3 months ago
1447ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ነገ ማለዳ 9 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል
#ethiopia | በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ነገ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ/ም የሚከበረውን 1447ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ ገልጿል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiofm #getutemesgen #getu

''ደምን በገንዘብ በሚሸጡ የጤና ተቋማት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል'' የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት
#ethiopia | የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ከበጎ ፈቃደኞች በነጻ የተሰበሰበውን ደም ለታካሚዎች በገንዘብ በሚሸጡ የመንግስትም ሆነ የግል የጤና ተቋማት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ታዬ እንደገለጹት፤ ደም የሚሰበሰበው የሰው ልጅን ህይወት ለማዳን ሲሆን፣ ማንኛውም የጤና ተቋም ለታካሚዎች በነጻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ሆኖም አንዳንድ ተቋማት ‘የአገልግሎት ክፍያ’ በሚል ስም ከታካሚዎች ገንዘብ እንደሚቀበሉ የሚደርሱ ጥቆማዎች እንዳሉ አመልክተዋል። ይህን ብልሹ አሰራር ለመግታት ተቋሙ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ተቋሙ ከጤና ተቋማቱ ጋር በገባው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ስርአት እየዘረጋ መሆኑንና በቀጣይም የደም አገልግሎትን የሚመለከት ህግ በማውጣት የቁጥጥር ስራውን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለፁት፤ አንድ ዩኒት ደም ለህክምና ዝግጁ ለማድረግ ከተሰበሰበ በኋላ እንደ ኤች.አይ.ቪ፣ ሄፓታይተስ እና ሲፊሊስ ካሉ በሽታዎች ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ምርመራዎች እንዲሁም ደሙን ወደ ቀይ የደም ሴል፣ ፕሌትሌት እና ፕላዝማ ለመለየት የሚሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃሉ።
ለነዚህ ስራዎች የሚጠይቁት የቴክኖሎጂና የኬሚካል ግብአቶች በሙሉ በውጭ ምንዛሬ የሚገዙ በመሆናቸው በአማካይ እስከ 46 ዶላር ወጪ ይደረግበታል።
አቶ አምሳሉ አያይዘውም የሀገሪቱ የደም አቅርቦት ከፍላጎቱ በአማካይ በግማሽ እንደሚያንስ ገልፀዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiofm #getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #ደምባንክ #ጤና #ህይወት #በጎፈቃደኝነት #ደምልገሳ #ቁጥጥር #እርምጃ

‹‹ኢራን 50 ሰሜን ኮሪያዎችን ትሆናለች›› የኔታንያሁ
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ አዲስና አደገኛ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተሰምቷል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እርስ በእርስ የሚወራወሯቸው ጠንካራ ቃላት፣ ዓለምን ለከፋ ስጋት ዳርገዋል።
ኔታንያሁ ለምን ኢራንን ከሰሜን ኮሪያ ጋር አነጻጸሩ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፣ ኢራን ለዓለም ሰላም ካላት አደገኝነት አንጻር "50 ሰሜን ኮሪያዎችን ትሆናለች" ሲሉ ገልጸዋል። እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር እና የባለስቲክ ሚሳኤል አቅም ቢኖራትም፣ እንደ ኢራን ግን "ሞት ለአሜሪካ" የሚል ግልጽ የጥፋት ርዕዮተ ዓለም አትከተልም።
"ኢራን የአሜሪካን እና የእስራኤልን መጥፋት እንደ ዋና ግብ ይዛ የተነሳች በመሆኗ፣ አጥፊነቷ ከሰሜን ኮሪያ በብዙ እጥፍ ይበልጣል" — ቤንያሚን ኔታንያሁ
የሰሜን ኮሪያው ምላሽ፦ "እስራኤልን ለማጥፋት አንድ ሚሳኤል ይበቃል"
የኔታንያሁ ንግግር ያልተዋጠላቸው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ለቴህራን ያላቸውን ወታደራዊ ድጋፍ በይፋ አረጋግጠዋል። እስራኤልን ከዓለም ካርታ ላይ ለማጥፋት "አንድ ሚሳኤል ብቻ" በቂ እንደሆነ የገለጹት መሪው፣ አስፈላጊ ከሆነም የላቁ ሚሳኤሎችን ለኢራን ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ይህ የፒዮንግያንግ መግለጫ የወጣው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች መሆኑ ይነገራል፡-
* አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፉሪ" (Operation Epic Fury) መጠናከሩ።
* የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ መገደላቸው መረጋገጡ።
አዲሱ የኃይል አሰላለፍ እና የዓለም ስጋት
በኢራን፣ ሩሲያ፣ ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ መካከል እየተፈጠረ ያለው ወታደራዊ ጥምረት፣ ግጭቱን ከቀጣናዊነት አልፎ ዓለም አቀፍ ጦርነት ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት አንዣብቧል።
* የቻይና ሚና፦ ቻይና ለኢራን የላቁ ሚሳኤሎችን እያቀረበች ነው የሚሉ ዘገባዎች ቢወጡም፣ ቤጂንግ ግን ውንጀላውን አስተባብላለች።
* የትራምፕ ማስጠንቀቂያ፦ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል "ትልቁ ጦርነት ሊመጣ ይችላል" ሲሉ የሰጡት ማስጠንቀቂያ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እየተገጣጠመ ይገኛል።
ይህ ወታደራዊ ውጥረት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ መናወጥን የፈጠረ ሲሆን፣ የጂኦ-ፖለቲካዊ መረጋጋትንም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከትቶታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiofm #middleeastcrisis #israeliranconflict #netanyahu #kimjongun #globalsecurity #operationepic Fury #breakingnews

