ቤድሮስ ስቫጅያን በኢትዮጵያውያን አጠራር ጴጥሮስ ስቫጅያን
የግርማዊ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት የወርቅና የጌጥ ዕቃ አቅራቢ
(አበበ ሙሉ)
#ethiopia | አርመናውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው በሰፊው የታወቀ ነው፡፡ አርመናውያን በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በንጉሱ ዘመን በብዙ ዘርፍ ውስጥ ድርሻ ነበራቸው፡፡
ከእነዚያ ውስጥ ቤድሮስ ስቫጅያን ወይም ጴጥሮስ ስቫጅያን ለተለያዩ አገራት መሪዎች የሚሰጡ ስጦታዎች ላይ ድርሻ ነበረው፤ ቤድሮስ ስቫጅያን ለቤተ መንግስት የወርቅና የጌጥ ዕቃ አቅራቢ በመሆን ለመንግስታት የሚሰጡ ስጦታዎችን፣ እውቅናዎችን ኒሻኖችን እና ሜዳሊያዎችን በማቅረብ ተጠቃሽ ነው፡፡
ስጦታ በተለይም ከሌላ አገርና ባህል ለመጣ ሰው ሲበረከት አገርን ማስተዋወቂያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ስጦታ ዓላማውም ሆነ ግቡ ግንኙነትን ማጠናከር ነው፡፡ በዚህ ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ ስጦታ ዘመናትን ተሻግሮ አይረሴነትን ይፈጥራል፡፡
ስጦታ ወዳጅነትን መግለጫና የግንኙነት ማጠናከሪያ መሳሪያዎች ከሆኑት መንገዶች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን በራስ ተነሳሽነት ወይም ከሌላ ወገን ለተበረከቱ ስጦታዎች በምላሽነት የሚሰጡ ሲሆን የሚበረከቱት ስጦታዎች ዓይነትና መጠን አብዛኛውን ጊዜ የስጦታውን አበርካች ባህል፣ ልማድና የአኗኗር ዘይቤን በሚያንጸባርቅ መልኩ የሚከናወኑ ናቸው፡፡ የስጦታዎች ዓይነት በሚመረጥበት ወቅት የራስን ባህል፣ ሃይማኖትና ማህበራዊ እሴቶች ብቻ እንዲያንጸባርቅ ከማድረግ አልፎ የተቀባዩን አገር ባህልና ሃይማኖት ከግምት ውስጥ ያስገባ ጭምር መሆን ይኖርበታል፡፡
ከቤድሮስ ስራዎች አንዱ የሆነውና በ1957 ንግሥት ኤልሳቤጥ አገራችንን ሊጎበኙ በመጡበት ወቅት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለመታሰቢያ የተሰጣቸው ከወርቅ የተሰራ ትሪ ዛሬ ላይ በባኪንግሃም ቤተ መንግስት ውስጥ ለጎብኝዎች ይታያል፡፡
ከኢትዮጵያ ምድር በተገኘና እጅግ ጥራት ባለው 22 ካራት ወርቅ የተሰራው ይህ ትልቅ ትሪ አስራ አራት (14) ኪሎ ክብደት ያለው ነው፤ቤድሮስ ከወርቅ፣ ከብርና ከነሐስ የተሰሩ የተለያዩ ስጦታዎችን በመስራትና ለስጦታ የሚሆኑ የእደ ጥበብ ውጤቶችን በማቅረብ ተጠቃሽ ነበር፡፡ ጴጥሮስ ሳቫጅያን አጼ ኃይለ ስላሴ ለሙያው እውቅና የሰጡት ወርቅና ብር አንጥረኛ ነበር፡፡ ኮንትራት እየወሰደ የመከላከያና ፖሊስ ሠራዊት የማዕረግ ምልክቶች፣ ሜዳልያዎች፣ የቀበቶ መቆለፊያና የተለያዩ ጌጣጌጦችን ይሠራ ነበር፡፡ በጥንት ዘመን የቤተ መንግስት አንጥረኛ፣ የቤተ መንግስት ካባ ሰፊና ሙካሽ ጠላፊ ባለሙያዎች በስፋት ይታወቁ ነበር፡፡
ጴጥሮስ ሳቫጂያን የተወለዱት በኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ የሳቫጅያን ቤተሰብ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በአጼ ምኒልክ ዘመን ንጉሱ የተለያዩ ባለሙያ አርመኖች እንዲመጡ በፈቀዱ ጊዜ ነበር፡፡
የጴጥሮስ ሳቫጅያን አጎት በዚያን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የቤተ መንግስት አትክልተኛ ሆነው ያገለግሉ ነበር፡፡ የጴጥሮስ ሳቫጅያን አባት አቨዲ ሳቫጅያን ይባላሉ፡፡
የሳቫጅያን ቤተሰቦች በኃላ ላይ በተለያዩ ስራዎች በመሰማራት ታዋቂና ባለጸጋ ሆነው ነበር፡፡ የጴጥሮስ ሳቫጅያን አባት የአስኮ ጫማ ፋብሪካን የመሰረቱና ባለቤትም ነበሩ፡፡ ከአቨዲ ሳቫጅያን ከሚወለዱት ልጆች አንዱ የሆኑት ጴጥሮስ ሳቫጅያን በወርቅና ብር ስራ ከሰለጠኑ በኃላ ዋነኛ ስራ አድርገው የተሰማሩትም በዚህ መስክ ነበር፡፡ እንደ እርሳቸው ሁሉ በዚህ ሙያ የተሰማሩ ብዙ አርመናውያን ነበሩ፡፡ በ1950ዎቹ ሁሉም የፒያሳ ወርቅና ብር ሰሪ መደብር ባለቤቶች አርመናውያን የሆኑበት ምክንያት ይህ ነበር፡፡ አርመናውያን በአገራችን የአንጥረኝነት ሙያ እንዲያድግና እንዲስፋፋ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
ጴጥሮስ ሳቫጅያን በዋነኛነት የሚታወቁበት ስራ በህትመት ቅርጽ እያወጡ ሜዳሊያዎችን፣ ኒሻኖችን፣ ለወታደራዊ ዩኒፎርም የሚያገለግሉ የልብስ ቁልፎችን ማምረት ነበር፡፡ ማህተም መቅረጽን ጨምሮ ለቤተ መንግስት በጣም ብዙ ነገሮችን እየሰሩ ያቀርቡ ነበር፡፡ በዘመኑ ለስራው ጨረታ የሚወዳደር ብዙ ባለሙያ አልነበረም፡፡ የጴጥሮስ ሳቫጅያን ኢንዱስትሪ በ1950ዎቹ በጣም ታዋቂና ብዙ ስራዎችን የሰራ ተቋም ነበር፡፡
የትራፊክ ፖሊሶች ፊሽካ፣ ለወታደር የክብር አልባሳት የሚሆኑ የተለያዩ የማዕረግ ምልክቶችና ቁልፎች፣ ለቤተ መንግስት መገልገያ የሚሆኑ ሰሃን፣ ትሪና መሰል ቁሳቁስ በሳቫጅያን ድርጅት ይሰራ ነበር፡፡ የንጉስ ኃይለሥላሴ 80ኛ የልደት በዓል ሲከበር ግለሰቦችና ተቋማት ለንጉሰ ነገስቱ ስጦታ ለማበርከት ከወርቅና ከብር ያሰሯቸው በርካታ የስጦታ ዕቃዎች በሳቫጂያን ተሰርተዋል፡፡
በዘመኑ እንዲህ ዓይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመስራት የሚታወቁት ጴጥሮስ ሳቫጅያንና የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጥይት ፋብሪካ ብቻ ነበሩ፡፡ በሳቫጅያ ድርጅት ለሚመረቱ ዕቃዎች ዲዛይን የሚሰሩ አንድ ጣሊያናዊ ነበሩ፡፡
በንጉሥ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ለነበረው የፖሊስ ሠራዊት የክብር አልባሳት የብረታ ብረት ጌጣጌጦችን በመስራት የሚታወቀው ይህ ድርጅት በብረት የልብስ ቁልፍ ምርቶቹ በውስጠኛው ክፍልም “ሳቫጅያን አዲስ አበባ” የሚል መለያ ጽሁፍ ያትም ስለነበር ምርቶቹ እጁ የገባ ሁሉ ለይቶ ያውቃቸዋል፡፡
የጴጥሮስ ሳቫጅያን መኖሪያ ቤት አሁን በቦሌ አካባቢ የብራዚል ኤምባሲ ሆኖ እያገለገለ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ቤት ነበር፡፡
በሰሯቸው የስጦታ እቃዎችና ጌጣጌጦች በአገራት መካከል አይረሴትን የፈጠሩት፣ ግንኙነቱ እንዲዳብርና እንዲጠናከር ትልቅ ድርሻ ነበራቸው፡፡ እርሳቸውም በሰሩት ዘመን ተሻጋሪ ስራ ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡
በአገሪቱ የሥርዓት ለውጥ ከተካሄደ በኃላ ጴጥሮስ ሳቫጅያንም እንደ ሌሎች ባለሃብቶች ጉዳት አግኝቷቸዋል፡፡ በወቅቱ ልጆቻቸው በውጭ አገራት ነበሩ፡፡ አንዷ ልጃቸው ባለችበት ሀገር ትዳር ስትመሰርት አባቷ እንዲገኙ ብትጋብዛቸውም ከኢትዮጵያ እንዲወጡ አልተፈቀደላቸውም፡፡ ወደ ውጭ እንዳይሄዱ ከተከለከሉ በኃላ በድሬዳዋ በኩል ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ ጉዞ ጀምረው ከዛ በኃላ የት እንደደረሱ ሳይታወቅ እንደወጡ እንደቀሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡
ድርጅታቸውም በኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራዎች ድርጅት ስር እንዲሆን ተደረገ፡፡
ከዓመታት በኃላ የጴጥሮስ ሳቫጅያን ልጆች በአዋጅ ያልተወረሰው የአባታቸውን ቤት ሲያስመልሱ የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅትም ቤቱን ለቆ ወጣ፡፡ እንዲህ ዓይነት ታሪኮችን ያሳለፈው ተቋም በመጨረሻ ለወርቅ አምራቾች ማህበር መሸጡ ታውቋል፡፡
(ለዚህ ዝግጅት በምንጭነት በቤጥሮስ ሳቫጂያን ስም የተከፈተውን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም በብርሃኑ ሰሙ የተጻፈውን የአዝራር ዲዛይንና ፋሽን በኢትዮጵያ የሚለውን መጽሀፍ ተጠቅመናል፡፡)

11 months ago