2 months ago
የወደፊት መሃንዲሶች መድረክ፦
የሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ነገ በሳይንስ ሙዚየም ይከፈታል!
#ethiopia | የዓመቱ "ምርጥ ችግር ፈቺ" ሽልማትን የሚወስደው ማን ይሆን? የኢትዮ ሮቦቲክስ "እኔ ችግር ፈቺ ነኝ" የፓን አፍሪካ ውድድር ነገ ሐሙስ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በደመቀ ሁኔታ ይከፈታል።
በውድድሩ ምን ይጠብቃችኋል?
የታዳጊዎች አስደናቂ ሮቦቶች፣ የኮዲንግ (Coding) እና የዲዛይኒንግ ውጤቶች ለዕይታ ይቀርባሉ።
ለሀገራዊ ችግሮች ምላሽ የሚሰጡ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች የሚቀርቡበት ልዩ መድረክ ነው።
የኢትዮጵያንና የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ጉዞ የሚመሩ ታዳጊዎችን የምናበረታታበት ታላቅ ክስተት ነው።
በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም
ነገ፣ ሐሙስ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም
ኑ!
የነገ መሃንዲሶቻችንን አብረን እናበረታታ!
የቴክኖሎጂ አቅማችንን በታዳጊዎቻችን ዓይን እንመልከት።
#getu #ethiorobotics #problemsolver #panafricanrobotics #sciencemuseum #ethiopiatech #codingforkids #stem #futureengineers #addisababa #ሮቦቲክስ #ሳይንስሙዚየም #ቴክኖሎጂ #ታዳጊዎች #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ48.8 ሚሊዮን ዶላር የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቱን እያፋጠነ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎችን የክፍያ ሥርዓት ወደ ዘመናዊ የዲጂታል መንገድ ለመቀየር የጀመረውን ግዙፍ ፕሮጀክት በስፋት እያከናወነ ይገኛል። ተቋሙ 500 ሺህ ስማርት የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን ለመግጠም ለጀመረው ለዚሁ ፕሮጀክት 48.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ማድረጉ ተገልጿል።
እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከ67 ሺህ በላይ ደንበኞች የዘመናዊው ቆጣሪ ተጠቃሚ መሆን የጀመሩ ሲሆን፣
ዝርዝር አፈጻጸሙም 🔎
* 60,457 ነጠላ ፌዝ (Single Phase) ቆጣሪዎች፦ እስከ 7.5 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ መኖሪያና ንግድ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ ነው።
* 7,013 ባለ ሦስት ፌዝ (Three Phase) ቆጣሪዎች፦ ከ8 እስከ 24 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችና ቤቶች ተገጥመዋል።
ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ሽግግር ደንበኞች ቀደም ሲል የኤሌክትሪክ ቶክን ለመግዛት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በማቅናት ያባክኑት የነበረውን ጊዜና ጉልበት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ነው።
ደንበኞች በፈለጉት ሰዓት (በ24 ሰዓት) ባሉበት ሆነው፦
* በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE Birr/App)
* በቴሌ ብር (telebirr)
* በአዋሽ ባንክ መተግበሪያዎች አማካኝነት
በቀላሉ ክፍያቸውን መፈጸም ይችላሉ።
ይህ እርምጃ የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ከማሳለጡ ባለፈ፣ ለኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትና አስተማማኝነት ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianelectricutility #eeu #digitaltransformation #smartmeter #prepaidelectric #ethiopiatech #cbe #telebirr #awashbank #energyupdate

3 months ago
🇪🇹 ድል ለኢትዮጵያ!
StriveInን በመምረጥ የሀገራችንን የቴክኖሎጂ ውጤት እናንግሥ! 🚀
#ethiopia | በመላው ዓለም ትኩረት የተሰጠው የFounders Live የንግድ ሃሳቦች ውድድር የአፍሪካ አህጉር ፍፃሜ ደርሷል።
በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው አሰሪና ሰራተኛን በዲጂታል መንገድ የሚያገናኘው StriveIn የተሰኘው የፍሪላንስ መተግበሪያ ነው።
📅 የውድድሩ መርሃ ግብር፦
የአፍሪካ ፍፃሜ፦
አርብ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት።
የዓለም ፍፃሜ፦
ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (የአፍሪካን አሸናፊ ለ 10,000 ዶላር ሽልማት ያበቃዋል)።
🗳️ እንዴት ድምፅ እንስጥ?
ላይቭ መከታተል፦
አርብ ምሽት 2:00 ሰዓት ሲሆን በዚህ የዩቱዩብ ሊንክ https://www.youtube.com/wa... ቀጥታ ስርጭቱን ይከታተሉ።
ማብራሪያውን መስማት፦
የStriveIn መስራች በረከት ሺመክት ስለ ስራው የ99 ሴኮንድ ገለጻ ያደርጋል።
ድምፅ መስጠት፦
ከገለጻው በኋላ በሚለቀቀው የድምፅ መስጫ ሊንክ ላይ StriveIn የሚለውን በመምረጥ ለሀገርዎ ተወዳዳሪ ድጋፍዎን ይግለጹ።
💡 ለምን StriveInን እንመርጣለን?
StriveIn ለብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድልን የሚፈጥር፣ የፍሪላንስ ሥራን የሚያቀላጥፍና ሀገራችን በዲጂታል ኢኮኖሚ ያላትን አቅም ለዓለም የሚያሳይ ፈጠራ በመሆኑ ሁላችንም ከጎኑ ልንቆም ይገባል።
የአፍሪካን አሸናፊነት አረጋግጠን ወደ ዓለም አቀፉ የ10,000 ዶላር ሽልማት እናሸጋግራቸው!
እባክዎን ይህንን መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ Share እናድርግ
#strivein #founderslive #ethiopiatech #startupethiopia #freelanceapp #africafinest #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን