2 months ago
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት 118.91 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት አስመዝግቦት የነበረውን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን አብዛኞቹን ዋና ዋና ግቦች በላቀ ደረጃ ማሳካት መቻሉን እና በተለይም በአዳዲስ ደንበኞች ትስስር ረገድ በተቋሙ ታሪክም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ውጤት ማስመዝገቡን ይፋ አድርገዋል።
በበጀት ዓመቱ 800 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ 664 ሺህ 505 አባወራዎችን በማገናኘት የ83.1 በመቶ ስኬት ተመዝግቧል።
ይህም አፈጻጸም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ32.5 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን፣ ተቋሙን በዓይነቱ ከአፍሪካ መሰል የኃይል አቅርቦት ኩባንያዎች የመሪነት ደረጃ ላይ አሰልፎታል።
በተጨማሪም የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራሙን በማጠናከር ከዋናው ግሪድ እና ከኦፍ-ግሪድ የፀሐይ ኃይል አማራጮች 205 አዳዲስ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም በአገሪቱ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ተደራሽ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን ቁጥር ወደ 7 ሺህ 908 አድርሶታል።
በፋይናንስና በገቢ አሰባሰብ ረገድም ተቋሙ አስደናቂ ስኬት ያስመዘገበ ሲሆን፣ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዳዲስ ደንበኞች መስተንግዶና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 115.86 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 118.91 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የ103 በመቶ አፈጻጸም አሳይቷል።
ይህ የገቢ መጠን ከቀደመው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ88.4 በመቶ ከፍተኛ እድገት ያሳየ ነው። ለዚህ አፈጻጸም መሻሻል የዲጂታል ክፍያ አማራጮች መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የዲጂታል ክፍያ የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር 95.3 በመቶ ደርሷል።
በተጨማሪም ተቋሙ ከስርቆትና ከኃይል ብክነት የመከላከል ሥራዎችን በማጠናከር ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ለተቋሙ ገቢ ማድረግ ችሏል።
ተቋሙ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማሻሻያ፣ የትራንስፎርመር ጥገናና የአቅም ማሳደግ ሥራዎችን ያከናወነ ቢሆንም፣ አሁንም የመሰረተ ልማት እርጅና፣ የግብዓትና የነዳጅ እጥረት እንዲሁም የመሰረተ ልማቶች ስርቆትና ውድመት ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተገልጿል።
ሆኖም ተቋሙ የተደቀኑበትን ተግዳሮቶች በመቋቋም የቴክኖሎጂ ትግበራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬት የሚጠበቅበትን የላቀ ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
ጌትነት ተመስገን
#ethiopianelectricutility #eeu #ethiopia #energysector #ethiopianeconomy #digitalethiopia2030 #ruralelectrification #offgridenergy #performancereport #africaenergy

የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የኃይል ዘርፍ ትብብር
******************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሀገሪቱን የኢነርጂ ዘርፍ ወደ ላቀ የዲጂታል እና የዘመናዊነት ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ወሳኝ ውይይት ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ልዑካን ጋር አካሂዷል።
ውይይቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፣ በአሜሪካ መንግስት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ሚስተር ማርክ ትራውንተር ሚቼል የተመራውን ልዑክ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
በምክክሩ ላይ የኤሌክትሪክ ስርጭት አውታር መረብን (Grid) ማዘመን፣ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠን፣ ስማርት ቆጣሪዎችን ማስፋፋት፣ ንጹህ ኢነርጂን ማልማት እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን (EVs) ማበረታታት ዋነኛ አጀንዳዎች ነበሩ። ከዚህም በተጨማሪ ያልተነኩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የአቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል።
ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በውይይቱ ወቅት፣ ተቋማቸው ለደንበኞች ምቹ፣ ጠንካራ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈጠራንና ቴክኖሎጂን አቅፎ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የረጅም ዓመታት ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ተጨባጭ የልማት ፕሮጀክቶች እንደሚሸጋገር ያላቸውን ጽኑ እምነት መግለጻቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
ሚስተር ማርክ ትራውንተር ሚቼል እና ልዑካን ቡድናቸው በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የዘመናዊነት እርምጃዎችን አድንቀው፣ የሀገሪቱን የኃይል ዘርፍ አስተማማኝነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ይህ የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በማስፋፋት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገትና የኢንዱስትሪ ሽግግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚደግፍ ተጠቁሟል።
#ethiopia #ethiopianelectricutility #energysector #cleanenergy #usethiopia

5 months ago
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞች የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው ቦታዎች ፦
✅ከጠዋቱ 2:00 እስከ 9:30
👉በኤሞሌስ ፋብሪካ፣ በካሰዴ፣ በጣፎ፣ በ44 ማዞሪያ ፣ በሰንዳፋ ጫፍ፣ በለገጣፎ፣ በሲዲሲ ፣ በኮሰሮ፤
✅ከጠዋቱ 3:00 እስከ 9:00
👉በላዘዘሪስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ በማርቆስ መጋዘን፣ በእ/አብ ሰፈር ከማርቆስ ከፍ ብሎ፣ በጸሐይ ጮራ ት/ቤት ፣ በስፓኒሽ ኤምባሲ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በተፈሪ መኮንን ውኃ ልማት ቢሮ፤
✅ከጠዋቱ 3:00 እስከ 12:00
👉በታጠቅ ሙገር ሲሚንት ፋብሪካ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻች የጥገና ሥራው ተጠናቆአገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
EthiopianElectricUtility

ነገ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን በአዲስ አበባ፣ ሸገር፣ ነቀምትና ወልድያ ከተሞች የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው ቦታዎች ፦
✅ ከጠዋቱ 2:00-9:30
👉 ቡራዩ ድሬ ከአስፋልትበላይ፣ ገፈርሳ ውሀ ግድብ እና አካባቢው፣ ሲሊ፣ ከረላ፣ መናገሻ፣ ግብፅ ኤምባሲ፣ 6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ፣ የካቲት 12 ሆስፒታል፣ ኤፍቢ ግቢ፣ ናይጄሪያ ኤምባሲ፣ 20 ቀበሌ፣ አምባሳደር አካባቢ፣ ሸራተን ፣ የውጭ ጉዳይ ፣ ታችኛው ቤ/መንግስት፣ ባሻወልዴ ኮንዶሚኒየም ፣ ቱሪስት ጀርባ ኮንዶሚኒየም
✅ከጠዋቱ 3:00-12:00
👉 አሻዋ ሜዳ ታጠቅ ሙገር ሲሚንት ፋብሪካ፣ ጂፕሰም ፋብሪካ፣ ጣፎ፣ MNS ሚሽን፣ 44 ማዞሪ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
✅ ከጠዋቱ 2:00-10:30
👉በነቀምቴ ሪጅን ደምቢደሎ ከተማ፣ ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ፣ ደምቢዶሎ አየር ማረፊያ፣ ሙጊ ከተማ፣ ረቡዕ ገበያ፣ መቻራ እና በአካባቢው (ግንቦት 15-17/2018 ዓ/ም)
✅ ከጠዋቱ 2:00-6:30
👉 በወልድያ ሪጅን መቻሬ፣ አዳጎ፣ ሰዋሜዳ፣ አመያመጫ፣ ሁርጌሳ፣ ኡድመን፣ ልብሶ፣ ጊረና፣ መሀለምብ
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻች የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

