6 months ago
''እንደ ወይን በክብር መብሰል''
📌 የሴቶችን ተፈጥሯዊ የህይወት ጉዞ የሚያከብር ልዩ መድረክ ተካሄደ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ሴቶች ዕድሜ መጨመር፣ ውበት እና ማህበራዊ ዋጋ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመቀየር ያለመ “እንደ ወይን በክብር መብሰል” የተሰኘ ልዩ ውይይት ተከናወነ።
በታዋቂዋ ጋዜጠኛ የሸዋ ማስረሻ መሥራችነት በሚመራው ኢምፓክት መልቲ ሚዲያ አዘጋጅነት የቀረበው ይህ ዝግጅት፤ ዕድሜ መጨመርን እንደ ፀጋ በመቁጠር ሴቶች በህይወት ጉዟቸው እንዲኮሩና እንዲነቃቁ ለማድረግ ያለመ ነው። በመርሀ ግብሩ ላይ ከ100 በላይ የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች እና ወንዶች ተሳትፈዋል።
በመርሃግብሩ ላይ ስለ ሴቶች ዕድሜ መጨመር የሚነገሩ አሉታዊ ትርክቶችን በማስቀረት፣ ሽግግሩን በክብርና በኩራት የመቀበል ባህልን ማሳደግ ፣ ሴቶች በዕድሜ መጨመር ሂደት ውስጥ የሚያልፉባቸውን አካላዊ፣ ስሜታዊ እና ማህበራዊ ለውጦች (ለምሳሌ፦ የወር አበባ መቆም ወይም Menopause) በተመለከተ ትምህርት መስጠት ላይ ያተኮረ ሲሆን ስኬታማና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች የህይወት ታሪካቸውንና የጥበብ ጉዟቸውን በማጋራት ለተሳታፊዎች ተነሳሽነትን መፍጠር ተችላል።
በትውልዶች መካከል መከባበር፣ መረዳዳት እና መደጋገፍ እንዲኖር የሚያስችሉ ውይይቶችን ማካሄድ።
ይህ መድረክ በኢትዮጵያ ስለ ውበት እና ስለ ስብዕና ያለውን ትርጉም በአዲስ መልክ የሚጽፍ ሲሆን፣ በአሳታፊ ታሪኮች እና በዲጂታል ይዘቶች የታጀበ በመሆኑ በማህበረሰቡ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያሳርፋል ተብሎ ይታመናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#agingwithgrace #celebrateher #womenempowerment #impactmultimedia #positiveaging #menopauseawareness #breakingstereotypes #wiseandbeautiful #timelessbeauty

Comments