2 months ago
ብልፅግና ፓርቲ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና የፓርቲውን የምርጫ ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀመረ
*********************
የብልፅግና ፓርቲ የጠቅላላ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲሁም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲውን የዕቅድ አፈጻጸም በጅግጅጋ ከተማ መገምገም ጀመረ።
ፓርቲው በምርጫ ዕቅዱ መሠረት በቅድመ ምርጫ እና በምርጫው ወቅት የነበረውን አጠቃላይ አፈጻጸም በጥልቀት እየገመገመ ነው።
በመድረኩ ላይ በሂደቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ ለማሳደግና በድክመት የተለዩ አፈጻጸሞችን በማረም ረገድ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #prosperityparty #ethiopiaelection2026 #jijiga

እየረበሽኩ ነው ለማለት ብቻ ከተማን ማሸበር ጤነኛ ስልት አይደለም ➡️
https://youtu.be/3_tebEkAl... #prosperityparty #pmabiyahmed #ethiopiaisvoting #7thgeneralelection
3 months ago
እንኳን ለዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን አደረሳችሁ፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
*******************
የአዲስ አበባ ሴቶች ዛሬ ማልዳችሁ ውቢቷን ቸርችል ጐዳና በመሙላት ለሰጣችሁን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ዛሬ በዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን መላው የከተማችን ሴቶች የተሳተፉበት በ7ኛው ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን ዓላማና ግብ የሚደግፍ፣ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
ባለፉት 5 ዓመታት በገባነው ቃል መሰረት የሴቶች ተጠቃሚነትንና ቁልፍ ውሣኔ ሰጪነት እንዲረጋገጥ ሰርተን ተሳክቶልናል።
የእናቶችን ጫና ለመቀነስ ልጆቻችሁ ያለምንም ሃሳብ ሁሉም ነገር ተሟልቶላቸው እንዲማሩ ከተማ አስተዳደራችን እጅግ ውጤታማ ስራ ሰርቷል።
በአበበች ጎበና የተሰየመ የእናቶችና የህፃናት ሆስፒታል በመገንባት፣ የነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ልህቀት ማዕከል በመገንባት፣ የእንጀራ ፋብሪካዎች ለሴቶች በመገንባት፣ በአጠቃላይ ባለፉት 5 ዓመታት ከፈጠርነው 2 ሚሊዮን የሥራ ዕድል 51 በመቶው ሴቶች እንዲሆኑ በመስራት፣ የሴቶችን አይተኬ ሚና እና ክብር የሚወክል አደባባይ በመገንባት እና የመሳሰሉ የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ክብር ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ፍሬ አፍርቷል።
አሁንም በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በከተማችን ካቀረብናቸው እጩዎች 54 በመቶ ሴቶች ናቸው። በከተማችን ምክር ቤት ከ40 በመቶ በላይ ሴቶች በመሆናቸው ከዚህ በፊት የነበረውን ተሳትፎ በበለጠ አልቀነዋል። ይህ ደግሞ ለአጃቢነት ሳይሆን የሴቶች ሚና አይተኬ መሆኑን በማመን ነው ።
በ7ኛው ምርጫ ብልፅግናን ስትመርጡ፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ታስቀጥላላችሁ፤ ሰላማችንም ዘላቂ ሆኖ ይረጋገጣል።
የምርጫ ምልክታችን የሥንዴ ነዶ ነው። ልክ እንደ ነዶው ተደምረን፤ ማንንም ያልተወ፣ ማንንም ያልዘነጋ አካታች ልማትን እያረጋገጥን እንቀጥላለን።
ባለፉት 5 ዓመታት የከተማችንን ሠላም በማረጋገጥ፣ ልማትን በማረጋገጥ አብራችሁን ስለነበራችሁ አዲስ አበባ ከልብ ታመስግናችኋለች።
መንገዳችን መደመር፤ መደረሻችን ብልፅግና ነው!
ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር !
#addisababa #womenempowerment #prosperityparty #adanechabiebie #ethiopia