ነገ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን በአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ከጠዋቱ 2:00-7:30
👉አፍሪካ ሕብረት ፣ መቻሬ ሜክሲኮ ፣ ትነብሆ ሞኖፖል፣ ሳር ቤት ቴሌ፣ መብራት ኃይል ክበብ ጀርባ፣ኳስ ሜዳ ፣ለጎፋ ስቶር ፣ ጎፋ ዳታ ሴንተር፣ ፣ አይሱዙ ጋራዥ፣ጎፋ ካምፕ ፣ ሶፉመር ብሎኬት ማምረቻ እና አካባቢው፣መካኒሳ መካነ ኢየሱስ አጠገብ ፣ባቱ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢ፣አሚጎ ካፌ ፊትለፊት ፣ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ፣ መካኒሳ አቦ ቤ/ክ አካባቢ፣ ቫቲካን ጀርባ ፣ የመከላከያ ሚ/ር መኖሪያ አካባቢ፣ ጥቁር አባይ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ፣ ሰላም አስከባሪ
✅ከጠዋቱ 2:00-8:00
👉አቃቂ ስታዲየም፣ መኮድ ፣ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ፣ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ፣ ሸገር ሕንፃ ፣ ቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ
✅ከጠዋቱ 3:00-12:00
👉ግብፅ ኤምባሲ፣ 6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ፣ የካቲት 12 ሆስፒታል፣ ኤፍቢ ግቢ፣ ናይጄሪያ ኤምባሲ፣ 20 ቀበሌ
✅ ከጠዋቱ 3:00-10:00
👉ጂፕሰም ፋብሪካ ፣ ጣፎ፣ MNS ሚሽን ፣ 44 ማዞሪ ፣10 ኪሎ በከፊል፣ ዶሮ እርባታ ፣ ቀንብሬ፣ አፍሪካ ልሕቀት ማዕከል እና አካበቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

6 months ago
📢 አዲስ አገልግሎት በአዲስ መንፈስ! - እንኳን ደስ አላችሁ🔋
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ተጠቃሚዎችን እርካታ ለማሳደግ 24 ሰዓት የሚሰሩ #ቻርጅ_ማድረጊያ_ጣቢያዎችን በከፍተኛ መዋለ ንዋይ በመገንባት ለአገልግሎት ዝግጁ ማደረጉን በደስታ ይገልፃል፡፡
🚗 የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎቹ የት ይገኛሉ❓
✨ ኮተቤ – ከማዕድን ሚኒስቴር ፊት ለፊት
✨ ፒያሳ – ኤሌክሪክ ህንፃ ግቢ ውስጥ | በቀድሞው የአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት
💵 የአገልግሎት ክፍያ
🖍️ የኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃቀም ባህልን ለማሻሻልና ከፍተኛ የኃይል ጭነት በማይኖርበት ጊዜ ደንበኞች ኃይል እንዲጠቀሙ ለማበረታታት
🖌️ በሚጠቀሙበት ጊዜ ላይ መሰረት ያደረገ ምክንያታዊ የቻርጅ ማድረጊያ ዋጋ እንዲተገበር ተደርጓል፡፡
🚘 ለአገልግሎቱ ተጠቀሚዎች ለአንድ ኪሎ ዋት ሶስት የክፍያ ዋጋ አማራጮች ቀርቧል፡-
☑️ Off-Peak:- (10:00፡01 PM - 6:00፡00 AM - ከምሽቱ 4:00 እስከ ጠዋቱ 12:00 ድረስ) - 14.85 ብር
☑️ Shoulder: - (10:00፡01 AM-5 - :00፡00 PM - ከጠዋቱ 4:00 አስከ ቀኑ 11:00 ድረስ) - 16.57 ብር
☑️ On-Peak: - (5:00፡01 PM – 10:00፡00 PM & 6:01AM - 10:00AM - ከቀኑ 11፡00 እስከ ምሽቱ 4፡00 እንዲሁም ከጠዋቱ 12፡00 እስከ 4:00 ድረስ) - 18.28 ብር
⚠️ልብ ይበሉ - የተዘጋጀው የቻርጅ ማድረጊያ ዋጋ ደንበኞች የኃይል ጭነት በማይኖርበት ጊዜ በዝቅተኛ ዋጋ ቻርጅ በማድረግ ገንዘባቸውን #እንዲቆጥቡ የሚያስችል ነው፡፡
#cleanenergy #poweryourjourney #eeu #ultrafast #driveclean #charge_green_drive_clean” #smart_power_for_smart_mobility”
#ethiopianelectricutility 🚗⚡️

