26 days ago
አዲስ አበባ — የBRICS እና የአፍሪካ አህጉር አዲሷ የኃይል ማዕከል
➡ https://youtu.be/OSXEjO5at...
#brics2026 #agenda2063 #africandiplomacy #ethiopianairlines #addisababa
8 months ago
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ
📍የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ ተጠናቀቀ
#ethiopia | በአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ፣ የአህጉሪቱን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያፋጥኑ ስልታዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጠናቋል።
ጉባኤው “ዘላቂ የውኃ አቅርቦት እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ የተመራ ሲሆን፣ የአህጉሪቱ መሪዎች በውኃ ደኅንነት፣ በኢኮኖሚ ትሥሥር እና በተቋማዊ ሪፎርሞች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
የጉባኤው ዋና ዋና አጀንዳዎች እና ውሳኔዎች
መሪዎቹ በ48ኛው የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት የቀረቡለትን የውሳኔ ሐሳቦች መነሻ በማድረግ በሚከተሉት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፦
✅ የውኃ ደኅንነትና አጀንዳ 2063፦ አስተማማኝ የውኃ አቅርቦት ለአህጉራዊው የዕድገት ዕቅድ (አጀንዳ 2063) ስኬታማነት መሠረታዊ መሆኑ ተገልጾ፣ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል።
✅ አህጉራዊ ትሥሥርና የሰው ኃይል ልማት፦ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ትሥሥር ማጠናከር እና በሰው ኃይል ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ለነገዋ አፍሪካ ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል።
✅ ተቋማዊ ሪፎርም፦ የኅብረቱን የፋይናንስ አቅም ማሳደግ፣ ተቋማዊ አወቃቀሩን ማዘመን እና አሠራሮችን ግልጽ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።
✅ ዓለም አቀፍ ተሰሚነት፦ አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ድምፅና ተሰሚነት ማሳደግ እንዲሁም ስልታዊ አጋርነቶችን ስለማጠናከር ውሳኔዎች ተላልፈዋል።
በጉባኤው ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ላደረጉት ደማቅ አቀባበል እና ጉባኤው በሰላም ተጀምሮ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋፅዖ የላቀ ምስጋና ቀርቧል።
ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ
ጌትነት ተመስገን
#au #africaunion #ethiopia #addisababa #globalsouth #agenda2063

#ethiopia | በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የሀገራት መሪዎች የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በተመለከተ ጠንካራ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪነት ያላትን ድርሻ በተመለከተ ደፋር ጥሪ አቅርበዋል። "ይህ 2026 እንጂ 1946 አይደለም" ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አፍሪካውያን ለችግሮቻቸው አፍሪካዊ መፍትሔ የመስጠት አቅም እንዳላቸው ጠቅሰው፤ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለጋራ ብልጽግና ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የአውሮፓ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በአፍሪካ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመጥቀስ፣ ጣሊያን በአህጉራቱ መካከል እንደ ድልድይ ሆና እንደምታገለግልና ስደትን ለመቀነስ የሥራ ዕድል መፈጠር እንዳለበት አሳስበዋል።
የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሙስጠፋ አፍሪካ ለፍልስጤም ነፃነትና ሉዓላዊነት ለምታሳየው ጽኑ አጋርነት ምስጋና አቅርበው፣ አህጉሪቱ ለሰላም የምታደርገውን ድጋፍ እንድታጠናክር ጠይቀዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ "ውሃ እና ንጽህና አጠባበቅ” " በሚል መሪ ቃል፤ የመሰረተ ልማት ትስስር፣ የነፃ ንግድ ቀጠና እና የወጣቶች የፈጠራ ክህሎት ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።

🌊 "የባህር በር ተደራሽነት ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው!"
— ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
📢
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በድጋሚ በዓለም አቀፍ መድረክ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
ቁልፍ መልዕክቶች፦
⚓️ የህልውና ጉዳይ፦
ኢትዮጵያ በሰላማዊ አማራጮች አስተማማኝ የባህር በር ተደራሽነትን ማረጋገጥ መሠረታዊ እና የማይታለፍ ጉዳይ መሆኑን በጽኑ ገልጸዋል።
📈 መሰረተ ልማት እና ብልጽግና፦
ሀገሪቱ በአየር መንገድ፣ በቴሌኮምና በመንገድ ዘርፎች የገነባቻቸው ግዙፍ መሰረተ ልማቶች ሙሉ ትርጉም እንዲኖራቸው የባህር በር ተደራሽነት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
🤝 ሰላማዊ አማራጭ፦
የባህር በር ጥያቄው ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰላማዊ መንገድ እና በጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) መርህ ላይ ተመስርቶ ሊፈታ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
🌍 ቀጣናዊ ትስስር፦
ይህ ስኬት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናዊ ትስስርና ለጋራ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ ይህ ጥረት አህጉራዊውን ‘አጀንዳ 2063’ ግቦችን ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
#pmabiyahmed #ethiopia #africanunion #ausummit #seaport #redsea #regionalintegration #agenda2063 #addisababa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

🌍 "የህዳሴው ግድብ (GERD) ለአፍሪካ የራስ አቅም ግንባታ ተምሳሌት ነው!"
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን
💡
#ethiopia | አፍሪካ ያላትን 4.6 ትሪሊዮን ዶላር ሀብት በመጠቀም የራሷን ፕሮጀክቶች መገንባት እንደምትችል ግድቡ አሳይቷል
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ መቃረቡን ተከትሎ፤ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) አፍሪካውያን በራሳቸው አቅም እና በሀገር ውስጥ ሀብት (Domestic Resources) ግዙፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት እንደሚችሉ ያሳየ "ሕያው ተምሳሌት" (Model) አድርጎ አቅርቦታል።
የኮሚሽኑ መልዕክት:
አሁን ላይ 300 ሚሊዮን አፍሪካውያን የንጹህ ውሃ አቅርቦት ችግር ያለባቸው ሲሆን፤ ይህንን ለመፍታት የ30 ቢሊዮን ዶላር ክፍተት አለ። ኮሚሽኑ አገራት ይህንን ክፍተት ለመሙላት የውጭ እርዳታን ከመጠበቅ ይልቅ፤ ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ እንዳደረገችው የአፍሪካን 4.6 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት የተፈጥሮ እና የገንዘብ ሀብት (Assets) ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስቧል።
ይህም የአፍሪካን የልማት ፕሮግራም (PIDA) ለማፋጠን እና የአጀንዳ 2063 ራዕይን ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ ነው።
የህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ኩራት ነው!
#gerd #africanunion #ausummit #agenda2063 #infrastructure #ethiopia #africarising #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
Comments