ኢትዮጵያዊቷ ሻለቃ ትዕግስት ፈረደ በተባበሩት መንግሥታት ተሸለሙ
#ethiopia | በደቡብ ሱዳን በተሰማራው የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (UNMISS) ውስጥ በመካኒክነት እያገለገሉ የሚገኙት ኢትዮጵያዊቷ ሻለቃ ትዕግስት ፈረደ፣ ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ የክብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኑ።
ሻለቃ ትዕግስት ሽልማቱን ያገኙት በተለምዶ "የወንድ ሥራ" ተብሎ በሚታሰበው የመካኒክነት ሙያ ላይ ተሰማርተው፣ የሰላም አስከባሪ ተሽከርካሪዎች ሁልጊዜ ለተልዕኮ ዝግጁ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ለተጫወቱት ቁልፍ ሚና ነው።
የሽልማቱና የሥራው ዝርዝር
በምዕራብ ኢኳቶሪያ (ያምቢዮ) በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ የሚገኙት ሻለቃ ትዕግስት፣ ስለ ሥራቸው ያላቸውን ኩራት እንዲህ ገልጸዋል፦
* የተልዕኮ ዝግጁነት፦ ተሽከርካሪዎች ሳይበላሹና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ለሰላም ማስከበር ሥራው መሳካት የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።
* ተስፋን የመጠገን ሙያ፦ "ሁሉም የምጠግናቸው ተሽከርካሪዎች ተስፋን ይሰንቃሉ። ደህንነታቸው ተጠብቆ ሲንቀሳቀሱ ለሰላም የበኩሌን እንደተወጣሁ ይሰማኛል" ሲሉ የሥራቸውን ትርጉም አብራርተዋል።
* የሚና ትልቅነት፦ ይህ የክብር ሜዳሊያ በሰላም ማስከበር ሂደት ውስጥ "ትንሽ" የሚባል ሚና እንደሌለ ያስገነዘበ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሙያ ዳራ
ሻለቃ ትዕግስት በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ያገለገሉ አንጋፋ ባለሙያ ናቸው፦
* በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ አገልግለዋል።
* ከደቡብ ሱዳን ተልዕኳቸው በፊት፣ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኳቸውን በሱዳን በስኬት ተወጥተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiofm #ኢትዮጵያ #የሰላም_አስከባሪ
#ሻለቃ_ትዕግስት_ፈረደ #ተባበሩት_መንግሥታት #ደቡብ_ሱዳን #የሴቶች_ጥንካሬ

