3 months ago
የኢትዮጵያ የደኅንነት እና የፀጥታ ተቋማት ሁለንተናዊ አቅም
**************************
ኢትዮጵያ ታሪካዊ ክብሯን እና የሕዝቦቿን ሰላም ለማስጠበቅ የገነባቻቸው የደኅንነት እና የፀጥታ ተቋማት በማንኛውም ዓይነት የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላት ሤራ የማትበገር እና የማትሸበር ጽኑ ሀገር መሆኗን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ።
ይህ አስተማማኝ አቅም የተገነባው ከሀገር መከላከያ ባሻገር ዘመኑ በደረሰበት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እና የሥልጠና ልክ ራሳቸውን ባደራጁ ልዩ ልዩ የደኅንነት፣ የቴክኖሎጂ እና የስትራቴጂክ ተቋማት ጥምረት ነው።
በዚህ ዘመናዊ የደኅንነት መዋቅር ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የኢፌዴሪ አየር ኃይል የላቁ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስልታዊ ድሮኖችን በመታጠቅ የአየር ክልሉ ፍፁም የማይደፈር አድርጎታል።
ከዚህ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የኢትዮጵያን የወደፊት ላይ ጥቅም እና ቀጣናዊ ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ሌት ተቀን እየተጋ የሚገኝ ስልታዊ ተቋም ነው።
የዘመኑ ጦርነት ከሜዳ ባለፈ በቴክኖሎጂ የሚመራ በመሆኑ በሳይበር ምህዳር ኢትዮጵያን ለመጠበቅ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (INSA) እና የስትራቴጂክ መረጃዎችን አስቀድሞ በመተንተን ሴራዎችን የሚያከሽፈው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት (NISS) ሌሎቹ የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንቶች ናቸው።
እነዚህ ተቋማት የሀገርን የዲጂታል ሉዓላዊነት የባንክ እና የኮሙኒኬሽን መዋቅሮችን ከሳይበር ጥቃት ከመታደግ ባለፈ ጠላቶች የሚነዙትን የሥነልቦና ጦርነት እና ድብቅ ሤራዎች አስቀድመው በማምከን ረገድ ወደር የለሽ አቅም ገንብተዋል።
ይህ የተቀናጀ የተቋማት ግንባታ ኢትዮጵያ በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆን የማትነቃነቅ በልጆቿ ጥበብ እና ፅናት የምትመራ መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ እና ለትውልድ የሚተርፍ ታላቅ ሀገራዊ ኩራት ነው።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #nationalsecurity #airforce #maritimedefense #insa #cybersecurity #ethiopiadefends

Comments