4 months ago
"ታላቋ ሴት"
በውቢቷ ሀዋሳ የደመቀው የሴቶች የክብር ምሽት!
#ethiopia | ሄራ ኢቨንት እና ፕሮሞሽን በወ/ት እውነት ይሻል አዘጋጅነት፣ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሳውዝ እስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን ማዕከል ያደረገ ደማቅ የሽልማትና የክብር ፕሮግራም አካሂዷል።
ሀዋሳን ያቀኑ 15 አንጋፋ ባለሀብትና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች የተሸለሙ ሲሆን፣ 10 ተስፋ የተጣለባቸው ወጣት ሴቶች ደግሞ ለቀጣይ ዓመት ትልቅ ኃላፊነት ተረክበዋል።
አንጋፋዋ ዲዛይነር ወ/ሮ አበባ ዘነበ ተሰማ (የአበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ባለቤት) የሲዳማን ባህላዊ ይዘት የጠበቁ ዘመናዊ አልባሳትን በአፍሮ እና አንቅ ሞዴሎች አማካኝነት ለታዳሚው አስነኝተዋል።
የሆሊ ቤቴል ልዩ የጥርስ ሕክምና ባለቤት ወ/ሮ መስከረም አበራ ካለፉበት ከባድ ውጣ ውረድ እስከ ዛሬው ስኬታማ ደረጃ ያደረሳቸውን የጥንካሬ ጉዞ በእንባ በተሞላ ስሜት ለታዳሚው አካፍለዋል።
የ3 ዶክተሮች እናትና ስኬታማዋ የቢዝነስ ሴት ወ/ሮ አያልነሽ አለሶ እንዲሁም በኢኮኖሚና በበጎ ተግባር ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑት ወ/ሮ ይርጋለም አሰፋ በልዩ ተሸላሚነት ደምቀው የታዩበት ምሽት ነበር።
የአዘጋጇ መልዕክት
የሄራ ኢቨንት እና ፕሮሞሽን መስራች ወ/ት እውነት ይሻል ዝግጅቱ በየዓመቱ በሴቶች ቀን የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው፣ ለፕሮግራሙ መሳካት አብረዋቸው የቆሙትን ደጋፊ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በሙሉ ከልብ አመስግነዋል።
🙏 ልዩ ምስጋና
ሳውዝ እስታር ሆቴል፣ የደቡብ ቴሌቪዥን፣ ንጉስ ቢራ፣ ቤዛ ስፕሪንግ ዋተር፣ አበባ ሹራብ፣ የሀዋሳ ከንቲባ ጽ/ቤት እና ለሄራ ኢቨንት ቡድን አባላት፣ አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻ ኢንተርፕራይዝ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ፣ አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻ ኢንተርፕራይዝ
#thegreatwomen #hawassa #ethiopia #heraevents #womenempowerment #successstories #fashionshow #southstarhotel #sidamaculture #inspiration #getutemesgenmedia

Comments