1 month ago
“የሕይወት መንገድ” ለንባብ በቃ
#ethiopia | የመጀመሪያው የጉራጊኛ ረጅም ልቦለድ ደራሲ 16ኛው መጽሐፋቸውን ለንባብ አብቅተዋል።
የመጀመሪያው የጉራጊኛ ረጅም ልቦለድ “የጫሙት ሽካ”ን በመጻፍ በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ የማይረሳ አሻራ ያኖሩት አንጋፋው ደራሲ አጋዝ ገብረኢየሱስ ኃይለማርያም “የሕይወት መንገድ” የተሰኘውን 16ኛው መጽሐፋቸው ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ አስመርቀዋል።
ደራሲው በጉራጊኛ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ 16 መጽሐፍትን የጻፉ ሲሆን፣ ለጉራጌ ቋንቋና ባህል ጥበቃ፣ አንድነትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ከዚህም ባሻገር የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት (ጉህራልድ) መሥራች በመሆን “በማኅበረሰብ ልማት” ዘርፍ ጉልህ ይታወሳሉ።
አጋዝ ገብረየሱስ በድርሰት ሥራ ላበረከቱት ልዩ አስተዋፅኦ ዕውቅና ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ተበርክቶላቸዋል።
እርሳቸውም መጻሕፍታቸውን ሲያሳትሙ ለትልቅ ማህበረሰባዊ ዓላማ እንደነበር በማስታወስ በ97 አመታቸው እንዲህ አይነት እውቅናና ክብር በማግኘታቸው የተሰማቸውን ልዩ ደስታ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት ደራሲ አበረ አዳሙ አጋዝ ገብረየሱስ የፅናት ተምሳሌት መሆናቸውን ያስረዱ ሲሆን “የደራሲያን ማህበርም እውቅና በመስጠቱ ኩራት ይሰማዋል” ብለዋል።
የጉራጌ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊና በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ደሳለኝ ገብሬ በመርሀ ግብሩ ባደረጉት ንግግር አጋዝ ገብረየሱስ ለአዲሱ ትውልድ አርአያ የሚሆኑ በተለይም በድርሰቱ መስክ ትልቅ አሻራ ያኖሩ በመሆናቸው እናከብራቸዋለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ደራሲ ገብረየሱስ በሁለቱ የጉራጌ ዞኖች ለሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚውል 1000 መጽሃፍትን በልገሳ ያበረከቱ ሲሆን የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልዴ መጻህፍቱን ለማሰራጨት ሀላፊነት ወስደዋል።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ካሚል ኑረዲን በመድረኩ የመጽሐፍ ዳሰሳ ያቀረቡ ሲሆን የደራሲው የበኩር ልጅ ኢትዮጵያ ገብረየሱስ የ“እንኳን ደስ አልዎ” መልዕክትና የቤተሰባዊ ምስክርነት ንግግር አድርገዋል።
መፅሐፉ በደራሲ ብርሀነ ዓለሙ የተሰናዳ ሲሆን የምረቃ ስነ-ስርዓቱን ተወዳጅ ሚድያና ኮሙኒኬሽን ከሶዶ ለማ ሚዲያ ጋር በመሆን አዘጋጅተውታል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#የሕይወትመንገድ #ደራሲአጋዝገብረየሱስሀይለማርያም #ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemsgen #mediacommunication

ሁሉ ነገራቸው ለሰጡን የኮርያ ዘማቾች የምናደርገው ድጋፍ የፍቅር ስጦታችን ነው፦በኢትዮጵያ የደቡብ ኮርያ አምባሳደር
#ethiopia | በኢትዮጵያ የሚገኙት ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ እና ወርልድ ቱጌዘር (World Together) በጋራ በመሆን 'ዘ ፋይናል ሳሉት' (The Final Salute) የተሰኘ የድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል።
ድጋፉ የኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞች ማህበር በመተባበር የሚደረግ ሲሆን በኮርያ ጦርነተ ለተሳተፉ አርበኞች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ይህ የ12 ወራት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞችን ታሪክ ለማክበር እና ያላቸውን ምኞት ለማሳካት ያለመ መሆኑን ነው የተገለጸው።
በአሁኑ ወቅት በህይወት የሚገኙት 46ቱ አርበኞች በአብዛኛው ከ90 ዓመት በላይ የሆናቸው ሲሆን፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ቢገጥሟቸውም ከኮሪያ ጋር ያላቸውን ታሪካዊ ትስስር ከፍ አድርገው እንደሚመለከቱ ተገልጿል።
ለዚህም አስፈላጊው የልብስ ወጪ ይሸፈናል፤ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በኮሪያኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች በተቀረጸ የመታሰቢያ መልእክት የታጀቡ ትላልቅ የፎቶ ምስሎች ይሰጣቸዋል ተብሏል።
በቃለ መጠይቅ አማካኝነት አምስት አርበኞች ተመርጠው እንደ የቤተሰብ መገናኘት፣ የህክምና ድጋፍ ወይም ወደ ደቡብ ኮሪያ የመመለስ ጉዞ ያሉ የረጅም ጊዜ ምኞቶቻቸው ይፈጸማሉ።
ፕሮጀክቱ የአርበኞቹን ፎቶግራፎች እና ዘጋቢ ፊልሞች የሚያሳይ የህዝብ ኤግዚቢሽን እና ለእነሱ ክብር የሚሰጥ ዝግጅት ያደርጋል ተብሏል።
ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ከ2012 ጀምሮ ለኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞች እና ቤተሰቦቻቸው በትምህርት፣ በኑሮ ማሻሻያ እና በቤቶች ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው።
ለዚህ መርሀ ግብር የገንዘብ ድጋፉን የሚያደርገው ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ነው ተብሏል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ኤልጂኤሌክትሮኒክስ #ወርልድቱጌዘር #ኮርያኤምባሲ #የኮርያዘማቾችማህበር #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

ራስ ገዝ ሊሆን የመጨረሻ ደረጃ የደረሰው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።
#ethiopia | ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ፣ በድኅረ ምረቃ ፣ በሰብስፔሻሊቲ እና በሦሥተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 4ሺህ 83 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 30 የጎንደር ከተማ እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በሊደርሺፕ በድህረ ምረቃ የሚመረቁ ይሆናል።
ከተመራቂ ተማሪዎች በተጨማሪ ለስምንት አንጋፋ የተቋሙ ምሁራን የሙሉ ፕሬሰርነት ማዕረግ ሲሰጥ፥
ለታዋቂው የሰው ዘር ጥናት ምሁር ለሆኑት ፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሃንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።
የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባኤ በሰው ልጅ አመጣጥ ሳይንስ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ፣ በምርምርና በትምህርት ዘርፍ ለአለም ያበረከቱትን የዕድሜ ልክ አገልግሎት ይህንን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል።
በዛሬ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ፣ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች ታድመል።
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህ የምረቃ ስነስርአት ዩኒቨርስቲው ራስ ገዝ ለመሆን ያደረገው የመጨረሻ የምረቃ ስነስርአት ነው ብለዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ጎንደርዩኒቨርስቲ #ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለታዋቂው የሰው ዘር ጥናት ምሁር ፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሃንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ።
#ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባኤ በሰው ልጅ አመጣጥ ሳይንስ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ፣ በምርምርና በትምህርት ዘርፍ ለአለም ያበረከቱትን የዕድሜ ልክ አገልግሎት ይህንን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ ምድር መሆኗን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስታወቅ ላደረጉት ታላቅ ሚና ዕውቅና በመስጠት ለፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሃንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት (Doctor of Science, Honoris Causa) ዲግሪ ሰጥቷል።
ፕሮፌሰር ጆሃንሰን በ1974 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ “ሉሲ” ወይም “ድንቅነሽ” በመባል የምትታወቀውን የ3.2 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላት የሰው ዘር ቅሪተ አካል በማግኘታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ሆነዋል።
ይህ ግኝት የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥን የሚመለከቱ ሳይንሳዊ እውቀቶችን በእጅጉ የቀየረ ሲሆን፣ የቀደሙ የሰው ዝርያዎች አእምሯቸው ከማደጉ በፊት በሁለት እግራቸው ቀጥ ብለው ይራመዱ እንደነበር ለማረጋገጥ ወሳኝ ማስረጃ ሆኗል።
ፕሮፌሰር ጆሃንሰን ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ በአንትሮፖሎጂ የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል።
በኋላም በሰው ልጅ መገኛ ጥናት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያለውን የሉሲን ግኝት በማሳካት ለሳይንሱ ዘርፍ የማይረሳ አሻራ አስቀምጠዋል።
ፕሮፌሰር ጆሃንሰን በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሰው ዝግመተ ለውጥና ማኅበራዊ ለውጥ ትምህርት ቤት (School of Human Evolution and Social Change) የክብር ፕሮፌሰር (Professor Emeritus) ሲሆኑ፣ እንዲሁም የ የሰው ልጅ አመጣጥ ጥናት ተቋም (Institute of Human Origins) መስራች ዳይሬክተር ናቸው።
“Lucy: The Beginnings of Humankind” የተሰኘውን መጽሀፍ ጨምሮ በርካታ ሳይንሳዊ ሥራዎችን በማበርከት፣ በማስተማርና ለሕዝብ ተደራሽ የሆኑ የሳይንስ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሳይንስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ቅርሶች ለመጠበቅና ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ጆሃንሰን ለሰው ልጅ መገኛ ሳይንስ ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋፅኦ፣ በሰው ዘር መነሻ ጥናት ውስጥ የኢትዮጵያን ሚና በማጉላት ያሳዩትን ክብር እና ለዓለም አቀፍ ትምህርትና ምርምር ያበረከቱትን ልዩ አገልግሎት በማድነቅ ይህንን ከፍተኛ ክብር አበርክቶላቸዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ጎንደርዩኒቨርስቲ #ፕሮፌሰርጆሃንሰን #ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

Sponsored by
Surafel
1 month ago
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስምንት ምሁራንን ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አሳደገ
#ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ባካሄደው ስብሰባ፣ በላቀ የትምህርትና የምርምር አፈጻጸማቸው አንቱታን ያተረፉ ስምንት ምሁራንን ከተባባሪ ፕሮፌሰርነት ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማሳደጉን አስታወቀ።
ይህ ከፍተኛ የአካዳሚክ ማዕረግ ዕድገት የተሰጣቸው
👉 ዶ/ር በውቀቱ መሐሪ፣
👉 ዶ/ር ሞላ ተፈራ፣
👉 ዶ/ር ምሳዬ ሙላቴ፣
👉 ዶ/ር ጌትነት ማስረሻ፣
👉 ዶ/ር ደሴ ጥበበ፣
👉 ዶ/ር ማስተዋል ብርሀን፣
👉 ዶ/ር አስማማው አጥናፉ እና
👉 ዶ/ር አስማማው ዓለሙ ናቸው።
የተሰጠው የዕድገት ማዕረግ በአዲሱ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ መሠረት የተከናወነ ሲሆን፣ ምሁራኑ በምርምር ሥራዎቻቸው፣ በማስተማር ሒደትና በተቋማዊ አመራር ላበረከቱት ጉልህና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እውቅና የሰጠ ነው።
