የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ48.8 ሚሊዮን ዶላር የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቱን እያፋጠነ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎችን የክፍያ ሥርዓት ወደ ዘመናዊ የዲጂታል መንገድ ለመቀየር የጀመረውን ግዙፍ ፕሮጀክት በስፋት እያከናወነ ይገኛል። ተቋሙ 500 ሺህ ስማርት የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን ለመግጠም ለጀመረው ለዚሁ ፕሮጀክት 48.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ማድረጉ ተገልጿል።
እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከ67 ሺህ በላይ ደንበኞች የዘመናዊው ቆጣሪ ተጠቃሚ መሆን የጀመሩ ሲሆን፣
ዝርዝር አፈጻጸሙም 🔎
* 60,457 ነጠላ ፌዝ (Single Phase) ቆጣሪዎች፦ እስከ 7.5 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ መኖሪያና ንግድ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ ነው።
* 7,013 ባለ ሦስት ፌዝ (Three Phase) ቆጣሪዎች፦ ከ8 እስከ 24 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችና ቤቶች ተገጥመዋል።
ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ሽግግር ደንበኞች ቀደም ሲል የኤሌክትሪክ ቶክን ለመግዛት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በማቅናት ያባክኑት የነበረውን ጊዜና ጉልበት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ነው።
ደንበኞች በፈለጉት ሰዓት (በ24 ሰዓት) ባሉበት ሆነው፦
* በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE Birr/App)
* በቴሌ ብር (telebirr)
* በአዋሽ ባንክ መተግበሪያዎች አማካኝነት
በቀላሉ ክፍያቸውን መፈጸም ይችላሉ።
ይህ እርምጃ የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ከማሳለጡ ባለፈ፣ ለኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትና አስተማማኝነት ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianelectricutility #eeu #digitaltransformation #smartmeter #prepaidelectric #ethiopiatech #cbe #telebirr #awashbank #energyupdate

2 months ago