5 months ago
የ‘U-GIRLS 2’ ፕሮጀክት የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተከናወነ
#ethiopia | በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለስድስት ዓመታት ሲተገበር የቆየውና በሴት ተማሪዎች ሕይወት ላይ ጉልህ ለውጥ ያመጣው የ‘U-GIRLS 2’ ፕሮጀክት የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተከናውኗል። ፕሮጀክቱ በኩሶ ኢንተርናሽናል ድጋፍ ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ በክልሉ የሚገኙ የሴት ተማሪዎችን የትምህርትና የማኅበራዊ ሕይወት ለመለወጥ የተሳካ ሥራዎችን አከናውኖ መጠናቀቁ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የቀረቡ ዋና ዋና ስኬቶች እነሆ፦
የተደራሽነትና የድጋፍ ስፋት
* ተጠቃሚዎች፦ ፕሮጀክቱ በክልሉ በሚገኙ ሰባት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ 23,816 ሴት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።
* የቁሳቁስ ድጋፍ፦ ለተማሪዎቹ የመማሪያ ቁሳቁሶች (ደብተር፣ ቦርሳ፣ ጫማ፣ ዩኒፎርም) ከመቅረባቸውም በላይ ለትምህርት ቤቶቹ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር (Desk) እና ኮምፒውተሮች ተከፋፍለዋል።
* መሰረተ ልማት፦ ሰባቱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተሟላ የሶላር ኃይል አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።
የአቅም ግንባታና ስልጠናዎች
* ለትማሪዎች፦ ከአካዳሚክ ማጠናከሪያ ትምህርት በተጨማሪ በሥራ ፈጠራ፣ በገንዘብ አያያዝ፣ በሕይወት ክህሎትና በሥነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ተከታታይ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል።
* ለማኅበረሰቡ፦ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራንና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በሥርዓተ-ጾታ እኩልነትና በተለያዩ የአቅም ግንባታ መስኮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የፕሮጀክቱ አበርክቶ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንደገለጸው፣ ፕሮጀክቱ ሴቶች በትምህርታቸው ጠንካራና መፍትሔ አምጪ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በተጨባጭ ከፍ አድርጓል። የማኅበረሰቡ አባላትና ትምህርት ቤቶችም ፕሮጀክቱ ለችግራቸው ተደራሽ እንደነበር ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
የመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ፕሮጀክቱ በይፋ መጠናቀቁ ቢበሰርም፣ ክልሉ መሰል የድጋፍ ፕሮግራሞች በቀጣይነት እንዲመቻቹ ያለውን ፍላጎት ገልጿል።
📸ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ #የሴቶች_ትምህርት #ኩሶ_ኢንተርናሽናል #u_girls_2 #ኢትዮጵያ #ትምህርት #genderequality #cusointernational

7 months ago
ዳሸን ባንክ ሴት ሰራተኞቹን የማብቃት መርሃ-ግብር አካሄደ
#ethiopia | ዳሸን ባንክ የሴት ሰራተኞቹን አቅም ለማጎልበትና ወደ ከፍተኛ አመራርነት ለማምጣት የጀመረው "አጠቃላይ የሴቶች አቅም ማጎልበት መርሃ-ግብር" አንደኛ ዓመት የምክክር መድረክ በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሂዷል።
✅ የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በመርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት ባንኩ ላለፉት 30 ዓመታት ሴቶችን ወደ አመራር በማምጣት ተጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ አሁንም ሴቶች ለባንኩ እድገት ትልቅ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አረጋግጠዋል።
✅ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከ140 በላይ ሴት ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ዕድል አግኝተዋል።
✅ በአንድ አመት ውስጥ አራት የትስስር የውይይት መድረኮች የተካሄደ ሲሆን በእያንዳንዱ የውይይት መድረኮች ላይ ከ200 በላይ ታዳሚዎች ተሳትፈዋል።
✅ ዳሽን ባንክ 11 ሺህ በላይ ቋሚ ሰራተኞች መካከል ከ3,300 በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
✅ በመድረኩ ላይ ኘሮፌሰር የዓለምፀሐይ መኮንን፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ተገኝተው ለተሳታፊዎች የህይወትና የሥራ ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።
ይህ መርሃ-ግብር የሴቶችን የአመራር ክህሎት በማሳደግ የባንኩን ስኬት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
📷 ከበደ መክብብ #dashenbank #womenempowerment #leadership #ethiopia #banking #genderequality

Comments