ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እናቶች የሚወክል የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ
#ethiopia | እናት ባንክ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እናቶች የሚወክል "እማዬ" የተሰኘ ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ በፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት አካባቢ የሴቶችን ጉዳይ ርእሰ ጉዳይ እንዲሆን ባደረገው በቀድሞው የኢትዮጵያ ሬዲዮ በነበረበት ህንጻ ላይ በደማቅ ሥነ ስርዓት በዛሬው እለት ተመርቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ቅርንጫፉ ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ሰዎች ስለእናታቸው የሚሰማችውን የሚጽፉበት መዝገብ የተዘጋጀለት ፣እናቶች በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸው ባህላዊ ቁሳቁሶች፣ ስለእናቶች የተጻፉ መጽሀፍት የሚገኝበት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ መሠራቱ በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።
እናት ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ በተለየ መልኩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበትና ለሁሉም ህብረተሰብ የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ታሳቢ በማድረግ ከዛሬ 13 አመት በፊት የተቋቋመ ሲሆን የሴቶችን የፋይናንስ አካታችነትና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎት መሰረት በማድረግ በመላ አገሪቱ 218 ቅርንጫፎችን በመክፈት እንዲሁም በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት በብቁና በተደራጀ የሰው ኃይል ቀልጣፋና ፈጣን የሆነ አገልግሎት በመሰጠት በባንክ ኢንዱስትሪው አበረታች ውጤት በማስመዝገብ ተወዳዳሪነቱን ከፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

12 months ago