በፖለቲካው ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ አየጨመረ ነው ተባለ
#ethiopia | ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) አስመልክቶ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በሀገሪቱ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራትን ይፋ አድርጓል።
ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመግለጫቸው እንደተናገሩት፣ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ የሴቶች የመሬት ባለቤትነት ድርሻ 28 በመቶ መድረስ ተችሏል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ 60 በመቶ ያህሉ ሴቶች የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር እንዲያገኙ መደረጉን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
በፖለቲካው ዘርፍም የሴቶች ተሳትፎ አበረታች ደረጃ ላይ መድረሱን የጠቆሙት ዶ/ር ኤርጎጌ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች የውክልና ድርሻ 41 በመቶ መድረሱን በዋቢነት ጠቅሰዋል።
ዘንድሮ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረው ይህ በዓል፣ ከ1950ዎቹ ጀምሮ የነበረውን የታሪካዊ ጉዞና የሴቶች ተሳትፎ ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚገመግም እንደሚሆን ታውቋል።
በተለይም፦
* የሴቶችን የልማት ትልም ያመጣው ለውጥ፤
* የሴቶች የመደራጀት እንቅስቃሴ ውጤታማነት፤
* እና በሁሉም ዘርፍ የነበሩ ተግዳሮቶችና ስኬቶች በስፋት የሚዳሰሱበት መድረክ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል።
በተጨማሪም ሚኒስቴሩ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና
ከተፈጸሙም በኋላ ተጎጂዎች የሚያገግሙባቸውን ማዕከላት የማስፋፋት ሥራ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል። ከዚሁ ጎን ለጎንም የሕግ አካሄዶችን ተከትሎ ጥቃት አድራሾችን ተጠያቂ የማድረግና የሴቶችን ደህንነት የማስጠበቅ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #የሴቶችቀን #ማርች8 #የሴቶችመብት #ልማት #landrights #womenempowerment #ethiopia

3 months ago