ጥንታዊው የቶንጎላ መስጂድ …
#ethiopia | በካፋ ሚንጅዎ ስርወ መንግስት እንደተቆረቆረ የሚነግርለት የቶንጎላ መስጂድ ከ600 ዓመታት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል።
ይህ ዕድሜ ጠገብ መስጂድ የሚገኘው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ውስጥ ነው፡፡
እስልምና በካፋ የተዋወቀውና መስፋፋት የጀመረው በካፋ ጠንካራ ራስ ገዝ አስተዳደር በተገነባበት በመካከለኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይነገራል።
የታሪክ ባለሙያ አቶ አሰፋ ገ/ማሪያም ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የካፋ ሚንጅዎ ስርወ መንግስት ከ13ኛው እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ቆይቷል።
ይህ ስርወ መንግስት ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የተመሰረተውን ጠንካራ የንግድ ግንኙነት ተከትሎ የእስልምና አስተምህሮ ወደ ካፋ ገብቷል ይላሉ።
በወቅቱ የነበረው የካፋ መንግስት ከውጭው ዓለም ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲና የንግድ ግንኙት መመስረቱን አስታውሰው÷ በተለይ ከአረብ ሀገራት ጋር የተዘረጋው የንግድ መስመር ለእስልምና ወደ ካፋ መምጣት ዋናው ምክንያት እንደሆነ ያስረዳሉ።
በርካታ የታሪክ ጸሀፊዎችም በዚህ ጉዳይ ላይ እንደሚስማሙ አቶ አሰፋ ይገልጻሉ።
እስልምናን ወደ ካፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ይዘው የመጡት የየመን ዜግነት ያላቸው አብዱልሰላም ቢን ሀጂ ሱሌማን መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሌላኛው የታሪክ ባለሙያ አቶ ወንድሙ ማሞ በበኩላቸው÷ አብዱልሰላም ቢን ሀጂ ሱሌማን በካፋው ንጉስ ተቀባይነት እንዳገኙ ያብራራሉ።
የካፋው ንጉስ ዓላማህ እምነትህን ማስተማር ብቻ ከሆነና ሌላ አላማ ከሌለህ እዚህ መቆዬት ትችላለህ ሲሉ ለአብዱልሰላም ቢን ሀጂ ሱሌማን ይሁንታቸውን እንደገለጹላቸው ያስረዳሉ።
በዚህም ከቦንጋ ከተማ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ማረፊያ ቦታ እንደሰጧቸው ይናገራሉ።
በዚህ ስፍራም አብዱልሰላም ከ600 ዓመታት በላይ ዕድሜ እንዳስቆጠረ የሚነገርለትን ጥንታዊን የቶንጎላ መስጂድን ለመመስረት በቅተዋል።
ጥንታዊው የቶንጎላ መስጂድ ጥንታዊ መንፈሳዊ መጽሀፍትን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች የያዘ ነው፡፡
በጥንታዊው የቶንጎላ አብዱልሰላም መስጂድ በየዓመቱ የመውሊድን በዓልን ለማክበር በርካቶች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ይሰባሰባሉ።
FMC

1 year ago