሩ በላይ
23.ገነት አየለ
24. መሳይ ወንድሜነህ
25. መቲ ሸዋዬ ይልማ
26. ተገኝ ጃለታ
27. አሸብር ጌትነት
28. አንድነት አማረ
29. እመቤት ደመቀ
30. ዮሀንስ አያሌው
31. ደረጀ ገብረማርያም
32. ጌጡ ተመስገን
33.ፍፁም ጌታቸው
34. መስከረም ጌታቸው
35.መዓዛ መላኩ
36.መኳንንት በርሄ
37. አንተነህ ደግፌ
38. ጀማል አህመድ
39. ከብካብ አስፋው
40. ሺበሺ ዓለማየሁ
41. ዘላለም ቱሉ
42. አስናቀች ፀጋዬ
43. አይናለም ባልቻ
44. ሻምበል አክሊሉ ዘለቀ
45. ሰብለወንጌል አሰፋ
46. ብዙወንድም አገኘሁ
47. ሀብቴ ገመዳ
48 ሰላማዊት ካሳ (ቱሪዝም ሚኒስትር)
49 . ሳሙኤል ፍቅሬ
50.ሀቢባ ፋሪስ
51.መልካሙ ደምሴ
52.መሰለ ገብረህይወት
53.መኮንን ተሾመ ቶሌራ
54.ሚሊዮን ተረፈ
55.ሰሎሜ ታደሠ
56.ሰሎሞን አባተ
57.ሰሎሞን አሞባቸው
58 .ስመኝ ቴሶ
59.በቀለ መንገሻ
60.ትሩፋት ገብረየስ
61.አስፋው ኢዶሳ
62.ኤልያስ ብሩ
63.እናትዓለም መለስ(ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚ/ር)
64.እዮብ እሸቱ
65.ካሣሁን ገርማሞ
66.አይናለም ባልቻ
67 ዓለሙ ቶሎሳ
68.ዓለም ብርሀኔ
69.ዘከሪያ መሀመድ
70.ፍቅሩ ካሳ
71ጌትነት ታደሰ
72 ዶክተር ፍሰሐ ይታገሱ(የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋ/ሥራ አስፈጻሚ
73 የሺጥላ አንተነህ
74 ዮናስ ከበደ
75.ግዛው ዳኜ
76.ፀጋዬ ተስፋሚካኤል
77.ፀሓይ አክሊሉ
78.አይናለም ሀድራ
79.ካሣ አያሌው ካሣ
80.ዘካሪያስ ብርሀኑ
81.ሌዊ ገሠሠ ተሰማ

በዚህ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ቲቪ ሰርተው ጉልህ አሻራ አኑረዋል የምትሏቸውን በቴክኒክ ፤ በጋዜጠኝነት እና በሚድያ አመራርነት ላይ ያሉ ሰዎችን በtewedajemediagmail.com ብትጠቁሙን ስራችንን የተሟላ ለማድረግ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡ ለኢቲቪ ያላችሁንም የእንኳን አደረሰህ መልእክት ማድረስ ትችላላችሁ፡፡

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.