#ጎንደርዩኒቨርስቲ #ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication
#ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ባካሄደው ስብሰባ፣ በላቀ የትምህርትና የምርምር አፈጻጸማቸው አንቱታን ያተረፉ ስምንት ምሁራንን ከተባባሪ ፕሮፌሰርነት ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማሳደጉን አስታወቀ።
ይህ ከፍተኛ የአካዳሚክ ማዕረግ ዕድገት የተሰጣቸው
👉 ዶ/ር በውቀቱ መሐሪ፣
👉 ዶ/ር ሞላ ተፈራ፣
👉 ዶ/ር ምሳዬ ሙላቴ፣
👉 ዶ/ር ጌትነት ማስረሻ፣
👉 ዶ/ር ደሴ ጥበበ፣
👉 ዶ/ር ማስተዋል ብርሀን፣
👉 ዶ/ር አስማማው አጥናፉ እና
👉 ዶ/ር አስማማው ዓለሙ ናቸው።
የተሰጠው የዕድገት ማዕረግ በአዲሱ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ መሠረት የተከናወነ ሲሆን፣ ምሁራኑ በምርምር ሥራዎቻቸው፣ በማስተማር ሒደትና በተቋማዊ አመራር ላበረከቱት ጉልህና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እውቅና የሰጠ ነው።
#ጎንደርዩኒቨርስቲ #ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication
2 months ago
አብረው ለመስራት ተስማሙ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የስፖርትና የቱሪዝም ዘርፍ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንደሚኖረው በሚጠበቀው የመጀመሪያው ከፍተኛ ደረጃ የMMA (Mixed Martial Arts) ውድድር ላይ ትብብር ለመፍጠር፣ Sweat Box እና Kuriftu Resorts የመግባቢያ ስምምነት (MOU) አድርገዋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ በከፍተኛ ዝግጅት የሚካሄደው ግዙፉ የ"MMA" (Mixed Martial Arts) ውድድር፣ ለስኬታማነቱ ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር ዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ስትራቴጂያዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።
የMMA ውድድር ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
ውድድሩ በሀገሪቱ የቱሪዝም እና የመዝናኛ ዘርፍ አቅም ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ተፅዕኖ በመገንዘብ፣ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
በስምምነቱ መሰረት ተወዳዳሪዎች ለ1 ወር በኩሪፍቱ ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን ስምምነቱ ለአንድ አመት እንደሚቆይ ተነግሯል።
ስምምነቱ የMMA ተወዳዳሪዎች በኩሪፍቱ ሪዞርቶች ልዩ ቅናሾችን እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በጋራ የጤና እና ደህንነት ፕሮግራሞችን፣ ሀገራዊ የጤና ንቅናቄዎችን እና የተለያዩ ስፖርታዊ ኩነቶችን ለማዘጋጀት መንገድ ይከፍታል።
እንደዚሁም ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሥራት በሀገሪቱ የስፖርትና የጤና (Wellness) ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ለመፍጠር አቅደዋል።
በዚህም መሠረት የጋራ የጤናና ደህንነት ፕሮግራሞችን፣ ሀገር አቀፍ የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎችን እና የተለያዩ የስፖርት ዝግጅቶችን በጋራ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#kurifturesort #sweatbox #ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

የፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል የISO 15189 የብቃት ማረጋገጫ አገኘ
#ethiopia | ከተመሠረተ 25 ዓመታትን ያስቆጠረው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ISO 15189:2022 የህክምና ላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት የምስክር ወረቀት አግኝቷል።
የሆስፒታሉ መስራች እና ባለቤት እንዲሁም ስራ አስኪያጅ የሆኑት ደ/ር ፍቅረማሪያም ጉድታ እንደተናገሩት ይህ ምዕራፍ ሆስፒታሉ ከ250 በላይ አለም አቀፍ የላቦራቶሪ የጥራት መስፈርቶችን ማሟላቱን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ለታካሚዎች የላቀውን እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ሆስፒታሉ ያሳየውን ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
የላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ስርዓት በሆስፒታል ላቦራቶሪ ውስጥ ሁሉንም ሂደቶች መደበኛ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው እንዲሆን የሚያደርግ ሆኖ የተዋቀረ ነውም ብለዋል።
ሆስፒታሉ ያሟላቸው ቁልፋ የጥራት መስፈርቶች የላቦራቶሪው የጥራት ቁርጠኝነት ፣ሰነድ አስተዳደር የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ብቃት እና ሌሎችም ይገኙበታል።
የኢፌድሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት ሬጉላተሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ያደረገው ተቋማዊ ግንባታ አስደናቂ መሆኑን ገልፀው ለተወዳዳሪነት አክሪዲቴሽን መሠረታዊ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ሚኒስትር ዲኤታው ገለፃ ኢኖቬሽን በዛሬ ዘመን ዋና ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ተቋማትም በቴክኖሎጂ ታግዘው ሥራቸውን በጥራትና በተወዳዳሪነት መሥራት አለባቸው ብለዋል።
ተቋሙ በአለም ለ19ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ የተከበረውን የአለም የአክሪዲቴሽን ቀን ዘንድሮ ሰኔ 15 2018 "አክሪዲቴሽን ለፈጠራ እምነት እና ዘላቂነት በሚል ቃል በዓሉን አክብሯል።
በዕለቱም ፍቅረሰላም ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትም የምዘና ብቃት ማረጋገጫ እንዳገኙ ታውቋል።
"ወርቃማ ልቦች ፣ አገልጋይ እጆች !" በሚል መርህ ከክሊኒክ አንስቶ እስከ አጠቃላይ ሆስፒታል 25 ዓመታት የዘለቀው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ነው።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ፍቅረሰላምሆስፒታልሆስፒታል #የንግድናቀጠናዊትስስርሚኒስትር #ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

ከስምምነት የደረሱባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?
#ethiopia | አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ከስምምነት የደረሱባቸው የመግባቢያ ነጥቦች ይፋ ሆኑ።
አሜሪካ እና ኢራን ከሦስት ወራት በላይ የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።
በመካከለኛው ምሥራቅ ብሎም በመላው ዓለም ከባድ ቀውስን አስከትሎ የቆየውን ጦርነት ለማስቆም ለወራት ሲደረግ የነበረው ድርድረ አርብ ዕለት ስዊትዘርላንድ ውስጥ በሚካሄድ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ይቋጫል ተብሏል።
አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱ እንዲቆም በደረሱት የመግባቢያ ስምምነት ላይ ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች ጦርነቱ እንደሚቆም እና የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደሚከፈት ተዘግቧል።
የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን በቴህራን እና ዋሺንግተን መካከል ጦርነቱን ለማስቆም ስምምነት በተደረሰበት የመግባቢያ ሰነድ ውስጥ የተካተቱ ነጥቦችን ይፋ አድረገዋል።
የመገናኛ ብዙኃኑ ባቀረቧቸው ዝርዝሮች ውስጥ የተካተቱት ነጥቦች በሁለቱም ወገን ማረጋገጫ አልተሰጠባቸውም።
ሜህር የዜና ወኪል ከዘረዘራቸው ነጥቦች መካከል፦