Sponsored by
Surafel
7 months ago
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ48.8 ሚሊዮን ዶላር የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቱን እያፋጠነ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎችን የክፍያ ሥርዓት ወደ ዘመናዊ የዲጂታል መንገድ ለመቀየር የጀመረውን ግዙፍ ፕሮጀክት በስፋት እያከናወነ ይገኛል። ተቋሙ 500 ሺህ ስማርት የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን ለመግጠም ለጀመረው ለዚሁ ፕሮጀክት 48.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ማድረጉ ተገልጿል።
እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከ67 ሺህ በላይ ደንበኞች የዘመናዊው ቆጣሪ ተጠቃሚ መሆን የጀመሩ ሲሆን፣
ዝርዝር አፈጻጸሙም 🔎
* 60,457 ነጠላ ፌዝ (Single Phase) ቆጣሪዎች፦ እስከ 7.5 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ መኖሪያና ንግድ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ ነው።
* 7,013 ባለ ሦስት ፌዝ (Three Phase) ቆጣሪዎች፦ ከ8 እስከ 24 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችና ቤቶች ተገጥመዋል።
ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ሽግግር ደንበኞች ቀደም ሲል የኤሌክትሪክ ቶክን ለመግዛት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በማቅናት ያባክኑት የነበረውን ጊዜና ጉልበት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ነው።
ደንበኞች በፈለጉት ሰዓት (በ24 ሰዓት) ባሉበት ሆነው፦
* በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE Birr/App)
* በቴሌ ብር (telebirr)
* በአዋሽ ባንክ መተግበሪያዎች አማካኝነት
በቀላሉ ክፍያቸውን መፈጸም ይችላሉ።
ይህ እርምጃ የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ከማሳለጡ ባለፈ፣ ለኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትና አስተማማኝነት ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianelectricutility #eeu #digitaltransformation #smartmeter #prepaidelectric #ethiopiatech #cbe #telebirr #awashbank #energyupdate

8 months ago
🔻ውድ ደንበኞቻችን ኢትዮጵያ አሁንም #ዝቅተኛ_የኤሌክትሪክ_ታሪፍ ተግባራዊ እንደምታደርግ ያውቃሉ?
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የተቋማችን ደንበኞችን የኑሮ ሁኔታ እንዳይጎዳ በመንግስት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፤ አሁንም ከአፍሪካ አገራት ጋር ሲነፃፀር በጣም ዝቅተኛ የሚባል የታሪፍ መጠን ነው፡፡
ለአብነትም #የኢትዮጵያ እና #የጎረቤት_የአፍሪካ_አገራት የመኖሪያ ቤት የአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት አማካይ የፍጆታ ሂሳብ በአሜሪካን ዶላር ያለውን ንፅፅር እንመልከት👇
☑️ ኢትዮጵያ - $0.005–$0.035
☑️ ጅቡቲ -$0.23–$0.30
☑️ ኬኒያ - $0.18–$0.20
☑️ ታንዛኒያ - $0.09–$0.11
☑️ ኡጋንዳ - $0.17–$0.19
☑️ ሩዋንዳ - $0.12–$0.14
#electrictariff #affordabletariff #lowestinafrica #ethiopiangovernment #ethiopianelectricutility

የተደራጀው የትራንስፎርመር ዘረፋ ሙከራ በፀጥታ አካላት ከሸፈ! ⚡️👮🏽♂️
#ethiopia | በሌሊት መኪና ይዘው የመጡት ዘራፊዎች 50 ኪሎ ቮልት ትራንስፎርመር ሊሰርቁ ሲሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ"
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለህዝብ አገልግሎት (ለመንገድ መብራት) የተቀመጠ ትራንስፎርመርን ዘርፈው ለመሰወር የሞከሩ ግለሰቦች በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የወንጀሉ ዝርዝር:
📅 ቀን: ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም (ከለሊቱ 8:00 ሰዓት)
📍 ቦታ: አቃቂ ቃሊቲ፣ ሀይዌይ አካባቢ
🚛 ዘዴው: ዘራፊዎቹ በተደራጀ ሁኔታ መኪና በመያዝ አዲስ እየተዘረጋ ያለውን ትራንስፎርመር ለመውሰድ ሙከራ አድርገው ነበር።
ሆኖም በፀጥታ ኃይሎች ጠንካራ ክትትል የህዝብ ንብረት የሆነው ትራንስፎርመር የዳነ ሲሆን፤ ተጠርጣሪዎቹም በህግ ጥላ ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
መልዕክት:
የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት የጋራ ሀብታችን ነው! ማንም ሰው በንብረቱ ላይ ጉዳት ሲያደርስ ወይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከተመለከቱ ለፀጥታ አካላት በመጠቆም ሀላፊነትዎን ይወጡ።
ለፀጥታ አካላት ምስጋና ይገባል! 👏
#ethiopianelectricutility #crimeprevention #akakikality #transformertheft #infrastructure #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