ብልጽግና ፓርቲ በባሕር ዳር ከተማ የአደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ
**********************
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌታዊት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል ሰፊውን የማኅበረሰብ ክፍል ያሳተፈ የአደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ በከተማዋ አካሂዷል።
በከተማ አስተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞላ ሁሴን በቅስቀሳ መርሐ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ “ባለፉት ዓመታት በባሕር ዳር ከተማ የጀመርናቸው ሥራዎች ከተማዋን ውብ ከማድረግ ባሻገር በልማት ሥራዎች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እና ምቹነት ያረጋገጡ ናቸው” ብለዋል።
ለአብነትም ለከተማዋ ድምቀት የፈጠረውን የኮሪደር ልማት እና ታላቁን የዓባይ ወንዝ ድልድይን እንደማሳያነት አንሥተዋል።
ይህ ገና ጅማሮ ነው ያሉት ኃላፊው ፓርቲው በምርጫው ካሸነፈ ዘላቂ ሰላምን፣ ልማትንና ህብረብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ይሰራል ብለዋል።
ከተማዋ ወደ ታላቅ ከፍታ እንድትደርስ ይሠራል ሲሉም ገልጸዋል።
ፓርቲው ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያቀረባቸው ዕጩዎች የከተማዋን የልማት ከፍታ እና የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አስተዋፅኦ ያበረከቱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው ፓርቲው፣ ግልጽ ዓለማ ያሉት ወንድማማችነትን እና አንድነትን በማጠናከር ጠንካራ እና ተምሳሌት የሆነችውን ኢትዮጵያን ለመገንባት አልሞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ የሰላም እና የልማት ፓርቲ ነው ብለዋል።
ለዜጎች እኩል ተጠቃሚነት የሚተጋ ፓርቲ መሆኑንም ገልጸዋል። ከተማዋን በለውጥ ጉዞ ናት ያሉት አቶ ጎሹ እንዳላማው ፓርቲው ምርጫውን ካሸነፈ ይህን የለውጥ ጉዞ በተሻለ በማስቀጠል ከተማዋን የኢንቨስትመንት መዳረሻ የማድረግ ልማቶቿን የበለጠ በማፋጠን የዜጎቿን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ነው ያሉት።
በምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ-ግብሩ ላይ በከተማዋ የፓርቲው ዕጩ፣ አባላት እና ደጋፊዎች ወጥተው ተሳትፈዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ፓርቲው አቶ ተመስገን ጥሩነህን የብልጽግና ፓርቲ የባሕር ዳር ከተማ ምርጫ ክልል የህዝብ ተወካዮች፣ አቶ አረጋ ከበደ እና ወ/ሮ ሰላማዊት አለማየሁን የክልል ም/ቤት ዕጩዎች በማድረግ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንደሚወዳደርም ተመላክቷል።
ብልጽግና ፓርቲ "የስንዴ ነዶ" የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምልክቱ ማድረግ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
በሳሙኤል ወርቅአየሁ
#ebc #ethiopia #prosperityparty #demonstration

በታማኝነት እናገለግላችኋለን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተላለፉት መልዕክት
#prosperityparty #addisababa #ብልጽግና #አዲስ_አበባ
3 months ago
ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም እያካሄደ ነው
***************
ብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ-ግብሩን “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ስታዲየም እያካሄደ ይገኛል።
በቅስቀሳ መርሐ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎችም ብልጽግና ፓርቲን በመወከል ለአዲስ አበባ ምክር ቤት እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች ተገኝተዋል።
ከአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችም በመርሐ-ግብሩ ላይ በመገኘት ለእጩዎቹ ያላቸውን ድጋፍ እየገለጹላቸው ይገኛሉ።
ብልጽግና ፓርቲ፣ “የመደመር፣ የአብሮነት እና የአንድነት መገለጫ” ሲል የገለጸው የስንዴ ነዶ የዘንድሮው የምርጫ ምልክቱ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል።
#ebc #ethiopia #prosperityparty

4 months ago
"ብልፅግናን የምደግፈው ኢትዮጵያን ስለምወድ ነው!"
አርቲስት ካሙዙ ካሳ
#ethiopia | ታዋቂው የዜማና የቅንብር ባለሙያ ካሙዙ ካሣ በ "Art + plus" ፕሮግራም ላይ ተገኝቶ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች፣ በፖለቲካ አቋሙና በኪነ-ጥበብ ዙሪያ የማያሻማ አንኳር ነጥቦችን አንስቷል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
"ልማትንና እድገትን መደገፍ ትልቅ ሀገር ወዳድነት ነው። ብዙ ጊዜ መቃወም ብቻ ሀገር ወዳድነት ተደርጎ መታሰቡ ስህተት ነው።"
"ክቡር ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድን የምደግፈው ሀገሬን እያሳደጉ ስለሆነ ነው። እኔ ስለደገፍኩ የሚደረግልኝ ነገር የለም፤ ብሔራዊ ግዴታዬ ነው።"
"ዜና እና ዜማ መለየት አለበት። ለትችት ብቻ ግጥምና ዜማ ሰርቶ ስቱዲዮ መግባት ዜና እንጂ ጥበብ አይደለም፤ ጥበብ መፍትሄን መጠቆም አለበት።"
"አርቲስቱ መብቴ አልተከበረም ብሎ ከመጮህ ይልቅ ወደ መንግስት ጠጋ ብሎ መብቱን መጠየቅና ምን ላግዝ ብሎ መጠየቅ አለበት።"
"ተቺዎች ቢተቹኝም ግድ አይሰጠኝም፤ ለሙዚቃና ለአርት እድገት መስራቴን እቀጥላለሁ።"
ኢትዮጵያን በኪን (በጥበብ) በዓለም ህዝብ ዘንድ ታላቅ መሆኗን አስመስክረናል!
https://youtu.be/hTo3GqMrA...
#getu #kamuzukassa #ethiopianart #artplus #prosperityparty #ethiopianmusic #patriotism #abiyahmed #musicindustry #ethiopia #ካሙዙካሳ #ብልፅግና #ኢትዮጵያ #ጥበብ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
Comments