የፍተሀብሔር የፍርድ ቤት ስልጣን መርሆች
የኢትዮጵያ ፍተሀብሔር ስነስረአት ህግ
በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
0929101037,0983337690
መግቢያ #ethiopia | ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ የፍርድ ቤት ስልጣን በኢትዮጵያ አስመልክቶ በድንጋጌዎቹ የሚያስቀምጠው የኢትዮጵያ ፍትሀብሔር ስነስረአት ህግ በአንደኛ መጽሀፍ በፍርድ ቤቶች ስልጣን በጠቅላላ ድንጋጌው የሚያስቀምጣቸውን አጠር አድርጎ በሚገባ መጠን ማቅረቡ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ማቅረብ ተገቢ መሆኑን አምኛለው። የፍትሀብሔር ስነስረአት ህጋችን በ1958 የወጣው የፍትሀብሄር ጉዳዮችን በፍርድ ቤት እና ህግ በሚፈቅዳቸው እንዴት መምራት እንደምንችል የሚያስቀምጥ ሲሆን በዘጠኝ መጽሀፍ የተከፈለ ነው። ከዚህ ውስጥ የመጀመሪያው መጽሀፍ ስለ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ሲሆን የመጀመሪያው መጽሀፍ በምእራፎች የተከፋፈለ ሆኖ የመጀመሪያው ጠቅላላ ድንጋጌዎች በሚል ስያሜ ሰጥቶ ይጀምረዋል። ድንጋጌዎቹም ከቁጥር 4 እስከ 11 የተቀመጡ ናቸው። እነዚህ ድንጋጌዎች እንዴት የፍርድ ቤት ስልጣን መርሆች እንደተባሉ ወደ እናንተ አጠር አጠር ባለ መንገድ እናቀርባለን።
1. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ አንድ
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 4
ክስን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው የፍርድ ቤት ብቻ መሆኑ
በሌላ ህግ ካልታገደ በቀር የፍትሀብሔር ጉዳዮችን ተቀብሎ ለማየት ለሌላ አካል ማለትም ከፍርድ ቤት ውጪ የሆነ ተቋም ወይም አካል ተቀብሎ ለማየት ስልጣን በህግ ካልተሰጠው በቀር ለማየት የፍትሀብሄር ክሶችን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ ነው።
2. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ሁለት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 5
የመጨረሻ ውሳኔ በፍርድ ቤት ያገኙ ጉዳዮች
የመጨረሻ ውሳኔ በፍርድ ቤት ያገኙ ጉዳዮች ድጋሜ ክስ ሊቀርብባቸውና ሊታዩ አይገባም።
3. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ሶስት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 6
ድጋሚ ዳኝነት ቀድሞ በተወሰነበት ጉዳይ የሚታይበት አግባብ
ፍርዱ የተሰጠው በቀረበ ማስረጃ በሀሰት፣በመደለያ፣በተሳሳተ ማስረጃ ከሆነ ይህንን ማስረጃ በማቅረብና እና በማስረዳት የተሰጠውን ፍርድ በመተው ድጋሚ ዳኝነት እኔዲታይ መጠየቅ ይቻላል።
4. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ አራት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 7
የቀደምትነት መብት
አንድን ጉዳይ አንድ ፍርድ ቤት ብቻ የማየት ስልጣን ያለው ሲሆን
የተለያዩ ፍርድ ቤቶች በአንድ ጉዳይ የማየት ስልጣን ሲኖራቸው ቅድምያ ለማየት የጀመረው ስልጣን ያለው በመሆኑ ሌሎቹ ፍርድ ቤት በአንዱ ቅድሚያ ከተጀመረ በኋላ የማየት ስልጣን የላቸውም።
የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ አምስት
5. የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 8
በሌላ ፍርድ ቤት በቀጠሮ ላይ ያለ ጉዳይ
በሌላ ፍርድ ቤት በቀጠሮ ላይ ክስ፣ክርክር እየለ በዚሁ በተመሳሳይ ጉዳይ ሌላ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ አይቻልም።
6. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ስድስት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 9
የስረነገር ስልጣን
ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ከሌላቸው ማየት አይችሉም።
የስረነገር ስልጣን ማለት የቀረበለትን ጉዳይ ከንብረቱ የገንዘብ ግምት ወይም ከጉዳዩ አይነት በህግ ከተደነገገው አንጻር ለማየት የሚያስችል ስልጣን ሲሆን ይህ ስልጣን ከሌለው ማየት አይችልም።
7. የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ሰባት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 10
የግዛት ስልጣን
ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የነገሩ መነሻ የሆነው ነገር ክስን ተቀብሎ ለማየት የአከባቢ ስልጣን ያለው ስለመሆኑ አረጋግጦ ፍርድ ቤቱ መቀበል ያለበት ሲሆን የግዛት ስልጣን ከሌለው ፍርድ ቤት ክሱን መመለስ አለበት። ይህንንም የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 19-30 መሠረት በማረጋገገጥ የግዛት ስልጠን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ሌላ ተመሳሳይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመቀበል የግዛት ስልጣን አለው በሚል ብቻ አልቀበልም ማለት አይችልም።
8.የፍርድ ቤት ስልጣን መርህ ስምንት
የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 11
ክሶችን ስለማጣመር
የተለያዩ ክሶች ወይም ይግባኝ በአንድ ፍርድ ቤት በመሰማት ላይ ሲገኙ የህግ ክርክር ወይም የነገሩ ጭብጥ ተመሳሳይ እንደሆነ እንዲሁም ተከራካሪዎች በአንድ ዘንግ የሚመደቡ ከሆነ እንዲጣመሩ አንዱ ተከራካሪ ወገን ሲያመለክት ወይም ፍርድ ቤቱ ካመነበት የሚጣመር ሲሆን በተመሳሳይ በተለያዩ ፍርድ ቤቶችም ክሱ በመሰማት ላይ ሲሆን አንዱ እንዲጣመር ማመልከት ይችላል።
9. ማጠቃለያ
በዚህ አጭር ጽሁፍ ያቀረብነው የፍርድ ቤቶችን አስመልክቶ መታወቅ የሚገባቸው ወሰኝ ነጥቦች እንደ መርህ ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን በፍትሃብሔር ጉዳይ ክስ ፍርድ ከመቅረባቸው በፊት በጥንቃቄ ተለይተው መታወቅ የሚገባቸው ናቸው።
ማጠቀሻ
1. የፍትሀብሄር ስነስርዓት ህግ 1958
2. አለን ስድለር የፍ/ስ/ስ/ህግ ማብራሪያ
https://www.facebook.com/s...
https://t.me/Fantahunlawye...

4 months ago