Logo
Getu Temesgen
በናይጄሪያ ያለዉ ቀውስ ቢቀጥልም ለሶስተኛ ተከታታይ ወር የዋጋ ግሽበት መቀነስ አሳይቷል ተባለ
#ethiopia | የናይጄሪያ የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ላይ መቀነሱን በመግለፅ ይህም ለተከታታይ ሶስተኛ ወር መሆኑን የሀገሪቱ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡

ግንቦት ወር ላይ ከነበረው የዋጋ ግሽበት 22.97 በመቶ በሰኔ ወር ወደ 22.22 በመቶ ቀንሷል ተብሏል።

በባለፈው ዓመት የዋጋ ግሽበቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መደረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በሀገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነት ቀውስ እየተባባሰ መጥቷል ነዉ የተባለዉ።

ካለፉት ዓመታት ሲነጻጸር የዋጋ ንረቱ መቀዛቀዝ ቢያሳይም፤ የምግብ እና የሸቀጦች ዋጋ በብዙ ናይጄሪያውያን ገቢ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ።

በናይጄሪያ በሰኔ ወር ላይ በዋና ዋና ከተሞች ላይ በተደረገ ሰልፍ የኑሮ ውድነት የብዙ ዜጎች አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በአገሪቱ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ውጥረት ገና እንዳልተጠናቀቀ የሚያሳዩ ምልክቶች አልጠፉም ሲል ያስነበበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ። #ethiofm

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.