Sponsored by
Surafel
3 months ago
የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያዎች ከቀረጥ ነፃ ሊሆኑ ነው?
#ethiopia | በኢትዮጵያ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች በገበያ ላይ ያላቸው ዋጋ መናር በርካታ ታዳጊዎችን ከትምህርት ገበታቸው እያራቃቸው ይገኛል።
ይህንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ ምርቶቹ ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የፖሊሲ ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል።
የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ማህበራት ህብረት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ከበደ እንደገለጹት፣ የጥናቱ ዋና ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፦
* የትምህርት ተሳትፎን ማሳደግ፦ በዋጋ መወደድ ምክንያት ምርቱን ማግኘት ያልቻሉ ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የሚቀሩበትን ሁኔታ ማስቀረት።
* ጤናን መጠበቅ፦ ተማሪዎች ንፅህናው የተጠበቀ ምርት በቀላሉ እንዲያገኙ በማድረግ የጤና እክሎችን መከላከል።
* ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ፦ ቀረጥ መነሳቱ በሀገር ኢኮኖሚና በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያመጣውን አዎንታዊ ተጽዕኖ ማመላከት።
"ምርቶቹ በገበያ ላይ ያላቸው ዋጋ ከፍተኛ መሆን በርካታ ታዳጊዎችን ከትምህርት ገበታቸው እንዲቀሩ እያደረገ ነው" — አቶ አበበ ከበደ
ቀጣይ እርምጃ ምን ይሆናል?
በአሁኑ ወቅት በህብረቱ እየተካሄደ ያለው ይህ ጥናት እንደተጠናቀቀ፣ ለውሳኔ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተለይም ለገንዘብ ሚኒስቴር እንደሚቀርብ ታውቋል። ጥናቱ ተቀባይነት ካገኘ፣ በሴቶች የትምህርትና የጤና ጉዞ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiofm #ethiopia #girlseducation #menstrualhygiene #policychange #healthequity #periodpoverty

6 months ago
ታጣቂዎች ከ200 በላይ ተማሪዎችና ሠራተኞችን ከትምህርት ቤት አግተው ወሰዱ፤ ፕሬዜዳንቱም የቡድን 20 ጉባዔ ተሳትፏቸውን ሰረዙ
#ethiopia | በማዕከላዊ ናይጀሪያ የናይጄሪያ ክርስቲያኖች ማኅበር እንደገለጸው አርብ ማለዳ ታጣቂዎች ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት 215 ተማሪዎች እና 12 ሠራተኞችን ወስደዋል።
እገታው የተፈጸመው በኒጀር ግዛት ፓፓሪ በሚገኘው የቅድስት ማርያም ትምህርት ቤት ሲሆን፣ ባለሥልጣናቱ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ሁሉም አዳሪ ትምህርት ቤቶች በጊዜያዊነት እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር።
የጅምላ እገታው በዚህ ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው። ሰኞ ዕለት በኬቢ ግዛት ከሚገኝ አዳሪ ትምህረት ቤት ከ20 በላይ ሴት ተማሪዎች ታግተው ተወስደዋል ተብሏል።
እንዲሁም፣ በክዋራ ግዛት የሚገኝ አንድ ቤተ ክርስትያን የአምልኮ ሥነ ስርዓቱ በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ምዕመናን ሲገደሉ 38 ደግሞ ታግተው ተወስደዋል።
ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ እነዚህን የጸጥታ ጉዳዮች ለመፍታት በሚል በዚህ ሳምንት መጨረሻ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል። #ethiofm

8 months ago
በህዳሴ ግድብ ላለዉ የአሳ ሀብት የአስተዳደር ልዩ መመሪያ መፅደቁ ተገለፀ
#ethiopia | በህዳሴ ግድብ ላይ የተገኘዉን የአሳ ሀብት ለማልማት እንዲቻል እና ሀብቱንም ለመጠበቅ የሚያስችል የአሳ ሀብት አስተዳደር ልዩ መመሪያ ተዘጋጅቷል ተብሏል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ሀላፊ ዶ/ር አለማየሁ መኮንን፤የአሳ ሀብቱ እንዳይሟጠጥ ለመጠበቅ እየተሞከረ እንደሆነ ይገልፃሉ።
ምን አይነት አሳ በምን አይነት ማጥመጃ መጠቀም ያስፈልጋል የሚለዉ ሁሉ መመሪያ እንደወጣላቸዉ ሀላፊዉ ገልፀዋል።
በዉሃ ክፍሉ የትኛዉ አካባቢ ነዉ ከፍተኛ የአሳ ምርት ያለዉ እና ምን አይነት ዝርያዎች የሚለዉን እየለዩ መጠቀም የሚቻልበት እንደሚሆን ዶ/ር አለማየሁ አንስተዋል።
የአሳ ሀብቱን በአግባቡ ለማስተዳደር ባለድርሻ አካላት እና የሙያ ዘርፉ ባለሙያዎች ባሉበት መመሪያዉ የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ መፅደቁን ሰምተናል።
በቀጣይ መመሪያ የትግበራ ምዕራፍ ላይ የሚደረስበት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅም ሀላፊዉ አክለዋል።
በቦታዉ በቀን 14 ሺህ ኪሎ ግራም ዓሣ የማምረት አቅም መፈጠሩን በቅርቡ የግብርና ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያመላክታል።
#ethiofm

11 months ago
የአይን ብሌን የሚሰበስቡ ባለሙያዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆናቸው ተገለፀ
#ethiopia | እንደ ሀገር በጅማ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ 3 ባለሙያዎችን ጨምሮ የአይን ብሌን የሚሰበስቡ 9 ባለሙያዎች ብቻ መኖራቸውን የኢትዮጲያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፤ ስልጠናው ከሀገር ውጪ በመሄድ መወሰድ ያሉባቸው ስልጠናዎችን የሚጠይቅ እና ግብዓቱም በስፋት ሀገር ውስጥ ባለመገኘቱ ሰፊ ስራን የሚፈልግ ነው ብለዋል፡፡
በሀገራችን እንደ አጠቃላይ የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ መስራት የሚችሉ ባለሙያዎች 13 ብቻ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡
በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ወደ 3መቶ10 የአይን ብሌን ለመሰብሰብ ታቅዶ 3መቶ50 የሚሆን የአይን ብሌን ማንሳት መቻላቸውን ነዉ የነገሩን፡፡
እንዲሁም አይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ ሰዎች ቁጥር 7መቶ19 እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
እንደ ሀገር ያለው የአይን ባንክ አዲስ አበባ ከተማ ብቻ ያለ በመሆኑ ክልሎች አካባቢ የተደራሽነት ጥያቄዎች መኖራቸውንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡
ይህንንም በመገንዘብ ጅማ ላይ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን እና ባለሙያዎችም ስልጠናዎችን ወስደው በመጨረስ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
በአጠቃላይ ቀደም ሲል ካለው የተሻለ የአይን ብሌን መሰብሰብ መቻሉን እንዲሁም የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡ #ethiofm

በማይናማር በአጋቾች እጅ ከሚገኙ 42 ኢትዮጵያውያን መካከል አንድ ሰው ራሱን እንዳጠፋ ተገለፀ
#ethiopia | በማይናማር በ3 ካምፕ ውስጥ 42 ኢትዮጵያውያን ታግተው የአካል ጉዳት እየደረሰባቸው እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን የታጋች ወላጆች አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ በፊት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ አገር የመለሳቸው መኖራቸውን ያስታወሱት የወላጅ ኮሚቴ አባላት፤ አሁን ያሉት ግን ምንም አይነት ፕሮሰስ እንዳልተጀመረላቸዉ ገልፀዋል።
14 ልጆች በቅርብ ይወጣሉ መባሉን አንስተው፤ ቦታዉ ድረስ ሲሄዱ ግን ከፖሊስ ጋር ትብብር ስለሚያደርጉ እና ቀድሞ መረጃ ስለሚደርሳቸው ልጆቹን እንደሚደብቋቸዉ ተናግረዋል።
ከ42ቱ ታጋቾች መካከል 7ቱ ሴቶች መሆናቸውንም ሰምተናል።
የሚደርስባቸው ስቃይ እና ድብደባ ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት የወላጅ ኮሚቴ አባላት፤ ምግብ እንደማያገኙ እና ለሞት እና ለአካል ጉዳት እየተዳረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት ኮሚቴው በተደጋጋሚ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ጥረት በመጠለያ ካምፕ የነበሩ ከ7መቶ በላይ ዜጎች ከማይናማር ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደተቻለ ይታወሳል።
አሁን ላይ ቀሪዎቹ ልጆቻችን ወደ ሀገር እንዲመለሱ ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል፡፡ #ethiofm

በናይጄሪያ ያለዉ ቀውስ ቢቀጥልም ለሶስተኛ ተከታታይ ወር የዋጋ ግሽበት መቀነስ አሳይቷል ተባለ
#ethiopia | የናይጄሪያ የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ላይ መቀነሱን በመግለፅ ይህም ለተከታታይ ሶስተኛ ወር መሆኑን የሀገሪቱ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡
ግንቦት ወር ላይ ከነበረው የዋጋ ግሽበት 22.97 በመቶ በሰኔ ወር ወደ 22.22 በመቶ ቀንሷል ተብሏል።
በባለፈው ዓመት የዋጋ ግሽበቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መደረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በሀገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነት ቀውስ እየተባባሰ መጥቷል ነዉ የተባለዉ።
ካለፉት ዓመታት ሲነጻጸር የዋጋ ንረቱ መቀዛቀዝ ቢያሳይም፤ የምግብ እና የሸቀጦች ዋጋ በብዙ ናይጄሪያውያን ገቢ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ።
በናይጄሪያ በሰኔ ወር ላይ በዋና ዋና ከተሞች ላይ በተደረገ ሰልፍ የኑሮ ውድነት የብዙ ዜጎች አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በአገሪቱ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ውጥረት ገና እንዳልተጠናቀቀ የሚያሳዩ ምልክቶች አልጠፉም ሲል ያስነበበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ። #ethiofm

ላሚን ያማል በባርሴሎና የ10 ቁጥር ማሊያን ተረክቧል።
#ethiopia | ተጨዋቹ የማሊያ ቁጥሩን እንደሚለብስ ለማሳወቅ 18 አመት እስኪሞላው ድረስ የተጠበቀ ሲሆን መጪዎቹ ጊዜያት ለበረከት እና እርግማን ከመዘጋጀት በላይ እንደሆነ ተግልጿል ።
በቅርቡ 18 አመቱን ያከበረው ያማል ላለፉት 3 አመታት ሲለብሰው ከነበረው አንሱ ፋቲ ወደ ሞናኮ ማቅናቱን ተከትሎ የክለቡን ድንቅ ቁጥር ተረክቧል ።
ባሳለፍነው አመት ከባርሴሎና ጋር የላሊጋ ፣ የኮፓ ዴላሬይ እና የሱፐር ካፕ ዋንጫን ማሳካት የቻለው ተጨዋቹ በርካታ ጥቅም የሚስገኝለትን አዲስ ኮንትራትም ተፈራርሟል ።
ውሳኔው በክለቡ እና በተጨዋቹ መካከል በስምምነት የተደረገ ሲሆን በሚቀጥሉት ጊዜያትም የማሊያው ሽያጭ ላይ የገንዘብ ጭማሪ እንደሚኖረውም ተግልፅዋል። #ethiofm

የግብርና ምርቶችን ጨምሮ በተለያዩ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት ገንዘቦችን ከጥቅም ውጭ እያደረጋቸው ይገኛል ተባለ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን ጨምሮ በተለያዩ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት የገንዘቦችን የመግዛት አቅም እየተፈታተነና አንዳንዶቹንም የመገበያያ ገንዘቦች ከጥቅም ውጭ እያደረጋቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፋይናስና የኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ ይርጋ ተስፋዬ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤አሁንላይ በሳንቲሞች የሚሸመቱ ቁሶች ከጠፉ ሰነባብተዋል ብለዋል፡፡
ከአምስ እስከ ሃምሳ ሳንቲም ያሉ የመገበያያ ገንዘቦችም ከገበያ ወጥተዋል ማለት ይቻላልም ነው ያሉት፡፡
አቶ ይርጋ ገንዘቦቹ እየጠፉ ለመምጣታቸው ምክንያቱ የምርቶች ዋጋ መናር ነው ያሉ ሲሆን፤ ፍላጎትና አቅርቦትን ማቀራረብ አንዱ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘዴ ነው ሲሉም ተናግረዋል ፡፡
ሌላኛው ጣቢያችን ያነጋገራቸው የፋይናስ ባለሙያው አቶ ጋማቹ ብረሃኑ፤የኢትዮጵያን የገንዘብ የመግዛት አቅም ማሳደግ እስካልተቻለ ድረስ ገንዘቦቻችን ላይ ቁጥር እየጨመርን ነው የምኔደው ብለዋል።
ይህ እንዳይሆን ከወዲሁ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን ምርት መቀነስና የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
የመሰረታዊ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ዋጋ ንረት በዚህ የሚቀጥል ከሆነ አሁን ባሉት ገንዘቦቻችን ብዙ ጊዜ መቆት እንደ ማይቻልም አንስተዋል።
ይሄ ደግሞ እንደሌሎች ሃገራት የራስን ገንዘብ ከአገልግሎት አውጥቶ ዶላርን ወደ ማስገባት ያመራል ይህ ሁኔታ ደግሞ በመጨረሻ ሉአላዊነትን እስከመፈታተን ያደርሳል ሲሉ ጣቢያችን ያነጋገራቸው የፋይናስ ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡ #ethiofm

ከ100 በላይ ሊቢያ ውስጥ ተይዘው የነበሩ ስደተኞች ነጻ ወጡ
#ethiopia | ሊቢያ ውስጥ በወሮበሎች ተይዘው የነበሩ ከ100 በላይ ስደተኞች ነጻ መመውጣታቸውን ሊቢያ አስታወቀች።
የሊቢያ አቃቤ ሕግ ዛሬ እንደተናገረው ምሥራቅ ሊቢያ ውስጥ በወሮበሎች ታግተው ገንዘብ እንዲያመጡ ሲጠየቁ የነበሩት እነዚሁ 5 ሴቶች የሚገኙባቸው ስደተኞች ከአጋቾቻቸው ነጻ ወጥተዋል።
ነጻ የወጡት ስደተኞች ከሊቢያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ከቤንጋዚ 160 ኪሎ ሜትር አካባቢ ወደሚርቀው አጃዳብያ በተባለው ከተማ ነበር የተያዙት።
ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ በማሻገር የተጠረጠሩ 5 የሊብያ የሱዳንና የግብጽ ዜጎች የተባሉ ሰዎች መታሰራቸውን ባለሥልጣናት ተናግረዋል። አቃቤ ሕግ ወንጀለኛ ያላቸው እነዚሁ ሰዎች ስደተኞችን ከአገር ወደ አገር በሕገ ወጥ መንገድ በማሻገር ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው።
ስደተኞቹን ለመልቀቅም ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ ያሰቃዩዋቸዋል። ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመሻገር ሊቢያ የሚሄዱ በርካታ ስደተኞች በነዚሁ ደላላዎች እጅ ይወድቃሉ።
ባለፈው የካቲት ኩፉራ ከተባለችው ከተማ በስተሰሜን በተገኝ አንድ የጅምላ መቃብር ውስጥ ቢያንስ የ28 ስደተኞች አስከሬን ተገኝቶ ነበር።
ከዚያ በኋላም በደቡብ ሊቢያ ሌላ የ19 ሰዎች አስከሬን ጂክሀራ በተባለው አካባቢ ተገኝቷል።
በግንቦት ወር ይፋ በተደረገ የተመድ አሃዛዊ መረጃ መሠረት በዚህ ዓመት ታህሳስ ወር ከ47 ሀገራት ሊቢያ የመጡ 825 ሺህ ስደተኞች ተመዝግበዋል።
ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ኅብረት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርና የኢጣልያ የማልታ እና የግሪክ ሚኒስትሮች ዓለም አቀፍ እውቅና ከተሰጣቸው የሊቢያ ብሔራዊ አንድነት መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሀሚድ ዴቢባህ ጋር በስደተኞች ቀውስ ላይ ተነጋግረው ነበር። #ethiofm

ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች ምልክት እንዲለጠፍባቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ
#ethiopia | ቢው ከአገራዊ ጠቅላላ ምርት 1.4 በመቶ እንዲሸፍን መታቀዱ ተሰምቷል።
የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈልባቸው በገንዘብ ሚኒስቴር የተመረጡ ምርቶች፣ ምልክት እንዲለጠፍባቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ፡፡
በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 (በተሻሻለው) አንቀጽ 29 እና 42 (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ‹‹የኤክሳይዝ ምልክቶች አስተዳደር ሥርዓትን ለመወሰን የወጣው መመርያ ቁጥር 1072/2017››፣ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው በተለይ በአልኮልና በትምባሆ ምርቶች ላይ የሚደረገውን ክትትልና ቁጥጥር የሚያጠናክር የኤክሳይዝ ምልክት እንዲለጠፍባቸው አስገዳጅ ሆኗል።
የአልኮል መጠጦች፣ አልኮል አልባ ቢራ፣ የወይን ጠጅ ወይም የተጣራ አልኮል የታከለበት ወይን ጠጅ፣ የአልኮል መጠናቸው ከ0.5 በመቶ በላይ የሆነ ተመሳሳይ ምርቶች የኤክሳይዝ ምልክት ሊደረግባቸው እንደሚገባ በመመርያው ተደንግጓል። #ethiofm

የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተቃዋሚዎችን አስጠንቅቀዋል
#ethiopia | ፕሬዝዳንቱ በኬኒያ እየተቀሰቀሰ ባለው ተቃውሞ ትእግስታቸው እየተሙዋጠጠ እንደሆነ አሳስበዋል ፡፡
ፕሬዝዳንት ሩቶ በተቃውሞ መንግስትን ለመገልበጥ በሃገሪቱ ሴራ እንዳለ የገለጹ ሲሆን የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው መንግስታቸውን በሴራ ለመጣል እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ዊሊያም ሩቶ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በተቃዋሚዎች በፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደ ጦርነት ይቆጠራል ሲለዚህም ትእግስታችን እየተሙዋጠጠ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር የኬኒያ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ህዝብ ነው ስለዚህም ኬኒያውያን የሃገራቸውን መሪ በምርጫ ይመርጣሉ ስለዚህም በአመጽ መሪን መቀየር በዚች ሃገር የሚሆን አይደለም ብለዋል፡፡
ሆኖም በኬኒያ የፖሊስ ከልክ ያለፈ ጭካኔ የኢኮኖሚ ቀውስ እና ሙስና እንዲሁም ሌሎችም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምክኒያ ኬኒያውያን ጠንከር ያለ ተቃውሞ ማሰማታቸው ተገልጹዋል፡፡
ከቅርብ ቀናት ወዲህ በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ኬኒያ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደማትገኝ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ የተሰራጩት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ያሳያሉ፡፡
ፕሬዚዳንት ሩቶ የኬኒያን ሰላም ለማስጠበቅ ያለውን ማንኛውንም መንገድ እጠቀማለሁ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ከዚህ ቦሃላ በህግ ተቁዋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችንም እንደማይታገሱ ማሳሰባቸውን #ethiofm

የ80 ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ በመጪው ዓመት ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ሆነው ቀረቡ
#ethiopia | የ80 ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ በመጪው ዓመት ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የገዢው ፓርቲ ዕጩ ሆነው በመመረጥ፤ 40 ዓመት ገደማ የቆዩበት ስልጣን ማስቀጠል የሚችሉበትን መንገድ አመቻችተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ እጩ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ባደረጉት ንግግር ለምርጫ እንዲቀርቡ ለተደረገላቸው ጥሪ ምላሽ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
ከተመረጡም የኡጋንዳን ወደ "ከፍተኛ መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር" እንድትሆን የማድረግ ተልዕኮአቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የሙሴቬኒ ተቺዎች፤ ፕሬዝዳንቱ እ.አ.አ በ1986 የአማጺ ቡድን መሪ ሆነው የሀገሪቱን ሥልጣን ከተቆናጠጡበት ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱን በአምባገነንነት ሲገዙ መቆየታቸውን ያነሳሉ።
ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ ጊዜ ጀምሮ በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ አሸንፈዋል።
በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ለማድረግም ለፕሬዝዳንትነት በሚወዳደሩ እጩዎች ላይ የተቀመጡት የዕድሜ እና የሥልጣን ዘመን ገደቦችን ለማስወገድ ሲባልም የሀገሪቱ ህገ መንግሥት ሁለት ጊዜ ተሻሽሏል።
በሚቀጥለው ዓመት ጥር በሚካሄደው ምርጫ የሙሴቬኒ ዋና ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ከፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝነት ወደ ፖለቲከኛነት የተለወጠው ቦቢ ዋይን ነው።
ዋይን፤ 'ናሽናል ዩኒቲ ፕላትፎርም' የተሰኘው ፓርቲው በእጩነት እንዲቀርብ የሚመርጠው ከሆነ ከሙሴቬኒ ጋር እንደሚፎካከር በሚያዝያ ወር ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። #ethiofm