27 days ago
የኢትዮጵያው የቴክኖሎጂ ስታርትአፕ ከአፍሪካ ምርጥ 15 ውስጥ ተካተተ
#ethiopia | በአለማየሁ ሰይፉ የተመሠረተውና በኢንተርፕራይዝ ሶፍትዌር መፍትሔዎች ላይ የሚሠራው ማራኪሶፍት (Marakisoft) የተባለው የኢትዮጵያ ስታርትአፕ፣ በመላው አፍሪካ ከ500 በላይ አመልካቾች መካከል ተመርጦ በአህጉሪቱ ምርጥ 15 ስታርትአፖች ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ተገለጸ።
ምርጫውን ያካሄደው ፓን-አፍሪካዊው የኢንቨስትመንት ተቋም ሪኒው ካፒታል (Renew Capital) ሲሆን፣ በመጀመሪያው "Renew Venture Lab" መርሃ ግብር ከ48 የአፍሪካ አገራት የቀረቡ ኩባንያዎችን አወዳድሯል። ከእነዚህም 47 ኩባንያዎች ለፒች (Pitch) ውድድር ከተመረጡ በኋላ፣ 10 አገራትን የሚወክሉ 15 ስታርትአፖች ለላቀ ቴክኒካዊ ስልጠናና ለቀጣይ የኢንቨስትመንት ግምገማ ተመርጠዋል።
ውድድሩ በEmbedded Finance ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ይህም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደ ብድር፣ ኢንሹራንስ እና የክፍያ አገልግሎቶችን በቀጥታ በራሳቸው ዲጂታል መድረኮች ላይ በማቀናጀት ለአነስተኛና መካከለኛ ንግዶች እንዲደርሱ የሚያስችል የፋይናንስ ሞዴል ነው።
ሪኒው ካፒታል እንደገለጸው፣ የአፍሪካ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በየዓመቱ 330 ቢሊዮን ዶላር የብድር ክፍተት ያጋጥማቸዋል። እንደ ማራኪሶፍት ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የደንበኞቻቸውን የንግድ መረጃ በመጠቀም ይህንን የፋይናንስ ክፍተት ለመቀነስ አስፈላጊ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉም አመልክቷል።
ማራኪሶፍት በ17 ዓመታት የሥራ ልምዱ ከ5,000 በላይ ደንበኞችን በማገልገል፣ የERP እና POS ሶፍትዌር መፍትሔዎችን በኢትዮጵያ በማልማት የሚታወቅ ኩባንያ ነው።
በመጨረሻ ዙር የደረሱት 47 ስታርትአፖች እያንዳንዳቸው ከ250,000 ዶላር በላይ ዋጋ ያለውን የድጋፍ ፓኬጅና የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ምክር ያገኙ ሲሆን፣ አሁን በምርጥ 15 ውስጥ የተካተቱት ኩባንያዎች ለቀጣይ የፋይናንስ ኢንቨስትመንት ምዘና ሂደት ላይ ይገኛሉ።
EBR
#ethiopiantech #marakisoft #renewcapital #embeddedfinance #startupethiopia #africatech #smes #getutemesgen

5 months ago
🇪🇹 ድል ለኢትዮጵያ!
StriveInን በመምረጥ የሀገራችንን የቴክኖሎጂ ውጤት እናንግሥ! 🚀
#ethiopia | በመላው ዓለም ትኩረት የተሰጠው የFounders Live የንግድ ሃሳቦች ውድድር የአፍሪካ አህጉር ፍፃሜ ደርሷል።
በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው አሰሪና ሰራተኛን በዲጂታል መንገድ የሚያገናኘው StriveIn የተሰኘው የፍሪላንስ መተግበሪያ ነው።
📅 የውድድሩ መርሃ ግብር፦
የአፍሪካ ፍፃሜ፦
አርብ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት።
የዓለም ፍፃሜ፦
ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (የአፍሪካን አሸናፊ ለ 10,000 ዶላር ሽልማት ያበቃዋል)።
🗳️ እንዴት ድምፅ እንስጥ?
ላይቭ መከታተል፦
አርብ ምሽት 2:00 ሰዓት ሲሆን በዚህ የዩቱዩብ ሊንክ https://www.youtube.com/wa... ቀጥታ ስርጭቱን ይከታተሉ።
ማብራሪያውን መስማት፦
የStriveIn መስራች በረከት ሺመክት ስለ ስራው የ99 ሴኮንድ ገለጻ ያደርጋል።
ድምፅ መስጠት፦
ከገለጻው በኋላ በሚለቀቀው የድምፅ መስጫ ሊንክ ላይ StriveIn የሚለውን በመምረጥ ለሀገርዎ ተወዳዳሪ ድጋፍዎን ይግለጹ።
💡 ለምን StriveInን እንመርጣለን?
StriveIn ለብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድልን የሚፈጥር፣ የፍሪላንስ ሥራን የሚያቀላጥፍና ሀገራችን በዲጂታል ኢኮኖሚ ያላትን አቅም ለዓለም የሚያሳይ ፈጠራ በመሆኑ ሁላችንም ከጎኑ ልንቆም ይገባል።
የአፍሪካን አሸናፊነት አረጋግጠን ወደ ዓለም አቀፉ የ10,000 ዶላር ሽልማት እናሸጋግራቸው!
እባክዎን ይህንን መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ Share እናድርግ
#strivein #founderslive #ethiopiatech #startupethiopia #freelanceapp #africafinest #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments