Logo
Getu Temesgen
ከ100 በላይ ሊቢያ ውስጥ ተይዘው የነበሩ ስደተኞች ነጻ ወጡ
#ethiopia | ሊቢያ ውስጥ በወሮበሎች ተይዘው የነበሩ ከ100 በላይ ስደተኞች ነጻ መመውጣታቸውን ሊቢያ አስታወቀች።

የሊቢያ አቃቤ ሕግ ዛሬ እንደተናገረው ምሥራቅ ሊቢያ ውስጥ በወሮበሎች ታግተው ገንዘብ እንዲያመጡ ሲጠየቁ የነበሩት እነዚሁ 5 ሴቶች የሚገኙባቸው ስደተኞች ከአጋቾቻቸው ነጻ ወጥተዋል።

ነጻ የወጡት ስደተኞች ከሊቢያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ከቤንጋዚ 160 ኪሎ ሜትር አካባቢ ወደሚርቀው አጃዳብያ በተባለው ከተማ ነበር የተያዙት።

ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ በማሻገር የተጠረጠሩ 5 የሊብያ የሱዳንና የግብጽ ዜጎች የተባሉ ሰዎች መታሰራቸውን ባለሥልጣናት ተናግረዋል። አቃቤ ሕግ ወንጀለኛ ያላቸው እነዚሁ ሰዎች ስደተኞችን ከአገር ወደ አገር በሕገ ወጥ መንገድ በማሻገር ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው።

ስደተኞቹን ለመልቀቅም ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ ያሰቃዩዋቸዋል። ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመሻገር ሊቢያ የሚሄዱ በርካታ ስደተኞች በነዚሁ ደላላዎች እጅ ይወድቃሉ።

ባለፈው የካቲት ኩፉራ ከተባለችው ከተማ በስተሰሜን በተገኝ አንድ የጅምላ መቃብር ውስጥ ቢያንስ የ28 ስደተኞች አስከሬን ተገኝቶ ነበር።

ከዚያ በኋላም በደቡብ ሊቢያ ሌላ የ19 ሰዎች አስከሬን ጂክሀራ በተባለው አካባቢ ተገኝቷል።

በግንቦት ወር ይፋ በተደረገ የተመድ አሃዛዊ መረጃ መሠረት በዚህ ዓመት ታህሳስ ወር ከ47 ሀገራት ሊቢያ የመጡ 825 ሺህ ስደተኞች ተመዝግበዋል።

ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ኅብረት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርና የኢጣልያ የማልታ እና የግሪክ ሚኒስትሮች ዓለም አቀፍ እውቅና ከተሰጣቸው የሊቢያ ብሔራዊ አንድነት መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሀሚድ ዴቢባህ ጋር በስደተኞች ቀውስ ላይ ተነጋግረው ነበር። #ethiofm

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.