የሙፍቲን የደግነትና የሰብአዊነት ሁለንተናዊ ሌጋሲ ለማስቀጠል አራት ፕሮጀክቶች በሂደት ላይ ናቸው፦
1- የሀይማኖት ትምህሮት ማዕከል
ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ ያለውን 8000 ካሬ ሜትር ያህል ቦታቸውን ሙፍቲ ለመስጊድና ለዲን ትምለህርት ማዕከልነት "ወቅፍ" ስላደረጉ የ500 ሚሊየን ብር ግኖባታ ለማሳረፍ ዲዛየኑ ተሠርቶ አልቋል። በአላህ ፈቃድ ወደፈንዶ ሬይዚንግና ግንባታ እንቅሶቃሴ በቅርቡ ይገባል።
2- የቁርአን ተፍሲር
ሙሉውን ቁርአን የፈሰሩበት ሥራ ኤዲቲንግና ሌሎች ሥራዎቹ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ለህዝብ ይለቀቃል።
በተጨማሪም ይኸንኑ ሥራቸውን በመጽሀፍ መልክ የማዘጋጀቱ ተግባር በሂደት ላይ ነው።
3- የህይወት ታሪክ ዝግጅት
የህይወት ታሪካቸውን በአማርኛና በዐረብኛ ለማዘጋጀት የታቀደ ሲሆን የአማርኛው ቅጅ ሥራ በመገባደድ ላይ በመሆኑ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ወደ ህትመት ይገባል። ኢንሻአላሀ።
የአረብኛው ቅጅም እርሱን ተከትሎ ይታተማል።
4- ሀገር አቀፍ የምስጋና ቀን
የሙፍቲን ክብርና የዘመናት አገልግሎት የሚመጥን ሀገር አቀፍ የምስጋና ቀን ከረመዳን በፊት ተዘጋጅቶ ሙፍቲን ለማመስገን ታቅዶ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን የርሳቸው ማረፍ በዝግጅት ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ቢኖረውም ከዳር ለማድረስ በአዘጋጆቹ በኩል ቁርጥ ውሳኔ ያለ በመሆኑ ዕወን ይሆን ዘንድ ጥረቶች የሚቀጥሉ ይሆናል።
ሙፍቲ ለነዚህ ፕሮጀክቶች ይሁንታ (ኢጃዛ) የሰጡ ሲሆን የቁርአን ተፍሲራቸው ጋር የተያያዙ ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ከማረፋቸው አሥር ቀናት ቀደም ብሎ አይተው ተደስተዋል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ ዕውን ይሆኑ ዘንድ የሁሉም ወገን ትብብር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ፕሮጀክቶችን በመምራት ላይ ያለው ኮሚቴ በጽኑ ያምናል።
ዑስታዝ ሀሰን ታጁ

10 months ago