* በሁሉም ግንባሮች ሊባኖስን ጨምሮ በቋሚነት ተኩስ ይቆማል
* አሜሪካ በኢራን ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ አትገባም
* በ30 ቀናት ውስጥ የአሜሪካ የባሕር ዕገዳ ይነሳል
* የአሜሪካ ጦር ከኢራን ለቅቆ ይወጣል
* የሆርሙዝ ወሽመጥ “በኢራናውያን ቁጥጥር” በ30 ቀናት ውስጥ ዳግም ይከፈታል
* አሜሪካ እና አጋሮቿ 300 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የመልሶ ግንባታ ዕቅድ ያቀርባሉ
* በኢራን የነዳጅ ዘይት እና ኢነርጂ ምርቶች ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ማንሳት
* ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ላለማምረት ዳግም ታረጋግጣለች
አሜሪካ በቀጣናው ያላትን ጦር አትጨምርም እና አዲስ ማዕቀብም አትጥልም።
* ሜህር አክሎም የስምምነቱ መጨረሻ የኢራን እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ ግማሽ ሃብቷ እስኪለቀቅ፣ የኢራን ነዳጅ ዘይት ላይ የተጣለው ማዕቀብ እና የባሕር ላይ ዕገዳው እስኪነሳ ድረስ የመጨረሻው ድርድር አይጀመርም ሲል ዘግቧል።
እንዲሁም የመጨረሻው ስምምነት በተባበሩት መንግሥታት በፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ እንደሚጸድቅ ዘግቧል።
#አሜሪካ #ኢራን #ጦርነት #ስምምነት #bbc #ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemsgen #mediacommunication

ካናዳ መግባት አትችልም
#ethiopia | ጋናዊው የመካከለኛ መስመር ተጨዋች ቶማስ ፓርቲይ ካናዳ ለመግባት መከልከሉን ተከትሎ አገሩ ከፓናማ ጋር የምታደርገው የመክፈቻ ጨዋታ ላይ አይሳተፍም።
የ32 ዓመቱ ተጨዋች እ.አ.አ ከ2020 እስከ 2022 ድረስ በአራት ሴቶች ሰባት የአስገድዶ መድፈር እና አንድ ከወሲባዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ ክሶች ቀርበውበታል።
ተጨዋቹ በሚቀጥለው ዓመት ፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን፤ ጥፋተኛ አይደለሁም ብሏል።
ፊፋ ባወጣው መግለጫ የቀድሞው የአርሰናል ተጨዋች እና የአሁኑ የስፔኑ ቪሪየል ተጨዋች የጋና ቡድን ስልጠና ማዕከል ከነበረው ቦስተን ወደ ካናዳ ለመግባት የቪዛ ማመልከቻው በካናዳ መንግሥት ውድቅ እንደተደረገበት አረጋግጧል።
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ መሪ ድርጅት "ፊፋ የቪዛ አሰጣጥን ጨምሮ በአስተናጋጅ አገራት የኢሚግሬሽን ሂደት ተሳትፎ የለውም።
"የአስተናጋጅ አገሩ መንግሥት ማን ቪዛ ማግኘት እንዳለበት እና ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ማን እንደሚፈቀድለት የመጨረሻውን ውሳኔ ይወስናል" ሲል አክሏል።
በካናዳ መንግሥት ድረ ገፅ የጉብኝት ሕግ ዝርዝር ላይ "ወንጀል ሰርተው ወይንም በወንጀል ፍርድ ተሰጥቶብዎ ከሆነ ወደ ካናዳ መግባት ላይፈቀድልዎ ይችላል" ይላል።
ቶማስ ፓርቲይ ሁሉንም የቀረቡበትን ክሶች ጥፋተኛ አለመሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ እስካሁንም የጥፋተኝነት ብይን ሳይሰጠው የፍርድ ቤት ቀጠሮውን እየተጠባበቀ ነው።
የካናዳ የኢምግሬሽን፣ ስደተኞች እና ዜግነት ቢሮ ለቢቢሲ በላከው መግለጫ "ካናዳ የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ በማስተናገዷ ኩራት ይሰማታል።
የካናዳዊያንን ደኅንነት እና ፀጥታ በመጠበቅ የተሳካ ሁነት ለማዘጋጀት እየሰራች ነው።
"ካናዳ ትላልቅ ሁነቶችን ማዘጋጀት የካናዳን የኢምግሬሽን ሕጎች አይቀይርም የሚል ፅኑ አቋም አላት" ብሏል።
"ወደ ካናዳ የሚመጣ ማንኛውም ሰው በግለሰብ ደረጃ ይመዘናል፤ ይህም ባሉ እውነታቸው እና በሚተገበሩ ሕጎች ተመስርቶ ነው" ሲል መግለጫው አክሏል።
የአሜሪካ የጉሙሩክ እና ድንበር ጥበቃ ቢሮ በበኩሉ አሜሪካ የፓርቲይ የፍርድ ቤት ጉዳይን እንደምታውቅ፤ ነገር ግን በዚህ ጊዜ በወንጀል ብይን ስላልተሰጠው ወደ አሜሪካ እንዲገባ መደረጉን ገልጿል።
#bbcnews #ቶማስፓርቴ #tomaspartie #ጊጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

Comments