Logo
Getu Temesgen
🌊 "የባህር በር ተደራሽነት ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው!"
— ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 🇪🇹📢
#ethiopia | ​ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በድጋሚ በዓለም አቀፍ መድረክ አጽንኦት ሰጥተውበታል።

​ቁልፍ መልዕክቶች፦
​⚓️ የህልውና ጉዳይ፦
ኢትዮጵያ በሰላማዊ አማራጮች አስተማማኝ የባህር በር ተደራሽነትን ማረጋገጥ መሠረታዊ እና የማይታለፍ ጉዳይ መሆኑን በጽኑ ገልጸዋል።

​📈 መሰረተ ልማት እና ብልጽግና፦
ሀገሪቱ በአየር መንገድ፣ በቴሌኮምና በመንገድ ዘርፎች የገነባቻቸው ግዙፍ መሰረተ ልማቶች ሙሉ ትርጉም እንዲኖራቸው የባህር በር ተደራሽነት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

​🤝 ሰላማዊ አማራጭ፦
የባህር በር ጥያቄው ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰላማዊ መንገድ እና በጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) መርህ ላይ ተመስርቶ ሊፈታ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

​🌍 ቀጣናዊ ትስስር፦
ይህ ስኬት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናዊ ትስስርና ለጋራ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።

​ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ ይህ ጥረት አህጉራዊውን ‘አጀንዳ 2063’ ግቦችን ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

​#pmabiyahmed #ethiopia #africanunion #ausummit #seaport #redsea #regionalintegration #agenda2063 #addisababa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.