⚡️ በግማሽ ዓመት ብቻ ከ266 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ብርሃን አግኝተዋል
#ethiopia | "ተቋሙ በ6 ወራት ከ52 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል" - ኢንጂነር ጌቱ ገረመው
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ይፋ አድርጓል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በሰጡት መግለጫ የሚከተሉት ዋና ዋና ውጤቶች ተመዝግበዋል፡-
✅ አዳዲስ ደንበኞች:
በስድስት ወራት ውስጥ 266,916 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኙ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ13.2% ጭማሪ አሳይቷል። አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥርም 5.46 ሚሊዮን ደርሷል።
✅ ገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን:
ከዋናው ቋት (Grid): 47 የገጠር ቀበሌዎች (ከዕቅድ በላይ)፣
ከፀሐይ ኃይል (Off-grid): 16 ቀበሌዎች፣
በድምሩ 63 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል።
✅ የገቢ አፈጻጸም:
ከተለያዩ አገልግሎቶች 52.26 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96% ማሳካት ተችሏል።
✅ መሰረተ ልማት:
አገልግሎቱን አስተማማኝ ለማድረግ ከ52 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመሰረተ ልማት ማሻሻያ እና መልሶ ግንባታ ተከናውኗል።
ተቋሙ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት እና ጥራቱን ለመጠበቅ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
#ethiopianelectricutility #eeu #energyaccess #ethiopia #development #infrastructure #power #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
⚡ በውሃ ላይ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ! 🌊
#ethiopia | የኢንዱስትሪውን ህልውና የታደገው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ልዩ ኦፕሬሽን
በሀገራችን ብቸኛ የሆነውና ለብርጭቆ፣ ለጠርሙስ እና ለጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ግብዓት የሚያቀርበው "አቢጃታ ሻላ ሶዳ አሽ አክሲዮን ማህበር"፤ በአቢጃታ ሐይቅ የውሃ ሙሌት ምክንያት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ በመውደሙ የምርት ስራውን ለማቆም ተገዶ ነበር።
ይሁንና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) ቴክኒሻኖች ይህንን ከባድ የተፈጥሮ እና የቴክኒክ ፈተና በመቋቋም፤ በሐይቁ ውሃ ላይ የኤሌክትሪክ መስመር በመዘርጋት ኢንዱስትሪውን ታድገዋል።
የስራው አስደናቂ ጎኖች፡-
🏗 600 ሜትር ርዝመት ያለው መስመር በሐይቁ ላይ ተዘርግቷል።
🏗 ለዚህም ሲባል 7 የብረት ምሰሶዎች በውሃ ውስጥ እንዲሁም 8 የእንጨት ምሰሶዎች በብስ ላይ ተተክለዋል።
🏗 መፍትሔው ለሚቀጥሉት 15 ዓመታት በአስተማማኝ ሁኔታ ያገለግላል።
ውጤቱስ?
✅ በቀን 24 ሰዓት የሚሰራው ፋብሪካ ኃይል አግኝቶ ወደ ስራ ተመልሷል።
✅ የ350+ ዜጎች የስራ ዕድል ቀጣይነት ተረጋግጧል።
✅ በአካባቢው የሚገኙ 150 አባወራዎችም የብርሃን ተጠቃሚ ሆነዋል።
ለባለሙያዎቹ እና ለተቋሙ ምስጋና ይገባል! 👏👏
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
#ethiopianelectricutility #eeu #engineering #abijattalake #sodaash #powersolution #ethiopia

Comments